text
stringlengths
4
267
“‘ፊቴን ከእነሱ አዞራለሁ፤ እነሱም የተሰወረውን ቦታዬን ያረክሳሉ፤ ዘራፊዎችም ወደ እሷ ይገባሉ፤ ደግሞም ያረክሷታል።
“‘ምድሪቱ ነፍስ ግድያ በሚያስከትል የተዛባ ፍርድ ስለተሞላች፣ ከተማዋም በዓመፅ ስለተሞላች ሰንሰለት ሥራ።
ከብሔራት መካከል እጅግ የከፉትን አመጣለሁ፤ እነሱም ቤቶቻቸውን ይወርሳሉ፤ የብርቱዎቹንም ኩራት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ።
መከራ ሲመጣባቸው ሰላምን ይሻሉ፤ ሆኖም ሰላም አይኖርም።
በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፤ በወሬም ላይ ወሬ ይናፈሳል፤ ሰዎችም ከነቢይ ራእይ ይሻሉ፤ ሆኖም ሕግ ከካህን፣ ምክርም ከሽማግሌዎች ዘንድ ይጠፋል።
ንጉሡ ያለቅሳል፤ አለቃውም በተስፋ መቁረጥ ስሜት ይዋጣል፤ የምድሪቱም ሕዝብ ከመሸበሩ የተነሳ እጁ ይንቀጠቀጣል። እንደ መንገዳቸው አደርግባቸዋለሁ፤ ደግሞም እነሱ እንደፈረዱት እፈርድባቸዋለሁ። እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ አሞናውያን አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር።
አሞናውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መቅደሴ በረከሰ ጊዜና የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ እንዲሁም የይሁዳ ቤት ሰዎች በግዞት በተወሰዱ ጊዜ ‘እሰይ!’ ስላላችሁ
ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እነሱ በእናንተ ውስጥ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውንም በመካከላችሁ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ።
ራባን የግመሎች መሰማሪያ፣ የአሞናውያንን ምድርም መንጋ የሚያርፍበት ስፍራ አደርጋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ ሐሴት ስላደረግክ፣
ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ። እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሞዓብና ሴይር “እነሆ፣ የይሁዳ ቤት ልክ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ነው” ስላሉ፣
በድንበሩ ላይ የሚገኙትና የምድሪቱ ውበት የሆኑት ከተሞች ማለትም ከቤትየሺሞትና ከበዓልመዖን አንስቶ እስከ ቂርያታይምድረስ ያለው የሞዓብ ክንፍ ለጠላት እንዲጋለጥ አደርጋለሁ።
ከአሞናውያን ጋር ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ይህም አሞናውያን በብሔራት መካከል እንዳይታወሱ ለማድረግ ነው።
በሞዓብም ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤
ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ። ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።
‘በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ። እነሱም፣ ኤዶም የምወስደውን የበቀል እርምጃ ይቀምስ ዘንድ ቁጣዬንና መዓቴን በኤዶም ላይ ያወርዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል።
ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ።
ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው የሚናገሩትንም እንዲህ በላቸው፦ ‘የይሖዋን ቃል ስሙ።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም ያዩት ነገር ሳይኖር የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉት ሞኝ ነቢያት ወዮላቸው!
እስራኤል ሆይ፣ ነቢያትህ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ሆነዋል።
እስራኤል፣ በይሖዋ ቀን በሚኖረው ውጊያ ጸንቶ ይቆም ዘንድ በድንጋይ ቅጥሩ ላይ የሚገኙትን የፈረሱ ቦታዎች ለእስራኤል ቤት መልሳችሁ ለመገንባት ወደዚያ አትሄዱም።”
“ይሖዋ ሳይልካቸው ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ የሚሉ ሰዎች ያዩአቸው ራእዮች ውሸት ናቸው፤ ትንቢታቸውም ሐሰት ነው፤ ይሁንና ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ።
እኔ የተናገርኩት ነገር ሳይኖር ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ ስትሉ ያያችሁት ራእይ ውሸት፣ የተናገራችሁትም ትንቢት ሐሰት መሆኑ አይደለም?”’
“‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ውሸት ስለተናገራችሁና ያያችኋቸው ራእዮች ሐሰት ስለሆኑ እኔ በእናንተ ላይ ተነስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
እጄ የውሸት ራእዮች በሚያዩና የሐሰት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስታለች። ሚስጥሬን ከማካፍላቸው ሰዎች መካከል አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብም ላይ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይመለሱም፤ እናንተም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።
ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰላም ሳይኖር “ሰላም አለ!” እያሉ ሕዝቤን በማሳታቸው ነው። ሕዝቡ ጥንካሬ የሌለው ግድግዳ ሲሠራ እነሱ በኖራ ይለስኑታል።’
“በኖራ የሚለስኑትን ሰዎች ግድግዳው ይፈርሳል በላቸው። ከባድ ዶፍ ይጥላል፤ የበረዶ ድንጋይ ይወርዳል፤ ኃይለኛ አውሎ ነፋስም ግድግዳውን ያፈርሰዋል።
ግድግዳው በሚወድቅበት ጊዜም ‘የለሰናችሁት ልስን የት አለ?’ ብለው ይጠይቋችኋል።
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በታላቅ ቁጣዬ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዲነሳ አደርጋለሁ፤ በቁጣዬም ከባድ ዶፍ አዘንባለሁ፤ ደግሞም ጥፋት በሚያስከትል ታላቅ ንዴት የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ።
እናንተ በኖራ የለሰናችሁትን ግድግዳ አፍርሼ ከመሬት እደባልቀዋለሁ፤ መሠረቱም ይታያል። ከተማዋ ስትወድቅ በውስጧ ትጠፋላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’
“‘ቁጣዬን ሁሉ በግድግዳውና ግድግዳውን በኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ በማወርድበት ጊዜ እንዲህ እላችኋለሁ፦ “ግድግዳው ፈርሷል፤ በኖራ የለሰኑት ሰዎችም የሉም።
ለኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእዮች የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል”’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው ወደሚናገሩት የሕዝብህ ሴቶች ልጆች ፊትህን አዙር፤ በእነሱም ላይ ትንቢት ተናገር።
እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሰዎችን ሕይወት ለማደን፣ በክንድ ሁሉ ላይ የሚታሰር ቀጭን ጨርቅ ለሚሰፉና ለሰው እንደየቁመቱ የራስ መሸፈኛ ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤን ሕይወት እያደናችሁ የራሳችሁን ሕይወት ለማዳን ትጥራላችሁ?
የእናንተን ውሸት ለሚያዳምጠው ሕዝቤ ውሸት እየተናገራችሁ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች በሕይወት በማቆየት፣ ለጥቂት እፍኝ ገብስና ለቁርስራሽ ዳቦ ብላችሁ በሕዝቤ መካከል ታረክሱኛላችሁ?”’
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ሴቶች፣ እነሆ ሰዎችን እንደ ወፎች ለማደን በምትጠቀሙበት ጨርቅ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤ ከክንዳችሁም ላይ እቀደዋለሁ፤ እንደ ወፎች ያደናችኋቸውንም ሰዎች ነፃ አወጣለሁ።
የራስ መሸፈኛችሁን እቀዳለሁ፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ አድናችሁ አትይዟቸውም፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።
እኔ እንዲያዝን ያላደረግኩትን ጻድቅ ሰው ሐሰት በመናገር ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጋችኋልና፤ ደግሞም ክፉው ሰው ከክፋት መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር እጁን አበርትታችኋል።
ስለዚህ እናንተ ሴቶች፣ ከእንግዲህ የውሸት ራእዮች አታዩም፤ ሟርትም አታሟርቱም፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙረህ ቅዱስ በሆኑት ስፍራዎች ላይ አውጅ፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር።
ለእስራኤል ምድር እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ሰይፌንም ከሰገባው መዝዤ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ አስወግዳለሁ።
ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ እስከ ሰሜን ድረስ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።
ሰዎች ሁሉ ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ያውቃሉ። ዳግመኛ ወደ ሰገባው አይመለስም።”’
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እየተንቀጠቀጥክ አቃስት፤ አዎ፣ በፊታቸው በምሬት አቃስት።
‘የምታቃስተው ለምንድን ነው?’ ቢሉህ ‘ከሰማሁት ወሬ የተነሳ ነው’ ትላለህ። በእርግጥ ይመጣልና፤ ልብም ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ መንፈስ ሁሉ ያዝናል፤ ጉልበትም ሁሉ በውኃ ይርሳል። ‘እነሆ፣ በእርግጥ ይመጣል! ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ሰይፍ! ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል።
የተሳለው ታላቅ እልቂት ለማስከተል ነው፤ የተወለወለውም እንደ መብረቅ እንዲያበራ ነው’ በል።”’” “ታዲያ ደስ ሊለን አይገባም?” “‘ማንኛውንም ዛፍ እንደሚንቅ ሁሉ የገዛ ልጄን በትረ መንግሥት ይንቃል?
“‘እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቷል። ገዳዩ በእጁ እንዲይዘው ይህ ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል።
“‘የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰይፍ በሕዝቤ ላይ ስለመጣ ጩኽ፤ ደግሞም ዋይ ዋይ በል፤ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ተነስቷል። እነዚህ ሰዎች ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ የሰይፍ ሰለባ ይሆናሉ። ስለዚህ ጭንህን በሐዘን ምታ።
ሰይፉ ተፈትሿልና፤ ደግሞስ በትረ መንግሥቱን ከናቀው ምን ይሆናል? ከሕልውና ውጭ ይሆናል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ በእጅህም አጨብጭብ፤ ደግሞም ‘ሰይፍ!’ የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ ደጋግመህ ተናገር። ሰለባዎቹን የሚገድልና ታላቅ እልቂት የሚያስከትል፣ እነሱን የሚከብ ሰይፍ ነው።
ልባቸው በፍርሃት ይቀልጣል፤ ብዙዎችም በከተሞቻቸው በር ላይ ይወድቃሉ፤ እኔም በሰይፉ እገድላለሁ። አዎ፣ ሰይፉ እንደ መብረቅ ያበራል፤ ለመግደልም ተወልውሏል!
በስተ ቀኝ በኩል በኃይል ቁረጥ! በስተ ግራ በኩል ተንቀሳቀስ! ስለትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ ሂድ!
እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤ ቁጣዬንም አበርዳለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።”
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን ሁለት መንገዶች ንድፍ አውጣ። ሁለቱም መንገዶች የሚነሱት ከአንድ ምድር ነው፤ መንገዱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አድርግ።
ሰይፍ በአሞናውያን ከተማ በራባ ላይ ይመጣ ዘንድ አንደኛውን መንገድ አመልክት፤ እንዲሁም በይሁዳ በምትገኘው በተመሸገችው ኢየሩሳሌም ላይ ይመጣ ዘንድ ሌላኛውን መንገድ አመልክት።
የባቢሎን ንጉሥ ያሟርት ዘንድ በመንታ መንገድ ይኸውም በሁለቱ መንገዶች መገንጠያ ላይ ይቆማልና። ፍላጾችን ይወዘውዛል። ጣዖቶቹን ያማክራል፤ ጉበት ይመረምራል።
በቀኝ እጁ የወጣው ሟርት የመደርመሻ መሣሪያዎችን ለመደገን፣ የግድያ ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ የጦርነት ሁካታ ለማሰማት፣ በበሮቿ ላይ የመደርመሻ መሣሪያዎች ለመደገን፣ በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ለመደልደልና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ አመለከተው።
ቃለ መሐላዎች የገቡላቸው ሰዎች ግን ይህ የሐሰት ሟርት ይመስላቸዋል። ይሁንና እሱ በደላቸውን በማስታወስ ማርኮ ይወስዳቸዋል።
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምትፈጽሙት ድርጊት ሁሉ መተላለፋችሁ እንዲገለጥና ኃጢአታችሁ እንዲታይ በማድረግ በደላችሁ እንዲታሰብ አድርጋችኋል። እናንተም አሁን ስለታሰባችሁ በኃይል ትወሰዳላችሁ።’
“አንተ ክፉኛ የቆሰልከው፣ መጥፎው የእስራኤል አለቃ፣ ቀንህ ይኸውም የመጨረሻ ቅጣት የምትቀበልበት ጊዜ ደርሷል።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥምጥሙን ፍታ፤ አክሊሉንም አንሳ። ይህ እንደ በፊቱ አይሆንም። ዝቅ ያለውን ከፍ አድርግ፤ ከፍ ያለውን ደግሞ ዝቅ አድርግ።
ባድማ፣ ባድማ፣ ባድማ አደርጋታለሁ። እሷም ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ ለማንም አትሆንም፤ ለእሱም እሰጣታለሁ።’
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል።’ እንዲህ በል፦ ‘ሰይፍ! ሰይፍ ለግድያ ተመዟል፤ እንዲበላና እንደ መብረቅ እንዲያበራ ተወልውሏል።
ስለ ራስሽ የሐሰት ራእዮች ያየሽና የውሸት ሟርት ያሟረትሽ ቢሆንም ቀናቸው፣ የመጨረሻ ቅጣት የሚቀበሉበት ጊዜ በደረሰባቸው ክፉዎች ማለትም በሚገደሉት ሰዎች ላይ ትከመሪያለሽ።
ሰይፉ ወደ ሰገባው ይመለስ። በተፈጠርሽበት ስፍራ፣ በተገኘሽበትም ምድር እፈርድብሻለሁ።
ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ። የታላቅ ቁጣዬን እሳት በላይሽ ላይ አነዳለሁ፤ በማጥፋትም ለተካኑ ጨካኝ ሰዎች አሳልፌ እሰጥሻለሁ።
ለእሳት ማገዶ ትሆኛለሽ፤ የገዛ ደምሽ በምድሪቱ ላይ ይፈስሳል፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ አትታወሺም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁና።’”
ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ያለውን ብላ። ይህን ጥቅልል ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ።
ስለዚህ አፌን ከፈትኩ፤ እሱም ጥቅልሉን እንድበላው ሰጠኝ።
ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን የሰጠሁህን ጥቅልል ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም ጥቅልሉን መብላት ጀመርኩ፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው።
የተላክኸው ወደ እስራኤል ቤት እንጂ ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገር ሕዝብ አይደለምና።
ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገሩና ቃላቸው ሊገባህ ወደማይችል ብዙ ሕዝቦች አልተላክህም። ወደ እነሱ ብልክህማ ኖሮ ይሰሙህ ነበር።
የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና። የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው።
እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።
ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ። አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።”
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ቃል ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ደግሞም አዳምጥ።
በምርኮ ወደተወሰዱት ወገኖችህ ሄደህ ንገራቸው። ቢሰሙም ባይሰሙም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።”
ከዚያም መንፈስ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ከበስተ ኋላዬም ታላቅ የጉምጉምታ ድምፅ “የይሖዋ ክብር ከስፍራው ይወደስ” ሲል ሰማሁ።
በዚያም የሕያዋን ፍጥረታቱ ክንፎች እርስ በርስ ሲነካኩ የሚያሰሙት ድምፅ፣ በአጠገባቸው ያሉት መንኮራኩሮች የሚያሰሙት ድምፅና የታላቅ ጉምጉምታ ድምፅ ነበር።
መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ ወሰደኝ፤ እኔም ተማርሬና መንፈሴ ተቆጥቶ ሄድኩ፤ የይሖዋም ብርቱ እጅ በእኔ ላይ አርፋ ነበር።
ስለሆነም በቴልአቢብ፣ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ይኖሩ ወደነበሩት በግዞት የተወሰዱ ሰዎች ሄድኩ፤ እነሱም በሚኖሩበት ስፍራ ተቀመጥኩ፤ በድንጋጤ ፈዝዤም በመካከላቸው ሰባት ቀን ቆየሁ።
ሰባቱ ቀናት ካለፉ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።
ክፉውን ሰው ‘በእርግጥ ትሞታለህ’ ባልኩት ጊዜ ባታስጠነቅቀው፣ ደግሞም ክፉው ሰው በሕይወት ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ ባትሰጠው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ በሠራው በደል ይሞታል፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።
ሆኖም ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው ከክፋቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን በእርግጥ ታድናለህ።
ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ እኔ በፊቱ መሰናክል አስቀምጣለሁ፤ እሱም ይሞታል። ሳታስጠነቅቀው ከቀረህ በሠራው ኃጢአት የተነሳ ይሞታል፤ ያከናወነውም የጽድቅ ሥራ አይታወስም፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።
ሆኖም ጻድቁን ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና ኃጢአት ባይሠራ፣ ማስጠንቀቂያውን በመስማቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም የገዛ ሕይወትህን ታድናለህ።”
በዚያም የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ሆነች፤ እሱም “ተነስተህ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሂድ፤ በዚያም አናግርሃለሁ” አለኝ።