text
stringlengths
4
267
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የበላይ አካል ለጉባኤዎች በጻፈው ደብዳቤ መጨረሻ ላይ የሰፈረው ይህ የመሰናበቻ ሐሳብ ጠንካራ ሁኑ ተብሎም ሊተረጎም ይችላል።
እኛም ጤናማ እና ጠንካራ ሆነን ታላቁን አምላካችንን ማገልገል እንደምንፈልግ ምንም ጥርጥር የለውም።
የምንኖረው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ከመሆኑም ሌላ ሁላችንም ፍጹማን አይደለንም፤ በመሆኑም ሕመም ማናችንም ልናመልጠው የማንችለው ነገር ነው።
በአሁኑ ወቅት ከሕመማችን ተአምራዊ በሆነ መንገድ እንደምንድን አንጠብቅም።
ይሁንና ፍጹም ጤና የምናገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል።
ሐዋርያው ዮሐንስ የሕይወት ውኃ ወንዝ እና ሕዝቦችን ለመፈወስ የሚያገለግሉ ቅጠሎች ያሏቸውን የሕይወት ዛፎች በራእይ ተመልክቶ ነበር።
ይህ በዛሬው ጊዜም ሆነ ወደፊት የሚኖርን ከዕፀዋት የተዘጋጀ መድኃኒት አያመለክትም።
ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት ለመስጠት በኢየሱስ በኩል ያደረገውን ዝግጅት ያመለክታል፤ በእርግጥም ይህ በጉጉት የምንጠብቀው ነገር ነው።
ይሖዋ የምንኖርበትን ዘመን አስመልክቶ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፦ በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን ይላሉ።
በዚህ ምሳሌያዊ አገላለጽ ላይ እንደተጠቀሱት አሥር ሰዎች ሁሉ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖችም የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው ይዘዋል።
ይሖዋ ቅቡዓኑን እየባረካቸው እንደሆነ ስለሚያውቁ በመንፈስ ከተቀቡት የአምላክ እስራኤል አባላት ጋር መተባበራቸው ያኮራቸዋል።
እንደ ነቢዩ ዘካርያስ ሁሉ ኢየሱስም በአምላክ ሕዝቦች መካከል የሚኖረውን አስደሳች አንድነት አጉልቷል።
ተከታዮቹ ትንሽ መንጋ እና ሌሎች በጎች ተብለው በሁለት ቡድኖች እንደሚከፈሉ ገልጿል፤ ያም ቢሆን ሁለቱም በአንድ እረኛ የሚመሩ አንድ መንጋ እንደሚሆኑ ተናግሯል።
እኛ ክርስቲያኖች መንፈሳዊነታችንን መጠበቅ ያስፈልገናል።
የምንኖረው ሰይጣን ዲያብሎስ በሚቆጣጠረው ዓለም ውስጥ ከመሆኑም ሌላ ፍጹማን አይደለንም፤ በመሆኑም የዓለምን የተሳሳተ አስተሳሰብና ምግባር በቀላሉ ልንኮርጅ እንችላለን።
የዓለም መንፈስ፣ ወደማንፈልገው አቅጣጫ ሊወስደን ከሚታገል ወንዝ ጋር ሊመሳሰል ይችላል።
ወንዙ ይዞን እንዳይሄድ ከፈለግን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ለመዋኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብን።
በተመሳሳይም የሰይጣን ዓለም መንፈስ እንዳይወስደን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።
ምሥራቹን ስንሰብክ እምነታችንን በሚሸረሽሩ ሐሳቦች ላይ ሳይሆን አስፈላጊና ጠቃሚ በሆኑ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን።
የስብከቱ ሥራ አምላክ የሰጣቸውን ተስፋዎችና ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውን መሥፈርቶቹን እንድናስታውስ ስለሚረዳን እምነታችንን ያጠናክርልናል።
መንፈሳዊ የጦር ትጥቃችን እንዳይላላም ይረዳናል።
በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችን መጠመዳችን በራሳችን ችግሮች ላይ ከልክ በላይ እንዳናተኩር ይረዳናል፤ ይህ ደግሞ ጥበቃ ይሆነናል።
ሩት ለይሖዋ ፍቅር እንደነበራት ልብ በል።
ሩት በይሖዋ ክንፎች ሥር ለመጠለል በመፈለጓ ከጊዜ በኋላ ቦዔዝ አድንቋታል።
ቦዔዝ የተጠቀመበት አገላለጽ፣ ጥላ ከለላ ለማግኘት በወላጆቿ ክንፎች ሥር የምትሸሸግን ጫጩት እንድናስብ ያደርገን ይሆናል።
ይሖዋ ለሩት እንደነዚህ ወላጆች ሆኖላታል።
ስላሳየችው እምነት ወሮታዋን የከፈላት ሲሆን በውሳኔዋ እንድትቆጭ የሚያደርግ ምንም ነገር አላጋጠማትም።
በዛሬው ጊዜ ብዙዎች ስለ ይሖዋ ቢያውቁም እሱን መጠጊያቸው ለማድረግ ያመነታሉ።
ራሳቸውን ወስነው በመጠመቅ እሱን ከማገልገል ወደኋላ ይላሉ።
ራስህን ለይሖዋ ለመወሰን የምታመነታ ከሆነ ምክንያትህ ምን እንደሆነ ቆም ብለህ አስበህበት ታውቃለህ?
ማንኛውም ፍጡር የሚያመልከው አካል መኖሩ አይቀርም።
ታዲያ ሊመለክ የሚገባውን ብቸኛ አምላክ ለምን መጠጊያህ አታደርገውም?
ለይሖዋ ራስህን መወሰንህ፣ በእሱ ላይ እምነት እንዳለህ ማሳየት የምትችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው።
ይሖዋ ከውሳኔህ ጋር ተስማምተህ መኖር እንድትችልና የሚያጋጥሙህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንድትወጣ ይረዳሃል።
አምላክ ለሩት እንዲህ አድርጎላታል።
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት የተጠሙት ቻርልስ ቴዝ ራስል እና ተባባሪዎቹ በ1800ዎቹ መገባደጃ አካባቢ መጽሐፍ ቅዱስን በተደራጀ መልኩ ማጥናት ጀመሩ።
መጀመሪያ ላይ የወንድም ራስል ዓላማ፣ ታዋቂ ከሆኑት ሃይማኖቶች መካከል እውነቱን የሚያስተምረው የትኛው ሃይማኖት እንደሆነ ማወቅ ነበር።
ክርስቲያን ያልሆኑትን ጨምሮ በርካታ ሃይማኖቶች የሚያስተምሩትን ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጥንቃቄ አነጻጸረው።
ከእነዚህ ሃይማኖቶች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ የአምላክን ቃል በጥብቅ እንደማይከተሉ ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደበትም።
እንዲያውም በአንድ ወቅት በአካባቢው ያሉ የተወሰኑ ቀሳውስትን ሰብስቦ አወያይቷቸው ነበር፤ ይህን ያደረገው እነዚህ ሰዎች፣ እሱና ተባባሪዎቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኟቸውን እውነቶች እንደሚቀበሉና ለጉባኤዎቻቸው አባላት እንደሚያስተምሩ ተስፋ አድርጎ ነው።
ቀሳውስቱ ግን ይህን ማድረግ አልፈለጉም።
በመሆኑም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ የሚከተለውን ሐቅ ለመገንዘብ ተገደዱ፦ የሐሰት ሃይማኖትን የሙጥኝ ለማለት ከመረጡ ሰዎች ጋር ተባብሮ መሥራት የማይቻል ነገር ነው።
ለአምላክ ጸጋ ያለን አድናቆት ምንዝርንና ስካርን ወይም የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ይፈጽሟቸው የነበሩ ሌሎች ኃጢአቶችን ከማስወገድ ያለፈ ነገር እንድናደርግ ይገፋፋናል።
ለአምላክ ጸጋ አድናቆት ካለን ከፆታ ብልግና ብቻ ሳይሆን ወራዳ ከሆኑ መዝናኛዎች በሙሉ እንርቃለን።
የአካል ክፍሎቻችንን የጽድቅ ባሪያዎች አድርገን ለማቅረብ እንድንችል፣ ከስካር በመራቅ ብቻ ከመወሰን ይልቅ ሞቅ እስኪለን ድረስ ከመጠጣትም እንቆጠባለን።
እንዲህ ያሉትን መጥፎ ድርጊቶች ማስወገድ ከፍተኛ ትግል የሚጠይቅ ቢሆንም በትግሉ ማሸነፍ እንችላለን።
ግባችን ከከባድ ኃጢአቶችም ሆነ ቀለል ተደርገው ከሚታዩ መጥፎ ድርጊቶች መራቅ ነው።
እርግጥ ከእነዚህ ድርጊቶች ሙሉ በሙሉ መራቅ አንችልም።
ያም ቢሆን እንደ ጳውሎስ ይህን ለማድረግ መጣር ይኖርብናል።
ጳውሎስ ወንድሞቹን ኃጢአት ለሰውነታችሁ ምኞት ተገዢ እንድትሆኑ በማድረግ ሟች በሆነው ሰውነታችሁ ላይ መንገሡን እንዲቀጥል አትፍቀዱ በማለት አሳስቧቸዋል።
ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱ የሚያበቃበት ጊዜ እንደሚመጣና ሥራውን ሌሎች እንደሚረከቡት ያውቅ ነበር።
ደቀ መዛሙርቱ ፍጹም ባይሆኑም እንኳ በእነሱ ላይ ይተማመን ስለነበር ከእሱ የሚበልጥ ሥራ እንደሚያከናውኑ ነግሯቸዋል።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በሚገባ ያሠለጠናቸው ሲሆን እነሱም በወቅቱ ይታወቅ በነበረው ዓለም ምሥራቹን ከዳር እስከ ዳር አዳርሰዋል።
ኢየሱስ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ከሰጠ በኋላ ትንሣኤ አግኝቶ ወደ ሰማይ ተመልሷል፤ በዚያም ከየትኛውም መስተዳድር፣ ሥልጣን፣ ኃይልና ጌትነት እጅግ የላቀ ቦታ ተሰጥቶታል።
እኛም አርማጌዶን ከመምጣቱ በፊት ታማኝ ሆነን ከሞትን ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ ከሞት እንነሳለን፤ በዚያ ወቅት እያንዳንዳችን የሚያስደስተንን ሥራ እንሠራለን።
እስከዚያው ድረስ ግን ሁላችንም የምናከናውነው በጣም አስፈላጊ ሥራ አለ፤ ይህም ምሥራቹን የመስበኩና ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ ነው።
እንግዲያው ወጣቶችም ሆንን በዕድሜ የገፋን፣ ምንጊዜም የጌታ ሥራ የበዛልን እንሁን።
አንድ አዲስ ኃላፊነት ከመቀበላችን በፊት በጸሎት በመታገዝ ያለንበትን ሁኔታ በሐቀኝነት መመርመራችን አቅማችንን ያላገናዘበ ነገር ከማድረግ እንድንቆጠብ ይረዳናል።
ልካችንን ማወቃችን ከአቅማችን በላይ የሆነን ነገር አልችልም ማለት እንዲቀለን ያደርጋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ጌድዮን ከሚናገረው ዘገባ መመልከት እንደሚቻለው አንድ አዲስ ኃላፊነት ስንቀበል ሊሳካልን የሚችለው የይሖዋን አመራርና በረከት ካገኘን ብቻ ነው።
ይሖዋም ቢሆን ልካችንን አውቀን ከእሱ ጋር እንድንሄድ ግብዣ አቅርቦልናል።
በመሆኑም ምንጊዜም ቢሆን አዲስ ኃላፊነት ስንቀበል ወደ ይሖዋ መጸለይ እንዲሁም እሱ በቃሉና በድርጅቱ አማካኝነት የሚሰጠንን መመሪያ በጥንቃቄ መመርመር ይኖርብናል።
አረማመዳችን ፍጹም ከሆነው የይሖዋ እርምጃ ጋር እንዲስማማ ማድረግን መማር አለብን።
ታላቅ የሚያደርገን የይሖዋ ትሕትና እንጂ የእኛ ችሎታ እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርብናል።
ልካችንን አውቀን ከአምላክ ጋር መሄዳችን ራሳችንን ከሚገባው በላይ ከፍ አድርገን ወይም በጣም ዝቅ አድርገን እንዳንመለከት ይረዳናል።
ውስጣዊ ሰላም ካለን ከቤተሰባችንም ሆነ ከጉባኤያችን አባላት ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ጥረት እናደርጋለን።
ይሁንና እኛም ሆንን ወንድሞቻችን ፍጽምና ይጎድለናል።
በዚህም ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ፤ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመን ከወንድምህ ጋር ታረቅ የሚለውን የኢየሱስ ምክር ተግባራዊ ማድረግ እንዳለብን ተምረናል።
ወንድሞቻችንም ሰላም የሚሰጠው አምላክ አገልጋዮች መሆናቸውን ማስታወሳችን ይህን ማድረግ ቀላል እንዲሆንልን አስተዋጽኦ ያበረክታል።
በዋጋ ሊተመን የማይችል ሌላም ዓይነት ሰላም አለ።
በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ከፈጣሪያችን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ያስችለናል።
ኢሳይያስ ስለ ይሖዋ ሲናገር ሙሉ በሙሉ በአንተ የሚመኩትን ትጠብቃለህ፤ በአንተ ስለሚታመኑ ዘላቂ ሰላም ትሰጣቸዋለህ ብሎ ነበር፤ ይህ ትንቢት በኢሳይያስ ዘመን ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን በዘመናችንም በላቀ ሁኔታ እየተፈጸመ ነው።
የሰይጣን ክፉ ሥርዓት ሊጠፋ በተቃረበበትና በጨለማ በተዋጠው በመጨረሻው ቀን ውስጥም እንኳ ይሖዋ ሕዝቡን እየባረከ ነው።
እውነተኛ አገልጋዮቹ በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ሐሴት እንዲያደርጉና የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ እንዲያገኙ እያደረገ ነው።
ኢየሱስ ቃል በገባው መሠረት፣ ይሖዋ በዛሬው ጊዜ አፍቃሪ በሆኑ ወንድሞችና እህቶች በተሞላ ዓለም አቀፋዊ መንፈሳዊ ቤተሰብ ውስጥ እንድንታቀፍ በማድረግ ወሮታ ከፍሎናል።
ከዚህም ሌላ አምላክን ከልባቸው የሚፈልጉ ሁሉ የአእምሮ ሰላም፣ እርካታና ደስታ ስላላቸው ወደር የሌለው ሽልማት እያገኙ ነው።
የአምላክን ፈቃድ ከፈጸምክ የተስፋው ቃል ሲፈጸም እንደምታይ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።
እንግዲያው እምነታችንን ማጠናከራችንን እና ለይሖዋ እንደምናደርገው በማሰብ በሙሉ ነፍሳችን ማገልገላችንን እንቀጥል።
ሽልማታችንን የምናገኘው ከይሖዋ ዘንድ እንደሆነ በማሰብ ይህን ማድረግ እንችላለን።
ብዙ ሰዎች እኛን የሚመዝኑን ውጫዊ ገጽታችንን ተመልክተው ነው።
በመሆኑም የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን ለእኛ የሚመቸንንና የምንወደውን ነገር ከመልበስ ባለፈ ልናስብበት የሚገባ ነገር አለ።
በአምላክ ቃል ውስጥ የሰፈሩት መሠረታዊ ሥርዓቶች፣ ሰውነት ላይ የሚጣበቅና ገላን የሚያጋልጥ ወይም የፆታ ስሜት የሚያነሳሳ ልብስ ከመልበስ እንድንቆጠብ ይገፋፉናል።
ይህም ሲባል እርቃንን የሚያጋልጡ ወይም የሰውነትን ቅርጽ አጉልተው የሚያሳዩ ልብሶችን ማስወገድ አለብን ማለት ነው።
አለባበሳችን ሌሎችን የሚያሸማቅቅ ወይም ዓይናቸውን የት እንደሚያሳርፉ እንዲጨንቃቸው የሚያደርግ መሆን የለበትም።
ሥርዓታማ፣ ንጹሕና ልከኛ አለባበስ ካለን ሰዎች ያከብሩናል፤ እንዲሁም ወደምናመልከው አምላክ ለመቅረብ ይነሳሳሉ።
ተገቢ የሆነ አለባበስ ለይሖዋ ድርጅትም ክብር ያመጣል።
ይህም ሰዎች ለምንነግራቸው ሕይወት አድን መልእክት ጆሮ እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል።
የምታነጋግሩት ሰው ምን ብሎ እንደሚያምን እንደምታውቁ አድርጋችሁ አታስቡ።
አንዳንዶች በዝግመተ ለውጥ እንደሚያምኑ ቢናገሩም አምላክ እንዳለም ያስባሉ።
አምላክ፣ ሕይወት ያላቸውን የተለያዩ ነገሮች ለመፍጠር ዝግመተ ለውጥን እንደተጠቀመ ይሰማቸዋል።
ሌሎች ደግሞ በዝግመተ ለውጥ እንደሚያምኑ የሚናገሩት ይህ ጽንሰ ሐሳብ እውነት ባይሆን ኖሮ በትምህርት ቤት አንማረውም ነበር ብለው ስለሚያስቡ ነው።
አንዳንዶች በአምላክ ማመን ያቆሙት በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸመው ነገር ቅር ስላሰኛቸው ነው።
በመሆኑም ስለ ሕይወት አመጣጥ ከአንድ ሰው ጋር ስትወያዩ በቅድሚያ ጥያቄ መጠየቁ የተሻለ ነው።
ግለሰቡ ምን ብሎ እንደሚያምን ለማወቅ ጥረት አድርጉ።
ምክንያታዊ ብሎም ለማዳመጥ ፈቃደኛ ከሆናችሁ ግለሰቡም እናንተ የምትናገሩትን ለማዳመጥ ሊነሳሳ ይችላል።
አንድ ሰው በፍጥረት በማመናችሁ እየተቻችሁ እንዳለ ከተሰማችሁ፣ ፈጣሪ ሳይኖር ሕይወት እንዴት ሊገኝ እንደቻለ እንዲያስረዳችሁ ልትጠይቁት ትችላላችሁ።
የመጀመሪያው ሕይወት ያለው ነገር በዝግመተ ለውጥ አማካኝነት ወደ ሌላ ሕያው ነገር መለወጥ እንዲችል መራባት ማለትም ራሱን ማባዛት መቻል አለበት።
አንድ የኬሚስትሪ ፕሮፌሰር እንዲህ ብለዋል፦ አንድ ሰው፣ ሕይወት ካላቸው ነገሮች መካከል ውስብስብ የማይባለው እንኳ ምን ያህል ውስብስብ እንደሆነ ሲመለከት በጣም መገረሙ አይቀርም።
ጳውሎስ ይህን የተናገረው እነማንን በአእምሮው ይዞ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ባንችልም አምላክን በመታዘዛቸውና የእሱን ፈቃድ በመፈጸማቸው በድንጋይ ተወግረው ስለሞቱት ስለ ናቡቴ እና ስለ ዘካርያስ መናገሩ ሊሆን ይችላል።
ዳንኤልና ጓደኞቹም ንጹሕ አቋማቸውን ቢያላሉ ነፃ መሆን የሚችሉበት አጋጣሚ ነበራቸው።