text
stringlengths
4
267
በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል። “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
ጠላቶችሽ ሁሉ በአንቺ ላይ አፋቸውን ከፍተዋል። እነሱ ያፏጫሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ፤ ደግሞም “ዋጥናት። ስንጠብቀው የነበረው ቀን ይህ ነው! ጊዜው ደርሶ ለማየት በቃን!” ይላሉ።
ይሖዋ ያሰበውን አድርጓል፤የተናገረውን፣ ከጥንትም ጀምሮ ያዘዘውን ፈጽሟል። ያላንዳች ርኅራኄ አፍርሷል። ጠላት በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ደስ እንዲሰኝ፣ የባላጋራዎችሽም ብርታት ከፍ ከፍ እንዲል አድርጓል።
የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፣ ልባቸው ወደ ይሖዋ ይጮኻል። እንባሽ እንደ ጅረት ቀን ከሌት ይፍሰስ። ለራስሽ ፋታ አትስጪ፤ ዓይንሽ እንባ ማፍሰሱን አያቋርጥ።
ተነሺ! ሌሊት፣ ክፍለ ሌሊቶቹ ሲጀምሩ ጩኺ። በይሖዋ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በረሃብ ምክንያት በየመንገዱ ማዕዘን ተዝለፍልፈው ለወደቁት ልጆችሽ ሕይወት ስትዪ፣እጆችሽን ወደ እሱ ዘርጊ።
ይሖዋ ሆይ፣ ክፉኛ የቀጣኸውን እይ፤ ደግሞም ተመልከት። ሴቶች የሆዳቸውን ፍሬ፣ የገዛ ራሳቸውን ልጆች ይብሉ?ደግሞስ ካህናቱና ነቢያቱ በይሖዋ መቅደስ ውስጥ ይገደሉ?
ወንድ ልጅና ሽማግሌ ሞተው በየመንገዱ ተዘርረዋል። ደናግሌና ወጣት ወንዶቼ በሰይፍ ወድቀዋል። በቁጣህ ቀን ገደልክ፤ ያላንዳች ርኅራኄ አረድክ።
በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ ሽብርን ከየአቅጣጫው ጠራህ። በይሖዋ የቁጣ ቀን ያመለጠም ሆነ በሕይወት የተረፈ የለም፤የወለድኳቸውንና ያሳደግኳቸውን ልጆች ጠላቴ ፈጃቸው።
ይሖዋ ሆይ፣ የደረሰብንን ነገር አስታውስ። ውርደታችንን እይ፤ ደግሞም ተመልከት።
ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለባዕድ አገር ሰዎች ተሰጡ።
አባት እንደሌላቸው ወላጅ አልባ ልጆች ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።
የገዛ ራሳችንን ውኃ ለመጠጣት መክፈል ነበረብን፤ የገዛ እንጨታችንን የምናገኘውም በግዢ ነበር።
አሳዳጆቻችን አንገታችንን ሊይዙ ተቃረቡ፤ዝለናል፤ እረፍት የሚባል ነገርም አላገኘንም።
በቂ ምግብ ለማግኘት ወደ ግብፅና ወደ አሦር እጃችንን ዘረጋን።
ኃጢአት የሠሩት አባቶቻችን አሁን በሕይወት የሉም፤ እኛ ግን የእነሱን በደል ለመሸከም ተገደድን።
አሁን አገልጋዮች ይገዙናል፤ ከእጃቸው የሚያስጥለን ማንም የለም።
በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሳ ምግባችንን የምናመጣው በሕይወታችን ቆርጠን ነው።
ከከባድ ረሃብ የተነሳ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጋለ።
በጽዮን ያሉ ሚስቶችና በይሁዳ ከተሞች ያሉ ደናግል ተዋረዱ።
መኳንንቱ በእጃቸው ተንጠለጠሉ፤ ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።
ወጣቶች ወፍጮውን ይሸከማሉ፤ ልጆችም ከባድ እንጨት ሲሸከሙ ይደናቀፋሉ።
ሽማግሌዎች ከከተማዋ በር ሄደዋል፤ ወጣቶችም ሙዚቃቸውን መጫወት አቁመዋል።
ደስታ ከልባችን ራቀ፤ ጭፈራችን በሐዘን ተተካ።
ራሳችን ላይ ያለው አክሊል ወድቋል። ኃጢአት ስለሠራን ወዮልን!
ከዚህ የተነሳ ልባችን ታመመ፤ከእነዚህም ነገሮች የተነሳ ዓይኖቻችን ፈዘዙ፤
ባድማ የሆነችው የጽዮን ተራራ አሁን የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ትቀመጣለህ። ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
ለዘላለም የረሳኸንና ለረጅም ዘመን የተውከን ለምንድን ነው?
ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም በፈቃደኝነት እንመለሳለን። ዘመናችንን እንደቀድሞው አድስልን።
አንተ ግን ፈጽሞ ጥለኸናል። አሁንም በእኛ ላይ እጅግ እንደተቆጣህ ነህ።
ያንጸባርቅ የነበረው ጥሩው ወርቅ፣ ምንኛ ደበዘዘ! የተቀደሱት ድንጋዮች በየመንገዱ ማዕዘኖች ላይ እንዴት ተበተኑ!
በጠራ ወርቅ የተመዘኑት የጽዮን ውድ ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራውየሸክላ ዕቃ እንዴት ተቆጠሩ!
ቀበሮዎች እንኳ ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡታቸውን ይሰጣሉ፤የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች ጨካኝ ሆነች።
ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል። ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም።
ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ ሰዎች በየጎዳናው ላይ ጠኔ ይዟቸው ይተኛሉ። ውድ ልብስ ለብሰው ያደጉም የአመድ ቁልል ያቅፋሉ።
የሕዝቤ ሴት ልጅ የደረሰባት ቅጣት፣የማንም እጅ ሳይረዳት በድንገት የተገለበጠችው ሰዶም፣ በሠራችው ኃጢአት የተነሳ ከደረሰባት ቅጣት ይበልጥ ታላቅ ነው።
ናዝራውያኗ ከበረዶ ይልቅ የጠሩ፣ ከወተትም ይልቅ የነጡ ነበሩ። ከዛጎል ይበልጥ የቀሉ ነበሩ፤ እንደተወለወለም ሰንፔር ነበሩ።
መልካቸው ከጥላሸት ይልቅ ጠቁሯል፤በጎዳና ላይ ማንነታቸውን መለየት የቻለ የለም። ቆዳቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፤ እንደደረቀ እንጨት ሆኗል።
በሰይፍ የሚወድቁት በረሃብ ከሚያልቁት ይሻላሉ፤እነዚህ የምድርን ፍሬ በማጣታቸው መንምነው ያልቃሉ።
ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል። የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል።
ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል። በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል።
የምድር ነገሥታትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉባላጋራም ሆነ ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል የሚል እምነት አልነበራቸውም።
ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።
ታውረው በየጎዳናው ተቅበዘበዙ። በደም ስለተበከሉማንም ልብሳቸውን ለመንካት አይደፍርም።
“እናንተ ርኩሳን! ሂዱ!” ይሏቸዋል። “ሂዱ! ሂዱ! አትንኩን!” ብለው ይጮኹባቸዋል። መኖሪያ አጥተው ይቅበዘበዛሉና። በብሔራት መካከል ያሉ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፦ “ከእንግዲህ ከእኛ ጋር እዚህ መኖር አይችሉም።
ይሖዋ ራሱ በታትኗቸዋል፤ዳግመኛም በሞገስ ዓይን አይመለከታቸውም። ሰዎች ለካህናቱ አክብሮት አይኖራቸውም፤ ለሽማግሌዎቹም ሞገስ አያሳዩም።”
አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ። ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን።
እግር በእግር ተከታተሉን፤ በመሆኑም በአደባባዮቻችን መንቀሳቀስ አልቻልንም። መጨረሻችን ቀርቧል፤ የሕይወት ዘመናችን አብቅቷል፤ ፍጻሜያችን ደርሷልና።
አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ። በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን።
በይሖዋ የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤“በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር።
በዑጽ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ሐሴት አድርጊ፤ ደስም ይበልሽ። ይሁንና ጽዋው ለአንቺም ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ እርቃንሽንም ትገልጫለሽ።
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል። ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም። ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል። ኃጢአትሽን ይገልጣል።
ከዚያም ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር ወሰደኝ።
በዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ድምፁም እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ ነበር፤ ከክብሩም የተነሳ ምድር አበራች።
ያየሁት ነገር ከተማዋን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ ያየሁትን ራእይ ይመስል ነበር፤ ደግሞም በኬባር ወንዝ አቅራቢያ አይቼው ከነበረው ነገር ጋር ይመሳሰል ነበር፤ እኔም መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ።
ከዚያም የይሖዋ ክብር ከምሥራቅ ትይዩ በሆነው በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።
መንፈስም አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ፤ እኔም ቤተ መቅደሱ በይሖዋ ክብር ተሞልቶ አየሁ።
ከዚያም አንድ ሰው ከቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ ሰውየውም መጥቶ አጠገቤ ቆመ።
አምላክም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህ የዙፋኔ መቀመጫ፣ የእግሬ ማሳረፊያና በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምኖርበት ስፍራ ነው። የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ እነሱም ሆኑ ንጉሦቻቸው በሚፈጽሙት መንፈሳዊ ምንዝርና በሞቱት ንጉሦቻቸው ሬሳ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
በእኔና በእነሱ መካከል ግንቡ ብቻ ሲቀር፣ ደፋቸውን ከቤቴ ደፍ አጠገብ፣ መቃናቸውንም ከቤቴ መቃን አጠገብ በማድረግ በሠሯቸው አስጸያፊ ነገሮች ቅዱስ ስሜን አርክሰዋል፤ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።
ከእንግዲህ የሚፈጽሙትን መንፈሳዊ ምንዝር ያስወግዱ፤ የንጉሦቻቸውንም ሬሳ ከእኔ ያርቁ፤ እኔም በመካከላቸው ለዘላለም እኖራለሁ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ከሠሩት በደል የተነሳ ኀፍረት እንዲሰማቸው ለእስራኤል ቤት ሰዎች ስለ ቤተ መቅደሱ ግለጽላቸው፤ ንድፉንም ያጥኑ።
በሠሩት ነገር ሁሉ ኀፍረት ከተሰማቸው የቤተ መቅደሱን ንድፍ፣ አቀማመጡን፣ መውጫዎቹንና መግቢያዎቹን አሳውቃቸው። አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን፣ ንድፉንና ሕጎቹን አሳያቸው፤ ደግሞም እነሱ እያዩ ጻፋቸው፤ ይህን የምታደርገው አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን አስተውለው በተግባር እንዲያውሉ ነው።
የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። በተራራው አናት ዙሪያ ያለው ቦታ ሁሉ እጅግ ቅዱስ ነው። እነሆ፣ የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው።
“የመሠዊያው ልክ በክንድ ሲለካ መጠኑ ይህ ነው፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። የመሠዊያው መሠረት አንድ ክንድ ነው፤ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። በጠርዙ ዙሪያ፣ ወርዱ አንድ ስንዝር የሆነ ክፈፍ አለው። ይህ የመሠዊያው መሠረት ነው።
መሬት ላይ ካረፈው መሠረት አንስቶ በዙሪያው እስካለው የታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ሲሆን ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። በዙሪያው ካለው ከትንሹ እርከን እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው።
የመሠዊያው ምድጃ ከፍታ አራት ክንድ ሲሆን ከምድጃው በላይ ወጣ ወጣ ያሉ አራት ቀንዶች አሉ።
የመሠዊያው ምድጃ አራት ማዕዘን ሲሆን ርዝመቱ 12 ክንድ፣ ወርዱም 12 ክንድ ነው።
በዙሪያው ያለው እርከን አራቱም ጎኖች ርዝመታቸው 14 ክንድ፣ ወርዳቸውም 14 ክንድ ነው፤ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ሲሆን መሠረቱም በሁሉም ጎኖች አንድ ክንድ ነው። “ደረጃዎቹም ከምሥራቅ ትይዩ ነበሩ።”
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመሠዊያው ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ እንዲቀርብና በላዩ ላይ ደም እንዲረጭበት፣ መሠዊያው ሲሠራ ሊከተሏቸው የሚገቡት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው።’
“‘እኔን ለማገልገል በፊቴ ለሚቀርቡት የሳዶቅ ዘር ለሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣ ከመንጋው መካከል ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
‘ከደሙ ጥቂት ወስደህ በመሠዊያው አራት ቀንዶች፣ በዙሪያው ባለው እርከን አራት ጎኖችና በዙሪያው ባለው ጠርዝ ላይ አድርግ፤ ይህን የምታደርገው መሠዊያውን ከኃጢአት ለማንጻትና ለመሠዊያው ማስተሰረያ ለማቅረብ ነው።
ከዚያም ከመቅደሱ ውጭ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተመደበው ቦታ ታቃጥለው ዘንድ የኃጢአት መባ የሆነውን ወይፈን ውሰድ።
በሁለተኛው ቀን የኃጢአት መባ የሚሆን እንከን የሌለበት ተባዕት ፍየል ታቀርባለህ፤ እነሱም በወይፈኑ መሠዊያውን ከኃጢአት እንዳነጹት ሁሉ በዚህም መሠዊያውን ከኃጢአት ያነጹታል።’
“‘መሠዊያውን ከኃጢአት ካነጻህ በኋላ ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ።
ለይሖዋ ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ከነሰነሱባቸው በኋላ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ያቀርቧቸዋል።
በየዕለቱ፣ ለሰባት ቀናት አንድ አውራ ፍየል የኃጢአት መባ አድርገህ ታቀርባለህ፤ እንዲሁም ከከብቶቹ መካከል አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ፤ የምታቀርባቸው እንስሳት እንከን የሌለባቸው ይሁኑ።
ለሰባት ቀናት ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያቀርባሉ፤ መሠዊያውንም ያነጹታል እንዲሁም ለአገልግሎት ያዘጋጁታል።
እነዚህ ቀናት ከተፈጸሙ በኋላ ከስምንተኛው ቀን አንስቶ ካህናቱ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በመሠዊያው ላይ ያቀርባሉ፤ እኔም በእናንተ ደስ እሰኛለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
ከዚያም በስተ ሰሜን ወዳለው ወደ ውጨኛው ግቢ ወሰደኝ። ደግሞም በአቅራቢያው ከሚገኘው ሕንፃ በስተ ሰሜን፣ ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ ወዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ያሏቸው ሕንፃዎች አመጣኝ።
ሕንፃዎቹ በሰሜኑ መግቢያ በኩል ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር፤ ወርዳቸው ደግሞ 50 ክንድ ነበር።
ሕንፃዎቹ የሚገኙት ወርዱ 20 ክንድ በሆነው በውስጠኛው ግቢና በውጨኛው ግቢ መመላለሻ መንገድ መካከል ነበር። ሕንፃዎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ሲሆኑ ትይዩ ሆነው የተሠሩ ሰገነቶች ነበሯቸው።
በመመገቢያ ክፍሎቹ ፊት ወርዱ 10 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 100 ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር፤ የክፍሎቹም መግቢያዎች የሚገኙት በስተ ሰሜን በኩል ነበር።
ከላይ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት የሕንፃው ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያሉ ነበሩ፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ሰፋ ያለ ቦታ ይዘውባቸው ነበር።
የመመገቢያ ክፍሎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ነበሩ፤ ይሁንና በግቢው ውስጥ እንዳሉት ዓይነት ዓምዶች አልነበሯቸውም። ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት ይበልጥ ከላይኛው ፎቅ ክፍሎች ሰፊ ቦታ የተወሰደው ለዚህ ነው።
ከሌሎቹ የመመገቢያ ክፍሎች ጋር ትይዩ ከሆኑትና በውጨኛው ግቢ በኩል ካሉት የመመገቢያ ክፍሎች አጠገብ የሚገኘው የውጨኛው የድንጋይ ቅጥር ርዝመት 50 ክንድ ነበር።
በውጨኛው ግቢ በኩል ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት 50 ክንድ ሲሆን ከመቅደሱ ትይዩ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት ግን 100 ክንድ ነበር።
የመመገቢያ ክፍሎቹ በስተ ምሥራቅ በኩል፣ ከውጨኛው ግቢ ወደ ክፍሎቹ የሚወስድ መግቢያ ነበራቸው።
በደቡብም በኩል ክፍት በሆነው ስፍራና በሕንፃው አቅራቢያ፣ በስተ ምሥራቅ ባለው የግቢው የድንጋይ ቅጥር ውስጥ የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ።
በስተ ሰሜን እንዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ በእነዚህ የመመገቢያ ክፍሎች ፊትም መተላለፊያ ነበር። ክፍሎቹ ተመሳሳይ ርዝመትና ወርድ ነበራቸው፤ መውጫዎቻቸውም ሆኑ ንድፎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። መግቢያዎቻቸው
በደቡብ በኩል ከሚገኙት የመመገቢያ ክፍሎች መግቢያዎች ጋር ተመሳሳይ ነበሩ። በስተ ምሥራቅ በኩል በአቅራቢያው ካለው የድንጋይ ቅጥር ፊት፣ በመተላለፊያው መንገድ መነሻ ላይ ሰው ሊገባበት የሚችል መግቢያ ነበር።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ የሚገኙት በስተ ሰሜን ያሉት የመመገቢያ ክፍሎችና በስተ ደቡብ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች፣ ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናት እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች የሚበሉባቸው የተቀደሱ መመገቢያ ክፍሎች ናቸው። በዚያም እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች፣ የእህል መባ፣ የኃጢአት መባና የበደል መባ ያስቀምጣሉ፤ ምክንያቱም ቦታው ቅዱስ ነው።
ካህናቱ በሚገቡበት ጊዜ፣ ሲያገለግሉ የሚለብሱትን ልብስ ሳያወልቁ ከቅዱሱ ስፍራ ወደ ውጨኛው አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ ልብሶቹ ቅዱስ ናቸውና። ለሕዝቡ ወደተፈቀዱት ቦታዎች ከመሄዳቸው በፊት ልብሳቸውን ይቀይሩ ነበር።”
የቤተ መቅደሱን የውስጠኛውን ስፍራ ለክቶ ሲጨርስ ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር በሚወስደው መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ወጣ፤ ከዚያም ስፍራውን በጠቅላላ ለካ።
በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን በመለኪያ ዘንግ ለካ። በመለኪያ ዘንጉ ከአንዱ ጎን እስከ ሌላው ጎን ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
በስተ ደቡብ በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
ከዚያም ወደ ምዕራብ ዞረ። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ።
ስፍራውን በአራቱም ጎን ለካ። ቅዱስ የሆነውንና ቅዱስ ያልሆነውን ስፍራ ለመለየት የሚያገለግል ርዝመቱ 500 ዘንግ፣ ወርዱም 500 ዘንግ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበር።
ከዚያም ወደ ውጨኛው መቅደስ አስገባኝ፤ በጎንና በጎን ያሉትንም ዓምዶች ለካ፤ የዓምዶቹ ወርድ በአንደኛው ጎን ስድስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ስድስት ክንድ ሆነ።