text stringlengths 4 267 |
|---|
እረኞችና መንጎቻቸው ይመጣሉ። በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤እያንዳንዳቸውም የሚጠብቋቸውን መንጎች ያሰማራሉ። |
“በእሷ ላይ ጦርነት ለማወጅ ተዘጋጁ! ተነሱ፣ እኩለ ቀን ላይ ጥቃት እንሰንዝርባት!” “ወዮልን፣ ቀኑ እየመሸ፣የምሽቱም ጥላ እየረዘመ ነውና!” |
“ተነሱ፣ በሌሊት ጥቃት እንሰንዝርባት፤የማይደፈሩትንም ማማዎቿን እንደምስስ።” |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እንጨት ቁረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያም የአፈር ቁልል ደልድሉ። ይህች ከተማ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል፤በውስጧ ከግፍ በቀር ምንም አይገኝም። |
የውኃ ጉድጓድ ውኃውን እንደቀዘቀዘ እንደሚያቆይ፣እሷም ክፋቷን እንዳለ ጠብቃ አቆይታለች። ዓመፅና ጥፋት በውስጧ ይሰማል፤ሕመምና ደዌ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው። |
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተጸይፌሽ ከአንቺ እንዳልርቅ ተጠንቀቂ፤ባድማና ሰው የማይኖርበት ምድር አደርግሻለሁ።” |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቀሪዎች በወይን ተክል ላይ እንደቀሩ የመጨረሻ የወይን ፍሬዎች ምንም ሳያስቀሩ ይቃርሟቸዋል። ከወይን ተክሎች ላይ የወይን ፍሬዎች እንደሚለቅም ሰው በድጋሚ እጅህን ዘርጋ።” |
“ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ ማዳመጥ አይችሉም። እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም። |
በመሆኑም በይሖዋ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤በውስጤ አፍኜ ስለያዝኩት ዝያለሁ።” “በጎዳና ባለ ልጅ፣ተሰብስበው ባሉ ወጣቶች ላይ አፍስሰው። ባልም ሆነ ሚስቱ፣አረጋውያኑም ሆኑ ያረጁት ይያዛሉ። |
ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸውለሌሎች ይሰጣሉ። እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ። |
“ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ እያንዳንዱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣል፤ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል። |
ሰላም ሳይኖር፣‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ የሕዝቤን ስብራት ላይ ላዩን ለመጠገን ይሞክራሉ። |
በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል? እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም! ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም! ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ። እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ። |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መስቀለኛ መንገዶቹ ላይ ቁሙና ተመልከቱ። ስለ ጥንቶቹ ጎዳናዎች፣መልካም የሆነው መንገድ የትኛው እንደሆነ ጠይቁ፤ በዚያም ሂዱ፤እረፍትም አግኙ።” እነሱ ግን “በዚያ አንሄድም” ይላሉ። |
“እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂዎችን ሾምኩ፤ጠባቂዎቹም ‘የቀንደ መለከቱን ድምፅ በትኩረት አዳምጡ!’ አሉ”፤ እነሱ ግን “አናዳምጥም” አሉ። |
“ስለዚህ እናንተ ብሔራት፣ ስሙ! እናንተ ሰዎች ሆይ፣ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ። |
ምድር ሆይ፣ ስሚ! በእነዚህ ሰዎች ላይ የገዛ ውጥናቸውን ፍሬ፣ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ፤እነሱ ለቃሌ ምንም ትኩረት አልሰጡምና፤ሕጌንም አልተቀበሉም።” |
“ነጭ ዕጣን ከሳባ፣ጠጅ ሣር ከሩቅ አገር ብታመጡልኝ ምን ይጠቅመኛል? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁን አልቀበልም፤መሥዋዕቶቻችሁም ደስ አያሰኙኝም።” |
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክል አስቀምጣለሁ፤አባቶችም ሆኑ ልጆች፣ጎረቤትም ሆነ ባልንጀራውበአንድነት ይሰናከላሉ፤ሁሉም ይጠፋሉ።” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ምድር አንድ ሕዝብ እየመጣ ነው፤ከምድር ዳርቻም ታላቅ ብሔር ይነሳል። |
ቀስትና ጦር ይይዛሉ። ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው። ድምፃቸው እንደ ባሕር ያስተጋባል፤ፈረሶችንም ይጋልባሉ። የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልክ እንደ ተዋጊ በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።” |
ወሬውን ሰምተናል። እጆቻችንም ዝለዋል፤በጭንቀት ተውጠናል፤ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ሥቃይ ቀስፎናል። |
ወደ ውጭ አትውጡ፤በመንገዱም ላይ አትዘዋወሩ፤ጠላት ሰይፍ ታጥቋልና፤በየቦታውም ሽብር ነግሦአል። |
የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ማቅ ልበሺ፤ በአመድም ላይ ተንከባለዪ። አንድ ልጁን እንዳጣ ሰው መራራ ለቅሶ አልቅሺ፤አጥፊው በእኛ ላይ በድንገት ይመጣልና። |
“አንተን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን፣በጥንቃቄም እንደሚመረምር ሰው አድርጌሃለሁ፤አንተም ልብ በል፤ መንገዳቸውንም መርምር። |
ሁሉም በጣም ግትር ናቸው፤እየዞሩ ስም ያጠፋሉ። እንደ መዳብና ብረት ናቸው፤ሁሉም ምግባረ ብልሹዎች ናቸው። |
ወናፎቹ በእሳት ተቃጠሉ። ከእሳቱም የሚወጣው እርሳስ ነው። አንጥረኛ በደንብ የሚያጣራው እንዲያው በከንቱ ነው፤መጥፎዎቹም ተለይተው አልወጡም። |
ሰዎች ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሯቸዋል፤ይሖዋ ጥሏቸዋልና።” |
የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ኤርምያስን ከራማ በነፃ ከለቀቀው በኋላ ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። ናቡዛራዳን ኤርምያስን ወደዚያ ሲወስደው እጆቹ በሰንሰለት ታስረው ነበር፤ ደግሞም ወደ ባቢሎን በግዞት እየተወሰዱ ከነበሩት የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ መካከል ነበር። |
ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ኤርምያስን ወስዶ እንዲህ አለው፦ “አምላክህ ይሖዋ በዚህ ስፍራ ላይ ይህ ጥፋት እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል፤ |
በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁና ቃሉን ስላልታዘዛችሁ ይሖዋ በተናገረው መሠረት ይህን ጥፋት አመጣ። ይህ ነገር በእናንተ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው። |
እጆችህ የታሰሩበትን ሰንሰለት ዛሬ እፈታልሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ መልካም መስሎ ከታየህ መሄድ ትችላለህ፤ እኔም እንከባከብሃለሁ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መሄድ ካልፈለግክ ግን መቅረት ትችላለህ። እነሆ፣ ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት። ወደመረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።” |
ኤርምያስ ከመመለሱ በፊት ናቡዛራዳን እንዲህ አለው፦ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ፣ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፤ በሕዝቡም መካከል ከእሱ ጋር ተቀመጥ፤ ወይም ደግሞ ወደመረጥከው ቦታ ሂድ።” ከዚያም የዘቦቹ አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው። |
በመሆኑም ኤርምያስ በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ሄዶ በምድሪቱ በቀሩት ሕዝብ መካከል ከእሱ ጋር መኖር ጀመረ። |
በኋላም ከሰዎቻቸው ጋር በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ እንደሾመው እንዲሁም ወደ ባቢሎን በግዞት ባልተወሰዱትና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት ድሆች የሆኑ ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ። |
ስለሆነም በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬሃ ልጆች የሆኑት ዮሃናን እና ዮናታን፣ የታንሁመት ልጅ ሰራያህ፣ የነጦፋዊው የኤፋይ ልጆችና የማአካታዊው ልጅ የዛንያህ እንዲሁም አብረዋቸው የነበሩት ሰዎች ናቸው። |
የሳፋን ልጅ፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነሱና አብረዋቸው ለነበሩት ሰዎች እንዲህ ብሎ ማለላቸው፦ “ከለዳውያንን ማገልገል አያስፈራችሁ። በምድሪቱ ላይ ኑሩ፤ የባቢሎንንም ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካምም ይሆንላችኋል። |
እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እናንተን ወክዬ ለመቅረብ በምጽጳ እቀመጣለሁ። እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬዎችና ዘይት አከማቹ፤ በማጠራቀሚያ ዕቃዎቻችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸው ከተሞችም ውስጥ ኑሩ።” |
በሞዓብ፣ በአሞንና በኤዶም እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩት አይሁዳውያንም በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ የተወሰኑ ቀሪዎች በይሁዳ ምድር እንዲኖሩ እንደፈቀደላቸውና የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በእነሱ ላይ እንደሾመ ሰሙ። |
በመሆኑም አይሁዳውያኑ በሙሉ ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ ይመለሱ ጀመር፤ በይሁዳ ምድር በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። እነሱም ወይንና የበጋ ፍሬዎችን በብዛት አከማቹ። |
የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና በየቦታው የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ በምጽጳ ወዳለው ወደ ጎዶልያስ መጡ። |
እንዲህም አሉት፦ “የአሞናውያን ንጉሥ ባአሊስ አንተን ለመግደል የነታንያህን ልጅ እስማኤልን እንደላከው አታውቅም?” የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም። |
ከዚያም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ ጎዶልያስን በምጽጳ በሚስጥር እንዲህ አለው፦ “ሄጄ የነታንያህን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ማንም አያውቅም። ለምን ይግደልህ? ወደ አንተ የተሰበሰቡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ለምን ይበተኑ? የይሁዳ ቀሪዎችስ ለምን ይጥፉ?” |
የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን “ስለ እስማኤል የምትነግረኝ ነገር እውነት ስላልሆነ እንዲህ አታድርግ” አለው። |
ነቢዩ ኤርምያስ፣ በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች መካከል በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ለወሰደው ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው ደብዳቤ ቃል ይህ ነው፦ |
ይህም የሆነው ንጉሥ ኢኮንያን፣ የንጉሡ እናት፣ ባለሥልጣናቱ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና አንጥረኞቹ ከኢየሩሳሌም ከሄዱ በኋላ ነው። |
ደብዳቤውን የላከው፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ናቡከደነጾር በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሳና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያህ እጅ ነው። ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ |
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወሰዱ ላደረጋቸው ለተማረኩት ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላል፦ |
‘ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ። |
ሚስት አግብታችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ውለዱ፤ እነሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲወልዱ፣ ወንዶች ልጆቻችሁንና ሴቶች ልጆቻችሁን ዳሩ። በዚያም ቁጥራችሁ ይብዛ እንጂ አይነስ። |
በግዞት ተወስዳችሁ እንድትኖሩባት ላደረግኳት ከተማም ሰላምን ፈልጉ፤ ስለ እሷም ወደ ይሖዋ ጸልዩ፤ እሷ ሰላም ከሰፈነባት እናንተም በሰላም ትኖራላችሁና። |
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ሟርተኞች አያታሏችሁ፤ የሚያልሙትንም ሕልም አትስሙ። |
‘በስሜ የሚተነብዩላችሁ ሐሰት ነውና። እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል ይሖዋ።”’” |
“ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በባቢሎን የምትኖሩበት 70 ዓመት ሲፈጸም ትኩረቴን ወደ እናንተ አዞራለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ መልሼ በማምጣት፣ የገባሁትን ቃል እፈጽማለሁ።’ |
“‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው። |
እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ወደ እኔም ቀርባችሁ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።’ |
“‘እኔን ትሻላችሁ፤ በሙሉ ልባችሁ ስለምትፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ። |
እኔም እገኝላችኋለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’ |
“እናንተ ግን ‘ይሖዋ በባቢሎን ነቢያት አስነስቶልናል’ ብላችኋል። |
“ይሖዋ በዳዊት ዙፋን ላይ ለተቀመጠው ንጉሥና በዚህች ከተማ ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ይኸውም ከእናንተ ጋር በግዞት ላልተወሰዱት ወንድሞቻችሁ እንዲህ ይላልና፦ |
‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በእነሱ ላይ ሰይፍን፣ ረሃብንና ቸነፈርን እሰዳለሁ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳ ሊበሉ እንደማይችሉ የበሰበሱ በለሶች አደርጋቸዋለሁ።”’ |
“‘በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር አሳድዳቸዋለሁ፤ በምድር ላይ ላሉ መንግሥታትም ሁሉ መቀጣጫ አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት ሁሉ መካከልም ለእርግማን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ደግሞም መደነቂያ፣ ማፏጫና መሳለቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ |
ምክንያቱም ደግሜ ደጋግሜ በላክኋቸው አገልጋዮቼ ይኸውም በነቢያት አማካኝነት ያስተላለፍኩትን ቃል አልሰሙም’ ይላል ይሖዋ። “‘ይሁንና እናንተም አልሰማችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
“ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኳችሁ እናንተ ግዞተኞች ሁሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። |
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚተነብዩላችሁ ስለ ቆላያህ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ ማአሴያህ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እሱም በፊታችሁ ይገድላቸዋል። |
በእነሱ ላይ የሚደርሰውንም ነገር በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ግዞተኞች ሁሉ እንደ እርግማን ይጠቀሙበታል፤ “ይሖዋ፣ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ!” ይላሉ፤ |
ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር በማመንዘርና እኔ ያላዘዝኳቸውን ቃል በስሜ በሐሰት በመናገር በእስራኤል የሚያሳፍር ድርጊት ፈጽመዋልና። “‘“እኔ ይህን አውቃለሁ፤ ለዚህም ነገር ምሥክር ነኝ” ይላል ይሖዋ።’” |
“ኔሄላማዊውን ሸማያህን እንዲህ ትለዋለህ፦ |
‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኢየሩሳሌም ላሉት ሰዎች ሁሉና ለማአሴያህ ልጅ ለካህኑ ሶፎንያስ እንዲሁም ለካህናቱ ሁሉ፣ በገዛ ስምህ እንዲህ ብለህ ደብዳቤዎችን ልከሃልና፦ |
‘በይሖዋ ቤት የበላይ ተመልካች እንድትሆን፣ እንደ ነቢይ የሚያደርገውን ማንኛውንም ያበደ ሰው እንድትይዝ እንዲሁም በእግር ግንድ ብሎም በአንገትና በእጅ መጠረቂያ እንድታስር ይሖዋ በካህኑ በዮዳሄ ምትክ ካህን አድርጎሃል፤ |
ታዲያ ነቢይ ነኝ የሚላችሁን የአናቶቱን ኤርምያስን ለምን አልገሠጽከውም? |
በባቢሎን ላለነው ሰዎችም እንኳ ሳይቀር እንዲህ የሚል መልእክት ልኮብናል፦ “በግዞት የምትቆዩበት ጊዜ ረጅም ነው! ቤት ሠርታችሁ በዚያ ኑሩ። አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ፤ . . .”’”’” |
ካህኑ ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ ነቢዩ ኤርምያስ እየሰማ ባነበበ ጊዜ |
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
“በግዞት ወዳሉት ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ላክ፦ ‘ይሖዋ ስለ ኔሄላማዊው ሸማያህ እንዲህ ይላል፦ “ሸማያህ እኔ ሳልከው ስለተነበየላችሁና በሐሰት እንድትታመኑ ለማድረግ ስለሞከረ፣ |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ትኩረቴን በኔሄላማዊው ሸማያህና በዘሮቹ ላይ አደርጋለሁ።’ በዚህ ሕዝብ መካከል የእሱ ዘር የሆነ አንድም ሰው አይተርፍም፤ ለሕዝቤ የማደርገውንም መልካም ነገር አያይም’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በይሖዋ ላይ ዓመፅ አነሳስቷልና።’”’” |
“በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳ ነገሥታት አጥንቶች፣ የመኳንንቱ አጥንቶች፣ የካህናቱ አጥንቶች፣ የነቢያቱ አጥንቶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አጥንቶች ከየመቃብራቸው ይወሰዳሉ። |
በወደዷቸው፣ ባገለገሏቸው፣ በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና በሰገዱላቸው በፀሐይ፣ በጨረቃና በሰማያት ሠራዊት ሁሉ ፊት ይሰጣሉ። አይሰበሰቡም፤ እንዲሁም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።” |
“ደግሞም ከዚህ ክፉ ወገን የሚተርፉት ቀሪዎች በሙሉ እኔ በምበትናቸው ቦታዎች ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
“አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሰዎች ከወደቁ በኋላ ዳግመኛ አይነሱም? አንዱ ከተመለሰ ሌላውስ አይመለስም? |
ታዲያ ይህ ሕዝብ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪ በክህደት ሥራው የጸናው ለምንድን ነው? ተንኮልን የሙጥኝ ብለዋል፤ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል። |
እኔም ትኩረት ሰጥቼ ማዳመጤን ቀጠልኩ፤ የሚናገሩበት መንገድ ግን ትክክል አልነበረም። ከክፋቱ ንስሐ የገባ ወይም ‘ምን መሥራቴ ነው?’ ብሎ የጠየቀ አንድም ሰው የለም። እያንዳንዱ ሰው ወደ ጦርነት እንደሚገሰግስ ፈረስ ብዙኃኑ ወደሚከተለው መንገድ ይመለሳል። |
በሰማይ የምትበረው ራዛ እንኳ ወቅቷን ታውቃለች፤ዋኖስ፣ ወንጭፊትና ጭሪ የሚመለሱበትን ጊዜ ያከብራሉ። የገዛ ሕዝቤ ግን የይሖዋን ፍርድ አይገነዘብም።”’ |
‘“ጥበበኞች ነን፤ የይሖዋም ሕግ አለን” እንዴት ትላላችሁ? እንዲያውም የጸሐፊዎቹ ሐሰተኛ ብዕር ያገለገለው ውሸት ለመጻፍ ብቻ ነው። |
ጥበበኞቹ ለኀፍረት ተዳርገዋል። ተሸብረዋል፤ ደግሞም ይያዛሉ። እነሆ፣ እነሱ የይሖዋን ቃል ንቀዋል፤ታዲያ ምን ዓይነት ጥበብ ይኖራቸዋል? |
ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል። |
ሰላም ሳይኖር፣“ሰላም ነው! ሰላም ነው!” እያሉ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት ላይ ላዩን ለመጠገን ይሞክራሉ። |
በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል? እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም! ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም! “‘ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ። እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ’ ይላል ይሖዋ። |
‘በምሰበስባቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘በወይን ተክሉ ላይ የቀረ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፉ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሉም ይጠወልጋል። የሰጠኋቸውም ነገር ይጠፋባቸዋል።’” |
“እዚህ የምንቀመጠው ለምንድን ነው? በአንድነት እንሰብሰብ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች ገብተን በዚያ እንጥፋ። አምላካችን ይሖዋ ያጠፋናልና፤የተመረዘ ውኃ እንድንጠጣ ይሰጠናል፤ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። |
ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም መልካም ነገር አልመጣም፤የፈውስ ጊዜ ይመጣል ብለን ጠበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ነገሠ! |
የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ። ድንጉላ ፈረሶቹ ሲያሽካኩምድሪቱ በሙሉ ትንቀጠቀጣለች። እነሱ መጥተው ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ይበላሉ።” |
“እነሆ፣ ድግምት የማይገታቸው እባቦችንና እፉኝቶችንበመካከላችሁ እልካለሁ፤እነሱም ይነድፏችኋል” ይላል ይሖዋ። |
ማጽናኛ የማይገኝለት ሐዘን ደርሶብኛል፤ልቤ ታሟል። |
የሕዝቤ ሴት ልጅ “ይሖዋ በጽዮን የለም?ወይስ ንጉሥዋ በዚያ የለም?” የሚል የእርዳታ ጥሪ ከሩቅ አገር ታሰማለች። “በተቀረጹት ምስሎቻቸውናከንቱ በሆኑት ባዕዳን አማልክታቸው ያስከፉኝ ለምንድን ነው?” |
“መከሩ አልፏል፤ በጋውም አብቅቷል፤እኛ ግን አልዳንም!” |
በሕዝቤ ሴት ልጅ ውድቀት የተነሳ ደቅቄአለሁ፤በጣም አዝኛለሁ፤ በፍርሃት ተውጫለሁ። |
በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም? ወይስ በዚያ ፈዋሽ የለም? ታዲያ የሕዝቤ ሴት ልጅ ያላገገመችው ለምንድን ነው? |
በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች! ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች! |
በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል። ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም። ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላት ሆነውባታል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.