text stringlengths 4 267 |
|---|
እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ሲል አውጇል፦ “የሰዎች አስከሬን በምድር ላይ ልክ እንደ ፍግ ይወድቃል፤አጫጅ አጭዶ እንደተወውም እህል ይሆናል፤የሚሰበስበው አይኖርም።”’” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጥበበኛው በጥበቡ አይኩራራ፤ኃያሉ በኃያልነቱ አይኩራራ፤ባለጸጋውም በሀብቱ አይኩራራ።” |
“ከዚህ ይልቅ የሚኩራራ በዚህ ነገር ይኩራራ፦ ስለ እኔ ጥልቅ ማስተዋልና እውቀት ያለው በመሆኑእንዲሁም በምድር ላይ ታማኝ ፍቅር የማሳየው፣ ደግሞም ፍትሕና ጽድቅ የማሰፍነው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ፤በእነዚህ ነገሮች ደስ እሰኛለሁና” ይላል ይሖዋ። |
“እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ቀን ይመጣል” ይላል ይሖዋ፣ “የተገረዘ ቢሆንም እንኳ ያልተገረዘውን ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤ |
ግብፅን፣ ይሁዳን፣ ኤዶምን፣ አሞናውያንን፣ ሞዓብንና በሰሪሳራቸው ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩትን በምድረ በዳ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ተጠያቂ አደርጋለሁ፤ ብሔራት ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነው።” |
የማታን ልጅ ሰፋጥያህ፣ የጳስኮር ልጅ ጎዶልያስ፣ የሸሌምያህ ልጅ ዩካልና የማልኪያህ ልጅ ጳስኮር፣ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን የሚከተለውን ቃል ሰሙ፦ |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ከተማ የሚቀር በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታል። ለከለዳውያን እጁን የሚሰጥ ግን ይተርፋል፤ ሕይወቱ እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤ በሕይወትም ይኖራል።’ |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት መሰጠቷ አይቀርም፤ እሱም ይይዛታል።’” |
መኳንንቱ ንጉሡን እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው እንዲህ ያለ ቃል በመናገር በዚህች ከተማ ውስጥ የቀሩትን ወታደሮችና የሕዝቡን ሁሉ ወኔ እያዳከመ ስለሆነ እባክህ አስገድለው። ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ጥፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝምና።” |
ንጉሥ ሴዴቅያስም “እነሆ፣ እሱ በእጃችሁ ነው፤ ንጉሡ እናንተን ለማስቆም ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልምና” ሲል መለሰላቸው። |
እነሱም ኤርምያስን ወስደው በክብር ዘቦቹ ግቢ በሚገኘው በንጉሡ ልጅ በማልኪያህ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ኤርምያስን በገመድ ወደ ጉድጓዱ አወረዱት። በጉድጓዱ ውስጥም ጭቃ ብቻ እንጂ ውኃ አልነበረም፤ ኤርምያስም ጭቃው ውስጥ መስመጥ ጀመረ። |
በንጉሡ ቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ እንደጣሉት ሰማ። በዚህ ጊዜ ንጉሡ በቢንያም በር ተቀምጦ ነበር፤ |
በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ከንጉሡ ቤት ወጥቶ ንጉሡን እንዲህ አለው፦ |
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ ኤርምያስ ላይ ክፉ ነገር ፈጽመዋል! በውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጥለውታል፤ ከረሃቡም የተነሳ እዚያው ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ዳቦ የሚባል ነገር የለምና።” |
ከዚያም ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን ኤቤድሜሌክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከዚህ 30 ሰዎች ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ከመሞቱ በፊት ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ጎትተህ አውጣው።” |
በመሆኑም ኤቤድሜሌክ ሰዎቹን ይዞ በንጉሡ ቤት ከግምጃ ቤቱ ሥር ወዳለው ቦታ ሄደ፤ ከዚያም የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ከዚያ ወስደው በውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ ላለው ለኤርምያስ በገመድ አወረዱለት። |
ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን “ይህን የተቦጫጨቀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ በብብትህና በገመዱ መካከል አድርገው” አለው። ኤርምያስም እንደተባለው አደረገ፤ |
እነሱም ኤርምያስን በገመዱ ጎትተው ከውኃ ማጠራቀሚያው ጉድጓድ ውስጥ አወጡት። ኤርምያስም በክብር ዘቦቹ ግቢ ተቀመጠ። |
ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰው ልኮ ነቢዩ ኤርምያስን እሱ ወዳለበት፣ በይሖዋ ቤት ወደሚገኘው ወደ ሦስተኛው መግቢያ አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን “አንድ ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ምንም ነገር እንዳትደብቀኝ” አለው። |
በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ሴዴቅያስን “ብነግርህ ትገድለኛለህ። ብመክርህም አትሰማኝም” አለው። |
ንጉሥ ሴዴቅያስም በሚስጥር ለኤርምያስ እንዲህ ሲል ማለለት፦ “ይህን ሕይወት በሰጠን ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ አልገድልህም፤ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹት ለእነዚህ ሰዎችም አሳልፌ አልሰጥህም።” |
ከዚያም ኤርምያስ ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን ብትሰጥ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በሕይወት ትተርፋላችሁ። |
ለባቢሎን ንጉሥ መኳንንት እጅህን የማትሰጥ ከሆነ ግን ይህች ከተማ ለከለዳውያን አልፋ ትሰጣለች፤ እነሱም በእሳት ያቃጥሏታል፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም።’” |
ከዚያም ንጉሥ ሴዴቅያስ ኤርምያስን “ወደ ከለዳውያን የኮበለሉትን አይሁዳውያን እፈራለሁ፤ ለእነሱ አሳልፈው የሰጡኝ እንደሆነ ሊያሠቃዩኝ ይችላሉ” አለው። |
ኤርምያስ ግን እንዲህ አለው፦ “ለእነሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እባክህ የምነግርህን የይሖዋን ቃል ታዘዝ፤ መልካምም ይሆንልሃል፤ በሕይወትም ትኖራለህ። |
እጅህን ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆንክ ግን ይሖዋ የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፦ |
እነሆ፣ በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ይወሰዳሉ፤ እነሱም እንዲህ ይላሉ፦‘ተማምነህባቸው የነበሩት ሰዎች አታለውሃል፤ ደግሞም አሸንፈውሃል። እግርህ ጭቃ ውስጥ እንዲሰምጥ አድርገዋል። አሁን አፈግፍገው ተመልሰዋል።’ |
“ሚስቶችህንና ወንዶች ልጆችህን ሁሉ ለከለዳውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይልቁንም የባቢሎን ንጉሥ ይይዝሃል፤ በአንተም ምክንያት ይህች ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” |
ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “ስለዚህ ጉዳይ ማንም ሰው እንዳይሰማ፤ አለዚያ ትሞታለህ። |
መኳንንቱ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርኩ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና ‘ለንጉሡ የነገርከውን ነገር እስቲ ንገረን። ምንም ነገር አትደብቀን፤ እኛም አንገድልህም። ንጉሡ የነገረህ ምንድን ነው?’ ቢሉህ፣ |
‘በዚያ እንዳልሞት ንጉሡ ወደ የሆናታን ቤት መልሶ እንዳይልከኝ ስለምነው ነበር’ በላቸው።” |
በኋላም መኳንንቱ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት። እሱም ንጉሡ እንዲናገር ያዘዘውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። እነሱም ከዚያ በኋላ ምንም አላሉትም፤ ያደረጉትን ውይይት የሰማ ሰው አልነበረምና። |
ኤርምያስ ኢየሩሳሌም እስከተያዘችበት ጊዜ ድረስ በክብር ዘቦቹ ግቢ ተቀመጠ፤ ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ጊዜም እዚያው ነበር። |
ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ |
“በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ። ምልክት አቁሙ፤ ይህን አውጁ። ምንም ነገር አትደብቁ! እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች። ቤል ኀፍረት ተከናንቧል። ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል። ምስሎቿ ተዋርደዋል። አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ ተሸብረዋል።’ |
ከሰሜን አንድ ብሔር በእሷ ላይ ተነስቷልና። እሱም ምድሪቷን አስፈሪ ቦታ ያደርጋታል፤በእሷ ውስጥ የሚኖር ሰው የለም። ሰውም ሆነ እንስሳ ሸሽቷል፤አካባቢውን ለቀው ሄደዋል።” |
“በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “የእስራኤል ሕዝብም ሆነ የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ይመጣሉ። እያለቀሱ ይሄዳሉ፤ በአንድነትም አምላካቸውን ይሖዋን ይፈልጋሉ። |
ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ ፊታቸውንም ወደዚያ አቅጣጫ አዙረው ‘ኑ፣ ከይሖዋ ጋር የማይረሳ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንግባ’ ይላሉ። |
ሕዝቤ የጠፉ በጎች መንጋ ሆኗል። የገዛ እረኞቻቸው እንዲባዝኑ አድርገዋቸዋል። ወደ ተራሮች ነዷቸው፤ እነሱም በየተራራውና በየኮረብታው ተቅበዘበዙ። ማረፊያ ቦታቸውን ረሱ። |
ያገኟቸውም ሁሉ ዋጧቸው፤ ጠላቶቻቸውም ‘በይሖዋ ይኸውም የጽድቅ መኖሪያና የአባቶቻቸው ተስፋ በሆነው በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠሩ እኛ በደለኞች አይደለንም’ ብለዋል።” |
“ከባቢሎን መካከል ወጥታችሁ ሽሹ፤ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፤መንጋውንም እንደሚመሩ እንስሳት ሁኑ። |
እነሆ፣ እኔ ከሰሜን ምድር የታላላቅ ብሔራትን ጉባኤ አስነስቼበባቢሎን ላይ አመጣባታለሁና። እነሱም እሷን ለመውጋት ይሰለፋሉ፤በዚያም በኩል ትያዛለች። ፍላጻዎቻቸው እንደ ተዋጊ ፍላጻዎች ናቸው፤ወላጆችን የወላድ መሃን ያደርጋሉ፤ዓላማቸውን ሳይፈጽሙ አይመለሱም። |
የከለዳውያን ምድር ትበዘበዛለች። የሚበዘብዟትም ሁሉ እስኪበቃቸው ድረስ ይመዘብሯታል” ይላል ይሖዋ። |
“እናንተ እጅግ ደስ ብሏችኋልና፤የገዛ ርስቴን ስትመዘብሩ ሐሴት አድርጋችኋል። በለምለም ሣር ላይ እንዳለች ጊደር ፈንጭታችኋልና፤እንደ ድንጉላ ፈረሶችም አሽካክታችኋል። |
እናታችሁ ለኀፍረት ተዳርጋለች። የወለደቻችሁም እጅግ አዝናለች። እነሆ፣ ከብሔራት ሁሉ ያነሰች፣ውኃ የሌለባት ምድረ በዳና በረሃ ሆናለች። |
ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ሰው የማይኖርባት ምድር ትሆናለች፤ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናለች። በባቢሎን በኩል የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታታል፤ከደረሱባትም መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳ ያፏጫል። |
እናንተ ደጋን የምትወጥሩ ሁሉ፣ባቢሎንን ለመውጋት በዙሪያዋ ተሰለፉ። ፍላጻ ወርውሩባት፤ በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለሠራችአንድም ፍላጻ አታስቀሩ። |
በዙሪያዋ ሁሉ ቀረርቶ አሰሙ። እጇን ሰጥታለች። ዓምዶቿ ወድቀዋል፤ ቅጥሮቿ ፈርሰዋል፤ይህ የይሖዋ በቀል ነውና። እሷን ተበቀሏት። እንዳደረገችው አድርጉባት። |
ዘር የሚዘራውንናበመከር ወቅት ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አስወግዱ። ከጨካኙ ሰይፍ የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለሳል፤እያንዳንዱም ወደ ገዛ ምድሩ ይሸሻል። |
“የእስራኤል ሕዝብ የባዘነ በግ ነው። እንዲባዝን ያደረጉት አንበሶች ናቸው። በመጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤ ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር አጥንቱን ቆረጣጠመው። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በአሦር ንጉሥ ላይ እንዳደረግኩት ሁሉ በባቢሎን ንጉሥና በምድሩ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ። |
እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤ እሱም በቀርሜሎስና በባሳን ይሰማራል፤ በኤፍሬምና በጊልያድ ተራሮችም ላይ እስኪጠግብ ድረስ ይመገባል።’” |
“በእነዚያ ቀናትና በዚያ ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣“የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ሆኖም አይገኝም፤የይሁዳም ኃጢአት አይገኝም፤እንዲተርፉ ያደረግኳቸውን ይቅር እላቸዋለሁና።” |
“በመረታይም ምድር ላይ ውጣ፤ በጰቆድ ነዋሪዎችም ላይ ተነሳ። ነዋሪዎቹ ይጨፍጨፉ፤ ሙሉ በሙሉም ይጥፉ” ይላል ይሖዋ። “ያዘዝኩህንም ሁሉ አድርግ። |
በምድሪቱ ላይ የጦርነትናየታላቅ ጥፋት ድምፅ ይሰማል። |
የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ተቆረጠ! እንዴትስ ተሰበረ! ባቢሎን በብሔራት መካከል እንዴት መቀጣጫ ሆነች! |
ባቢሎን ሆይ፣ በአንቺ ላይ ወጥመድ ዘርግቻለሁ፤ ደግሞም ተይዘሻል፤አንቺ ግን አልታወቀሽም። ተገኘሽ፤ እንዲሁም ተያዝሽ፤የተቃወምሽው ይሖዋን ነውና። |
ይሖዋ ግምጃ ቤቱን ከፍቷል፤የቁጣ የጦር መሣሪያዎቹንም ያወጣል። ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋበከለዳውያን ምድር የሚሠራው ሥራ አለና። |
ከሩቅ ቦታ መጥታችሁ በእሷ ላይ ውጡ። ጎተራዎቿን ክፈቱ። እንደ እህል ክምር ከምሯት። ፈጽማችሁ አጥፏት። አንድም ሰው አታስቀሩላት። |
ወይፈኖቿን ሁሉ እረዱ፤ወደ እርድ ቦታ ይውረዱ። ቀናቸው ይኸውም የሚመረመሩበት ጊዜስለደረሰ ወዮላቸው! |
የአምላካችንን የይሖዋን በቀል፣ስለ ቤተ መቅደሱ ሲል የወሰደውን የበቀል እርምጃ በጽዮን ለማወጅከባቢሎን ምድር የሚሸሹናአምልጠው የሚሄዱ ሰዎች ድምፅ ይሰማል። |
ቀስተኞችን፣ ደጋን የሚወጥሩትንም ሁሉበባቢሎን ላይ ጥሩ። በዙሪያዋም ስፈሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ። እንደ ሥራዋ መልሱላት። እሷ እንዳደረገችው ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉባት። በይሖዋ ላይ ይኸውም በእስራኤል ቅዱስ ላይየእብሪት ድርጊት ፈጽማለችና። |
በመሆኑም ወጣቶቿ በአደባባዮቿ ይወድቃሉ፤በዚያም ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይጠፋሉ” ይላል ይሖዋ። |
“አንቺ ዓመፀኛ፣ እነሆ፣ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤“ቀንሽ ይኸውም አንቺን ተጠያቂ የማደርግበት ጊዜ ይመጣልና። |
አንቺ ዓመፀኛ ተሰናክለሽ ትወድቂያለሽ፤የሚያነሳሽም አይኖርም። ከተሞችሽንም በእሳት አነዳለሁ፤በዙሪያሽም ያለውን ሁሉ ይበላል።” |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቁነዋል፤ማርከው የወሰዷቸውም ሁሉ ጠፍረው ይዘዋቸዋል። እነሱን ለመልቀቅ ፈቃደኞች አልሆኑም። |
ይሁንና የሚቤዣቸው ብርቱ ነው። ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። ለምድሪቱ እረፍት ለመስጠትናየባቢሎንን ነዋሪዎች ለማሸበርያላንዳች ጥርጥር ይሟገትላቸዋል።” |
“በከለዳውያን፣ በባቢሎን ነዋሪዎች፣ በመኳንንቷእንዲሁም በጥበበኞቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል” ይላል ይሖዋ። |
“ከንቱ ነገር በሚናገሩ ሰዎች ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም የሞኝነት ድርጊት ይፈጽማሉ። በተዋጊዎቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም በሽብር ይዋጣሉ። |
በፈረሶቻቸው፣ በጦር ሠረገሎቻቸውናበመካከሏ በሚኖሩ ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤እነሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ። ውድ በሆኑ ሀብቶቿ ላይ ሰይፍ ተመዟል፤ እነሱም ይዘረፋሉ። |
ውኃዎቿ ይበከላሉ፤ ይደርቃሉም። የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፤አስፈሪ በሆኑት ራእዮቻቸው የተነሳ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል። |
ስለዚህ የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሳት ጋር ይኖራሉ፤በእሷም ውስጥ ሰጎኖች ይኖራሉ። ከዚህ በኋላ የሚኖርባት አይገኝም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ማንም አይቀመጥባትም።” |
“አምላክ ሰዶምንና ገሞራን እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉትን ከተሞች በደመሰሰ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም። |
እነሆ፣ አንድ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፤አንድ ታላቅ ብሔርና ታላላቅ ነገሥታትከምድር ዳርቻዎች ይነሳሉ። |
ቀስትና ጦር ይይዛሉ። ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው። ፈረሶቻቸውን እየጋለቡ ሲመጡድምፃቸው እንደሚጮኽ ባሕር ነው። የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ አንቺን ለመውጋት በአንድ ልብ ሆነው ይሰለፉብሻል። |
የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነሱ ወሬ ሰምቷል፤እጆቹም ይዝለፈለፋሉ። ጭንቀት ይይዘዋል፤ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ይሠቃያል። |
“እነሆ፣ አንድ ሰው፣ እንደ አንበሳ በዮርዳኖስ ዳርቻ ከሚገኙ ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ወጥቶ አስተማማኝ በሆነው መሰማሪያ ላይ ይመጣል፤ እኔ ግን ወዲያውኑ ከእሷ አባርራቸዋለሁ። የተመረጠውን በእሷ ላይ እሾማለሁ። እንደ እኔ ያለ ማነው? ማንስ ሊሟገተኝ ይችላል? በእኔ ፊት ሊቆም የሚችል እረኛ የትኛው ነው? |
ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ ይሖዋ በባቢሎን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔና በከለዳውያን ምድር ላይ ያሰበውን ሐሳብ ስሙ። ከመንጋው መካከል ትናንሽ የሆኑት ተጎትተው መወሰዳቸው አይቀርም። ከእነሱ የተነሳ መሰማሪያቸውን ባድማ ያደርጋል። |
ባቢሎን ስትያዝ ከሚሰማው ድምፅ የተነሳ ምድር ትናወጣለች፤ከብሔራትም መካከል ጩኸት ይሰማል።” |
ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው። |
በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም። |
ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።” |
ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ። |
መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ። እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም። |
እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ። በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ። |
“‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ። |
ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ። |
ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣ ረሃብና ቸነፈር እሰዳለሁ።”’” |
ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው። |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው። የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል። ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል። ሰዎቹ ይጮኻሉ፤በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ። |
ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅናከመንኮራኩሮቹ የማያባራ ድምፅ የተነሳአባቶች እጃቸው ስለሚዝልልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤ |
ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን ሁሉ ያጠፋል፤በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል። ይሖዋ ፍልስጤማውያንንይኸውም ከካፍቶር ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና። |
ጋዛ ትመለጣለች። አስቀሎን ጸጥ ትላለች። ሸለቋሟ በሆነው ሜዳቸው የምትኖሩ ቀሪዎች ሆይ፣ሰውነታችሁን የምትቆርጡት እስከ መቼ ነው? |
አንተ የይሖዋ ሰይፍ! የማታርፈው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ። እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ። |
ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለእንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል? ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤በዚያ መድቦታል።” |
በኢዮስያስ ልጅ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
“ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ለራስህ ማሰሪያና ቀንበር ሠርተህ አንገትህ ላይ አድርገው። |
ከዚያም በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች እጅ፣ ወደ ኤዶም ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብ ንጉሥ፣ ወደ አሞናውያን ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስ ንጉሥና ወደ ሲዶና ንጉሥ ላከው። |
ለጌቶቻቸው ይህን ትእዛዝ እንዲያስተላልፉ ንገራቸው፦ “‘“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ እንዲህ በሏቸው፦ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.