text
stringlengths
4
267
እነሱ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን እንደተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ለእኛ ምሳሌ ሆነውልናል።
“ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ። ከዚያም ሊጨፍሩ ተነሱ” ተብሎ እንደተጻፈው ከእነሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።
ከእነሱ አንዳንዶቹ የፆታ ብልግና ፈጽመው ከመካከላቸው 23,000 የሚሆኑት በአንድ ቀን እንደረገፉ እኛም የፆታ ብልግና አንፈጽም።
ከእነሱ አንዳንዶቹ ይሖዋን ተፈታትነው በእባቦች እንደጠፉ እኛም አንፈታተነው።
በተጨማሪም ከእነሱ አንዳንዶቹ በማጉረምረማቸው በአጥፊው እንደጠፉ አጉረምራሚዎች አትሁኑ።
እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ በእነሱ ላይ ደረሱ፤ የተጻፉትም የሥርዓቶቹ ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅ ነው።
በመሆኑም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው ፈተና የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም። ይሁንና አምላክ ታማኝ ነው፤ ልትሸከሙት ከምትችሉት በላይ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤ ከዚህ ይልቅ ፈተናውን በጽናት መቋቋም እንድትችሉ ፈተና ሲደርስባችሁ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።
ይህን የምናገረው ማስተዋል ላላቸው ሰዎች ነው፤ የምናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።
የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም መቋደስ አይደለም? የምንቆርሰውስ ቂጣ ከክርስቶስ አካል መቋደስ አይደለም?
ምክንያቱም እኛ ብዙ ብንሆንም ቂጣው አንድ ስለሆነ አንድ አካል ነን፤ ሁላችንም የምንካፈለው ከዚሁ አንድ ቂጣ ነውና።
እስቲ ሥጋዊ እስራኤላውያንን ተመልከቱ፦ መሥዋዕቱን የሚበሉት ከመሠዊያው ጋር ተቋዳሾች አይደሉም?
እንግዲህ ምን እያልኩ ነው? ለጣዖት የተሠዋ ነገር የተለየ ፋይዳ አለው ማለቴ ነው? ወይስ ጣዖት ዋጋ አለው ማለቴ ነው?
እንዲህ ማለቴ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ አሕዛብ መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቧቸውን ነገሮች የሚሠዉት ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት ነው ማለቴ ነው፤ ከአጋንንት ጋር እንድትተባበሩ ደግሞ አልፈልግም።
የይሖዋን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም፤ “ከይሖዋ ማዕድ” እና ከአጋንንት ማዕድ መካፈል አትችሉም።
ወይስ ‘ይሖዋን እያስቀናነው ነው’? እኛ ከእሱ ይበልጥ ብርቱዎች ነን እንዴ?
ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፤ ሆኖም ሁሉም ነገር ይጠቅማል ማለት አይደለም። ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፤ ሆኖም ሁሉም ነገር ያንጻል ማለት አይደለም።
እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ።
ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ማንኛውንም ነገር ብሉ፤
“ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የይሖዋ ነውና።”
አማኝ ያልሆነ ሰው ቢጋብዛችሁና መሄድ ብትፈልጉ ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ የቀረበላችሁን ሁሉ ብሉ።
ይሁንና አንድ ሰው “ይህ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበ ነው” ቢላችሁ ይህን ለነገራችሁ ሰውና ለሕሊና ስትሉ አትብሉ።
እንዲህ ስል ስለ ራሳችሁ ሕሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ሕሊና መናገሬ ነው። ነፃነቴ በሌላው ሰው ሕሊና ለምን ይፈረድበት?
አመስግኜ የምበላ ከሆነ ባመሰገንኩበት ነገር ለምን እነቀፋለሁ?
ስለዚህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉ።
ለአይሁዳውያንም ሆነ ለግሪካውያን እንዲሁም ለአምላክ ጉባኤ እንቅፋት አትሁኑ፤
እኔ ብዙዎች እንዲድኑ የእነሱን እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በማደርገው ነገር ሁሉ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ።
ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ።
መዋጮ የሚሰባሰበው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አቅሙ በሚፈቅድለት መጠን የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ።
ስመጣም የመረጣችኋቸውንና የድጋፍ ደብዳቤ የጻፋችሁላቸውን ሰዎች የልግስና ስጦታችሁን ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ።
ይሁን እንጂ የእኔም መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አብረውኝ ይሄዳሉ።
ይሁንና በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር በዚያ ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤
ወደምሄድበትም ቦታ የተወሰነ መንገድ እንድትሸኙኝ ምናልባት እናንተ ጋ ልቆይ እችላለሁ፤ እንዲያውም ክረምቱን ከእናንተ ጋር አሳልፍ ይሆናል።
ይሖዋ ቢፈቅድ ከእናንተ ጋር የተወሰነ ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ ተስፋ ስለማደርግ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ላያችሁ አልፈልግም።
ይሁንና እስከ ጴንጤቆስጤ በዓል ድረስ በኤፌሶን እቆያለሁ፤
ምክንያቱም ትልቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ሆኖም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉ።
ጢሞቴዎስ ከመጣ በመካከላችሁ በሚቆይበት ጊዜ ፍርሃት እንዳይሰማው ተባበሩት፤ እሱም እንደ እኔ የይሖዋን ሥራ የሚሠራ ነውና።
ስለዚህ ማንም አይናቀው። ከወንድሞች ጋር እየጠበቅኩት ስለሆነ ወደ እኔ እንዲመጣ በሰላም ሸኙት።
ወንድማችንን አጵሎስን በተመለከተ ደግሞ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር። እሱ አሁን የመምጣት ሐሳብ የለውም፤ ሆኖም ሁኔታው ሲመቻችለት ይመጣል።
ነቅታችሁ ኑሩ፤ በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ፤ ወንድ ሁኑ፤ ብርቱዎች ሁኑ።
የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ።
እንግዲህ ወንድሞች ይህን አሳስባችኋለሁ፦ የእስጢፋናስ ቤተሰብ በአካይያ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንደሆኑና ቅዱሳንን ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ።
እናንተም እንደ እነሱ ላሉት እንዲሁም ከእኛ ጋር ለሚተባበሩትና በትጋት ለሚሠሩት ሁሉ ተገዙ።
እስጢፋናስ እና ፈርጡናጦስ እንዲሁም አካይቆስ እዚህ በመገኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ፤ ምክንያቱም የእናንተ እዚህ አለመኖር በእነሱ ተካክሷል።
እነሱ የእኔንም ሆነ የእናንተን መንፈስ አድሰዋልና። ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እውቅና ስጡ።
በእስያ ያሉ ጉባኤዎች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ እንዲሁም በቤታቸው ያለው ጉባኤ ሞቅ ያለ ክርስቲያናዊ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ።
እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ።
ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፣ ና!
የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆናችሁ ሁሉ፣ ፍቅሬ ይድረሳችሁ።
በመካከላችሁ ዝሙት እንደተፈጸመ ይወራል፤ እንዲህ ዓይነቱ ዝሙት ደግሞ በአሕዛብ መካከል እንኳ ታይቶ አይታወቅም፤ ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ሰው አለ ተብሏል።
ታዲያ በዚህ ትኩራራላችሁ? ይልቁንም በዚህ ማዘንና ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ማስወጣት አይገባችሁም?
ምንም እንኳ እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ደግሞም እንዲህ ያለ ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ አብሬያችሁ ያለሁ ያህል ሆኜ ፈርጄበታለሁ።
በጌታችን በኢየሱስ ስም አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኃይል በመንፈስ ከእናንተ ጋር እንደምሆን በመገንዘብ
እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል፤ ይህም እሱ በጉባኤው ላይ ያሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲወገድና የጉባኤው መንፈስ በጌታ ቀን ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ነው።
መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?
አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ ከእርሾ ነፃ ናችሁ።
ስለዚህ በዓሉን በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር።
ከሴሰኞች ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ በደብዳቤዬ ላይ ጽፌላችሁ ነበር፤
እንዲህ ስል ግን በአጠቃላይ ከዚህ ዓለም ሴሰኞች፣ ስግብግብ ሰዎች፣ ቀማኞች ወይም ጣዖት አምላኪዎች ጋር አትገናኙ ማለቴ አይደለም። እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ጨርሶ ከዓለም መውጣት ያስፈልጋችሁ ነበር።
አሁን ግን የጻፍኩላችሁ፣ ወንድም ተብሎ እየተጠራ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ቀማኛ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ አልፎ ተርፎም እንዲህ ካለው ሰው ጋር ምግብ እንኳ እንዳትበሉ ነው።
በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ የምፈርደው እኔ ምን አግብቶኝ ነው? በውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱም?
በውጭ ባሉት ላይ አምላክ ይፈርዳል። “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”
ፍቅርን ተከታተሉ፤ ሆኖም መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን ለማግኘት ጥረት አድርጉ።
በልሳን የሚናገር ለአምላክ እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ በመንፈስ አማካኝነት ቅዱስ ሚስጥሮችን ቢናገርም እንኳ ማንም አይሰማውም።
ይሁን እንጂ ትንቢት የሚናገር በንግግሩ ሰዎችን ያንጻል፣ ያበረታታል እንዲሁም ያጽናናል።
በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢት የሚናገር ግን ጉባኤን ያንጻል።
ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ሆኖም ትንቢት ብትናገሩ እመርጣለሁ። ደግሞም ትንቢት የሚናገር በልሳን ከሚናገር ይበልጣል። ምክንያቱም በልሳን የሚናገር የተናገረውን ካልተረጎመው ጉባኤው ሊታነጽ አይችልም።
አሁን ግን ወንድሞች፣ ወደ እናንተ መጥቼ ራእይን በመግለጥ ወይም በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኳችሁ በስተቀር በልሳን ብነግራችሁ ምን እጠቅማችኋለሁ?
እንደ ዋሽንትና በገና ካሉ ድምፅ የሚያወጡ ግዑዝ ነገሮች ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። የሚያወጡት የድምፅ ቃና ግልጽ የሆነ ልዩነት ከሌለው ከዋሽንቱም ሆነ ከበገናው የሚወጣው ዜማ እንዴት ይለያል?
ደግሞም መለከት ለመለየት የሚያስቸግር ድምፅ ቢያሰማ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?
ልክ እንደዚሁም ከአንደበታችሁ የሚወጣው ቃል በቀላሉ የሚገባ ካልሆነ ስለ ምን እየተናገራችሁ እንዳለ ማን ሊያውቅ ይችላል? እንዲህ ከሆነ ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ።
በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ሆኖም ትርጉም የሌለው ቋንቋ የለም።
አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጉም ካላወቅኩ እኔ ለሚናገረው ሰው የባዕድ አገር ሰው እሆንበታለሁ፤ እሱም ለእኔ የባዕድ አገር ሰው ይሆንብኛል።
ስለዚህ እናንተም የመንፈስን ስጦታዎች እጅግ ስለምትፈልጉ ጉባኤውን የሚያንጹ ስጦታዎች በብዛት ለማግኘት ጥረት አድርጉ።
ስለሆነም በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረውን መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።
ምክንያቱም በልሳን የምጸልይ ከሆነ፣ የሚጸልየው የተቀበልኩት የመንፈስ ስጦታ ነው፤ አእምሮዬ ግን ምንም የሚያከናውነው ነገር የለም።
ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? በመንፈስ ስጦታ እጸልያለሁ፤ ሆኖም የምጸልየው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው። በመንፈስ ስጦታ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤ ሆኖም የምዘምረው ትርጉሙ ገብቶኝ ነው።
እንዲህ ካልሆነ በመንፈስ ስጦታ ውዳሴ ብታቀርብ በመካከልህ ያለው ምንም የማያውቅ ሰው ምን እየተናገርክ እንዳለህ ስለማይገባው ላቀረብከው ምስጋና እንዴት “አሜን” ሊል ይችላል?
እርግጥ አንተ ግሩም በሆነ መንገድ ምስጋና ታቀርብ ይሆናል፤ ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም።
ከሁላችሁ የበለጠ በብዙ ልሳኖች ስለምናገር አምላክን አመሰግናለሁ።
ይሁንና በጉባኤ ውስጥ አሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ሌሎችንም ማስተማር እችል ዘንድ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ብናገር እመርጣለሁ።
ወንድሞች፣ በማስተዋል ችሎታችሁ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ግን ሕፃናት ሁኑ፤ በማስተዋል ችሎታችሁም የጎለመሳችሁ ሁኑ።
በሕጉ ላይ “‘በባዕዳን አንደበትና እንግዳ በሆኑ ሰዎች ቋንቋዎች ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ እነሱ ግን በዚያን ጊዜም እንኳ አይሰሙኝም’ ይላል ይሖዋ” ተብሎ ተጽፏል።
በመሆኑም ልሳን ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑት ምልክት ነው፤ ትንቢት ግን አማኝ ላልሆኑት ሳይሆን ለአማኞች ነው።
ስለዚህ ጉባኤው በሙሉ አንድ ላይ ተሰብስቦ ባለበት ወቅት ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና በዚህ መሃል ምንም የማያውቁ ሰዎች ወይም አማኞች ያልሆኑ ቢገቡ እነዚህ ሰዎች ‘አእምሯችሁን ስታችኋል’ አይሏችሁም?
ሆኖም ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ሳለ አማኝ ያልሆነ ወይም ምንም የማያውቅ ሰው ቢገባ ሁላችሁም የምትናገሩት ቃል እንደ ወቀሳ የሚያገለግለው ከመሆኑም በላይ ራሱን በሚገባ እንዲመረምር ያነሳሳዋል።
በዚህ ጊዜ በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በመሆኑም “አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው” እያለ በግንባሩ ተደፍቶ ለአምላክ ይሰግዳል።
እንግዲህ ወንድሞች፣ ምን ማድረግ ይሻላል? አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ አንዱ ይዘምራል፣ ሌላው ያስተምራል፣ ሌላው ራእይን ይገልጣል፣ ሌላው በልሳን ይናገራል፣ ሌላው ደግሞ ይተረጉማል። ሁሉም ነገር ለማነጽ ይሁን።
በልሳን የሚናገሩ ካሉ ከሁለት ወይም ከሦስት አይብለጡ፤ በየተራም ይናገሩ፤ የሚናገሩትንም ሌላ ሰው ይተርጉም።
የሚተረጉም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበሉና ለራሳቸውና ለአምላክ ይናገሩ።
ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉሙን ለመረዳት ይጣሩ።
ሆኖም አንድ ሰው እዚያ ተቀምጦ ሳለ ራእይ ቢገለጥለት የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል።
ሁሉም እንዲማሩና ሁሉም እንዲበረታቱ ሁላችሁም በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።
ነቢያት የመንፈስ ስጦታዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው ይገባል።
አምላክ የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና። በቅዱሳን ጉባኤዎች ሁሉ እንደሚደረገው
ሴቶች በጉባኤ ውስጥ እንዲናገሩ ስላልተፈቀደላቸው ዝም ይበሉ። ከዚህ ይልቅ ሕጉም እንደሚለው ይገዙ።
ያልገባቸው ነገር ካለ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።