text
stringlengths
4
267
አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምነቅል፣ እንደማፈርስና እንደማጠፋ በተናገርኩ ጊዜ፣
ያ ብሔር እኔ ያወገዝኩትን ክፉ ነገር ቢተው፣ ሐሳቤን ለውጬ በእሱ ላይ ላመጣው ያሰብኩትን ጥፋት እተወዋለሁ።
ሆኖም አንድን ብሔር ወይም አንድን መንግሥት እንደምገነባውና እንደምተክለው በተናገርኩ ጊዜ፣
በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ቢያደርግና ድምፄን ባይሰማ እኔም ሐሳቤን ለውጬ ለእሱ አደርገዋለሁ ብዬ ያሰብኩትን መልካም ነገር እተወዋለሁ።’
“አሁንም ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እባክህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት እየተዘጋጀሁ ነው፤ በእናንተም ላይ ክፉ ነገር እየጠነሰስኩ ነው። እባካችሁ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁንም አስተካክሉ።”’”
እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ያበቃለት ጉዳይ ነው! እኛ እንደሆነ በራሳችን ሐሳብ እንሄዳለን፤ እያንዳንዳችንም ግትር የሆነውን ክፉ ልባችንን እንከተላለን።”
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ራሳችሁ ብሔራትን ጠይቁ። እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቷል? የእስራኤል ድንግል እጅግ የሚሰቀጥጥ ነገር አድርጋለች።
የሊባኖስ ዓለታማ ተረተር በረዶ ተለይቶት ያውቃል? ወይስ ከሩቅ ስፍራ የሚፈስሱት ቀዝቃዛ ውኃዎች ይደርቃሉ?
ሕዝቤ ግን እኔን ረስቶኛል። ለማይረባ ነገር መሥዋዕት ያቀርባሉና፤ሰዎችም በመንገዳቸው፣ በጥንቶቹ ጎዳናዎች እንዲሰናከሉደግሞም ባልተስተካከሉና ባልተደለደሉ ተለዋጭ መንገዶች እንዲሄዱ ያደርጋሉ፤
ስለዚህ ምድራቸው አስፈሪ ቦታ፣ለዘላለምም ማፏጫ ትሆናለች። በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።
እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላት ፊት እበትናቸዋለሁ። በሚጠፉበት ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”
እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር፤ ሕጉ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን ወይም ቃሉ ከነቢያት አይጠፋምና። ኑና በአንደበታችን እናጥቃው፤ የሚናገረውንም ቃል አንስማ።”
ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረትህን ወደ እኔ አድርግ፤ተቃዋሚዎቼ የሚናገሩትንም ስማ።
ስለ መልካም ነገር ክፉ መመለስ አግባብ ነው? እነሱ ጉድጓድ ቆፍረውልኛልና። ቁጣህ ከእነሱ እንዲመለስ፣ ስለ እነሱ መልካም ነገር ለመናገር ምን ያህል ጊዜ በፊትህ እንደቆምኩ አስብ።
ስለዚህ ወንዶች ልጆቻቸውን ለረሃብ ዳርጋቸው፤ለሰይፍ ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው። ሚስቶቻቸው የወላድ መሃንና መበለት ይሁኑ። ወንዶቻቸው በገዳይ መቅሰፍት ይሙቱ፤ወጣቶቻቸው በጦር ሜዳ በሰይፍ ተመተው ይውደቁ።
በድንገት ወራሪዎችን ስታመጣባቸውከየቤታቸው ጩኸት ይሰማ። እኔን ለመያዝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፤ለእግሮቼም ወጥመድ ዘርግተዋል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግንእኔን ለመግደል የጠነሰሱትን ሴራ ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። በደላቸውን አትሸፍን፤ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ። በቁጣ ተነሳስተህ እርምጃ ስትወስድባቸውበፊትህ ይሰናከሉ።
“በማሰማሪያዬ ያሉትን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ይሖዋ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሕዝቡን በሚጠብቁት እረኞች ላይ እንዲህ ይላል፦ “በጎቼን በትናችኋል፤ አባራችኋቸዋል፤ ትኩረትም አልሰጣችኋቸውም።” “ስለዚህ ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳ ትኩረቴን በእናንተ ላይ አደርጋለሁ” ይላል ይሖዋ።
“ከዚያም የቀሩትን በጎቼን ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ መሰማሪያቸውም መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ደግሞም ይበዛሉ።
እኔም በሚገባ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሳላቸዋለሁ። ከእንግዲህ አይፈሩም፣ አይሸበሩም እንዲሁም አንዳቸውም አይጎድሉም” ይላል ይሖዋ።
“እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው” ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።
በእሱ ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ያለስጋት ይኖራል። የሚጠራበትም ስም ‘ይሖዋ ጽድቃችን ነው’ የሚል ይሆናል።”
“ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ባወጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ!’ የማይሉበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤
“ከዚህ ይልቅ ‘የእስራኤልን ቤት ዘሮች ከሰሜን ምድርና እነሱን ከበተነባቸው አገሮች ሁሉ ባወጣውና መልሶ ባመጣው ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ’ ይላሉ፤ እነሱም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”
ነቢያቱን በተመለከተ፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሯል። አጥንቶቼ ሁሉ እየተንቀጠቀጡ ነው። ከይሖዋና ከቅዱስ ቃሉ የተነሳእንደሰከረ ሰውናየወይን ጠጅ እንዳሸነፈው ሰው ሆንኩ።
ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለችና፤ከእርግማኑ የተነሳ ምድሪቱ አዝናለች፤በምድረ በዳ ያሉት ማሰማሪያዎችም ደርቀዋል። መንገዳቸው መጥፎ ነው፤ ሥልጣናቸውንም አላግባብ ይጠቀሙበታል።
“ነቢዩም ሆነ ካህኑ ተበክለዋል። በገዛ ቤቴ እንኳ ሳይቀር የሠሩትን ክፋት አግኝቻለሁ” ይላል ይሖዋ።
“ስለሆነም መንገዳቸው የሚያዳልጥና ጨለማ ይሆናል፤ይገፋሉ እንዲሁም ይወድቃሉ። በሚመረመሩበት ዓመት፣ጥፋት አመጣባቸዋለሁና” ይላል ይሖዋ።
“በሰማርያ ነቢያት ላይ ደግሞ አስጸያፊ ነገር አይቻለሁ። ትንቢት የሚናገሩት በባአል አነሳሽነት ነው፤ሕዝቤ እስራኤልም እንዲባዝን አድርገዋል።
በኢየሩሳሌም ነቢያትም ላይ የሚዘገንኑ ነገሮች አይቻለሁ። ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይመላለሳሉ፤ክፉ አድራጊዎችን ያደፋፍራሉ፤ከክፋታቸውም አይመለሱም። ለእኔ ሁሉም እንደ ሰዶም፣ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ናቸው።”
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በነቢያቱ ላይ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ ጭቁኝ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤የተመረዘም ውኃ እንዲጠጡ እሰጣቸዋለሁ። የኢየሩሳሌም ነቢያት በምድሪቱ ሁሉ ላይ ክህደት አሰራጭተዋልና።”
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትንቢት የሚተነብዩላችሁ ነቢያት የሚናገሩትን ቃል አትስሙ። እነሱ እያሞኟችሁ ነው። የሚናገሩት ራእይ ከይሖዋ አፍ የወጣ ሳይሆንከገዛ ልባቸው የመነጨ ነው።
እነሱ እኔን ለሚንቁ ሰዎች ደግመው ደጋግመው‘ይሖዋ “ሰላም ታገኛላችሁ” ብሏል’ ይላሉ። ግትር የሆነ ልባቸውን የሚከተሉትን ሁሉ‘ጥፋት አይደርስባችሁም’ ይሏቸዋል።
ቃሉን ለማየትና ለመስማትከይሖዋ የቅርብ ወዳጆች ጋር የቆመ ማን ነው? ይሰማስ ዘንድ ለቃሉ ትኩረት የሰጠ ማን ነው?
እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤እንደሚሽከረከር ኃይለኛ ነፋስ በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ ይወርዳል።
ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽምቁጣው አይመለስም። በዘመኑ መጨረሻ ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ።
ነቢያቱን እኔ አልላክኋቸውም፤ እነሱ ግን ሮጡ። እኔ የነገርኳቸው ነገር የለም፤ እነሱ ግን ትንቢት ተናገሩ።
ከእኔ የቅርብ ወዳጆች ጋር ቢቆሙ ኖሮሕዝቤ ቃሌን እንዲሰማ ባደረጉ ነበር፤ደግሞም ከክፉ መንገዱና ከመጥፎ ድርጊቱ እንዲመለስ ባደረጉ ነበር።”
“እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ? የሩቅስ አምላክ አይደለሁም?” ይላል ይሖዋ።
“እኔ እንዳላየው በስውር ቦታ መሸሸግ የሚችል ሰው ይኖራል?” ይላል ይሖዋ። “ሰማያትንና ምድርን የሞላሁት እኔ አይደለሁም?” ይላል ይሖዋ።
“‘ሕልም አይቻለሁ! ሕልም አይቻለሁ!’ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩ ነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ።
የሐሰት ትንቢት ይናገሩ ዘንድ ይህ ነገር በነቢያት ልብ ውስጥ የሚኖረው እስከ መቼ ነው? እነሱ ከገዛ ልባቸው ያመነጩትን ማታለያ የሚናገሩ ነቢያት ናቸው።
አባቶቻቸው በባአል የተነሳ ስሜን እንደረሱ ሁሉ፣ እነሱም አንዳቸው ለሌላው በሚናገሩት ሕልም አማካኝነት ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ማድረግ ይፈልጋሉ።
ሕልም ያየ ነቢይ ሕልሙን ይናገር፤ ይሁንና ቃሌ ያለው ቃሌን በእውነት ይናገር።” “ገለባና እህል አንድ የሚያደርጋቸው ምን ነገር አለ?” ይላል ይሖዋ።
“ቃሌ እንደ እሳት አይደለም?” ይላል ይሖዋ፤ “ቋጥኝንስ እንደሚያደቅ መዶሻ አይደለም?”
“ስለዚህ እርስ በርስ ቃሌን በሚሰራረቁ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።
“እነሆ፣ በምላሳቸው እየቀባጠሩ ‘እሱ እንዲህ ይላል!’ ብለው በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ።
“እነሆ፣ ሐሰትን በሚያልሙና በሚናገሩ እንዲሁም የሐሰት ወሬ እያናፈሱና ጉራ እየነዙ ሕዝቤን በሚያስቱ ነቢያት ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ። “ሆኖም እኔ አልላክኋቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም። ስለዚህ ይህን ሕዝብ ምንም አይጠቅሙትም” ይላል ይሖዋ።
“ይህ ሕዝብ ወይም አንድ ነቢይ አሊያም አንድ ካህን ‘የይሖዋ ሸክም ምንድን ነው?’ ብለው በሚጠይቁህ ጊዜ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘“ሸክሙ እናንተ ናችሁ! እኔም እጥላችኋለሁ” ይላል ይሖዋ።’
ነቢይ ወይም ካህን አሊያም ማንኛውም ሰው ‘ይህ የይሖዋ ሸክም ነው!’ እያለ ቢናገር በእሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።
እያንዳንዳችሁ ባልንጀራችሁንና ወንድማችሁን ‘ይሖዋ የሰጠው መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው?’ ትላላችሁ።
ሆኖም ከእንግዲህ የይሖዋ ሸክም ብላችሁ አትናገሩ፤ ሸክሙ የእያንዳንዱ ሰው የገዛ ራሱ ቃል ነውና፤ እናንተም ሕያው አምላክ የሆነውን የአምላካችንን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቃል ለውጣችኋል።
“ነቢዩን እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘ይሖዋ የሰጠህ መልስ ምንድን ነው? ይሖዋ የተናገረውስ ምንድን ነው?
“የይሖዋ ሸክም!” ማለታችሁን የማታቆሙ ከሆነ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘“የይሖዋ ሸክም!” አትበሉ’ ብዬ ከነገርኳችሁ በኋላ እናንተ ‘ይህ ቃል የይሖዋ ሸክም ነው’ በማለታችሁ፣
እነሆ፣ እናንተንም ሆነ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ የሰጠኋትን ከተማ አንስቼ ከፊቴ እወረውራችኋለሁ።
የማይረሳ የዘላለም ኀፍረትና የዘላለም ውርደት በእናንተ ላይ አመጣለሁ።”’”
በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም የግዛት ዘመን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“ወደ ሬካባውያን ቤት ሄደህ አነጋግራቸው፤ ወደ ይሖዋም ቤት አምጥተህ ወደ አንዱ መመገቢያ ክፍል አስገባቸው፤ ከዚያም የሚጠጡትን የወይን ጠጅ አቅርብላቸው።”
ስለዚህ የሃባጺንያን ልጅ፣ የኤርምያስን ልጅ፣ ያአዛንያህን፣ ወንድሞቹን፣ ወንዶች ልጆቹን ሁሉና የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኩ፤
ወደ ይሖዋ ቤትም አመጣኋቸው። የእውነተኛው አምላክ ሰው፣ የይግዳልያ ልጅ፣ የሃናን ልጆች መመገቢያ ወደሆነው ክፍል አስገባኋቸው፤ ክፍሉም የሚገኘው ከበር ጠባቂው ከሻሉም ልጅ፣ ከማአሴያህ መመገቢያ ክፍል በላይ ካለው ከመኳንንቱ መመገቢያ ክፍል አጠገብ ነው።
ከዚያም ከሬካባውያን ወገን በሆኑት ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ጽዋዎችንና ዋንጫዎችን አቅርቤ “የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኳቸው።
እነሱ ግን እንዲህ አሉ፦ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ ምክንያቱም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ሲል አዞናል፦ ‘እናንተም ሆናችሁ ወንዶች ልጆቻችሁ መቼም ቢሆን የወይን ጠጅ አትጠጡ።
ቤት አትሥሩ፤ ዘር አትዝሩ፤ ወይን አትትከሉ ወይም የወይን እርሻ አይኑራችሁ። ይልቁንም የባዕድ አገር ሰዎች ሆናችሁ በተቀመጣችሁበት ምድር ረጅም ዘመን እንድትኖሩ ምንጊዜም በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ።’
ስለዚህ እኛም ሆንን ሚስቶቻችን እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን የአባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ቃል ሁሉ በማክበር የወይን ጠጅ የሚባል ነገር መቼም ቢሆን አንጠጣም።
መኖሪያ ቤትም አንሠራም፤ የወይን እርሻ፣ መሬትም ሆነ የእህል ዘር የለንም።
በድንኳን ውስጥ መኖራችንንና አባታችን ኢዮናዳብ የሰጠንን ትእዛዝ ማክበራችንን እንቀጥላለን።
ሆኖም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ምድሪቱን ሊወጋ በመጣ ጊዜ እንዲህ አልን፦ ‘ኑ፣ ከከለዳውያንና ከሶርያውያን ሠራዊት ለማምለጥ ወደ ኢየሩሳሌም እንግባ’፤ በመሆኑም አሁን በኢየሩሳሌም እየኖርን ነው።”
የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ በል፦ “ቃሌን እንድትታዘዙ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ አልተሰጣችሁም?” ይላል ይሖዋ።
“የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ፣ ዘሮቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዝዞ ነበር፤ እነሱም እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ ባለመጠጣት ቃሉን ጠብቀዋል፤ በዚህም መንገድ የአባታቸውን ትእዛዝ አክብረዋል። ይሁንና እኔ ደግሜ ደጋግሜ ብነግራችሁም አልታዘዛችሁኝም።
እኔም አገልጋዮቼን ነቢያትን ሁሉ እንዲህ በማለት ደግሜ ደጋግሜ ወደ እናንተ ላክኋቸው፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር አድርጉ! ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ደግሞም አታገልግሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ።’ እናንተ ግን ጆሯችሁን አልሰጣችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁም።
የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋል፤ እነዚህ ሰዎች ግን እኔን አልሰሙም።”’”
“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልኩትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤ ብነግራቸውም እንኳ አይሰሙኝምና፤ ደጋግሜ ብጠራቸውም አይመልሱልኝም።’”
ኤርምያስም ለሬካባውያን ወገኖች እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአባታችሁን የኢዮናዳብን ትእዛዝ ስላከበራችሁ እንዲሁም ትእዛዙን ሁሉ ስለጠበቃችሁና ያዘዛችሁን በትክክል ስለፈጸማችሁ፣
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ዘር በፊቴ የሚያገለግል ሰው ፈጽሞ አይታጣም።”’”
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ ሠራዊቱ ሁሉ፣ በእሱ ግዛት ሥር ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች በሙሉ እየወጉ ሳሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦
“የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሂድና የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አናግረው፤ እንዲህም በለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።
አንተም ከእጁ አታመልጥም፤ ያለጥርጥር ትያዛለህና፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ። የባቢሎንንም ንጉሥ በዓይኖችህ ታየዋለህ፤ ፊት ለፊትም ያነጋግርሃል፤ ወደ ባቢሎንም ትወሰዳለህ።’
ይሁንና የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስማ፤ ‘ይሖዋ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ “በሰይፍ አትሞትም።
በሰላም ትሞታለህ፤ ለአባቶችህ ይኸውም ከአንተ ቀድሞ ለነበሩት ነገሥታት እንዳደረጉት ለክብርህ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ፣ ጌታችን!’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ ‘እኔ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና’ ይላል ይሖዋ።”’”’”
ከዚያም ነቢዩ ኤርምያስ በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ ይህን ሁሉ ቃል ነገረው፤
በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ይኸውም ለኪሶንና አዜቃን እየወጋ ነበር፤ ከይሁዳ ከተሞች መካከል ድል ሳይደረጉ የቀሩት እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች ብቻ ነበሩና።
ንጉሥ ሴዴቅያስ ነፃነት ለማወጅ በኢየሩሳሌም ከነበረው ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤
ቃል ኪዳኑ፣ እያንዳንዱ ሰው ዕብራውያን የሆኑ ወንድና ሴት ባሪያዎቹን በነፃ እንዲለቅ፣ ደግሞም ማንኛውም ሰው ወገኑ የሆነውን አይሁዳዊ፣ ባሪያው አድርጎ እንዳያሠራ የሚያዝዝ ነበር።
በመሆኑም መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ እንደተባሉት አደረጉ። እያንዳንዳቸው ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን በነፃ ለመልቀቅና ከዚያ በኋላ ባሪያ አድርገው ላለማሠራት ቃል ኪዳን ገቡ። እንደተባሉት በማድረግ ባሪያዎቻቸውን አሰናበቷቸው።
በኋላ ግን ነፃ ለቀዋቸው የነበሩትን ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን መለሷቸው፤ እንደገናም አስገድደው በባርነት ገዟቸው።
ስለዚህ የይሖዋ ቃል ከይሖዋ ዘንድ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ቤት ባወጣኋቸው ጊዜ እንዲህ ስል ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፦
“እያንዳንዳችሁ የተሸጠላችሁንና ስድስት ዓመት ሲያገለግላችሁ የቆየውን ዕብራዊ የሆነውን ወንድማችሁን በሰባተኛው ዓመት ማብቂያ ላይ ልቀቁት፤ በነፃ ልታሰናብቱት ይገባል።” አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡኝም።
እናንተም በቅርቡ ተመልሳችሁ ለወገኖቻችሁ ነፃነት በማወጅ በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር አደረጋችሁ፤ ስሜ በተጠራበትም ቤት በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ።
በኋላ ግን ሐሳባችሁን ቀይራችሁ፣ እንደ ፍላጎታቸው በነፃ የለቀቃችኋቸውን ወንድና ሴት ባሪያዎቻችሁን መልሳችሁ በማምጣት ስሜን አረከሳችሁ፤ አስገድዳችሁም ወደ ባርነት መለሳችኋቸው።’
“ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁና ለወገናችሁ ነፃነት በማወጅ አልታዘዛችሁኝም። በመሆኑም እኔ ለእናንተ ያወጅኩት ነፃነት ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በሰይፍ፣ በቸነፈርና በረሃብ ታልቃላችሁ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋችኋለሁ።
ጥጃውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ ባለፉ ጊዜ በፊቴ የገቡትን ቃል ኪዳን ባለማክበር ቃል ኪዳኔን የጣሱት ሰዎች የሚደርስባቸው ነገር ይህ ነው፤
ይኸውም የይሁዳ መኳንንት፣ የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት፣ ካህናቱና ለሁለት በተከፈለው ጥጃ መካከል ያለፈው የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህ ነገር ይደርስባቸዋል፦
ለጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ ሰዎች አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ለጠላቶቻቸው፣ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ ሰዎችና እናንተን መውጋት ትቶ ለተመለሰው የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።’
“‘እነሆ፣ እኔ ይህን ትእዛዝ አስተላልፋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱንም ወደዚህች ከተማ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ይወጓታል፣ ይይዟታል፣ በእሳትም ያቃጥሏታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርበት ጠፍ መሬት አደርጋቸዋለሁ።’”
እናንተ የቢንያም ልጆች፣ ተሸሸጉ፤ ከኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ሽሹ። በተቆአ ቀንደ መለከት ንፉ፤በቤትሃኬሬም እሳት በማንደድ ምልክት አሳዩ! ከሰሜን ጥፋት፣ ይኸውም ታላቅ መዓት እያንዣበበ ነውና።
የጽዮን ሴት ልጅ ያማረችና ቅምጥል ሴት ትመስላለች።