text stringlengths 4 267 |
|---|
“‘አንድ ሰው ጻድቅ ነው እንበል፤ ይህ ሰው ፍትሐዊና ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል። |
በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም ወይም ከሴት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ግንኙነት አይፈጽምም፤ |
ማንንም ሰው አይበድልም፤ ይልቁንም ተበዳሪ መያዣ አድርጎ የሰጠውን ይመልሳል፤ ማንንም ሰው አይዘርፍም፤ ይልቁንም ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ |
ወለድ አይጠይቅም ወይም በአራጣ አያበድርም፤ ይልቁንም ፍትሕ የጎደለው ድርጊት ከመፈጸም ይቆጠባል፤ በሰዎች መካከል እውነተኛ ፍትሕ ያሰፍናል፤ |
ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል፤ እንዲሁም በታማኝነት ይመላለስ ዘንድ ድንጋጌዎቼን ይጠብቃል። እንዲህ ያለው ሰው ጻድቅ ነው፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘ይሁንና ይህ ሰው ዘራፊ ወይም ነፍሰ ገዳይ የሆነ ወይም ከእነዚህ ነገሮች አንዱን የሚያደርግ ልጅ አለው እንበል፤ |
(አባቱ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱንም ባያደርግ እንኳ) ልጁ በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን ይበላል፤ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ |
የተቸገረውንና ድሃውን ይበድላል፤ ሰዎችን ይዘርፋል፤ መያዣ አድርጎ የወሰደውን አይመልስም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶች ይመለከታል፤ ጸያፍ የሆኑ ልማዶችን ይፈጽማል፤ |
በአራጣ ያበድራል፤ እንዲሁም ወለድ ይቀበላል፤ በመሆኑም ይህ ልጅ ፈጽሞ በሕይወት አይኖርም። እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች በመሥራቱ በእርግጥ ይሞታል። ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል። |
“‘ይሁንና አንድ አባት የተለያዩ ኃጢአቶች ሲሠራ ልጁ ይመለከተዋል እንበል፤ ልጁ ይህን ቢመለከትም እንዲህ ያሉ ነገሮች አይሠራም። |
በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ |
ማንንም ሰው አይበድልም፤ መያዣ እንዲሆን የተሰጠውን አይወስድም፤ ከሰው ላይ ምንም ነገር አይዘርፍም፤ ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ |
ድሃውን ሰው ከመጨቆን ይቆጠባል፤ በአራጣ አያበድርም ወይም ወለድ አይጠይቅም፤ ድንጋጌዎቼንም ያከብራል፤ እንዲሁም ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል። እንዲህ ያለ ሰው አባቱ በፈጸመው በደል የተነሳ አይሞትም። በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። |
አባቱ ግን የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ፣ ወንድሙን በመዝረፉና በሕዝቡ መካከል መጥፎ የሆነ ነገር በመሥራቱ በፈጸመው በደል የተነሳ ይሞታል። |
“‘እናንተ ግን “ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ የማይሆነው ለምንድን ነው?” ትላላችሁ። ልጁ ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ስላደረገ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ሁሉ ስለጠበቀና በሥራ ላይ ስላዋለ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። |
ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች። ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም፤ አባትም ልጁ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም። የጻድቁ ሰው ጽድቅ የሚታሰብለት ለራሱ ብቻ ነው፤ የክፉውም ሰው ክፋት የሚታሰበው በራሱ ላይ ብቻ ነው። |
“‘ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ቢጠብቅ እንዲሁም ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። |
ከሠራው በደል ውስጥ አንዱም አይታሰብበትም። በሠራው ጽድቅ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።’ |
“‘እኔ በክፉ ሰው ሞት ደስ እሰኛለሁ?’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘እኔ ደስ የምሰኘው ከመንገዱ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለም?’ |
“‘ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ ደግሞም ክፉው ሰው እንደሚያደርገው አስጸያፊ ነገሮችን ሁሉ ቢሠራ በሕይወት ይኖራል? ካከናወነው የጽድቅ ሥራ መካከል አንዱም አይታወስም። ታማኝነቱን በማጉደሉና ኃጢአት በመሥራቱ የተነሳ ይሞታል። |
“‘ይሁንና እናንተ “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ! በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም? ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም? |
“‘ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህም የተነሳ ቢሞት፣ የሚሞተው በገዛ ራሱ በደል ነው። |
“‘ክፉ ሰው ከሠራው ክፉ ድርጊት ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ማድረግ ቢጀምር የራሱን ሕይወት ያድናል። |
የሠራውን በደል ሁሉ ተገንዝቦ ከዚያ ቢመለስ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። |
“‘ይሁንና የእስራኤል ቤት ሰዎች “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም? ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?’ |
“‘ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደየመንገዳችሁ እፈርዳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ተመለሱ፤ አዎ፣ ተጠያቂ እንድትሆኑ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ እንዳይሆንባችሁ ከሠራችሁት በደል ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተመለሱ። |
የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ከራሳችሁ ላይ አስወግዱ፤ ደግሞም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?’ |
“‘እኔ በማንም ሰው ሞት ደስ አልሰኝም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።’” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ነበሩ። |
እነሱም በግብፅ ዝሙት አዳሪዎች ሆኑ፤ ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ አመነዘሩ። በዚያም ጡታቸው ተሻሸ፤ የድንግልናቸውም ጉያ ተዳበሰ። |
የታላቂቱ ስም ኦሆላ፣ የእህቷም ስም ኦሆሊባ ነበር። እነሱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውን በተመለከተ፣ ኦሆላ ሰማርያ ስትሆን ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። |
“ኦሆላ የእኔ ሆና ሳለች ታመነዝር ጀመር። ጎረቤቶቿ የሆኑትን ፍቅረኞቿን አሦራውያንን በፍትወት ተመኘች። |
እነሱ ሰማያዊ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች እንዲሁም ፈረሰኞች ነበሩ። |
እሷ ምርጥ ከሆኑት የአሦር ልጆች ሁሉ ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች፤ ደግሞም በፍትወት የምትመኛቸው ሰዎች በሚያመልኳቸው አስጸያፊ ጣዖቶች ራሷን አረከሰች። |
በግብፅ ትፈጽመው የነበረውን ምንዝር አልተወችም፤ እነሱ በወጣትነቷ ከእሷ ጋር ተኝተዋልና፤ የድንግልናዋን ጉያ ዳብሰዋል እንዲሁም ፍትወታቸውን በእሷ ላይ አፍስሰዋል። |
ስለዚህ በፍትወት ለተመኘቻቸው፣ ፍቅረኞቿ ለሆኑት አሦራውያን አሳልፌ ሰጠኋት። |
እነሱ እርቃኗን ገለጡ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ማረኩ፤ እሷንም በሰይፍ ገደሏት። በሴቶች መካከል መጥፎ ስም አተረፈች፤ እነሱም የፍርድ እርምጃ ወሰዱባት። |
“እህቷ ኦሆሊባ ይህን ስትመለከት ፍትወቷ እጅግ የከፋ ሆነ፤ አመንዝራነቷም ከእህቷ የባሰ ሆነ። |
ጎረቤቶቿ የሆኑትን የአሦርን ልጆች በፍትወት ተመኘች፤ እነሱ ያማረ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች ነበሩ። |
እሷ ራሷን ባረከሰች ጊዜ ሁለቱም በአንድ መንገድ እንደሄዱ ተገነዘብኩ። |
ይሁን እንጂ እሷ በአመንዝራነቷ ገፋችበት። በግድግዳው ላይ የተቀረጹትን የወንድ ምስሎች ይኸውም ቀይ ቀለም የተቀቡትን የከለዳውያን የተቀረጹ ምስሎች አየች፤ |
እነሱ ወገባቸው ላይ ቀበቶ ታጥቀዋል፤ በራሳቸውም ላይ የተንዘረፈፈ ጥምጥም አድርገዋል፤ ደግሞም ተዋጊዎች ይመስላሉ፤ ሁሉም በከለዳውያን ምድር የተወለዱትን ባቢሎናውያን ያመለክታሉ። |
እሷም እነሱን እንዳየቻቸው በፍትወት ትመኛቸው ጀመር፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር መልእክተኞች ላከችባቸው። |
በመሆኑም የባቢሎን ልጆች ከእሷ ጋር ለመተኛት ወደ እሷ መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት። በእነሱ ከረከሰች በኋላ ተጸይፋቸው ከእነሱ ራቀች። |
“ዓይን አውጣ በመሆን ማመንዘሯንና እርቃኗን መግለጧን በቀጠለች ጊዜ እህቷን ተጸይፌ እንደራቅኳት ሁሉ እሷንም ተጸይፌ ራቅኳት። |
እሷ ግን በግብፅ ምድር ስታመነዝር የነበረበትን የወጣትነቷን ዘመን በማስታወስ በአመንዝራነቷ ይባስ ገፋችበት። |
ብልታቸው እንደ አህያ ብልት፣ አባለዘራቸውም እንደ ፈረስ አባለዘር በሆኑ ወንዶች የተያዙ ቁባቶች እንደሚያደርጉት እሷም በፍትወት ተመኘቻቸው። |
በግብፅ ምድር ጉያሽን በዳበሱበት፣ የወጣትነትሽንም ጡቶች ባሻሹበት ጊዜ በወጣትነትሽ ትፈጽሚው የነበረውን ጸያፍ ምግባር ተመኘሽ። |
“ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ተጸይፈሽ የራቅሻቸውን ፍቅረኞችሽን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ፤ እነሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ |
እነሱም የባቢሎን ልጆችና ከለዳውያን ሁሉ እንዲሁም የአሦርን ልጆች ሁሉ ጨምሮ የጰቆድ፣ የሾአ እና የቆአ ሰዎች ናቸው። ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች፣ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች፣ ተዋጊዎችና የተመረጡ አማካሪዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ናቸው። |
እነሱም የጦር ሠረገሎችንና መንኮራኩሮችን ሁሉ እያንጋጉ፣ ትልቅና ትንሽ ጋሻ የያዘ እንዲሁም የራስ ቁር የደፋ ብዙ ሠራዊት አስከትለው ጥቃት ይሰነዝሩብሻል። በዙሪያሽም ይሰለፋሉ፤ እኔም የመፍረድ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም ትክክል መስሎ በታያቸው መንገድ ይፈርዱብሻል። |
እኔም ቁጣዬን በአንቺ ላይ እገልጣለሁ፤ እነሱም በታላቅ ቁጣ እርምጃ ይወስዱብሻል። አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቆርጣሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በእሳት ይበላሉ። |
ልብሶችሽን ይገፉሻል፤ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይነጥቁሻል። |
በግብፅ ምድር የጀመርሽው ጸያፍ ምግባርና አመንዝራነትሽ እንዲያበቃ አደርጋለሁ። ከእንግዲህ ዓይንሽን ወደ እነሱ አታነሺም፤ ግብፅንም አታስታውሺም።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ለጠላሻቸው ሰዎች፣ ተጸይፈሽ ለራቅሻቸው ሰዎች አሳልፌ ልሰጥሽ ነው። |
እነሱ በጥላቻ እርምጃ ይወስዱብሻል፤ የደከምሽበትን ነገር ሁሉ ይወስዳሉ፤ ራቁትሽንና እርቃንሽን ያስቀሩሻል። የፆታ ብልግና ስትፈጽሚ የተገለጠው አሳፋሪ የሆነው እርቃንሽ፣ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ ይፋ ይወጣል። |
እንደ ዝሙት አዳሪ ብሔራትን ተከትለሽ ስለሄድሽና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራስሽን ስላረከስሽ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይፈጸሙብሻል። |
የእህትሽን መንገድ ተከትለሻል፤ ስለዚህ የእሷን ጽዋ አስጨብጥሻለሁ።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥልቅና ሰፊ የሆነውን የእህትሽን ጽዋ ትጠጫለሽ፤ደግሞም መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ፤ ጽዋውም በዚህ የተሞላ ነው። |
በስካርና በሐዘን፣በሽብርና በጥፋት ጽዋ ትዋጫለሽ፤ይህም የእህትሽ የሰማርያ ጽዋ ነው። |
ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽ፤ የጽዋውንም ስብርባሪዎች ትቆረጣጥሚያለሽ፤ከዚያም ጡቶችሽን ትቆርጫለሽ። “እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’ |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለረሳሽኝና ጨርሶ ቸል ስላልሽኝ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ የሚያስከትለውን መዘዝ ትቀበያለሽ።’” |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሆላና በኦሆሊባ ላይ ትፈርዳለህ? አስጸያፊ ተግባራቸውንስ ፊት ለፊት ትነግራቸዋለህ? |
እነሱ አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻቸው ጋር ከማመንዘራቸውም በተጨማሪ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆች ለጣዖቶቻቸው መብል እንዲሆኑ ለእሳት አሳልፈው ሰጥተዋል። |
በተጨማሪም በእኔ ላይ እንዲህ አድርገዋል፦ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፤ ሰንበቶቼንም አቃለዋል። |
ልጆቻቸውን አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻቸው ከሠዉ በኋላ በዚያው ቀን ወደ መቅደሴ መጥተው አረከሱት። እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ይህን አድርገዋል። |
አልፎ ተርፎም ከሩቅ ቦታ ወንዶች እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ። እነሱ በመጡ ጊዜ ገላሽን ታጠብሽ፤ ዓይንሽን ተኳልሽ፤ በጌጣጌጥም ተዋብሽ። |
እጅግ ባማረ ድንክ አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ በፊቱም በተሰናዳ ማዕድ ላይ ዕጣኔንና ዘይቴን አኖርሽ። |
በዚያም በፈንጠዝያ ላይ ያሉ ብዙ ወንዶች ሁካታ ይሰማ ነበር፤ በመካከላቸውም ከምድረ በዳ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ። እነሱም በሴቶቹ እጆች ላይ አምባር አጠለቁ፤ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። |
“ከዚያም እኔ ሰውነቷ በምንዝር ስላለቀው ሴት፣ ‘አሁንም ማመንዘሯን ትቀጥላለች’ አልኩ። |
ሰው ወደ ዝሙት አዳሪ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ወደ እሷ መሄዳቸውን ቀጠሉ። በዚህ መንገድ፣ ባለጌ ወደሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ። |
ጻድቃን ግን ለምንዝርና ለደም አፍሳሽነት የሚገባውን ፍርድ ይፈርዱባታል፤ እነሱ አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል። |
ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል። |
በምድሪቱ ላይ የሚፈጸመው ጸያፍ ምግባር እንዲወገድ አደርጋለሁ፤ ሴቶቹም ሁሉ ከዚህ ይማራሉ፤ የእናንተንም ጸያፍ ምግባር ከመከተል ይርቃሉ። |
የፈጸማችሁት ጸያፍ ምግባር እንዲሁም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ የሠራችሁት ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ እንድትቀበሉ ያደርጋሉ፤ እኔም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ተራራማ ወደሆነው የሴይር ምድር አዙረህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር። |
እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ እነሆ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ወና አደርግሃለሁ። |
ከተሞችህን አፈራርሳለሁ፤ አንተም ባድማና ወና ትሆናለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ። |
የእስራኤል ልጆች ጥፋት በደረሰባቸውና የመጨረሻውን ቅጣት በተቀበሉበት ጊዜ የማያባራ የጠላትነት ስሜት በማሳየት ለሰይፍ አሳልፈህ ሰጥተሃቸዋልና።”’ |
“‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእርድ አዘጋጅሃለሁ፤ ደምህም ይፈስሳል። ደም ጠልተህ ስለነበር ደምህ ይፈስሳል። |
የሴይርን ተራራማ ምድር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤ በዚያ የሚያልፈውንም ሆነ የሚመለሰውን ማንኛውንም ሰው አጠፋለሁ። |
ተራሮቹን በታረዱ ሰዎች እሞላለሁ፤ በሰይፍ የታረዱት በኮረብቶችህ፣ በሸለቆዎችህና በጅረቶችህ ላይ ይወድቃሉ። |
ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው አልባ ይሆናሉ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ |
“ይሖዋ ራሱ በዚያ ቢኖርም እንኳ፣ አንተ ‘እነዚህ ሁለት ብሔራትና ሁለት አገሮች የእኔ ይሆናሉ፤ እኛም ሁለቱን አገሮች እንወርሳለን’ ስላልክ፣ |
‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእነሱ ካደረብህ የጥላቻ ስሜት የተነሳ በእነሱ ላይ በገለጥከው በዚያው ዓይነት ቁጣና ቅናት እኔም እርምጃ እወስድብሃለሁ፤ በአንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ በእነሱ መካከል ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ። |
አንተ “ወና ሆነዋል፤ ለእኛም እንደ መብል ተሰጥተዋል” ባልክ ጊዜ በእስራኤል ተራሮች ላይ በንቀት የተናገርከውን ነገር ሁሉ እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።” |
እናንተ በእኔ ላይ በእብሪት ተናግራችኋል፤ ደግሞም በእኔ ላይ ብዙ ነገር ተናግራችኋል። የተናገራችሁትን ሁሉ ሰምቻለሁ።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ መላዋ ምድር ሐሴት ታደርጋለች። |
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር። ትንቢት ተናገር፤ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ራሳቸውን ለሚመግቡ የእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞቹ ሊመግቡ የሚገባው መንጋውን አይደለም? |
ጮማውን ትበላላችሁ፤ ሱፉን ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም እንስሳ ታርዳላችሁ፤ መንጋውን ግን አትመግቡም። |
የደከመውን አላበረታችሁም፣ የታመመውን አልፈወሳችሁም፣ የተጎዳውን በጨርቅ አላሰራችሁትም፣ የባዘኑትን መልሳችሁ አላመጣችሁም ወይም የጠፋውን አልፈለጋችሁም፤ ከዚህ ይልቅ በጭካኔና በግፍ ገዛችኋቸው። |
በጎቹ እረኛ በማጣታቸው ተበታተኑ፤ ተበታትነው ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። |
በጎቼ በየተራራውና ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ባዘኑ፤ በምድር ሁሉ ላይ ተበተኑ፤ የፈለጋቸው ወይም እነሱን ለማግኘት የጣረ አንድም ሰው የለም። |
“‘“ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ |
‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በጎቼ እረኛ ስላጡና እረኞቼ በጎቼን ስላልፈለጉ፣ ይልቁንም እረኞቹ ራሳቸውን ስለመገቡና በጎቼን ስላልመገቡ፣ በጎቼ ለአደን ተዳርገዋል፤ ለዱር አራዊትም ሁሉ መብል ሆነዋል፤”’ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.