text stringlengths 4 267 |
|---|
አንድ ሌላ ሰው ደግሞ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እከተልሃለሁ፤ በመጀመሪያ ግን ቤተሰቤን እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው። |
ኢየሱስም “ዕርፍ ጨብጦ በኋላው ያሉትን ነገሮች የሚመለከት ሰው ለአምላክ መንግሥት የሚገባ አይደለም” አለው። |
ይሁን እንጂ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ ያዘጋጇቸውን ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ይዘው ጠዋት በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄዱ። |
ሆኖም ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፤ |
ወደ ውስጥ ሲገቡም የጌታ ኢየሱስን አስከሬን አላገኙም። |
በሁኔታው ግራ ተጋብተው እያሉ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ። |
ሴቶቹ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ እንዲህ አሏቸው፦ “ሕያው የሆነውን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ? |
እሱ እዚህ የለም፤ ከሞት ተነስቷል። ገና በገሊላ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳላችሁ አስታውሱ፤ |
‘የሰውን ልጅ ለኃጢአተኞች አሳልፈው ሊሰጡት፣ በእንጨት ላይ ሊሰቀልና በሦስተኛው ቀን ሊነሳ ይገባል’ ብሎ ነበር።” |
በዚህ ጊዜ ሴቶቹ የተናገረውን ቃል አስታወሱ፤ |
ከዚያም መቃብሩ ካለበት ስፍራ ተመልሰው እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለአሥራ አንዱና ለቀሩት ሁሉ ነገሯቸው። |
እነሱም መግደላዊቷ ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም ነበሩ። ከእነሱ ጋር የነበሩት ሌሎቹ ሴቶችም እነዚህን ነገሮች ለሐዋርያት ነገሯቸው። |
ይሁን እንጂ እንዲሁ የሚቀባጥሩ ስለመሰላቸው ሴቶቹ የሚናገሩትን አላመኗቸውም። |
ጴጥሮስ ግን ተነስቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ ጎንበስ ብሎም ወደ ውስጥ ሲመለከት በፍታውን ብቻ አየ። በሆነውም ነገር እየተገረመ ከዚያ ሄደ። |
ይሁንና በዚያው ቀን ከመካከላቸው ሁለቱ ከኢየሩሳሌም አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ ወደምትገኝ ኤማሁስ ወደምትባል መንደር እየተጓዙ ነበር፤ |
እነሱም ስለሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ ነበር። |
ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ አብሯቸው መሄድ ጀመረ፤ |
ሆኖም ማንነቱን እንዳይለዩ ዓይናቸው ተጋርዶ ነበር። |
እሱም “እየተጓዛችሁ እንዲህ እርስ በርስ የምትወያዩበት ጉዳይ ምንድን ነው?” አላቸው። በዚህ ጊዜ በሐዘን እንደተዋጡ ባሉበት ቆሙ። |
ቀለዮጳ የተባለውም መልሶ “በኢየሩሳሌም ውስጥ ለብቻህ የምትኖር እንግዳ ሰው ነህ እንዴ? ሰሞኑን በዚያ የተፈጸመውን ነገር አታውቅም ማለት ነው?” አለው። |
እሱም “ምን ተፈጸመ?” አላቸው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክና በሰው ሁሉ ፊት በሥራም ሆነ በቃል ኃያል ነቢይ ከሆነው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ነገር ነዋ! |
የካህናት አለቆቻችንና ገዢዎቻችን ለሞት ፍርድ አሳልፈው ሰጡት፤ እንዲሁም በእንጨት ላይ ቸነከሩት። |
እኛ ግን ይህ ሰው እስራኤልን ነፃ ያወጣል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ከዚህም በላይ ይህ ነገር ከተፈጸመ እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው። |
ደግሞም ከእኛው መካከል አንዳንድ ሴቶች በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄደው ስለነበር የሚያስገርም ነገር ነገሩን፤ |
አስከሬኑንም ባጡ ጊዜ ተመልሰው መጥተው በተአምር የተገለጡላቸውንና እሱ ሕያው እንደሆነ የነገሯቸውን መላእክት እንዳዩ ነገሩን። |
ከዚያም ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ነበር፤ እነሱም ሴቶቹ እንደተናገሩት ሆኖ አገኙት፤ እሱን ግን አላዩትም።” |
እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁና ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ! |
ክርስቶስ እነዚህን መከራዎች መቀበልና ክብር ማግኘት አይገባውም?” |
ከዚያም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እሱ በቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን በሚገባ አብራራላቸው። |
በመጨረሻም ወደሚሄዱበት መንደር ተቃረቡ፤ ይሁንና እሱ አልፎ የሚሄድ ይመስል ነበር። |
እነሱ ግን “ቀኑ እየተገባደደና ምሽቱ እየተቃረበ ስለሆነ እኛ ጋ እደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት። እሱም እነሱ ጋ ለማደር ገባ። |
ከእነሱ ጋር እየበላ ሳለም ዳቦውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ይሰጣቸው ጀመር። |
በዚህ ጊዜ ዓይናቸው ሙሉ በሙሉ ተከፈተና ማን መሆኑን በሚገባ አወቁ፤ እሱ ግን ከአጠገባቸው ተሰወረ። |
እነሱም እርስ በርሳቸው “በመንገድ ላይ ሲያነጋግረንና ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ ሲገልጥልን ልባችን እንደ እሳት ይቃጠልብን አልነበረም?” ተባባሉ። |
በዚያኑም ሰዓት ተነስተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ አሥራ አንዱንና ከእነሱ ጋር የነበሩትንም አንድ ላይ ተሰብስበው አገኟቸው፤ |
እነሱም “ጌታ በእርግጥ ተነስቷል፤ ለስምዖንም ተገልጦለታል!” ይሉ ነበር። |
ሁለቱ ደግሞ በመንገድ ላይ ያጋጠማቸውን ነገርና ዳቦውን በቆረሰበት ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው። |
እነዚህን ነገሮች እየተነጋገሩ ሳለ እሱ ራሱ በመካከላቸው ቆመ፤ ከዚያም “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። |
እነሱ ግን ከመደንገጣቸውና ከመፍራታቸው የተነሳ መንፈስ ያዩ መሰላቸው። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ለምን ትረበሻላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ውስጥ ጥርጣሬ ያድራል? |
እኔ ራሴ መሆኔን እንድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ ደግሞም ዳስሳችሁኝ እዩ፤ መንፈስ በእኔ ላይ እንደምታዩት ሥጋና አጥንት የለውምና።” |
ይህን እያለም እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። |
እነሱ ግን በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው በነገሩ እየተገረሙ ሳሉ “የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። |
እነሱም የተጠበሰ ቁራሽ ዓሣ ሰጡት፤ |
እሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ። |
ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት ስለ እኔ የተጻፉት ነገሮች ሁሉ መፈጸም አለባቸው’ ብዬ የነገርኳችሁ ቃሌ ይህ ነው።” |
ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም መረዳት እንዲችሉ አእምሯቸውን ከፈተላቸው፤ |
እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤ |
በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል። |
እናንተም ለእነዚህ ነገሮች ምሥክር ትሆናላችሁ። |
እኔም አባቴ ቃል የገባውን ነገር እልክላችኋለሁ። እናንተ ግን ከላይ የሚመጣውን ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በከተማዋ ውስጥ ቆዩ።” |
ከዚያም እስከ ቢታንያ ይዟቸው ሄደ፤ እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። |
እየባረካቸውም ሳለ ከእነሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ተወሰደ። |
እነሱም ሰገዱለት፤ ከዚያም በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። |
ዘወትር በቤተ መቅደስ እየተገኙም አምላክን ያወድሱ ነበር። |
በዚያ ዘመን፣ አውግስጦስ ቄሳር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ። |
(ይህ የመጀመሪያ ምዝገባ የተካሄደው ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዢ በነበረበት ጊዜ ነው።) |
ሁሉም ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ። |
ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለነበር በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነስቶ በይሁዳ ወዳለች ቤተልሔም ተብላ ወደምትጠራ የዳዊት ከተማ ወጣ። |
ለመመዝገብ የሄደውም በታጨችለት መሠረት ካገባትና የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከማርያም ጋር ነበር። |
በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ። |
የበኩር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅም ወለደች፤ በእንግዶች ማረፊያም፣ ቦታ ስላላገኙ ልጁን በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ውስጥ አስተኛችው። |
በዚያው ክልል፣ ሌሊት ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። |
በድንገት የይሖዋ መልአክ መጥቶ በፊታቸው ቆመ፤ የይሖዋም ክብር በዙሪያቸው አንጸባረቀ፤ እነሱም በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። |
መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ እነሆ፣ ለሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚያስገኝ ምሥራች እነግራችኋለሁ፤ |
በዛሬው ዕለት በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋልና፤ እሱም ጌታ ክርስቶስ ነው። |
ይህም ምልክት ይሁናችሁ፦ አንድ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” |
በድንገት ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ታዩ፤ አምላክንም እያመሰገኑ እንዲህ አሉ፦ |
“በሰማያት ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም አምላክ ሞገስ ለሚያሳያቸው ሰዎች ሰላም ይሁን።” |
መላእክቱም ከእነሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ እረኞቹ እርስ በርሳቸው “አሁኑኑ ወደ ቤተልሔም ሄደን ይሖዋ በገለጠልን መሠረት በዚያ የተፈጸመውን ነገር ማየት አለብን” ተባባሉ። |
በፍጥነትም ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኟቸው፤ ሕፃኑም በግርግም ተኝቶ ነበር። |
ይህን ባዩ ጊዜ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን መልእክት አወሩ። |
ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ |
ማርያም ግን የሰማቻቸውን ነገሮች በውስጧ ይዛ በልቧ ታሰላስል ነበር። |
እረኞቹም የሰሙትና ያዩት ነገር ሁሉ ልክ እንደተነገራቸው ሆኖ ስላገኙት አምላክን እያከበሩና እያወደሱ ተመለሱ። |
ከስምንት ቀን በኋላ፣ ሕፃኑ የሚገረዝበት ጊዜ ሲደርስ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ። |
በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ |
ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት” ተብሎ በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው። |
ደግሞም የይሖዋ ሕግ በሚያዘው መሠረት “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች” መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። |
እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር። |
በተጨማሪም ይሖዋ የቀባውን ሳያይ እንደማይሞት አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ነበር። |
እሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ፤ ሕጉ ለልጁ እንዲደረግ በሚያዘው የተለመደ ሥርዓት መሠረት ወላጆቹ ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘውት በገቡ ጊዜ |
ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈውና አምላክን አወደሰ፤ እንዲህም አለ፦ |
“ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ በተናገርከው ቃል መሠረት አሁን ባሪያህን በሰላም እንዲያርፍ ታደርገዋለህ፤ |
ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤ |
ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤ |
ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ የሚገልጥ ብርሃን እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።” |
አባቱና እናቱም ስለ ልጁ በሚነገሩት ነገሮች ይደነቁ ነበር። |
ስምዖንም እነሱን ከባረካቸው በኋላ እናቱን ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅም ሆነ መነሳት ምክንያት ይሆናል፤ እንዲሁም ብዙዎች የሚቃወሙት ምልክት ይሆናል፤ |
ይህም የሚሆነው በብዙዎች ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ ነው፤ በአንቺም ውስጥ ትልቅ ሰይፍ ያልፋል።” |
ከአሴር ነገድ፣ የፋኑኤል ልጅ የሆነች ሐና የምትባል ነቢዪት ነበረች። ይህች ሴት በዕድሜ የገፋች ነበረች፤ ካገባች በኋላ ከባሏ ጋር የኖረችው ለሰባት ዓመት ብቻ ነበር፤ |
በዚህ ጊዜ 84 ዓመት የሆናት መበለት ነበረች። ሌትና ቀንም በጾምና በምልጃ ቅዱስ አገልግሎት እያቀረበች ከቤተ መቅደስ ፈጽሞ አትጠፋም ነበር። |
በዚያን ሰዓትም ቀርባ አምላክን ታመሰግን ጀመር፤ አምላክ ኢየሩሳሌምን ነፃ ያወጣል ብለው ለሚጠባበቁም ሁሉ ስለ ሕፃኑ መናገር ጀመረች። |
የይሖዋ ሕግ በሚለው መሠረት ሁሉንም ነገር ከፈጸሙ በኋላ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ። |
ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ እንዲሁም በጥበብ እየተሞላ ሄደ፤ የአምላክም ሞገስ በእሱ ላይ ነበር። |
ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው። |
ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ እንደተለመደው በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። |
በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ተጠናቀው መመለስ በጀመሩ ጊዜ ኢየሱስ እዚያው ኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹም ይህን አላስተዋሉም ነበር። |
አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰዎች ጋር ያለ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላም ዘመዶቻቸውና የሚያውቋቸው ሰዎች ጋ ይፈልጉት ጀመር። |
ባጡት ጊዜ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እሱን ለማግኘትም ብዙ ደከሙ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.