text stringlengths 4 267 |
|---|
ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉም አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል እንደ እህል መባ አድርጎ ያቅርብ። እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። |
“‘አለቃው ሲገባ፣ በበሩ በረንዳ በኩል ይግባ፤ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ። |
የምድሪቱም ነዋሪዎች በበዓል ወቅቶች በይሖዋ ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ፣ የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም በሰሜን በር የሚገቡ፣ በደቡብ በር ይውጡ፤ በደቡብ በር የሚገቡ ደግሞ በሰሜን በር ይውጡ። ማንም ሰው በገባበት በር ተመልሶ አይውጣ፤ ይልቁንም በተቃራኒ አቅጣጫ ባለው በር ይውጣ። |
በመካከላቸው ያለው አለቃ እነሱ በሚገቡበት ጊዜ ይግባ፤ እነሱ በሚወጡበት ጊዜም ይውጣ። |
በበዓላትና በተወሰኑት የበዓል ወቅቶች፣ ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። |
“‘አለቃው ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባን ወይም የኅብረት መሥዋዕትን የፈቃደኝነት መባ አድርጎ ለይሖዋ የሚያቀርብ ከሆነ በምሥራቅ ትይዩ ያለው በር ይከፈትለታል፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባውንና የኅብረት መሥዋዕቱን ያቀርባል። ከወጣ በኋላ በሩ ይዘጋ። |
“‘በየዕለቱ፣ እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባዕት የበግ ጠቦት ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህን በየማለዳው አድርግ። |
ከዚህም ጋር በየማለዳው የኢፍ አንድ ስድስተኛ የእህል መባ እንዲሁም በላመው ዱቄት ላይ የሚፈስ የሂን አንድ ሦስተኛ ዘይት የዘወትር የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህ የዘላለም ደንብ ነው። |
ተባዕቱን የበግ ጠቦት፣ የእህል መባውንና ዘይቱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል የዘወትር መባ አድርገው በየማለዳው ያቅርቡ።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አለቃው ለወንዶች ልጆቹ፣ ለእያንዳንዳቸው ውርስ አድርጎ ስጦታ ቢሰጣቸው፣ ስጦታው የልጆቹ ንብረት ይሆናል። ይህ በውርስ ያገኙት ንብረታቸው ነው። |
ሆኖም ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ላይ ስጦታ ቢሰጥ፣ ነፃ እስከሚወጣበት ዓመት ድረስ ስጦታው የእሱ ይሆናል፤ ከዚያም ለአለቃው ይመለስለታል። ርስቱን ለዘለቄታው የራሳቸው አድርገው መያዝ የሚችሉት ወንዶች ልጆቹ ብቻ ናቸው። |
አለቃው ሕዝቡን ከይዞታቸው በማፈናቀል የትኛውንም ርስት ሊወስድባቸው አይገባም። ከሕዝቤ መካከል አንዳቸውም ከይዞታቸው እንዳይፈናቀሉ ለወንዶች ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ይዞታ ላይ ነው።’” |
ከዚያም ከሰሜን ትይዩ ወደሚገኙት ቅዱስ ወደሆኑት የካህናቱ መመገቢያ ክፍሎች ከሚወስደው በር አጠገብ ባለው መግቢያ በኩል አድርጎ አመጣኝ፤ በዚያም በምዕራብ በኩል ከበስተ ኋላ አንድ ቦታ አየሁ። |
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ካህናቱ አንድም ነገር ወደ ውጨኛው ግቢ ይዘው በመውጣት ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ ሲባል የበደል መባውንና የኃጢአት መባውን የሚቀቅሉት እንዲሁም የእህል መባውን የሚጋግሩት በዚህ ቦታ ነው።” |
ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ ከወሰደኝ በኋላ በአራቱ የግቢው ማዕዘኖች በኩል አዞረኝ፤ በውጨኛው ግቢ በአራቱም ማዕዘኖች በኩል ግቢ አየሁ። |
በአራቱም የግቢው ማዕዘኖች፣ ርዝመታቸው 40 ክንድ፣ ወርዳቸው 30 ክንድ የሆኑ ትናንሽ ግቢዎች ነበሩ። አራቱም መጠናቸው እኩል ነበር። |
በአራቱም ዙሪያ እርከን የነበረ ሲሆን ከእርከኑ ሥር መባዎቹ የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች ተሠርተው ነበር። |
ከዚያም “እነዚህ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ቦታዎች ናቸው” አለኝ። |
ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። |
ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ለመከተል ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ታዲያ እኔን እንዲጠይቁኝ ልፈቅድላቸው ይገባል? |
እንግዲህ ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ እስራኤላዊ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ አንድን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ እንደ አስጸያፊ ጣዖቶቹ ብዛት በተገቢው መንገድ እመልስለታለሁ። |
የእስራኤልን ቤት ሰዎች ልብ አሸብራለሁና፤ ምክንያቱም ሁሉም ከእኔ ርቀዋል፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ተከትለዋል።”’ |
“ስለሆነም የእስራኤልን ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ተመለሱ፤ አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ራቁ፤ ቀፋፊ ከሆኑት ልማዶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ። |
ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ከእኔ በመለየት አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ የእኔን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ አዎ እኔ ራሴ እመልስለታለሁ። |
ፊቴን ወደዚህ ሰው አዞራለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’ |
“‘ይሁንና ነቢዩ ቢሞኝና ምላሽ ቢሰጥ፣ ያንን ነቢይ ያሞኘሁት እኔ ይሖዋ ነኝ። ከዚያም እጄን በእሱ ላይ ዘርግቼ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። |
የፈጸሙት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ፤ ነቢዩን ሊጠይቅ የመጣው ሰው በደል ነቢዩ ከፈጸመው በደል ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል፤ |
ይህም የሚሆነው የእስራኤል ቤት ሰዎች ከእኔ ርቀው እንዳይባዝኑና በሚፈጽሙት በደል ሁሉ ራሳቸውን ከማርከስ እንዲቆጠቡ ነው። እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ አገር ታማኝ ሳይሆን ቀርቶ በእኔ ላይ ኃጢአት ቢፈጽም እጄን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ የምግብ አቅርቦቱም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ ረሃብም እሰድበታለሁ እንዲሁም ሰውንም ሆነ እንስሳን ከዚያ አጠፋለሁ።” |
“‘እነዚህ ሦስት ሰዎች ይኸውም ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ በዚያ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
“‘ወይም አደገኛ የዱር አራዊትን ወደዚያ አገር ብሰድ፣ በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቢፈጁና አገሩ በዱር አራዊቱ የተነሳ ማንም ሰው የማያልፍበት ወና እንዲሆን ቢያደርጉ፣ |
በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ አገሩም ባድማ ይሆናል።’” |
“‘ወይም ደግሞ በአገሩ ላይ ሰይፍ ባመጣና “በአገሩ መካከል ሰይፍ ይለፍ” ብል፣ በአገሩም ላይ ያለውን ሰውም ሆነ እንስሳ ባጠፋ፣ |
እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’” |
“‘ወይም በአገሩ ላይ ቸነፈር ብሰድና ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት ደም በማፍሰስ በአገሩ ላይ ቁጣዬን ባወርድ፣ |
ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’” |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት በኢየሩሳሌም ላይ አራት ቅጣቶቼን ይኸውም ሰይፍን፣ ረሃብን፣ አደገኛ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በምሰድበት ጊዜ ምንኛ የከፋ ይሆን! |
ሆኖም በዚያ የሚቀሩ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በሕይወት ይተርፋሉ፤ ደግሞም ከዚያ ይወሰዳሉ። ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ መንገዳቸውንና ሥራቸውንም በምታዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ ካመጣሁት ጥፋት፣ በእሷም ላይ ካደረስኩት ነገር ሁሉ በእርግጥ ትጽናናላችሁ።’” |
“‘መንገዳቸውንና ሥራቸውን ስታዩ ያጽናኗችኋል፤ በእሷም ላይ ላደርገው የሚገባኝን ነገር ያደረግኩት ያለምክንያት አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልብህ ከመታበዩ የተነሳ ‘እኔ አምላክ ነኝ። በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ። በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንምአንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም። |
እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል። ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ። |
በጥበብህና በማስተዋልህ ራስህን አበልጽገሃል፤በግምጃ ቤቶችህም ውስጥ ወርቅና ብር ማከማቸትህን ቀጥለሃል። |
በንግድህ ስኬታማ ከመሆንህ የተነሳ ብዙ ሀብት አፈራህ፤ካካበትከውም ሀብት የተነሳ ልብህ ታበየ።”’ |
“‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በልብህ አምላክ እንደሆንክ ስለተሰማህ፣ |
ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑትን ባዕዳን አመጣብሃለሁ፤እነሱም በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ግርማህንም ያረክሳሉ። |
ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤በተንጣለለውም ባሕር መካከል አስከፊ ሞት ትሞታለህ። |
ያም ሆኖ በገዳይህ ፊት ‘እኔ አምላክ ነኝ’ ትላለህ? በሚያረክሱህ ሰዎች እጅ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።”’ |
‘በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙ ሰዎችን አሟሟት ትሞታለህ፤እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ ጥበብ የተሞላህና ፍጹም ውበት የተላበስክየፍጽምና ተምሳሌት ነበርክ። |
በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ። በከበሩ ድንጋዮች ሁሉይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና በመረግድ አጊጠህ ነበር፤እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ። በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር። |
የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ አድርጌ ሾምኩህ። በአምላክ ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርክ፤ በእሳታማ ድንጋዮችም መካከል ትመላለስ ነበር። |
ከተፈጠርክበት ቀን አንስቶ ዓመፅ እስከተገኘብህ ጊዜ ድረስበመንገድህ ሁሉ ምንም እንከን አልነበረብህም። |
ከንግድህ ብዛት የተነሳውስጥህ በዓመፅ ተሞላ፤ ኃጢአትም መሥራት ጀመርክ። የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፣ እንደ ርኩስ ቆጥሬ ከአምላክ ተራራ እጥልሃለሁ፤ከእሳታማዎቹ ድንጋዮች መካከልም አስወግድሃለሁ። |
በውበትህ ምክንያት ልብህ ታበየ። ከታላቅ ግርማህ የተነሳ ጥበብህን አበላሸህ። ወደ ምድር እጥልሃለሁ። በነገሥታት ፊት ትዕይንት አደርግሃለሁ። |
ታላቅ በደል በመፈጸምና በንግድ ሥራ በማጭበርበር መቅደሶችህን አረከስክ። እኔም ከመካከልህ እሳት እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላሃል። በሚያዩህ ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሃለሁ። |
ከሕዝቦች መካከል የሚያውቁህ ሁሉ በመገረም አተኩረው ያዩሃል። ፍጻሜህ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆናለህ።”’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ሲዶና አዙረህ በእሷ ላይ ትንቢት ተናገር። |
እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሲዶና ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ በመካከልሽም እከበራለሁ፤ደግሞም በእሷ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበትና በእሷ አማካኝነት በምቀደስበት ጊዜ ሰዎች እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
በእሷ ላይ ቸነፈር እሰዳለሁ፤ በጎዳናዎቿም ላይ ደም ይፈስሳል። ከየአቅጣጫው ሰይፍ በሚመጣባት ጊዜ የታረዱት ሰዎች በመካከሏ ይወድቃሉ፤እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
“‘“ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ አደገኛ በሆነ አሜኬላና በሚያሠቃይ እሾህ ይኸውም በሚንቁት ብሔራት ዳግመኛ አይከበብም፤ ሰዎችም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’ |
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ። እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ላይ ይኖራሉ። |
በላይዋ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ደግሞም በዙሪያቸው ባሉት በሚንቋቸው ሁሉ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ያለስጋት ይኖራሉ፤ እኔም አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተስ የደም ዕዳ ባለባት ከተማ ላይ ፍርድ ለማወጅና አስጸያፊ ነገሮቿን ሁሉ ለማሳወቅ ተዘጋጅተሃል? |
እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከልሽ ደም የምታፈሺ፣ ፍርድ የምትቀበዪበት ጊዜ የደረሰብሽ፣ ትረክሺም ዘንድ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች የምትሠሪ ከተማ ሆይ፣ |
ያፈሰስሽው ደም በደለኛ አድርጎሻል፤ ደግሞም አስጸያፊ ጣዖቶችሽ አርክሰውሻል። የቀኖችሽን መጨረሻ አፋጥነሻል፤ የዘመኖችሽም መጨረሻ ደርሷል። ስለዚህ ብሔራት ነቀፋ እንዲሰነዝሩብሽ፣ አገሩም ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ። |
አንቺ ስምሽ ርኩስ የሆነና ሽብር የሞላብሽ ከተማ ሆይ፣ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉት አገሮች ይሳለቁብሻል። |
እነሆ፣ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል አለቃ ሥልጣኑን ደም ለማፍሰስ ይጠቀምበታል። |
በአንቺ ውስጥ ያሉት ሰዎች አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን ያቃልላሉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ያጭበረብራሉ፤ ደግሞም አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይበድላሉ።”’” |
“‘ቅዱስ ስፍራዎቼን ታቃልያለሽ፤ ሰንበቶቼንም ታረክሻለሽ። |
በአንቺ ውስጥ ደም የማፍሰስ ዓላማ ያላቸው ስም አጥፊዎች አሉ። በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ መሥዋዕቶችን ይበላሉ፤ በመካከልሽም ጸያፍ ምግባር ይፈጽማሉ። |
በአንቺ ውስጥ የአባታቸውን መኝታ ያረክሳሉ፤ ደግሞም በወር አበባዋ የረከሰችን ሴት አስገድደው ይደፍራሉ። |
በአንቺ ውስጥ አንዱ ከባልንጀራው ሚስት ጋር አስጸያፊ ነገር ይሠራል፤ ሌላው ጸያፍ ምግባር በመፈጸም የገዛ ምራቱን ያረክሳታል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ አባቱ ልጅ የሆነችውን እህቱን አስገድዶ ይደፍራል። |
በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ። ወለድና ትርፍ ለማግኘት ታበድሪያለሽ፤ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ። አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘እነሆ፣ ያገኘሽውን አግባብ ያልሆነ ጥቅምና በመካከልሽ ያፈሰስሽውን ደም በመጸየፍ አጨበጭባለሁ። |
በአንቺ ላይ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ልብሽ ሊጸና፣ እጆችሽስ ብርቱ ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ? እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አደርገዋለሁ። |
በብሔራት መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤ ርኩሰትሽንም አስወግዳለሁ። |
አንቺም በብሔራት ፊት ትዋረጃለሽ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ።’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ሆነውብኛል። ሁሉም ምድጃ ውስጥ ያለ መዳብ፣ ቆርቆሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው። ብር ሲቀልጥ ከላይ እንደሚሰፍ ቆሻሻ ሆነዋል። |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሁላችሁም ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ስለሆናችሁ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ። |
እሳት በላያቸው ላይ እንዲነድባቸውና እንዲቀልጡ ብር፣ መዳብ፣ ብረት፣ እርሳስና ቆርቆሮ በምድጃ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ሁሉ እኔም እናንተን በንዴትና በታላቅ ቁጣ እሰበስባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ እሳት በማንደድ አቀልጣችኋለሁ። |
አንድ ላይ እሰበስባችኋለሁ፤ በላያችሁም ላይ የቁጣዬን እሳት አነዳለሁ፤ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ። |
ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ ሁሉ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ፤ በእናንተ ላይ ቁጣዬን ያፈሰስኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ እንዲህ በላት፦ ‘አንቺ በቁጣ ቀን የማትጸጂ ወይም ዝናብ የማይዘንብብሽ ምድር ነሽ። |
ነቢያቷ ያደነውን እንስሳ እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ በውስጧ ሴራ ጠንስሰዋል። ሰዎችን ይውጣሉ። ውድ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ። በውስጧ ያሉትን ብዙ ሴቶች መበለት አድርገዋል። |
ካህናቷ ሕጌን ጥሰዋል፤ ቅዱስ ስፍራዎቼንም ያረክሳሉ። ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው ነገር መካከል ምንም ልዩነት አያደርጉም፤ ደግሞም ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አያስታውቁም፤ ሰንበቶቼንም ለማክበር አሻፈረኝ ይላሉ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስኩ። |
በመካከሏ ያሉት አለቆቿ ያደኑትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ደም ያፈሳሉ፤ የሰዎችንም ሕይወት ያጠፋሉ። |
ነቢያቷ ግን እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በኖራ ይለስናሉ። የሐሰት ራእዮች ያያሉ፤ የውሸት ሟርትም ያሟርታሉ፤ ደግሞም ይሖዋ ራሱ ምንም ሳይናገር “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል” ይላሉ። |
የምድሪቱ ሰዎች የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል፤ ሌሎችን ዘርፈዋል፤ ችግረኛውንና ድሃውን በድለዋል፤ ደግሞም ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አጭበርብረዋል፤ ፍትሕንም ነፍገውታል።’ |
“‘ከመካከላቸው የድንጋይ ቅጥሩን የሚጠግን ወይም ምድሪቱ እንዳትጠፋ በፈረሰው ቦታ ላይ በፊቴ የሚቆምላት ሰው ይኖር እንደሆነ ተመለከትኩ፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም። |
ስለዚህ ቁጣዬን በእነሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በታላቅ ቁጣዬም እሳት ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ። የመረጡት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል? |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.