text stringlengths 4 267 |
|---|
ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ? |
እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? |
ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!” |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ። |
ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” |
“‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
በ12ኛውም ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፦‘በብሔራት መካከል እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ ነበርክ፤አሁን ግን አክትሞልሃል። አንተ እንደ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት ነበርክ፤ በወንዞችህ ውስጥ ትንቦጫረቅ፣በእግርህም ውኃውን ታደፈርስ፣ ወንዞቹንም ታቆሽሽ ነበር።’ |
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በብዙ ብሔራት ጉባኤ አማካኝነት መረቤን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤እነሱም በማጥመጃ መረቤ ጎትተው ያወጡሃል። |
በምድር ላይ እተውሃለሁ፤አውላላ ሜዳ ላይ እጥልሃለሁ። የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲሰፍሩ አደርጋለሁ፤በመላው ምድር የሚገኙትን የዱር እንስሳትም በአንተ አጠግባለሁ። |
ሥጋህን በተራሮች ላይ እጥላለሁ፤ከሬሳህ በተረፉት ነገሮችም ሸለቆዎቹን እሞላለሁ። |
ምድሪቷ እስከ ተራሮች ድረስ በሚፈሰው ደምህ እንድትርስ አደርጋለሁ፤ጅረቶችም በደምህ ይሞላሉ።’ |
‘አንተም በምትጠፋበት ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ። ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፤ጨረቃም ብርሃኗን አትፈነጥቅም። |
በሰማያት ያሉትን ብርሃን ሰጪ አካላት ሁሉ ከአንተ የተነሳ አጨልማቸዋለሁ፤ምድርህንም ጨለማ አለብሳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
‘ከአንተ የተማረኩትን ወደ ሌሎች ብሔራት ይኸውም ወደማታውቃቸው አገሮች በምወስድበት ጊዜየብዙ ሰዎችን ልብ አስጨንቃለሁ። |
ብዙ ሕዝቦች እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ሰይፌንም በፊታቸው ሳወዛውዝ ከአንተ የተነሳ ንጉሦቻቸው በፍርሃት ይርዳሉ። አንተ በምትወድቅበት ቀንእያንዳንዳቸው ለሕይወታቸው በመፍራት ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ።’ |
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል። |
ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብህ በኃያላን ተዋጊዎች ሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ሁሉም ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኞች ናቸው። እነሱም የግብፅን ኩራት ያንኮታኩታሉ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧም ሁሉ ይደመሰሳል። |
ከብቶቿን ሁሉ ከብዙ ውኃዎቿ አጠገብ አጠፋለሁ፤የሰው እግርም ሆነ የከብቶች ኮቴ ዳግመኛ አያደፈርሳቸውም።’ |
‘በዚያን ጊዜ ውኃዎቻቸውን አጠራለሁ፤ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
‘ግብፅን ባድማና ወና በማድረግ ምድሪቱን የሞላውን ነገር ሁሉ በማስወግድበት ጊዜ፣ነዋሪዎቿንም ሁሉ በምመታበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ይህ ሙሾ ነው፤ ሰዎችም ያንጎራጉሩታል፤የብሔራት ሴቶች ልጆች ያንጎራጉሩታል። በግብፅና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቧ ሁሉ የተነሳ ያንጎራጉሩታል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
ከዚያም በ12ኛው ዓመት፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ስፍር ቁጥር ለሌለው የግብፅ ሕዝብ ዋይ ዋይ በል፤ እሷንና የኃያላን ብሔራትን ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ከምድር በታች አውርዳቸው። |
“‘በውበት ማንን ትበልጣለህ? ወደ ታች ውረድ፤ ካልተገረዙትም ጋር ተጋደም!’ |
“‘በሰይፍ በታረዱት መካከል ይወድቃሉ። እሷ ለሰይፍ ተሰጥታለች፤ እሷንም ሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝቧን ሁሉ ጎትቱ። |
“‘ኃያላኑ ተዋጊዎች እሱንና ረዳቶቹን ከጥልቅ መቃብር ውስጥ ያነጋግሯቸዋል። እነሱ በእርግጥ ወደ ታች ይወርዳሉ፤ ደግሞም በሰይፍ ታርደው፣ እንዳልተገረዙት ሰዎች ይጋደማሉ። |
አሦር ከመላ ጉባኤዋ ጋር በዚያ ትገኛለች። መቃብሮቻቸው በእሱ ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። |
መቃብሮቿ በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ይገኛሉ፤ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም በሰይፍ ተመትተው ወድቀዋል፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር። |
“‘ኤላም ስፍር ቁጥር ከሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር በመቃብሯ ዙሪያ ትገኛለች፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የፈጠሩት እነዚህ ሰዎች ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል። ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። |
በመቃብሯ ዙሪያ ከሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር፣ በታረዱት መካከል መኝታ አዘጋጅተውላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የታረዱ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። እሱ በታረዱት መካከል እንዲቀመጥ ተደርጓል። |
“‘መሼቅና ቱባል እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝባቸው ሁሉ በዚያ ይገኛሉ። መቃብሮቿ በዙሪያው ናቸው። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተወጉ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረዋል። |
እነሱ፣ ከወደቁትና ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ወደ መቃብር ከወረዱት ያልተገረዙ ኃያላን ተዋጊዎች ጋር ይጋደሙ የለም? ሰይፎቻቸውን ከራሳቸው በታች ያደርጋሉ፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ የሚደርስባቸው ቅጣት በአጥንታቸው ላይ ይሆናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች የሕያዋንን ምድር አሸብረዋል። |
አንተ ግን ባልተገረዙት መካከል ትደቅቃለህ፤ በሰይፍ ከታረዱትም ጋር ትጋደማለህ። |
“‘ኤዶም፣ ነገሥታቷና አለቆቿ ሁሉ በዚያ ይገኛሉ፤ ኃያላን ሆነው ሳለ በሰይፍ በታረዱት መካከል ተጋድመዋል፤ እነሱም ካልተገረዙትና ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ይጋደማሉ። |
“‘የሰሜን ገዢዎች በሙሉ ከሲዶናውያን ሁሉ ጋር በዚያ ይገኛሉ፤ ኃይላቸው ሽብር የፈጠረ ቢሆንም ከታረዱት ሰዎች ጋር ኀፍረት ተከናንበው ወርደዋል። በሰይፍ ከታረዱት ጋር ሳይገረዙ ይጋደማሉ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱትም ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። |
“‘ፈርዖን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይመለከታል፤ ደግሞም ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ከደረሰው ነገር ሁሉ ይጽናናል፤ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ ይታረዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘በሕያዋን ምድር ሽብር ስለፈጠረ ፈርዖንና ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቡ ሁሉ በሰይፍ ከታረዱት፣ ካልተገረዙት ሰዎች ጋር ለማረፍ ይጋደማሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። |
ከተማዋን ክበብ፤ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት። |
የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዋ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው። ፊትህንም በእሷ ላይ አዙር፤ ከተማዋም ትከበባለች፤ አንተም ትከባታለህ። ይህ ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል። |
“ከዚያም በግራ ጎንህ ትተኛለህ፤ የእስራኤልንም ቤት በደል በላይህ ላይ ታኖራለህ። በጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር በደላቸውን ትሸከማለህ። |
እኔም በደል በፈጸሙባቸው ዓመታት መጠን 390 ቀናት በአንተ ላይ እመድባለሁ፤ አንተም የእስራኤልን ቤት በደል ትሸከማለህ። |
እነዚህንም ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርብሃል። “ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተኛለህ፤ የይሁዳንም ቤት በደል ለ40 ቀናት ትሸከማለህ። ለአንድ ዓመት አንድ ቀን፣ ለአንድ ዓመት አንድ ቀን ሰጥቼሃለሁ። |
ክንድህን ገልጠህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ታዞራለህ፤ በእሷም ላይ ትንቢት ትናገራለህ። |
“እነሆ፣ የከበባህን ጊዜ እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ። |
“አንተም ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ማሽላና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ ለራስህም ዳቦ ጋግር። በጎንህ በምትተኛባቸው 390 ቀናት ትበላዋለህ። |
በየቀኑ 20 ሰቅል እየመዘንክ ትበላለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ። |
“ደግሞም የሂን አንድ ስድስተኛ ለክተህ ውኃ ትጠጣለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ። |
“የገብስ ሙልሙል እንደምትበላ ትበላዋለህ፤ የደረቀን የሰው ዓይነ ምድር እንደ ማገዶ ተጠቅመህ በፊታቸው ትጋግረዋለህ።” |
ከዚያም ይሖዋ “ልክ እንደዚሁ እስራኤላውያንም እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት መካከል የረከሰ ምግብ ይበላሉ” አለ። |
ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህስ አይሁን! እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሞቶ የተገኘም ሆነ አውሬ የቦጫጨቀው እንስሳ ሥጋ በልቼ የረከስኩበት ጊዜ የለም፤ የረከሰም ሥጋ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም።” |
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “መልካም፣ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ኩበት እንድትጠቀም ፈቅጄልሃለሁ፤ የምትበላውንም ዳቦ በእሱ ትጋግራለህ።” |
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦት እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ። |
ይህም የሚሆነው ምግብና ውኃ አጥተው እርስ በርስ በድንጋጤ እንዲተያዩ እንዲሁም ከበደላቸው የተነሳ እንዲመነምኑ ነው። |
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። |
እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ። |
በግራ እጅህ ያለውን ደጋንህንም ሆነ በቀኝ እጅህ የያዝካቸውን ፍላጻዎችህን አስጥልሃለሁ። |
አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር የሚሆኑት ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ለተለያዩ አዳኝ አሞሮች ሁሉና ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።”’ |
“‘አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘በማጎግና ያለስጋት በደሴቶች በሚኖሩት ላይም እሳት እሰዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ ብሔራትም እኔ ይሖዋ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ |
“‘አዎ፣ በትንቢት የተነገረው ነገር ይመጣል፤ ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ያ ያልኩት ቀን ይህ ነው። |
በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወጥተው፣ የጦር መሣሪያዎቹን ይኸውም ትናንሾቹንና ትላልቆቹን ጋሻዎች፣ ደጋኖቹን፣ ፍላጻዎቹን፣ የጦር ቆመጦቹንና ጦሮቹን እሳት ያነዱባቸዋል። ለሰባት ዓመታትም እሳት ለማንደድ ይጠቀሙባቸዋል። |
የጦር መሣሪያዎቹን እሳት ለማንደድ ስለሚጠቀሙባቸው ከሜዳ እንጨት መልቀም ወይም ከጫካ ማገዶ መሰብሰብ አያስፈልጋቸውም።’ “‘የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ የመዘበሯቸውንም ይመዘብራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር፣ ከባሕሩ በስተ ምሥራቅ በሚጓዙት ሰዎች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ በዚያ የሚያልፉትንም ሰዎች መንገድ ይዘጋል። ጎግንና ስፍር ቁጥር የሌለውን ሠራዊቱን ሁሉ በዚያ ይቀብራሉ፤ ሸለቆውንም የሃሞን ጎግ ሸለቆ ብለው ይጠሩታል። |
የእስራኤል ቤት ሰዎች እነሱን ቀብረው ምድሪቱን ለማንጻት ሰባት ወር ይፈጅባቸዋል። |
የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እነሱን ይቀብራል፤ ይህም ራሴን በማስከብርበት ቀን ዝና ያስገኝላቸዋል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘ምድሪቱ ትነጻ ዘንድ፣ ሰዎች በየጊዜው በምድሪቱ ላይ እንዲያልፉና በምድሪቱ ላይ የቀሩትን አስከሬኖች እንዲቀብሩ ይመደባሉ። ለሰባት ወራትም ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። |
በምድሪቱ ላይ የሚያልፉት ሰዎች የሰው አፅም ሲያዩ በአጠገቡ ምልክት ያደርጋሉ። ከዚያም እንዲቀብሩ የተመደቡት አፅሙን በሃሞን ጎግ ሸለቆ ይቀብሩታል። |
በዚያም ሃሞና ተብላ የምትጠራ ከተማ ትኖራለች። እነሱም ምድሪቱን ያነጻሉ።’ |
“አንተም፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለተለያዩ ወፎችና ለዱር አራዊት ሁሉ እንዲህ በል፦ “አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ኑ። ለእናንተ በማዘጋጀው መሥዋዕቴ ዙሪያ ተሰብሰቡ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚዘጋጅ ታላቅ መሥዋዕት ነው። ሥጋ ትበላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ። |
የኃያላንን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች ደም ትጠጣላችሁ፤ እነሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ አውራ ፍየሎችና ወይፈኖች ሲሆኑ ሁሉም የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው። |
እናንተም እኔ ከማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት፣ እስክትጠግቡ ድረስ ስብ ትሰለቅጣላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።”’ |
“‘በማዕዴም ፈረሶችንና ሠረገለኞችን እንዲሁም ኃያላን ሰዎችንና ሁሉንም ዓይነት ተዋጊዎች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል ያያሉ። |
ከዚያ ቀን አንስቶ የእስራኤል ቤት ሰዎች እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ብሔራትም የእስራኤል ቤት ሰዎች በግዞት የተወሰዱት በገዛ ራሳቸው በደል ይኸውም ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ ያውቃሉ። ስለዚህ ፊቴን ከእነሱ ሰወርኩ፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ። |
እንደ ርኩሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን አደረግኩባቸው፤ ፊቴንም ከእነሱ ሰወርኩ።’ |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ። |
ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ውርደት ከደረሰባቸው በኋላ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በምድራቸው ላይ ያለስጋት ይኖራሉ። |
ከሕዝቦች መካከል መልሼ ሳመጣቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮች ስሰበስባቸው፣ በብዙ ብሔራት ፊት፣ በመካከላቸው ራሴን እቀድሳለሁ።’ |
“‘በብሔራት መካከል በግዞት እንዲኖሩ ሳደርግና ከዚያም አንዳቸውንም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው መልሼ ሳመጣቸው፣ እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
በሰባተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ይሖዋን ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። |
ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመጣችሁት እኔን ለመጠየቅ ነው? ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? አባቶቻቸው የሠሯቸውን አስጸያፊ ነገሮች አሳውቃቸው። |
እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን በመረጥኩበት ቀን፣ ለያዕቆብ ቤት ዘሮች ማልኩላቸው፤ በግብፅም ምድር ራሴን አሳወቅኳቸው። አዎ፣ ማልኩላቸው፤ ደግሞም ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ’ አልኳቸው። |
በዚያ ቀን፣ ከግብፅ ምድር አውጥቼ ለእነሱ ወደመረጥኳት ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንደማስገባቸው ማልኩላቸው። እሷም ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ ነበረች። |
ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በዓይናችሁ ፊት ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አስወግዱ፤ አስጸያፊ በሆኑት የግብፅ ጣዖቶች ራሳችሁን አታርክሱ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’ |
“‘“እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ፤ እኔን ለመስማትም ፈቃደኞች አልነበሩም። በፊታቸው ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አላስወገዱም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑትን የግብፅ ጣዖቶች አልተዉም። በመሆኑም በግብፅ ምድር ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። |
ይሁንና እነሱ በሚኖሩባቸው ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ። እነሱን ከግብፅ ምድር ባወጣሁበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ፊት ማንነቴን አሳውቄአቸዋለሁና። |
ስለሆነም ከግብፅ ምድር አውጥቼ ወደ ምድረ በዳ መራኋቸው። |
“‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው። |
ደግሞም በእኔና በእነሱ መካከል ምልክት እንዲሆን ሰንበቶቼን ሰጠኋቸው፤ ይህን ያደረግኩት የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ እንዲያውቁ ነው። |
“‘“ሆኖም የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድረ በዳ በእኔ ላይ ዓመፁ። ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አቃለዋል። ሰንበቶቼንም ፈጽሞ አረከሱ። በመሆኑም ጨርሶ አጠፋቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነሱ ላይ ታላቅ ቁጣዬን ለማፍሰስ ቃል ገባሁ። |
እነሱን ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ። |
ደግሞም ለእነሱ ወደሰጠኋት ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣ ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ ወደሆነችው ምድር እንደማላስገባቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤ |
ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አቃለዋል፤ ደንቦቼንም አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰንበቶቼንም አርክሰዋል፤ ልባቸው አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻቸውን ተከትሏልና። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.