text
stringlengths
4
267
“ባቢሎን ተጠያቂ የሆነችው ታርደው ለወደቁት እስራኤላውያን ብቻ አይደለም፤ከዚህ ይልቅ ከመላው ምድር የመጡ ሰዎችም በባቢሎን ታርደው ወድቀዋል።
እናንተ ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ መንገዳችሁን ቀጥሉ፤ ፈጽሞ አትቁሙ! በሩቅ ቦታ ሆናችሁ ይሖዋን አስታውሱ፤ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።”
“ዘለፋውን ስለሰማን በኀፍረት ተውጠናል። ባዕድ ሰዎች በይሖዋ ቤት ባሉት ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ስለተነሱውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።”
“ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴንበተቀረጹ ምስሎቿ ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤“በምድሪቱም ሁሉ፣ የቆሰሉት ሰዎች ያቃስታሉ።”
“ባቢሎን ወደ ሰማያት ብትወጣ፣ከፍ ያሉ ምሽጎቿንም ብታጠናክር እንኳ፣እሷን የሚያጠፉ ከእኔ ዘንድ ይመጡባታል” ይላል ይሖዋ።
“ስሙ! ከባቢሎን ጩኸት፣ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል፤
ይሖዋ ባቢሎንን ያጠፋልና፤ታላቅ ድምፅዋን ጸጥ ያሰኛል፤ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኃዎች ያስተጋባል። የድምፃቸው ጩኸት ይሰማል።
በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣልና፤ተዋጊዎቿ ይያዛሉ፤ቀስቶቻቸው ይሰባበራሉ፤ይሖዋ የሚበቀል አምላክ ነውና። በእርግጥ ብድራትን ይመልሳል።
መኳንንቷንና ጥበበኞቿን፣ገዢዎቿንና የበታች ገዢዎቿን እንዲሁም ተዋጊዎቿን አሰክራለሁ፤እነሱም ጨርሶ ላይነቁእስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ” ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው ንጉሥ።
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ቅጥር ሰፊ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፤በሮቿ ረጃጅም ቢሆኑም በእሳት ይጋያሉ። ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ብሔራትም እሳት ለሚበላው ነገር ራሳቸውን እንዲሁ ያደክማሉ።”
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የማህሴያህ ልጅ፣ የነሪያህ ልጅ ሰራያህ ከንጉሡ ጋር ወደ ባቢሎን በተጓዘ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለእሱ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ሰራያህ የቤተ መንግሥት አስተዳዳሪ ነበር።
ኤርምያስ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ፣ ደግሞም በባቢሎን ላይ ስለሚደርሰው ነገር የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው።
በተጨማሪም ኤርምያስ ሰራያህን እንዲህ አለው፦ “ባቢሎን ስትደርስና ከተማዋን ስታይ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብ።
ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ይህች ስፍራ እንደምትጠፋና ሰውም ሆነ እንስሳ፣ አንድም የሚኖርባት እንደማይገኝ፣ እንዲሁም ለዘላለም ባድማ እንደምትሆን ተናግረሃል።’
ይህን መጽሐፍ አንብበህ ከጨረስክ በኋላም መጽሐፉን ከድንጋይ ጋር አስረህ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ወርውረው።
ከዚያም እንዲህ በል፦ ‘ባቢሎን በእሷ ላይ ከማመጣው ጥፋት የተነሳ እንዲህ ትሰምጣለች፤ ዳግመኛም አትነሳም፤ እነሱም ይዝላሉ።’” የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።
ንጉሥ ሴዴቅያስ የማልኪያህን ልጅ ጳስኮርንና የማአሴያህን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ በላካቸው ጊዜ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ እነሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ሊወጋን ስለሆነ እባክህ፣ ስለ እኛ ይሖዋን ጠይቅልን። ንጉሡ ከእኛ እንዲመለስ ይሖዋ እንደቀድሞው ሁሉ አሁንም ተአምር ይፈጽምልን ይሆናል።”
ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፦ “ሴዴቅያስን እንዲህ በሉት፦
‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎንን ንጉሥና ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን ከለዳውያንን ለመውጋት የምትጠቀሙባቸውን በገዛ እጃችሁ ላይ ያሉትን የጦር መሣሪያዎች በእናንተው ላይ አዞራለሁ። በዚህችም ከተማ መሃል እሰበስባቸዋለሁ።
እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በኃያል ክንድ እንዲሁም በመዓትና በታላቅ ቁጣ እዋጋችኋለሁ።
የዚህችን ከተማ ነዋሪዎች፣ ሰውንም ሆነ እንስሳን እመታለሁ። እነሱም በታላቅ ቸነፈር ይሞታሉ።”’
“‘“ከዚያም በኋላ” ይላል ይሖዋ፣ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ አገልጋዮቹን እንዲሁም ከቸነፈር፣ ከሰይፍና ከረሃብ ተርፎ በከተማዋ ውስጥ የሚቀረውን ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ፣ በጠላቶቻቸው እጅና ሕይወታቸውን ለማጥፋት በሚሹ ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። እሱም በሰይፍ ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፤ ርኅራኄም ሆነ ምሕረት አያሳያቸውም።”’
“ደግሞም ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ።
በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሰዎች በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። ይሁንና ከከተማዋ ወጥቶ፣ ለከበቧችሁ ከለዳውያን እጁን የሚሰጥ በሕይወት ይኖራል፤ ሕይወቱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች።”’
“‘“መልካም ነገር ሳይሆን ጥፋት ለማምጣት ፊቴን ወደዚህች ከተማ አዙሬአለሁና” ይላል ይሖዋ። “ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤ እሱም በእሳት ያቃጥላታል።”
“‘የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፦ የይሖዋን ቃል ስሙ።
የዳዊት ቤት ሆይ፣ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከክፉ ድርጊታችሁ የተነሳቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይቀጣጠልናማንም ሊያጠፋው እስከማይችል ድረስ እንዳይነድበየማለዳው ለፍትሕ ቁሙ፤የተዘረፈውንም ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ።”’
‘አንቺ በሸለቆ ውስጥ የምትኖሪ፣ በደልዳላው መሬት ላይ የተቀመጥሽ ዓለት ሆይ፣እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ እነሳለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘“በእኛ ላይ ማን ይወርዳል? ደግሞስ መኖሪያዎቻችንን ማን ይወራል?” የምትሉ ይህን እወቁ፤
እንደ ሥራችሁ መጠንተጠያቂ አደርጋችኋለሁ’ ይላል ይሖዋ። ‘ጫካዋን በእሳት አነዳለሁ፤እሳቱም በዙሪያዋ ያለውን ነገር ሁሉ ይበላል።’”
ሰዎች እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፦ “አንድ ሰው ሚስቱን ቢያሰናብታት፣ እሷም ተለይታው ብትሄድና የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን፣ ዳግመኛ ወደ እሷ መመለስ ይኖርበታል?” ይህች ምድር ጨርሶ ተበክላ የለም? “አንቺ ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመነዘርሽ፤ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ይገባሻል?” ይላል ይሖዋ።
“ዓይንሽን አንስተሽ የተራቆቱትን ኮረብቶች ተመልከቺ። አንቺ ያልተደፈርሽበት ቦታ ይገኛል? በምድረ በዳ እንዳለ ዘላንአንቺም በመንገዶቹ ዳር ተቀምጠሽ ጠበቅሻቸው። በዝሙትሽና በክፋትሽምድሪቱን በከልሽ።
ስለዚህ ዝናብ እንዳይዘንብ ተከልክሏል፤የኋለኛው ዝናብም አልዘነበም። አንቺ ዝሙት አዳሪ እንደሆነች ሚስት፣ ዓይን አውጣ ነሽ፤ኀፍረት የሚባል ነገር አታውቂም።
አሁን ግን ወደ እኔ ተጣርተሽ እንዲህ ትያለሽ፦‘አባቴ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምሮ ወዳጄ ነህ!
ለዘላለም ቅር ትሰኛለህ?ወይስ ቂም እንደያዝክ ትኖራለህ?’ አንቺ እንዲህ ትያለሽ፤ይሁንና የቻልሽውን ያህል ክፉ ነገር መሥራትሽን ቀጥለሻል።”
በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል ያደረገችውን አይተሃል? ከፍ ባለው ተራራ ሁሉ ላይና ቅጠሉ ከተንዠረገገው ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ሄዳለች።
ይህን ሁሉ ነገር ካደረገች በኋላ እንኳ ወደ እኔ እንድትመለስ መወትወቴን ቀጠልኩ፤ እሷ ግን አልተመለሰችም፤ ይሁዳም ከሃዲ የሆነችውን እህቷን ተመለከተች።
ይህን ባየሁ ጊዜ፣ በማመንዘሯ የተነሳ ታማኝነቷን ላጎደለችው ለእስራኤል የፍችዋን የምሥክር ወረቀት ሰጥቼ አሰናበትኳት። ያም ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ አልፈራችም፤ እሷም ሄዳ አመነዘረች።
አመንዝራነቷን አቅልላ ተመለከተችው፤ ምድሪቱን መበከሏን እንዲሁም ከድንጋዮችና ከዛፎች ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች።
ይህም ሁሉ ሆኖ ከሃዲ የሆነችው እህቷ ይሁዳ ለይስሙላ እንጂ በሙሉ ልቧ ወደ እኔ አልተመለሰችም’ ይላል ይሖዋ።”
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ታማኝነቷን ያጎደለችው እስራኤል፣ ከሃዲ ከሆነችው ይሁዳ ይልቅ ጻድቅ ሆና ተገኝታለች።
ሂድና እነዚህን ቃላት ወደ ሰሜን አውጅ፦ “‘“ከዳተኛይቱ እስራኤል ሆይ፣ ተመለሽ” ይላል ይሖዋ።’ ‘“እኔ ታማኝ ስለሆንኩ እናንተን በቁጣ አልመለከትም” ይላል ይሖዋ።’ ‘“ለዘላለም ቅር አልሰኝም።
ብቻ የሠራሽውን በደል አምነሽ ተቀበይ፤ በአምላክሽ በይሖዋ ላይ ዓምፀሻልና። ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር ከእንግዶች ጋር አመነዘርሽ፤ ቃሌንም አትታዘዢም” ይላል ይሖዋ።’”
“እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ” ይላል ይሖዋ። “እኔ እውነተኛ ጌታችሁ ሆኛለሁና፤ ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድም ሁለት እያደረግኩ እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ።
እንደ ልቤ የሆኑ እረኞችም እሰጣችኋለሁ፤ እነሱም በእውቀትና በጥልቅ ማስተዋል ይመግቧችኋል።
በዚያ ዘመን በምድሪቱ ላይ ትበዛላችሁ፤ ፍሬያማም ትሆናላችሁ” ይላል ይሖዋ። “ከእንግዲህ ‘የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት!’ አይሉም፤ ስለ እሱ አያስቡም፤ ጨርሶ አያስታውሱትም ወይም እንዳጎደላቸው ሆኖ አይሰማቸውም፤ ታቦቱም ዳግመኛ አይሠራም።
በዚያን ጊዜ ኢየሩሳሌምን የይሖዋ ዙፋን ብለው ይጠሯታል፤ ብሔራትም ሁሉ በአንድነት የይሖዋን ስም ለማወደስ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤ ከዚያ በኋላ ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን አይከተሉም።”
“በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
እኔም እንዲህ ብዬ አሰብኩ፦ ‘በወንዶች ልጆች መካከል ባስቀምጥሽ፣ የተወደደችውንም ምድር፣ በብሔራት መካከል የምትገኘውን እጅግ ያማረች ርስት ብሰጥሽ ምንኛ ደስ ባለኝ!’ በተጨማሪም እናንተ ‘አባቴ!’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሱም ብዬ አስቤ ነበር።
‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’ ይላል ይሖዋ።”
በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ድምፅ ተሰምቷል፤አዎ፣ የእስራኤል ልጆች ለቅሶና ልመና ተሰምቷል፤እነሱ መንገዳቸውን አጣመዋልና፤አምላካቸውን ይሖዋን ረስተዋል።
“እናንተ ከዳተኛ ልጆች፣ ተመለሱ። ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።” “እነሆ፣ እኛ ወደ አንተ መጥተናል!ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላካችን ነህና።
ኮረብቶቹና በተራሮቹ ላይ የሚሰማው ሁካታ የሐሰት ናቸው። በእርግጥ የእስራኤል መዳን በአምላካችን በይሖዋ ነው።
ይሁንና አሳፋሪው ነገር ከልጅነታችን ጀምሮ አባቶቻችን የደከሙበትን ሁሉ፣መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በልቷል።
ኀፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ውርደታችንም ይሸፍነን፤እኛና አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ እስካሁን ድረስበአምላካችን በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፤ የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅም አልታዘዝንም።”
ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦
“የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የምነግርህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።
“እነሆ፣ ተማርከው የተወሰዱትን ሕዝቤን፣ እስራኤልንና ይሁዳን የምሰበስብበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ለአባቶቻቸው ወደሰጠኋት ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ ይወርሷታል” ይላል ይሖዋ።’”
ይሖዋ ለእስራኤልና ለይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሚንቀጠቀጡ ሰዎችን ድምፅ ሰምተናል፤ሽብር ነግሦአል፤ ሰላምም የለም።
ወንድ፣ መውለድ ይችል እንደሆነ እስቲ ጠይቁ። ታዲያ ብርቱ የሆነ ወንድ ሁሉ፣ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት እጁን ሆዱ ላይ አድርጎ የማየው ለምንድን ነው? የሰዉ ሁሉ ፊት የገረጣው ለምንድን ነው?
ወዮ! ያ ቀን አስፈሪ ነውና። በዓይነቱ ልዩ የሆነ ቀን ነው፤ለያዕቆብ የጭንቅ ጊዜ ይሆናል። ሆኖም ከዚያ ቀን ይተርፋል።”
“በዚያም ቀን፣” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “ቀንበሩን ከአንገትህ ላይ እሰብራለሁ፤ ማሰሪያህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ እንግዶች ባሪያቸው አያደርጉትም።
እነሱም አምላካቸውን ይሖዋንና የማስነሳላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።”
“አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤“እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር። አንተን ከሩቅ አገር፣ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና። ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸው አይኖርም።”
“እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ። “አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ግን ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ይሁን እንጂ አንተን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም። በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ እንጂበምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።”
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ስብራትሽ ፈውስ የለውም። ቁስልሽ የማይድን ነው።
የሚሟገትልሽ የለም፤ቁስልሽ በምንም መንገድ ሊድን አይችልም። ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም።
አጥብቀው የሚወዱሽ ሁሉ ረስተውሻል። ከእንግዲህ አይፈልጉሽም። ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽጠላት በሚማታበት መንገድ መትቼሻለሁና፤እንደ ጨካኝ ቀጥቼሻለሁ።
ከስብራትሽ የተነሳ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኗል! ከባድ በደል ስለፈጸምሽና ብዙ ኃጢአት ስለሠራሽይህን አድርጌብሻለሁ።
በእርግጥ የሚውጡሽ ሁሉ ይዋጣሉ፤ጠላቶችሽም ሁሉ በምርኮ ይወሰዳሉ። የሚዘርፉሽ ሁሉ ይዘረፋሉ፤የሚበዘብዙሽንም ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።”
“ይሁንና ጤንነትሽን እመልስልሻለሁ፤ ቁስሎችሽንም እፈውሳለሁ” ይላል ይሖዋ፤“እነሱ ግን የተገለለች፣ ‘ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሻል።”
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከያዕቆብ ድንኳኖች የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤ለማደሪያ ድንኳኖቹም እራራለሁ። ከተማዋ በጉብታዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤የማይደፈረውም ማማ በተገቢው ቦታ ላይ ይቆማል።
ከእነሱም የምስጋናና የሳቅ ድምፅ ይሰማል። እኔ አበዛቸዋለሁ፤ እነሱም ጥቂት አይሆኑም፤ቁጥራቸው እንዲጨምር አደርጋለሁ፤የተናቁም አይሆኑም።
ወንዶች ልጆቹ እንደቀድሞው ጊዜ ይሆናሉ፤ጉባኤውም በፊቴ ጸንቶ ይመሠረታል። እሱን በሚጨቁኑት ሁሉ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ።
ታላቅ ግርማ የተላበሰው መሪ ከራሱ ወገን ይገኛል፤ገዢውም ከመካከሉ ይወጣል። ወደ እኔ እንዲቀርብ እፈቅድለታለሁ፤ እሱም ወደ እኔ ይቀርባል።” “አለዚያ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው?” ይላል ይሖዋ።
“እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።”
እነሆ፣ የይሖዋ አውሎ ነፋስ በታላቅ ቁጣ ይነሳል፤በክፉዎች ራስ ላይ እየተሽከረከረ የሚወርድ ኃይለኛ ነፋስ ይነፍሳል።
ይሖዋ የልቡን ሐሳብ ሳያከናውንና ሳይፈጽም፣የሚነደው ቁጣው አይመለስም። በዘመኑ መጨረሻ ይህን ትረዳላችሁ።
ምነው ራሴ በውኃ በተሞላ!ዓይኖቼ የእንባ ምንጭ በሆኑ! ለታረዱት ወገኖቼቀን ከሌት ባለቀስኩ ነበር።
ምነው በምድረ በዳ ለተጓዦች የሚሆን ማረፊያ ቦታ ባገኘሁ ኖሮ! በዚያን ጊዜ ሕዝቤን ትቼና ከእነሱ ተለይቼ በሄድኩ ነበር፤ሁሉም አመንዝሮች፣የከዳተኞች ጥርቅም ሆነዋልና።
ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል። “በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤እኔንም ጨርሶ አይሰሙም” ይላል ይሖዋ።
“እያንዳንዳችሁ ራሳችሁን ከባልንጀራችሁ ጠብቁ፤ወንድማችሁን እንኳ ሳይቀር አትመኑ። እያንዳንዱ ወንድም ከሃዲ ነውና፤እያንዳንዱ ባልንጀራም ስም አጥፊ ነው።
እያንዳንዱ ባልንጀራውን ያታልላል፤አንድም ሰው እውነትን አይናገርም። ምላሳቸውን ውሸት መናገር አስተምረውታል። ትክክል ያልሆነ ነገር በማድረግ ራሳቸውን ያደክማሉ።
የምትኖረው አታላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው። አታላይ ከመሆናቸውም የተነሳ እኔን ለማወቅ እንቢተኞች ሆነዋል” ይላል ይሖዋ።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ አቀልጣቸዋለሁ፤ ደግሞም እፈትናቸዋለሁ፤ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጋር በተያያዘ ከዚህ ሌላ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ምላሳቸው ማታለያ የሚናገር፣ ገዳይ ፍላጻ ነው። ሰው በአፉ ለባልንጀራው ስለ ሰላም ይናገራል፤በውስጡ ግን ለማጥቃት ያደባል።”
“ታዲያ በእነዚህ ነገሮች የተነሳ ተጠያቂ ላደርጋቸው አይገባም?” ይላል ይሖዋ። “እንዲህ ዓይነቱን ሕዝብ ልበቀል አይገባም?
በተራሮቹ የተነሳ አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤በምድረ በዳ ባሉት ማሰማሪያዎችም የተነሳ ሙሾ አወርዳለሁ፤ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና፤የከብቶችም ድምፅ አይሰማም። የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊት ሸሽተዋል፤ ከአካባቢው ጠፍተዋል።
ኢየሩሳሌምን የድንጋይ ክምር፣ የቀበሮም ጎሬ አደርጋታለሁ፤የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ይህን ይረዳ ዘንድ ጥበበኛ የሆነ ማን ነው? ይህን ያሳውቅ ዘንድ የይሖዋ አፍ የተናገረው ለማን ነው? ምድሪቱ የጠፋችው ለምንድን ነው? ማንም እንዳያልፍባትእንደ ምድረ በዳ የተለበለበችው ለምንድን ነው?”
ይሖዋ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በፊታቸው ያኖርኩትን ሕጌን ስለተዉና ስላልተከተሉ እንዲሁም ድምፄን ስላልሰሙ ነው።
ከዚህ ይልቅ ግትር ሆነው የገዛ ልባቸውን እንዲሁም አባቶቻቸው ባስተማሯቸው መሠረት የባአልን ምስሎች ተከተሉ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ይህ ሕዝብ ጭቁኝ እንዲበላ አደርጋለሁ፤ የተመረዘም ውኃ እንዲጠጣ አደርጋለሁ።
እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው በማያውቋቸው ብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ ከኋላቸው ሰይፍን እሰዳለሁ።’
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘በማስተዋል ተመላለሱ። ሙሾ የሚያወርዱትን ሴቶች ጥሩ፤የሠለጠኑ አልቃሽ ሴቶችንም ልካችሁ አስመጡ፤
ዓይኖቻችን እንባ ያጎርፉ ዘንድ፣ሽፋሽፍቶቻችንም ውኃ ያንጠባጥቡ ዘንድፈጥነው እንዲመጡና የሐዘን እንጉርጉሮ እንዲያንጎራጉሩልን ጥሯቸው።
ከጽዮን የሐዘን እንጉርጉሮ ድምፅ ተሰምቷልና፦ “ከባድ ጥፋት ደርሶብናል! ታላቅ ኀፍረት ተከናንበናል! ምድሪቱን ጥለን ሄደናልና፤ እነሱም ቤቶቻችንን አፈራርሰዋል።”
እናንተ ሴቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። ጆሯችሁ የአፉን ቃል ያዳምጥ። ሴቶች ልጆቻችሁን ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ አስተምሯቸው፤አንዳችሁም ለሌላው ይህን ሙሾ አስተምሩ።
ሞት በመስኮቶቻችን በኩል ገብቷልና፤ልጆቹን ከጎዳናዎቹ፣ወጣቶቹንም ከአደባባዮቹ ለመውሰድወደማይደፈሩት ማማዎቻችን ገብቷል።’