text
stringlengths
4
267
‘ምድርን እንዲሁም በምድር ላይ ያሉትን ሰዎችና እንስሳት በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ የሠራሁት እኔ ነኝ፤ ለወደድኩትም ሰጥቼዋለሁ።
አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ።
የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’
“‘“‘የትኛውም ብሔር ወይም መንግሥት የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ለማገልገል ፈቃደኛ ባይሆን እንዲሁም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ለማስገባት እንቢተኛ ቢሆን ያንን ብሔር በእሱ እጅ ፈጽሞ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እቀጣዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።
“‘“‘ስለዚህ “የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም” የሚሏችሁን በመካከላችሁ ያሉትን ነቢያት፣ ሟርተኞች፣ ሕልም አላሚዎች፣ አስማተኞችና መተተኞች አትስሙ።
የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ ከምድራችሁ ተፈናቅላችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ትወሰዳላችሁ፤ እኔም እበትናችኋለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።
“‘“‘ሆኖም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር የሚያስገባንና እሱን የሚያገለግልን ብሔር ምድሪቱን እንዲያርስና በዚያ እንዲኖር በገዛ ምድሩ እንዲቀር አደርገዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።”’”
ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ተመሳሳይ ነገር ነገርኩት፤ እንዲህም አልኩት፦ “አንገታችሁን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር አስገቡ፤ እሱንና ሕዝቡንም አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
ይሖዋ የባቢሎንን ንጉሥ የማያገለግልን ብሔር አስመልክቶ በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ አንተም ሆንክ ሕዝብህ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ለምን ታልቃላችሁ?
‘የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም’ የሚሏችሁን ነቢያት ቃል አትስሙ፤ ምክንያቱም የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነው።
“‘እኔ አልላክኋቸውምና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱ ግን በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ እናንተንና የሚተነብዩላችሁን ነቢያት እበትናለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’”
ደግሞም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልኩ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“እነሆ፣ የይሖዋ ቤት ዕቃዎች ከባቢሎን በቅርቡ ይመለሳሉ!” እያሉ የሚተነብዩላችሁን የነቢያታችሁን ቃል አትስሙ፤ የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና።
እነሱን አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ። ይህች ከተማ ለምን ትፈራርስ?
ሆኖም እነሱ ነቢያት ከሆኑና የይሖዋ ቃል እነሱ ጋር ካለ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና በኢየሩሳሌም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ እስቲ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ይለምኑ።’
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ዓምዶቹ፣ ስለ ባሕሩ፣ ስለ ዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎቹና በዚህች ከተማ ስለቀሩት የተረፉ ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፦
እነዚህ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የኢዮዓቄምን ልጅ የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባጋዘበት ወቅት ሳይወስዳቸው የቀሩ ነገሮች ናቸው፤
አዎ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ በይሖዋ ቤት፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤትና በኢየሩሳሌም ስለቀሩት ዕቃዎች እንዲህ ይላል፦
‘“ትኩረቴን ወደ እነሱ እስከማዞርበት ጊዜ ድረስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ በዚያም ይቆያሉ” ይላል ይሖዋ። “ከዚያ በኋላ አመጣቸዋለሁ፤ ወደዚህ ስፍራም እመልሳቸዋለሁ።”’”
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“ሂድና ኢየሩሳሌም ጆሮዋ እየሰማ ይህን አውጅ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በወጣትነትሽ ጊዜ ለአምላክ ያደርሽ እንደነበርሽ፣ደግሞም ለጋብቻ በታጨሽበት ጊዜ ያሳየሽውን ፍቅር፣ዘር በማይዘራበት ምድር፣ በምድረ በዳእንዴት እንደተከተልሽኝ በሚገባ አስታውሳለሁ።
እስራኤል ለይሖዋ የተቀደሰ፣ የመከሩ በኩር ነበር።”’ ‘እሱን የሚውጥ ሁሉ በደለኛ ይሆናል። በእነሱም ላይ ጥፋት ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”
የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ፣የይሖዋን ቃል ስሙ።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ ከእኔ እጅግ የራቁት፣ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የተከተሉትናእነሱ ራሳቸው ከንቱ የሆኑት ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
እነሱ ‘ከግብፅ ምድር ያወጣን፣በምድረ በዳ፣ በረሃማ በሆነናጉድጓድ ባለበት ምድር፣በድርቅ በተጠቃና ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ምድርእንዲሁም ማንም ሰው በማይጓዝበትናሰው በማይኖርበት ምድርየመራን ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም።
በዚያን ጊዜ እኔ ፍሬዋንና በውስጧ ያሉትን ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንድትበሉየፍራፍሬ ዛፎች ወዳሉባት ምድር አመጣኋችሁ። እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ርስቴንም አስጸያፊ ነገር አደረጋችሁት።
ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤ ሕጉ በአደራ የተሰጣቸውም እኔን አላወቁም፤እረኞቹ በእኔ ላይ ዓመፁ፤ነቢያቱ በባአል ስም ትንቢት ተናገሩ፤ምንም ጥቅም የማያስገኙላቸውንም አማልክት ተከተሉ።
‘በመሆኑም ከእናንተ ጋር ገና እሟገታለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ከልጅ ልጆቻችሁም ጋር እሟገታለሁ።’
‘እስቲ ወደ ኪቲም የባሕር ዳርቻዎች ተሻግራችሁ ተመልከቱ። አዎ፣ መልእክተኞችን ወደ ቄዳር ልካችሁ ጉዳዩን በጥሞና መርምሩ፤እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ እንደሆነ እዩ።
አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ? የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።
እናንተ ሰማያት በዚህ ተደነቁ፤በታላቅ ድንጋጤም ተርበትበቱ’ ይላል ይሖዋ፤
‘ምክንያቱም ሕዝቤ ሁለት መጥፎ ነገሮች ፈጽመዋል፦ የሕያው ውኃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተውየውኃ ማጠራቀሚያዎችን ይኸውም ውኃ መያዝ የማይችሉና የሚያፈሱየውኃ ማጠራቀሚያዎችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።’
‘እስራኤል፣ አገልጋይ ወይም የቤት ውልድ ባሪያ ነው? ታዲያ እንዲበዘበዝ የተደረገው ለምንድን ነው?
ደቦል አንበሶች በእሱ ላይ አገሡ፤በኃይለኛ ድምፅ ጮኹበት። ምድሩን የሚያስፈራ ቦታ አደረጉት። ከተሞቹ ማንም እንዳይኖርባቸው በእሳት ተቃጠሉ።
የኖፍና የጣፍነስ ሕዝቦች፣ መሃል አናትሽን ይበላሉ።
አምላክሽ ይሖዋ በመንገዱ በመራሽ ወቅትእሱን በመተውይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽም?
ደግሞስ የሺሆርን ውኃዎች ለመጠጣትወደ ግብፅ የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው? የወንዙን ውኃዎች ለመጠጣትወደ አሦር የሚወስደውን መንገድ የመረጥሽው ለምንድን ነው?
ከክፋትሽ ትምህርት ልታገኚ ይገባል፤ታማኝነት በማጉደል የፈጸምሻቸው ድርጊቶችም ወቀሳ ያስከትሉብሻል። አምላክሽን ይሖዋን መተውሽመጥፎና መራራ እንደሆነ ማወቅና መገንዘብ ይኖርብሻል፤እኔን ፈጽሞ አልፈራሽም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ።
‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ። አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥርለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።
እኔ፣ እንደ ምርጥ ቀይ የወይን ተክል፣ ሙሉ በሙሉ ንጹሕ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ታዲያ በፊቴ እንዲህ ተለውጠሽ የተበላሸ ባዕድ የወይን ተክል የሆንሽው እንዴት ነው?’
‘በሶዳ ብትታጠቢና ብዛት ያለው እንዶድ ብትጠቀሚ እንኳከበደልሽ የተነሳ ዕድፍሽ በፊቴ ይኖራል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
‘ራሴን አላረከስኩም። ባአልንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆው ውስጥ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ። ያደረግሽውን ነገር ልብ በይ። በመንገዷ ላይ ወዲያና ወዲህ እንደምትፋንንየደረሰች ፈጣን ግመል ነሽ፤
በምድረ በዳ መኖር እንደለመደች፣በፍትወቷ ነፋሱን እንደምታነፈንፍ የዱር አህያ ነሽ። ስሜቷ ሲነሳሳ ማን ሊመልሳት ይችላል? የሚፈልጓት ሁሉ እሷን ለማግኘት ብዙ ድካም አይጠይቅባቸውም። በመራቢያዋ ወቅት ያገኟታል።
እግርሽ እስኪነቃ አትዙሪ፤ጉሮሮሽም በውኃ ጥም አይቃጠል። አንቺ ግን ‘አይሆንም! ምንም ተስፋ የሌለው ነገር ነው! እኔ ከባዕዳን ጋር ፍቅር ይዞኛል፤እነሱንም እከተላለሁ’ አልሽ።
ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍር፣የእስራኤል ቤት ሰዎችም እንዲሁ አፍረዋል፤እነሱም ሆኑ ነገሥታታቸው፣ መኳንንታቸው፣ካህናታቸውና ነቢያታቸው ውርደት ተከናንበዋል።
ዛፉን ‘አንተ አባቴ ነህ’፤ ድንጋዩንም ‘የወለድከኝ አንተ ነህ’ ይላሉ። ለእኔ ግን ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጥተውኛል። ጥፋት ሲመጣባቸውም‘ተነስተህ አድነን!’ ይላሉ።
ለራስህ የሠራሃቸው አማልክት ታዲያ የት አሉ? ጥፋት ሲደርስብህ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ ይነሱ፤ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና።
‘አሁንም ከእኔ ጋር የምትሟገቱት ለምንድን ነው? ሁላችሁም በእኔ ላይ ያመፃችሁት ለምንድን ነው?’ ይላል ይሖዋ።
ልጆቻችሁን የመታሁት በከንቱ ነው። ለመታረም ፈቃደኞች አይደሉም፤የገዛ ራሳችሁ ሰይፍ እንደሚያደባ አንበሳነቢያታችሁን በልቷል።
የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ልብ በሉ። እኔ ለእስራኤል፣ እንደ ምድረ በዳወይም ድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠው ምድር ሆኛለሁ? የእኔ ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ‘እኛ ወደፈለግንበት እንሄዳለን። ከእንግዲህ ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላሉ?
ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን ትረሳለች? የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።
አንቺ ሴት፣ ፍቅረኛ ለማግኘት መንገድሽን ምንኛ በጥበብ አመቻቸሽ! የክፋትን መንገዶች ተምረሻል።
ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች ደም ቆሽሸዋል፤ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።
አንቺ ግን ‘እኔ ንጹሕ ነኝ። በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ተመልሷል’ ትያለሽ። ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ስለምትዪ፣በአንቺ ላይ ፍርድ አመጣለሁ።
መንገድሽን በመለዋወጥ የምትፈጽሚውን ድርጊት አቅልለሽ የምትመለከቺው ለምንድን ነው? በአሦር እንዳፈርሽ ሁሉበግብፅም ታፍሪያለሽ።
በዚህም የተነሳ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፤ይሖዋ የምትተማመኚባቸውን ነገሮች አስወግዷልና፤እነሱ ለስኬት አያበቁሽም።”
በግብፅ ምድር ይኸውም በሚግዶል፣ በጣፍነስ፣ በኖፍ እና በጳትሮስ ምድር ለሚኖሩ አይሁዳውያን ሁሉ እንዲነገር ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች በሙሉ ያመጣሁትን ጥፋት ሁሉ አይታችኋል፤ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው የፍርስራሽ ክምር ሆነዋል።
ይህም የሆነው እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ወደማታውቋቸው ሌሎች አማልክት ሄደው ለእነሱ መሥዋዕት በማቅረብና እነሱን በማገልገል እኔን ለማስቆጣት በፈጸሙት ክፉ ድርጊት የተነሳ ነው።
አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላክኋቸው፤ “እባካችሁ፣ እኔ የምጠላውን ይህን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ ላክኋቸው።
እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ከማቅረብ በመቆጠብም ከክፉ መንገዳቸው ለመመለስ ጆሯቸውን አልሰጡም።
በመሆኑም ቁጣዬና ንዴቴ ፈሰሰ፤ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎችም ላይ ነደደ፤ እነሱም ዛሬ እንደሚታዩት የፍርስራሽ ክምርና ጠፍ መሬት ሆነዋል።’
“አሁንም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት ሁሉ ከይሁዳ ጠፍተው ለራሳችሁ አንድም ቀሪ እንዳይተርፍ በራሳችሁ ላይ ለምን ታላቅ ጥፋት ታመጣላችሁ?
ለመኖር በሄዳችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ በእጃችሁ ሥራ የምታስቆጡኝ ለምንድን ነው? ትጠፋላችሁ፤ በምድር ብሔራትም ሁሉ መካከል ለእርግማንና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ።
በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አባቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ፣ የይሁዳ ነገሥታት የሠሩትን ክፉ ሥራና ሚስቶቻቸው የሠሩትን ክፉ ሥራ እንዲሁም እናንተ ራሳችሁ የሠራችሁትን ክፉ ሥራና ሚስቶቻችሁ የሠሩትን ክፉ ሥራ ረሳችሁት?
እነሱ እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ዝቅ አላደረጉም፤ የፍርሃትም ስሜት አላደረባቸውም፤ በእናንተና በአባቶቻችሁ ፊት ያኖርኩትን ሕጌንና ሥርዓቴንም አልተከተሉም።’
“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቆርጬ ተነስቻለሁ።
በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱትንም የይሁዳ ቀሪዎች እወስዳለሁ፤ ሁሉም በግብፅ ምድር ይጠፋሉ። በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ በረሃብ ያልቃሉ፤ በሰይፍና በረሃብ ይሞታሉ። ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ይዳረጋሉ፤ መቀጣጫም ይሆናሉ።
ኢየሩሳሌምን እንደቀጣሁ ሁሉ በግብፅ ምድር የሚኖሩትንም በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እቀጣለሁ።
በግብፅ ምድር ለመኖር የሄዱት የይሁዳ ቀሪዎችም አምልጠው ወይም በሕይወት ተርፈው ወደ ይሁዳ ምድር አይመለሱም። ወደዚያ ለመመለስና በዚያ ለመኖር ቢመኙም እንኳ ከጥቂት ሰዎች በስተቀር አምልጦ የሚመለስ አይኖርም።’”
ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርቡ እንደነበረ የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፣ ብዙ ሆነው የተሰበሰቡት ሚስቶቻቸው ሁሉ እንዲሁም በግብፅ ምድር ይኸውም በጳትሮስ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ለኤርምያስ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦
“በይሖዋ ስም የነገርከንን ቃል አንሰማም።
ይልቁንም አፋችን የተናገረውን ቃል ሁሉ መፈጸማችን አይቀርም፤ እኛና አባቶቻችን እንዲሁም ነገሥታታችንና መኳንንታችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እናደርግ እንደነበረው ‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት እናቀርባለን፤ ለእሷም የመጠጥ መባ እናፈሳለን፤ በዚያን ጊዜ እስክንጠግብ ድረስ እንበላና ተመችቶን እንኖር ነበር፤ ጥፋት የሚባል ነገርም አልገጠመንም።
‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት ማቅረብና የመጠጥ መባ ማፍሰስ ካቆምንበት ጊዜ ጀምሮ ግን ሁሉን ነገር አጥተናል፤ እንዲሁም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።”
ሴቶቹም አክለው እንዲህ አሉ፦ “ደግሞስ ‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት እናቀርብና የመጠጥ መባ እናፈስ በነበረበት ጊዜ፣ በእሷ ምስል የመሥዋዕት ቂጣ የምንጋግረውና ለእሷ የመጠጥ መባ የምናፈሰው ባሎቻችንን ሳናማክር ነበር?”
በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ ይኸውም ለወንዶቹ፣ ለሚስቶቻቸውና እያናገሩት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አለ፦
“እናንተ፣ አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁ፣ መኳንንታችሁና በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ያቀረባችኋቸውን መሥዋዕቶች ይሖዋ አልዘነጋም፤ በልቡም አኑሯቸዋል!
በመጨረሻም ይሖዋ የፈጸማችኋቸውን ክፉ ድርጊቶችና የሠራችኋቸውን አስጸያፊ ነገሮች ሊታገሥ አልቻለም፤ ምድራችሁም ዛሬ እንደምታዩት ባድማ ስፍራ፣ አስፈሪ ቦታና ሰው የማይኖርባት ቦታ ሆነች፤ ለእርግማንም ተዳረገች።
እነዚህን መሥዋዕቶች ስላቀረባችሁ፣ ደግሞም የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ እንዲሁም የእሱን ሕግ፣ ደንብና ማሳሰቢያ ባለመከተል በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ይህ ጥፋት ደርሶባችኋል።”
ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ ሲል አክሎ ተናገረ፦ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ።
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ የተናገራችሁትን በእጃችሁ ፈጽማችሁታል፤ እንዲህ ብላችኋልና፦ “‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት ለማቅረብና ለእሷ የመጠጥ መባ ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለት በእርግጥ እንፈጽማለን።” እናንተ ሴቶች የገባችሁትን ስእለት በእርግጥ ታደርሳላችሁ፤ ስእለታችሁንም ትፈጽማላችሁ።’
“ስለዚህ በግብፅ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ‘“እነሆ፣ በገዛ ራሴ ታላቅ ስም እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “በመላው የግብፅ ምድር፣ የትኛውም የይሁዳ ሰው ‘ሕያው በሆነው በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ እምላለሁ’ በማለት ከእንግዲህ ስሜን በመሐላ አይጠራም።
መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት እከታተላቸዋለሁ፤ በግብፅ ምድር የሚኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በረሃብ ያልቃሉ።
ጥቂት ሰዎች ብቻ ከሰይፍ አምልጠው ከግብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ። ከዚያም በግብፅ ምድር ለመኖር ወደዚያ የመጡት የይሁዳ ቀሪዎች ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነሱ፣ የማን ቃል እንደተፈጸመ ያውቃሉ!”’”
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት የተናገርኩት ቃል መፈጸሙ እንደማይቀር ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሆናችኋል።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነውና ሕይወቱን ሊያጠፋ ይፈልግ ለነበረው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ እንደሰጠሁ ሁሉ የግብፁን ንጉሥ፣ ፈርዖን ሆፍራንም ለጠላቶቹና ሕይወቱን ለማጥፋት ለሚፈልጉት ሰዎች አሳልፌ እሰጣለሁ።”’”
የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የብሔራትን መንገድ አትማሩ፤በሰማያት ምልክቶችም አትሸበሩ፤ምክንያቱም ብሔራት በእነዚህ ነገሮች ተሸብረዋል።
የእነዚህ ሕዝቦች ልማድ ከንቱ ነውና፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዛፍ ከጫካ ይቆርጥናበመሣሪያው ጠርቦ ጣዖት ይሠራል።
በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤እንዳይወድቅም በመዶሻና በምስማር ይቸነክሩታል።
እነሱ በኪያር እርሻ ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያነት እንደሚተከል ማስፈራርቾ መናገር አይችሉም፤መራመድ ስለማይችሉ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል። ጉዳት ማድረስም ሆነምንም ዓይነት መልካም ነገር መሥራት ስለማይችሉ አትፍሯቸው።”
ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም። አንተ ታላቅ ነህ፤ ስምህም ታላቅና ኃያል ነው።
የብሔራት ንጉሥ ሆይ፣ አንተን የማይፈራ ማን ነው? አንተ ልትፈራ ይገባሃልና፤ምክንያቱም ከብሔራት ጠቢባን ሁሉ እንዲሁም ከመንግሥቶቻቸው ሁሉ መካከልእንደ አንተ ያለ ማንም የለም።
ሁሉም የማመዛዘን ችሎታ የጎደላቸውና ሞኞች ናቸው። ከእንጨት ምስል የሚመጣ መመሪያ ፈጽሞ ከንቱ ነው።
በእጅ ጥበብ ባለሙያና በአንጥረኛ የተሠራየተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከዑፋዝ ይመጣል። ልብሳቸው በሰማያዊ ክርና በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። ሁሉም በባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው።
ይሖዋ ግን እውነተኛ አምላክ ነው። እሱ ሕያው አምላክና ዘላለማዊ ንጉሥ ነው። ከቁጣው የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤የእሱን ውግዘት ሊቋቋም የሚችል አንድም ብሔር የለም።
እናንተ እንዲህ በሏቸው፦ “ሰማያትንና ምድርን ያልሠሩት አማልክትከምድር ገጽ፣ ከእነዚህም ሰማያት በታች ይጠፋሉ።”
ምድርን በኃይሉ የሠራው፣ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውናሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው።
ድምፁን ሲያሰማበሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤ደመና ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል። በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል። እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤ከብረት የተሠራው ምስሉ ሐሰት ነውና፤በውስጣቸውም መንፈስ የለም።
እነሱ ከንቱና መሳለቂያ ናቸው። የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ።