text
stringlengths
4
267
ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።
ከዚያም መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤ አምላክም አናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ወደ ቤትህ ሄደህ በርህን ዘግተህ ተቀመጥ።
የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን በገመድ ይጠፍሩሃል፤ በመካከላቸውም እንዳትመላለስ ያስሩሃል።
እኔም ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቃለሁ፤ ዱዳም ትሆናለህ፤ ልትወቅሳቸውም አትችልም፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።
በማናግርህ ጊዜ ግን አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው። የሚሰማ ይስማ፤ የማይሰማም አይስማ፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ዋይ ዋይ በሉ፤ ‘ቀኑ ስለቀረበ ወዮ!’
ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል። የደመናት ቀን፣ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል።
ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ሲወሰድ እንዲሁም መሠረቶቿ ሲፈራርሱ ኢትዮጵያ በሽብር ትዋጣለች።
ኢትዮጵያ፣ ፑጥ፣ ሉድና ድብልቅ ሕዝቦች ሁሉእንዲሁም ኩብ፣ ከቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች ጋርሁሉም በሰይፍ ይወድቃሉ።”’
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለግብፅ ድጋፍ የሚሰጡም ይወድቃሉ፤የምትታበይበት ኃይሏም ይወገዳል።’ “‘ከሚግዶል እስከ ሰዌኔ በምድሪቱ ላይ በሰይፍ ይወድቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
‘ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ይወድማሉ።
በግብፅም ላይ እሳት በማነድበትና ተባባሪዎቿ ሁሉ በሚደቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።
በዚያን ቀን በራሷ የምትታመነውን ኢትዮጵያን ለማንቀጥቀጥ መልእክተኞችን በመርከብ እልካለሁ፤ ግብፅ በምትጠፋበት ቀን በሽብር ይዋጣሉ፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስፍር ቁጥር የሌለውን የግብፅ ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ አጠፋለሁ።
ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እሱና ሠራዊቱ ምድሪቱን ለማውደም ይመጣሉ። እነሱም በግብፅ ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ።
የአባይን የመስኖ ቦዮች አደርቃለሁ፤ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ በባዕዳን እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አስጸያፊ የሆኑትንም ጣዖቶች አጠፋለሁ፤ ከንቱ የሆኑትንም የኖፍ አማልክት አስወግዳለሁ። ከእንግዲህ ከግብፅ ምድር የሚወጣ ገዢ አይኖርም፤ በግብፅም ምድር ፍርሃት እሰዳለሁ።
ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጾዓን እሳት አነዳለሁ፤ ደግሞም በኖእ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ።
የግብፅ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ ቁጣዬን አፈስሳለሁ፤ የኖእንም ሕዝብ አጠፋለሁ።
በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ሲን በሽብር ትዋጣለች፤ ኖእ ቅጥሯ ይፈርሳል፤ ኖፍ ደግሞ በጠራራ ፀሐይ ጥቃት ይሰነዘርባታል!
የኦንና የጲበሰት ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የከተሞቹም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ።
በዚያ የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ በጣፍነስ ቀኑ ይጨልማል። የምትታበይበት ኃይሏ ይጠፋል፤ ደመናት ይሸፍኗታል፤ የከተሞቿም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ።
በግብፅ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
በ11ኛውም ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ እንዲድን አይታሰርም፤ ወይም ጠንክሮ ሰይፍ እንዲይዝ በጨርቅ አይጠቀለልም።”
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ፤ ብርቱውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ ላይ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።
ከዚያም ግብፃውያንን በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።
የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስጨብጠዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንዶች እሰብራለሁ፤ እሱም ሊሞት እያጣጣረ እንዳለ ሰው በፊቱ እጅግ ያቃስታል።
የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንዶች ግን ይዝላሉ፤ ሰይፌንም ለባቢሎን ንጉሥ ሳስጨብጠውና በግብፅ ምድር ላይ ሲሰነዝረው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።
ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
ከዚያም በጆሮዬ እየሰማሁ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከተማዋን የሚቀጡት፣ እያንዳንዳቸው አጥፊ መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው እንዲመጡ ጥሯቸው!” አለ።
እኔም እያንዳንዳቸው በእጃቸው የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎች በሰሜን ትይዩ ባለው በላይኛው በር በኩል ሲመጡ አየሁ፤ ከእነሱም ጋር በፍታ የለበሰ፣ በወገቡ ላይም የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘ አንድ ሰው ነበር፤ እነሱም መጥተው ከመዳብ በተሠራው መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
ከዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር፣ አርፎበት ከነበረው ከኪሩቦቹ በላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ አምላክም በፍታ የለበሰውንና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራው።
ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “በከተማዋ መካከል ይኸውም በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።”
ሌሎቹን ደግሞ እኔ እየሰማሁ እንዲህ አላቸው፦ “እሱን ተከትላችሁ በከተማዋ መካከል እለፉ፤ ሰዉንም ግደሉ። ዓይናችሁ አይዘን፤ ደግሞም አትራሩ።
ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ። ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ። ከመቅደሴም ጀምሩ።” ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ከዚያም “ቤተ መቅደሱን አርክሱ፤ ግቢዎቹንም ሬሳ በሬሳ አድርጓቸው። ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የከተማዋን ሕዝብ ገደሉ።
እነሱ ሰዉን እየገደሉ ሳሉ ብቻዬን ቀረሁ፤ በግንባሬም ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣህን በማፍሰስ የእስራኤልን ቀሪዎች ሁሉ ልታጠፋ ነው?” በማለት ጮኽኩ።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው። ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች። ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና።
እኔ ግን ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም። የተከተሉት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
ከዚያም በፍታ የለበሰውና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ልክ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ” አለ።
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ በሆነውና በማጎግ ምድር በሚገኘው በጎግ ላይ አድርገህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር።
እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ።
እመልስሃለሁ፤ በመንጋጋህም መንጠቆ አስገባለሁ፤ ከመላው ሠራዊትህ ይኸውም ከፈረሶች፣ ያማረ ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞች፣ ትልቅ ጋሻና ትንሽ ጋሻ ከያዘ እንዲሁም ሰይፍ ከሚመዝ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፤
ትንሽ ጋሻ የያዙና የራስ ቁር የደፉ የፋርስ፣ የኢትዮጵያና የፑጥ ሰዎች ከእነሱ ጋር አሉ፤
ጎሜርንና ወታደሮቹን ሁሉ፣ ራቅ ባለው የሰሜን ምድር የሚገኙትን የቶጋርማ ቤት ሰዎችንና ወታደሮቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ከአንተ ጋር አሉ።
“‘“አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር የተሰበሰበው ሠራዊትህ ሁሉ ተነሡ፣ ተዘጋጁም፤ አንተም አዛዣቸው ትሆናለህ።
“‘“ከብዙ ቀናት በኋላ በአንተ ላይ ትኩረት ይደረጋል። በመጨረሻዎቹ ዓመታት ከሰይፍ ጥቃት የተረፈውንና ከብዙ ሕዝቦች መካከል ተሰብስቦ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆነው ወደቆዩት የእስራኤል ተራሮች የተመለሰውን ሕዝብ ምድር ትወራለህ። የምድሪቱ ነዋሪዎች ከተለያዩ ሕዝቦች መካከል ተመልሰው የመጡ ናቸው፤ ደግሞም ሁሉም ያለስጋት ተቀምጠዋል።
አንተም በእነሱ ላይ እንደ አውሎ ነፋስ ትመጣለህ፤ አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር ያሉት ብዙ ሕዝቦች ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።”’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ ልብህ ይገባል፤ ክፉ ዕቅድም ታወጣለህ፤
እንዲህ ትላለህ፦ “ከለላ የሌላቸው ሰፈሮች የሚገኙበትን ምድር እወራለሁ። ያለስጋት ተረጋግተው በሚኖሩት ላይ እመጣለሁ፤ ሁሉም የሚኖሩት ቅጥር፣ መቀርቀሪያና በር በሌላቸው ሰፈሮች ነው።”
ዓላማህ ብዙ ሀብት መበዝበዝና መዝረፍ፣ ደግሞም አሁን የሰው መኖሪያ የሆኑትን ባድማ የነበሩ ስፍራዎችና ከብሔራት ሁሉ መካከል ዳግመኛ የተሰበሰበውን ሕዝብ ማጥቃት ነው፤ ይህ ሕዝብ ሀብትና ንብረት አከማችቷል፤ በምድርም እምብርት ላይ ይኖራል።
“‘ሳባ፣ ዴዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና ተዋጊዎቹ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “ወረራ የምታካሂደው ብዙ ሀብት ለመበዝበዝና ለመዝረፍ ነው? ሠራዊትህን የሰበሰብከው ብርና ወርቅ ለማጋበስ፣ ሀብትና ንብረት ለመውሰድ እንዲሁም ብዙ ምርኮ ለመንጠቅ ነው?”’
“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል ያለስጋት በሚቀመጥበት ጊዜ፣ አንተ በዚያን ቀን ይህን ማወቅህ ይቀራል?
አንተ ከስፍራህ ይኸውም ርቆ ከሚገኘው የሰሜን ምድር ትመጣለህ፤ አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝቦች ትመጣላችሁ፤ ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፣ ታላቅ ጉባኤና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ናቸው።
ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትመጣለህ። ጎግ ሆይ፣ በዘመኑ መጨረሻ በአንተ አማካኝነት በፊታቸው ራሴን በምቀድስበት ጊዜ ብሔራት ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።”’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በእነሱ ላይ እንደማመጣ ለብዙ ዓመታት ትንቢት በተናገሩትና አገልጋዮቼ በሆኑት የእስራኤል ነቢያት አማካኝነት በቀድሞ ዘመን የተናገርኩት ስለ አንተው አይደለም?’
“‘በዚያ ቀን፣ ጎግ የእስራኤልን ምድር በሚወርበት ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ታላቅ ቁጣዬ ይነድዳል።
በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት እናገራለሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል።
የባሕር ዓሣዎች፣ የሰማይ ወፎች፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ከእኔ የተነሳ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይናዳሉ፤ ገደላማ ቦታዎችም ይደረመሳሉ፤ ቅጥሩም ሁሉ ይፈርሳል።’
“‘በተራሮቼ ሁሉ፣ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በገዛ ወንድሙ ላይ ይሆናል።
እኔም በቸነፈርና በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤ በእሱ፣ በወታደሮቹና ከእሱ ጋር ባሉ ብዙ ሕዝቦች ላይ ኃይለኛ ዶፍ፣ በረዶ፣ እሳትና ድኝ አዘንባለሁ።
ደግሞም ራሴን ገናና አደርጋለሁ፤ እንዲሁም ራሴን እቀድሳለሁ፤ በብዙ ብሔራትም ፊት ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
የይሖዋ ቃል በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ቀን፣ አዎ ይህንኑ ቀን መዝግብ። የባቢሎን ንጉሥ በዚሁ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምሯል።
ዓመፀኛውን ቤት አስመልክቶ ምሳሌ ተናገር፤ ስለ እነሱም እንዲህ በል፦ “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ድስቱን ጣደው፤ እሳት ላይ ጣደው፤ ውኃም ጨምርበት።
ጭኑንና ወርቹን ጨምሮ ጥሩ ጥሩ የሆነውን ሙዳ ሥጋ ሁሉ ሰብስበህ ጨምርበት፤ምርጥ የሆኑ አጥንቶችንም ሙላበት።
ከመንጋው ምርጥ የሆነውን በግ ውሰድ፤ በድስቱም ሥር ዙሪያውን ማገዶ ጨምር። ሥጋውን ቀቅለው፤ በውስጡ ያለውንም አጥንት አብስለው።”’
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የዛገ ድስት ለሆነችውና ዝገቷ ላለቀቀው እንዲሁም ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት! ሥጋውን አንድ በአንድ አውጣ፤ ዕጣ መጣል አያስፈልግህም።
ያፈሰሰችው ደም በውስጧ ይገኛልና፤ በገላጣ ዓለት ላይ አፍስሳዋለች። በአፈር እንዲሸፈን መሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
ቁጣዬ ተነሳስቶ እበቀላት ዘንድያፈሰሰችው ደም እንዳይሸፈንደሙን በሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለት ላይ አደረግኩት።’
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት! ማገዶውን እቆልለዋለሁ።
እንጨቱን ከምር፤ እሳቱን አቀጣጥል፤ሥጋውን በደንብ ቀቅል፤ መረቁን አፍስ፤ አጥንቶቹም ይረሩ።
ባዶውን ድስት እንዲግል ፍሙ ላይ ጣደው፤መዳቡም በጣም ይግላል። ቆሻሻው በውስጡ ይቀልጣል፤ ዝገቱንም እሳት ይበላዋል።
ድስቱ በጣም ከመዛጉ የተነሳ ስለማይለቅ ከንቱ ልፋት ነው፤ደግሞም እንዲሁ ድካም ብቻ ነው። ከነዝገቱ እሳት ውስጥ ጣለው!’
“‘በጸያፍ ምግባርሽ የተነሳ ረክሰሻል። ላነጻሽ ሞክሬ ነበር፤ አንቺ ግን ከርኩሰትሽ ንጹሕ ልትሆኚ አትችዪም። በአንቺ ላይ ያደረብኝ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ንጹሕ አትሆኚም።
እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ። በእርግጥ ይፈጸማል። ምንም ሳላቅማማ፣ ያላንዳች ሐዘንና ጸጸት እርምጃ እወስዳለሁ። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ተወዳጅ የሆነውን በአንድ ምት ልወስድብህ ነው። አንተም ዋይታ አታሰማ ወይም አታልቅስ ወይም ደግሞ እንባህን አታፍስ።
ሐዘንህን በውስጥህ አምቀህ ያዝ፤ ለሞተው በወጉ መሠረት ሐዘንህን አትግለጽ። ጥምጥምህን እሰር፤ ጫማህንም አድርግ። ሪዝህን አትሸፍን፤ ሰዎች የሚያመጡልህንም ምግብ አትብላ።”
እኔም በጠዋት ለሕዝቡ ተናገርኩ፤ ሚስቴም ማታ ላይ ሞተች። ስለሆነም ጠዋት፣ ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ።
ሕዝቡም “ይህ የምታደርገው ነገር ለእኛ ምን መልእክት እንዳለው አትነግረንም?” አሉኝ።
እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን መቅደሴን ላረክስ ነው። ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
ከዚያም እኔ እንዳደረግኩት ታደርጋላችሁ። ሪዛችሁን አትሸፍኑም፤ ሰዎች የሚያመጡላችሁንም ምግብ አትበሉም።
ጥምጥማችሁ አይፈታም፤ ጫማችሁ ከእግራችሁ ላይ አይወልቅም። ዋይታ አታሰሙም ወይም አታለቅሱም። ይልቁንም በበደላችሁ ትመነምናላችሁ፤ አንዳችሁ ለሌላው እሮሮ ታሰማላችሁ።
ሕዝቅኤል ምልክት ይሆንላችኋል። እሱ እንዳደረገው ሁሉ ታደርጋላችሁ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”’”
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ምሽጋቸውን ይኸውም ደስ የሚሰኙበትን ያማረ ነገር፣ በፊታቸው ተወዳጅ የሆነውን ነገርና የልባቸውን ምኞት እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በምወስድባቸው ቀን፣
አምልጦ የመጣ ሰው ወሬውን ይነግርሃል።
በዚያን ቀን አፍህን ከፍተህ፣ ካመለጠው ሰው ጋር ትነጋገራለህ፤ ከዚያ በኋላ ዱዳ አትሆንም። ምልክት ትሆንላቸዋለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መልሶ አመጣኝ፤ በዚያም ከቤተ መቅደሱ ደፍ ሥር ወደ ምሥራቅ የሚፈስ ውኃ ተመለከትኩ፤ የቤተ መቅደሱ ፊት ከምሥራቅ ትይዩ ነበር። ውኃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ከሥር ወጥቶ ከመሠዊያው በስተ ደቡብ ይወርድ ነበር።
ከዚያም ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ በኩል አምጥቶ ወደ ውጭ ካወጣኝ በኋላ ከምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የውጨኛው በር አዙሮ አመጣኝ፤ እኔም በስተ ቀኝ በኩል ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ አየሁ።
ሰውየው መለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ 1,000 ክንድ ለካ፤ ከዚያም በውኃው መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃው እስከ ቁርጭምጭሚት ይደርስ ነበር።
ከዚያም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ። ደግሞም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።
እንደገናም 1,000 ክንድ በለካ ጊዜ ውኃው ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ወንዝ ሆኖ ነበር።
እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ጅረቱ ዳርቻ ወሰደኝ።
በተመለስኩ ጊዜ በጅረቱ ዳርቻ፣ በግራና በቀኝ በጣም ብዙ ዛፎች አየሁ።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ውኃ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ምድር ይፈስሳል፤ አረባን አቋርጦም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ይገባል። ወደ ባሕሩ በሚገባበት ጊዜ በዚያ ያለው ውኃ ይፈወሳል።