text
stringlengths
4
267
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ሕዝብ መልካም ሁኔታ እንዲገጥመው አትጸልይ።
በሚጾሙበት ጊዜ የሚያቀርቡትን ልመና አልሰማም፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የእህል መባዎች በሚያቀርቡበት ጊዜም በእነሱ ደስ አልሰኝም፤ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር አጠፋቸዋለሁና።”
በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሆ፣ ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ለረሃብም አትዳረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በዚህ ስፍራ እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይሏቸዋል።”
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ። እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኳቸውም ወይም አላናገርኳቸውም። የሐሰት ራእይን፣ ከንቱ የሆነ ሟርትንና የገዛ ልባቸውን ማታለያ ይተነብዩላችኋል።
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ሳልካቸው በስሜ የሚተነብዩትና በዚህች ምድር ላይ ሰይፍም ሆነ ረሃብ አይከሰትም የሚሉት እነዚህ ነቢያት በሰይፍና በረሃብ ይጠፋሉ።
የሚተነብዩለትም ሕዝብ ከረሃቡና ከሰይፉ የተነሳ አስከሬኑ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ይጣላል፤ እነሱን፣ አዎ እነሱን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቀብራቸው አይኖርም፤ የሚገባቸውን ጥፋት በላያቸው ላይ አመጣለሁና።’
“ይህን ቃል ንገራቸው፦‘ዓይኖቼ ሌት ተቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ፤ድንግሊቱ የሕዝቤ ሴት ልጅ እጅግ አስከፊ በሆነ ቁስል ሙሉ በሙሉ ደቃለችና፤ደግሞም ተሰብራለች።
ወደ መስክ ብወጣ፣እነሆ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ! ወደ ከተማም ብገባ፣በረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎችን አያለሁ! ነቢዩና ካህኑ በማያውቁት አገር ተቅበዝብዘዋልና።’”
ይሁዳን ጨርሶ ትተኸዋል? ወይስ ጽዮንን ተጸይፈሃታል? ታዲያ ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ የመታኸን ለምንድን ነው? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ!
ይሖዋ ሆይ፣ ክፋት መሥራታችንን፣አባቶቻችንም በደል መፈጸማቸውን አምነን እንቀበላለን፤በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና።
ስለ ስምህ ስትል አትናቀን፤ክብር የተላበሰውን ዙፋንህን አታቃልል። ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አስታውስ፤ አታፍርሰውም።
ከንቱ ከሆኑት የአሕዛብ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለ?ሰማያትስ በራሳቸው ዝናብ ማውረድ ይችላሉ? አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ይህን የምታደርገው አንተ ብቻ አይደለህም? እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረግከው አንተ ብቻ ስለሆንክአንተን ተስፋ እናደርጋለን።
በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።
በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ።’”
“‘የኢዮዓቄምን ልጅ፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት የተወሰዱትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።’”
ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በካህናቱ ፊትና በይሖዋ ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት ነቢዩ ሃናንያህን አናገረው።
ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ አለ፦ “አሜን! ይሖዋ ይህን ያድርግ! የይሖዋን ቤት ዕቃዎችና በግዞት የተወሰዱትን ሰዎች ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ እንዲመለሱ በማድረግ ይሖዋ የተነበይከውን ቃል ይፈጽም!
ይሁንና እባክህ፣ በጆሮህና በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ የምናገረውን ይህን መልእክት ስማ።
በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩት ነቢያት፣ ብዙ አገሮችና ታላላቅ መንግሥታት ስለሚያጋጥማቸው ጦርነት እንዲሁም ስለሚደርስባቸው ጥፋትና ቸነፈር ይተነብዩ ነበር።
አንድ ነቢይ ስለ ሰላም ትንቢት ከተናገረና ነቢዩ የተናገረው ቃል ከተፈጸመ ይሖዋ ይህን ነቢይ በእርግጥ እንደላከው ይታወቃል።”
በዚህ ጊዜ ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ሰበረው።
ከዚያም ሃናንያህ በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ልክ እንዲሁ እኔም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነጾርን ቀንበር ከብሔራት ሁሉ አንገት ላይ እሰብራለሁ።’” ነቢዩ ኤርምያስም ትቶት ሄደ።
ነቢዩ ሃናንያህ ቀንበሩን ከነቢዩ ኤርምያስ አንገት ላይ ወስዶ ከሰበረው በኋላ ይህ የይሖዋ መልእክት ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“ሄደህ ሃናንያህን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የእንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤ ይሁንና በእሱ ምትክ የብረት ቀንበር ትሠራለህ።”
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እንዲያገለግሉ በእነዚህ ሁሉ ብሔራት አንገት ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነሱም ያገለግሉታል። የዱር አራዊትንም እንኳ እሰጠዋለሁ።”’”
ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ ነቢዩ ሃናንያህን እንዲህ አለው፦ “ሃናንያህ ሆይ፣ እባክህ ስማ! ይሖዋ ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ። በይሖዋ ላይ ዓመፅ ስላነሳሳህ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’”
በመሆኑም ነቢዩ ሃናንያህ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ወርደህ ይህን መልእክት ተናገር።
እንዲህ በል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የተቀመጥከው የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ እንዲሁም በእነዚህ በሮች የሚገባው ሕዝብህ የይሖዋን ቃል ስሙ።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለፍትሕና ለጽድቅ ቁሙ። የተዘረፈውን ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አታንገላቱ፤ አባት የሌለውን ልጅ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።
ይህን ቃል በሚገባ ብትጠብቁ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታት በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው ከአገልጋዮቻቸውና ከሕዝቦቻቸው ጋር በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ።”’
“‘ይህን ቃል ባትታዘዙ ግን’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ይህ ቤት እንደሚወድም በራሴ እምላለሁ።’
“ይሖዋ የይሁዳን ንጉሥ ቤት አስመልክቶ እንዲህ ይላልና፦‘አንተ ለእኔ እንደ ጊልያድናእንደ ሊባኖስ ተራራ አናት ነህ። ይሁንና ምድረ በዳ አደርግሃለሁ፤ከተሞችህን በሙሉ ሰው አልባ አደርጋቸዋለሁ።
በአንተ ላይ ጥፋት የሚያደርሱ ሰዎችን፣እያንዳንዳቸውን ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር እሾማለሁ። ምርጥ የሆኑ አርዘ ሊባኖሶችህን ይቆርጣሉ፤ለእሳትም ይማግዷቸዋል።
“‘ብዙ ብሔራትም በዚህች ከተማ በኩል ያልፋሉ፤ እርስ በርሳቸውም “ይሖዋ በዚህች ታላቅ ከተማ ላይ ይህን ያደረገው ለምንድን ነው?” ይባባላሉ።
እነሱም እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፦ “የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለሰገዱና እነሱን ስላገለገሉ ነው።”’
ለሞተው ሰው አታልቅሱ፤ደግሞም አትዘኑለት። ይልቁንም በግዞት ለተወሰደው አምርራችሁ አልቅሱ፤ከእንግዲህ የትውልድ አገሩን ለማየት አይመለስምና።
“በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለነገሠው፣ ከዚህም ቦታ ስለሄደው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሻሉም ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከእንግዲህ ወደዚያ አይመለስም።
በግዞት በተወሰደበት በዚያው ስፍራ ይሞታል እንጂ ይህን ምድር ዳግመኛ አያይም።’
ጽድቅን በሚጻረር መንገድ ቤቱን ለሚገነባ፣ፍትሕን በማዛባት ደርብ ለሚሠራ፣የወገኑን ጉልበት እንዲሁ ለሚበዘብዝናደሞዙን ለማይከፍለው ወዮለት፤
‘ለራሴ ሰፊ ቤትናየተንጣለለ ደርብ እገነባለሁ። መስኮቶች እንዲኖረው አደርጋለሁ፤በአርዘ ሊባኖስም እለብጠዋለሁ፤ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ’ ለሚል ወዮለት!
በአርዘ ሊባኖስ እንጨት ከሌሎች ስለምትበልጥ በንግሥና የምትቀጥል ይመስልሃል? አባትህም ቢሆን ይበላና ይጠጣ ነበር፤ሆኖም ለፍትሕና ለጽድቅ ቆሟል፤እንዲህ በማድረጉም ተሳክቶለት ነበር።
ለተጎሳቆለው ሰውና ለድሃው ተሟግቷል፤ስለዚህ መልካም ሆኖለት ነበር። ‘እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለም?’ ይላል ይሖዋ።
‘አንተ ግን ዓይንህና ልብህ ያረፈው አላግባብ በምታገኘው ጥቅም፣ንጹሕ ደም በማፍሰስእንዲሁም በማጭበርበርና በቅሚያ ላይ ብቻ ነው።’
“ስለዚህ ይሖዋ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮዓቄም እንዲህ ይላል፦‘“ወይኔ ወንድሜን! ወይኔ እህቴን!” ብለው አያለቅሱለትም። “ወይኔ ጌታዬን! ክብሩ ሁሉ እንዲህ ይጥፋ!” ብለው አያለቅሱለትም።
አህያ እንደሚቀበረው ይቀበራል፤ከኢየሩሳሌም በሮች ውጭጎትተው ይጥሉታል።’
ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤በባሳን ድምፅሽን አሰሚ፤በአባሪም ሆነሽ ጩኺ፤አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ደቀዋልና።
ተማምነሽ በተቀመጥሽበት ጊዜ አነጋገርኩሽ። አንቺ ግን ‘አልታዘዝም’ አልሽ። ከልጅነትሽ ጀምሮ ይህን ጎዳና ተከተልሽ፤ቃሌን አልታዘዝሽምና።
ነፋስ እረኞችሽን በሙሉ ይነዳቸዋል፤አጥብቀው የሚወዱሽም በግዞት ይወሰዳሉ። በዚያን ጊዜ ከሚደርስብሽ ጥፋት ሁሉ የተነሳ ታፍሪያለሽ፤ ውርደትም ትከናነቢያለሽ።
አንቺ በሊባኖስ የምትኖሪ፣በአርዘ ሊባኖሶች መካከል ተደላድለሽ የተቀመጥሽ፣ጣር ሲይዝሽ፣አዎ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ጭንቅ ሲይዝሽ ምንኛ ታቃስቺ ይሆን!”
“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘አንተ የይሁዳ ንጉሥ፣ የኢዮዓቄም ልጅ፣ ኮንያሁ በቀኝ እጄ እንዳለ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ ከዚያ አውጥቼ እጥልሃለሁ!
ሕይወትህን ለማጥፋት በሚሹ ሰዎች እጅ፣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅና በከለዳውያን እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።
አንተንና የወለደችህን እናትህን ወዳልተወለዳችሁበት፣ ወደ ሌላ አገር እወረውራችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ።
ወደሚናፍቋትም ምድር ፈጽሞ አይመለሱም።
ኮንያሁ የተባለው ይህ ሰው የተናቀና የተሰበረ ገንቦ፣ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነው? እሱም ሆነ ዘሮቹ ወደማያውቋት ምድር የተወረወሩትናየተጣሉት ለምንድን ነው?’
ምድር፣ ምድር፣ አንቺ ምድር ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሚ።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ሰው፣ ልጅ እንደሌለውናበሕይወት ዘመኑ ሁሉ ምንም እንደማይሳካለት አድርጋችሁ መዝግቡት፤ከዘሮቹ መካከል አንዱም እንኳ አይሳካለትምና፤በዳዊት ዙፋን ላይ አይቀመጥም እንዲሁም ይሁዳን ዳግመኛ አይገዛም።’”
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙ እንኳ ለዚህ ሕዝብ አልራራም። ከፊቴ አስወጣቸው። ይሂዱ።
እነሱም ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ በመቅሰፍት እንዲሞት ይሂድ፤ ሰይፍ የሚገባው ሁሉ በሰይፍ ይሙት፤ ረሃብ የሚገባው ሁሉ በረሃብ ይሙት፤ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ደግሞ ተማርኮ ይወሰድ!”’
“‘እኔም አራት ዓይነት ጥፋት አዝባቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ጎትቶ ለመውሰድ ውሾች እንዲሁም ለመሰልቀጥና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።
የይሁዳ ንጉሥ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ከፈጸመው ድርጊት የተነሳ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ማን ይራራልሻል?ማንስ ያዝንልሻል?ደህንነትሽንስ ማን ጎራ ብሎ ይጠይቃል?’
‘ትተሽኛል’ ይላል ይሖዋ። ‘አሁንም ጀርባሽን ሰጥተሽኛል። ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ። ለአንቺ አዘኔታ ማሳየት ታክቶኛል።
በምድሪቱ በሮች፣ በመንሽ እበትናቸዋለሁ። የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ። ሕዝቤን አጠፋዋለሁ፤ከመንገዱ ለመመለስ አሻፈረኝ ብሏልና።
መበለቶቻቸው በፊቴ ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይበዛሉ። በእነሱ ይኸውም በእናቶችና በወጣት ወንዶች ላይ በቀትር አጥፊ አመጣለሁ። ከባድ ጭንቀትና ሽብር በድንገት አመጣባቸዋለሁ።
ሰባት ልጆች የወለደችው ሴት ተዝለፍልፋለች፤ትንፋሽ አጥሯት ታጣጥራለች። ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ጠልቃለች፤ይህም ኀፍረትና ውርደት አስከትሎባታል።’ ‘ከእነሱ መካከል የተረፉትንም ጥቂት ሰዎችበጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”
እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ!በምድሪቱ ሁሉ ላይ የጠብና የጭቅጭቅ መንስኤ የሆንኩትን እኔን ወልደሻልና። እኔ ለማንም አላበደርኩም፤ ከማንም አልተበደርኩም፤ይሁንና ሁሉም ይረግሙኛል።
ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ በእርግጥ ለአንተ መልካም ነገር አደርግልሃለሁ፤በጥፋትና በጭንቀት ጊዜበአንተና በጠላት መካከል ጣልቃ ገብቼ እረዳሃለሁ።
ሰው ብረትን ይኸውም ከሰሜን የመጣን ብረትናመዳብን መሰባበር ይችላል?
በመላው ክልልህ ከፈጸምከው ኃጢአት ሁሉ የተነሳንብረትህንና ውድ ሀብትህን፣ ያለዋጋ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።
እነዚህን ነገሮች ጠላቶችህ ወደማታውቀው አገር እንዲወስዷቸውአሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ቁጣዬ እሳት አስነስቷልና፤በእናንተም ላይ እየነደደ ነው።”
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ታውቃለህ፤አስበኝ፤ ትኩረትህንም ወደ እኔ አዙር። አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ። ቁጣህን በማዘግየት እንድጠፋ አታድርግ። ይህን ነቀፋ የተሸከምኩት ለአንተ ስል እንደሆነ እወቅ።
ቃልህ ተገኝቷል፤ እኔም በልቼዋለሁ፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ቃልህ ሐሴት፣ ለልቤም ደስታ ሆነልኝ።
ፈንጠዝያ ከሚወዱ ሰዎች ጋር አልተቀመጥኩም፤ ከእነሱም ጋር ሐሴት አላደረግኩም። እጅህ በእኔ ላይ ስለሆነ ብቻዬን እቀመጣለሁ፤በቁጣ ሞልተኸኛልና።
ሕመሜ ሥር የሰደደው፣ ቁስሌም የማይፈወስ የሆነው ለምንድን ነው? ጨርሶ አልድን ብሏል። እምነት ሊጣልበት እንደማይችልየሚያታልል የውኃ ምንጭ ትሆንብኛለህ?
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ብትመለስ፣ እኔም ወደ ቀድሞው ሁኔታህ እመልስሃለሁ፤በፊቴም ትቆማለህ። ውድ የሆነውን ነገር ከማይረባው ነገር ብትለይ፣እንደ አፌ ትሆናለህ። እነሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂአንተ ወደ እነሱ አትመለስም።”
“ለዚህ ሕዝብ ጠንካራ የመዳብ ቅጥር አደርግሃለሁ። እነሱ በእርግጥ ይዋጉሃል፤ሆኖም በአንተ ላይ አያይሉም፤እኔ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።
“ከክፉዎች እጅ እታደግሃለሁ፤ከጨካኞችም መዳፍ እቤዥሃለሁ።”
ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም? ወራሽስ የለውም? ታዲያ ማልካም፣ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው? ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”
“‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ ላይየጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። ‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤በእሷም ሥር ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’ ‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’ ይላል ይሖዋ።
‘ሃሽቦን ሆይ፣ ጋይ ስለወደመች ዋይ ዋይ በዪ! በራባ ሥር ያላችሁ ከተሞች ሆይ፣ ጩኹ። ማቅ ልበሱ። ማልካም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋርበግዞት ስለሚወሰድከድንጋይ በተሠራ የእንስሳት ማጎሪያ ውስጥ ወዲያ ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ።
አንቺ በውድ ሀብቶችሽ የምትታመኚ፣“ማን ይነካኛል?” የምትዪከዳተኛ የሆንሽ ሴት ልጅ ሆይ፣በሸለቆዎችሽ ይኸውም ውኃ በሚንዶለዶልበት ሜዳሽ የምትኩራሪው ለምንድን ነው?’”
“‘እነሆ፣ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ፣በአንቺ ላይ የሚያስፈራ ነገር አመጣለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ። ‘እናንተም በየአቅጣጫው ትበታተናላችሁ፤የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።’”
“‘ከዚያ በኋላ ግን ተማርከው የተወሰዱትን አሞናውያንን እሰበስባለሁ’ ይላል ይሖዋ።”
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቷል? ጥሩ ምክርስ ከአስተዋዮች ጠፍቷል? ጥበባቸውስ ተበላሽቷል?
የዴዳን ነዋሪዎች ሆይ፣ ሽሹ! ወደ ኋላ ተመለሱ! ወደ ጥልቁ ወርዳችሁ ተደበቁ! ትኩረቴን ወደ እሱ በማዞርበት ጊዜበኤሳው ላይ ጥፋት አመጣለሁና።
ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም? ሌቦች በሌሊት ቢመጡ፣የሚዘርፉት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ነው።
እኔ ግን ኤሳውን እርቃኑን አስቀረዋለሁ። መደበቅ እንዳይችልመሸሸጊያ ቦታዎቹን እገልጣለሁ። ልጆቹ፣ ወንድሞቹና ጎረቤቶቹ በሙሉ ይጠፋሉ፤እሱም ከሕልውና ውጭ ይሆናል።
አባት የሌላቸው ልጆችህን ተዋቸው፤እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ፤መበለቶችህም በእኔ ይታመናሉ።”
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፣ ጽዋውን እንዲጠጡ ያልተፈረደባቸውም እንኳ ለመጠጣት የሚገደዱ ከሆነ አንተ እንዴት ከቅጣት ታመልጣለህ? ከቅጣት አታመልጥም፤ ጽዋውን ትጠጣለህና።”
“በራሴ ምያለሁና” ይላል ይሖዋ፤ “ቦስራ አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤ ለነቀፋ፣ ለጥፋትና ለእርግማንም ትዳረጋለች፤ ከተሞቿም ሁሉ ለዘለቄታው ባድማ ይሆናሉ።”
ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ በእሷም ላይ ውጡ፤ለጦርነት ተዘጋጁ።”
“እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር፣በሰዎችም መካከል የተናቅክ አድርጌሃለሁና።
አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣በጣም ረጅሙን ኮረብታ የያዝክ ሆይ፣የነዛኸው ሽብርናየልብህ እብሪት አታሎሃል። ጎጆህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ላይ ብትሠራም፣እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ።
“ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች። በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል።
ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።
“እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርረዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው?
ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በኤዶም ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና በቴማን ነዋሪዎች ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ፦ ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም። ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል።