text stringlengths 4 267 |
|---|
ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። |
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ በእረኞቹ ላይ ተነስቻለሁ፤ ስለ በጎቼ እጠይቃቸዋለሁ፤ በጎቼን እንዳያሰማሩም እከለክላቸዋለሁ፤ እረኞቹም ከእንግዲህ ራሳቸውን አይመግቡም። በጎቼን ከአፋቸው አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ለእነሱ መብል አይሆኑም።’” |
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ። |
የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ። በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ። |
ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ። |
ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል። በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።” |
“‘“በጎቼን እኔ ራሴ አሰማራለሁ፤ እኔ ራሴም አሳርፋቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“የጠፋውን እፈልጋለሁ፤ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።” |
“‘በጎቼ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በበግና በበግ መካከል እንዲሁም በአውራ በጎችና በአውራ ፍየሎች መካከል ልፈርድ ነው። |
እናንተ ምርጥ ከሆነው የግጦሽ ስፍራ መመገባችሁ አነሳችሁ? የቀሩትን የግጦሽ ስፍራዎች ደግሞ በእግራችሁ መረጋገጥ ይገባችኋል? እጅግ የጠራውን ውኃ ከጠጣችሁ በኋላስ ውኃውን በእግራችሁ እየመታችሁ ማደፍረሳችሁ ተገቢ ነው? |
ታዲያ በጎቼ በእግራችሁ በረጋገጣችሁት የግጦሽ መስክ ላይ መሰማራትና በእግራችሁ እየመታችሁ ያደፈረሳችሁትን ውኃ መጠጣት ይኖርባቸዋል?” |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላቸዋል፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በሰባው በግና ከሲታ በሆነው በግ መካከል እፈርዳለሁ፤ |
እናንተ የታመሙት ሁሉ በየአቅጣጫው እስኪበታተኑ ድረስ በጎናችሁና በትከሻችሁ ገፍታችኋቸዋልና፤ በቀንዳችሁም ገፍትራችኋቸዋል። |
በጎቼንም አድናለሁ፤ እነሱም ከእንግዲህ ለአደን አይዳረጉም፤ እኔም በበግና በበግ መካከል እፈርዳለሁ። |
በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን አስነሳለሁ፤ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል። |
ደግሞም እኔ ይሖዋ አምላካቸው እሆናለሁ፤ አገልጋዬ ዳዊት ደግሞ በመካከላቸው አለቃ ይሆናል። እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ። |
“‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ። |
እነሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያለውን ቦታ በረከት አደርጋቸዋለሁ፤ ዝናብም በወቅቱ እንዲዘንብ አደርጋለሁ። በረከት እንደ ዝናብ ይወርዳል። |
የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት እነሱን ለማደን አይነሱም፤ የምድር አራዊትም አይበሏቸውም፤ ያለስጋትም ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም። |
“‘“ዝና የሚያስገኝ የእርሻ ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ በምድሪቱ ላይ በረሃብ አያልቁም፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት አያዋርዷቸውም። |
‘በዚህ ጊዜ እኔ አምላካቸው ይሖዋ ከእነሱ ጋር እንደሆንኩና እነሱ ይኸውም የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እንደሆኑ ያውቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ |
“‘እናንተ በጎቼ፣ የምንከባከባችሁ በጎች፣ ከአፈር የተሠራችሁ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። |
እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮቹ፣ ለኮረብቶቹ፣ ለጅረቶቹና ለሸለቆዎቹ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ፤ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎቻችሁንም አጠፋለሁ። |
መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ይሰባበራሉ፤ የታረዱ ወገኖቻችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ፊት እጥላለሁ። |
የእስራኤልን ሕዝብ ሬሳ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ። |
በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ያሉት ከተሞች ይወድማሉ፤ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎቹም ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ። መሠዊያዎቻችሁ ፈራርሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ አስጸያፊ የሆኑት ጣዖቶቻችሁ ይወገዳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ተገንድሰው ይወድቃሉ፤ የሠራችኋቸው ሥራዎችም ተጠራርገው ይጠፋሉ። |
የታረዱትም ሰዎች በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። |
“‘“ይሁንና የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ በየአገሩ በምትበተኑበት ጊዜ፣ ከእናንተ ውስጥ አንዳንዶቻችሁ በብሔራት መካከል ስትኖሩ ከሰይፍ ታመልጣላችሁና። |
የተረፉትም ሰዎች በምርኮ በተወሰዱባቸው ብሔራት መካከል ሆነው እኔን ያስታውሳሉ። ከእኔ በራቀው ከሃዲ ልባቸውና አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በፍትወት ስሜት በተመለከቱት ዓይኖቻቸው የተነሳ ምን ያህል ልቤ እንዳዘነ ይገነዘባሉ። በሠሯቸው መጥፎና አስነዋሪ ነገሮች ሁሉ ያፍራሉ፤ እነዚህንም ነገሮች ይጸየፋሉ። |
እኔ ይሖዋ እንደሆንኩና ይህን ጥፋት እንደማመጣባቸው የዛትኩት በከንቱ እንዳልሆነ ያውቃሉ።”’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎች በሠሯቸው ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ስለሚወድቁ በእጅህ እያጨበጨብክ፣ በእግርህም መሬቱን እየደበደብክ አልቅስ። |
በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ ከእነዚህ ነገሮች ያመለጠና በሕይወት የተረፈ ሁሉ በረሃብ ያልቃል፤ ቁጣዬንም ሁሉ በእነሱ ላይ አወርዳለሁ። |
የታረዱት ወገኖቻቸው አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉና በተራሮች አናት ሁሉ ላይ፣ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች እንዲሁም በትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፎች ሥር ይኸውም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ቁጣ ለማብረድ፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያላቸው መባዎች ባቀረቡባቸው ቦታዎች በሚወድቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
በእነሱ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መኖሪያ ቦታዎቻቸውም ሁሉ በዲብላ አቅራቢያ ካለው ምድረ በዳ የባሰ ባድማ ይሆናሉ። እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” |
በግዞት በተወሰድን በ25ኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በወሩ አሥረኛ ቀን፣ ከተማዋ በወደቀች በ14ኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ እሱም ወደ ከተማዋ ወሰደኝ። |
አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ በአንድ ትልቅ ተራራም ላይ አስቀመጠኝ፤ በዚያም በስተ ደቡብ በኩል ከተማ የሚመስል ሕንፃ ነበር። |
ወደዚያ በወሰደኝ ጊዜ መዳብ የሚመስል መልክ ያለው አንድ ሰው አየሁ። በእጁም ከተልባ እግር የተሠራ ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ መግቢያው ላይ ቆሞ ነበር። |
ሰውየው እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በደንብ ተመልከት፤ በጥሞና አዳምጥ፤ የማሳይህንም ሁሉ በትኩረት ተመልከት፤ እዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና። የምታየውን ነገር ሁሉ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ተናገር።” |
ከቤተ መቅደሱ ውጭ በዙሪያው ያለውን ቅጥር አየሁ። ሰውየው ስድስት ክንድ ርዝመት ያለው የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበር፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። እሱም ቅጥሩን መለካት ጀመረ፤ የቅጥሩ ውፍረት አንድ ዘንግ፣ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። |
ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ በደረጃዎቹም ወጣ። የበሩን ደፍ ሲለካ ወርዱ አንድ ዘንግ ነበር፤ የሌላኛውም ደፍ ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። |
እያንዳንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ርዝመቱ አንድ ዘንግ፣ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበር፤ በዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ መካከል ደግሞ አምስት ክንድ ስፋት ነበር። ከበሩ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ ደፍ አንድ ዘንግ ነበር። |
በውስጥ በኩል ያለውን የበሩን በረንዳ ለካ፤ አንድ ዘንግም ሆነ። |
ከዚያም የበሩን በረንዳ ሲለካ ስምንት ክንድ ሆነ፤ በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶችም ሲለካ ሁለት ክንድ ሆኑ፤ የበሩም በረንዳ በውስጥ በኩል ነበር። |
በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። ሦስቱም መጠናቸው እኩል ነበር፤ በሁለቱም በኩል ያሉት ዓምዶችም መጠናቸው እኩል ነበር። |
ከዚያም የበሩን መግቢያ ወርድ ሲለካ 10 ክንድ ሆነ፤ የበሩ ስፋት ከውጭ በኩል 13 ክንድ ነበር። |
ከዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ ፊት ለፊት ያለው የተከለለ ቦታ በሁለቱም በኩል አንድ አንድ ክንድ ነበር። የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ በሁለቱም በኩል ስድስት ስድስት ክንድ ነበሩ። |
ከዚያም በሩን ከአንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ እስከ ሌላኛው የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ ድረስ ለካ፤ ወርዱም 25 ክንድ ነበር፤ አንደኛው መግቢያ ከሌላኛው መግቢያ ትይዩ ነበር። |
ከዚያም በጎንና በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶች ቁመት ሲለካ 60 ክንድ ሆነ፤ በግቢው ዙሪያ በሚገኙት በሮች ላይ ያሉትንም ዓምዶች ለካ። |
ከመግቢያው በር ፊት አንስቶ በበሩ ውስጠኛ ክፍል በኩል እስካለው በረንዳ ፊት ድረስ 50 ክንድ ነበር። |
ከበሩ በውስጥ በኩል በግራና በቀኝ፣ የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹና በጎን ያሉት ዓምዶቻቸው እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶች ነበሯቸው። በረንዳዎቹም በውስጥ በኩል፣ በግራም በቀኝም መስኮቶች ነበሯቸው፤ በጎን ያሉት ዓምዶች ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸውባቸው ነበር። |
ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ አመጣኝ፤ በግቢውም ዙሪያ የመመገቢያ ክፍሎችና መመላለሻ መንገድ አየሁ። በመንገዱ ላይ 30 የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ። |
በበሮቹ ጎን ያለው መመላለሻ መንገድ ከበሮቹ ርዝመት ጋር እኩል ነበር፤ ይህም የታችኛው መመላለሻ መንገድ ነበር። |
ከዚያም ከታችኛው በር አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ እስከሚያስገባው በር ድረስ ያለውን ርቀት ለካ። በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት 100 ክንድ ነበር። |
የውጨኛው ግቢ ከሰሜን ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ርዝመቱንና ወርዱን ለካ። |
በሁለቱም ጎን ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከመጀመሪያው በር ጋር እኩል ነበር። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። |
የመስኮቶቹ፣ የበረንዳውና የዘንባባ ዛፍ ምስሎቹ መጠን በምሥራቁ በር ካሉት ጋር እኩል ነበር። ሰዎች ሰባት ደረጃዎች ወጥተው ወደዚያ መግባት ይችላሉ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። |
በውስጠኛው ግቢ፣ ከሰሜኑ በር ትይዩ አንድ በር፣ ከምሥራቁ በር ትይዩ ደግሞ ሌላ በር ነበር። እሱም ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። |
ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ አመጣኝ፤ በስተ ደቡብ በኩል አንድ በር አየሁ። እሱም በጎን ያሉትን ዓምዶቹንና በረንዳውን ለካ፤ መጠናቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። |
በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ እንደ ሌሎቹ ዓይነት መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። |
ወደዚያ የሚወስዱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ አንድ አንድ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጾ ነበር። |
የውስጠኛው ግቢ ከደቡብ ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ለካ፤ ርቀቱም 100 ክንድ ሆነ። |
ከዚያም በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ወሰደኝ፤ የደቡቡን በር ሲለካ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ሆነ። |
የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። |
ዙሪያውን በረንዳዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው 25 ክንድ፣ ወርዳቸው ደግሞ 5 ክንድ ነበር። |
በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በጎን ባሉት ዓምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። |
በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ሲወስደኝ በሩን ለካ፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። |
የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤ በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። |
በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። |
ከዚያም ወደ ሰሜን በር ወሰደኝና ለካው፤ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። |
የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በግራና በቀኝ መስኮቶች ነበሩት። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። |
በጎን ያሉት ዓምዶቹ ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበሩ፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶቹ ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። |
በበሮቹ ጎንና ጎን ባሉት ዓምዶች አጠገብ የመመገቢያ ክፍል ነበር፤ መግቢያም ነበረው፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ የሚያጥቡት በዚያ ነበር። |
በበሩም በረንዳ ላይ በግራና በቀኝ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የኃጢአት መባና የበደል መባ የሚታረድባቸው ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። |
ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ ላይ ከመግቢያው ውጭ ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። በተጨማሪም ከበሩ በረንዳ በሌላኛው በኩል ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። |
በበሩ ግራና ቀኝ አራት አራት ጠረጴዛዎች፣ በድምሩ መሥዋዕት የታረደባቸው ስምንት ጠረጴዛዎች ነበሩ። |
ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ የሚያገለግሉት አራቱ ጠረጴዛዎች ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ ነበሩ። ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመታቸው ደግሞ አንድ ክንድ ነበር። በእነሱም ላይ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቱን ለማረድ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ተቀምጠው ነበር። |
ከውስጠኛው ግንብ ጋር ተያይዘው ዙሪያውን የተሠሩ መደርደሪያዎች የነበሩ ሲሆን ወርዳቸው አንድ ጋት ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የስጦታ መባው ሥጋ ይቀመጥ ነበር። |
ከውስጠኛው በር ውጭ የዘማሪዎቹ መመገቢያ ክፍሎች ነበሩ፤ ክፍሎቹ ከደቡብ ትይዩ ባለው የሰሜን በር አጠገብ በሚገኘው በውስጠኛው ግቢ ውስጥ ነበሩ። ከሰሜን ትይዩ ባለው የምሥራቅ በር አጠገብ ሌላ የመመገቢያ ክፍል ነበር። |
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “በደቡብ ትይዩ ያለው ይህ የመመገቢያ ክፍል የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው። |
በሰሜን ትይዩ ያለው የመመገቢያ ክፍል ከመሠዊያው ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው። እነዚህ የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ ከሌዋውያን መካከል ይሖዋን ለማገልገል ወደ እሱ እንዲቀርቡ የተመደቡ ናቸው።” |
ከዚያም የውስጠኛውን ግቢ ለካ። ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱም 100 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ነበር። መሠዊያው ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር። |
ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ በረንዳ አመጣኝ፤ በጎን በኩል ያለውንም የበረንዳውን ዓምድ ለካ፤ ዓምዱም በአንደኛው ጎን አምስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን አምስት ክንድ ነበር። የበሩ ወርድ በአንደኛው ጎን ሦስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ሦስት ክንድ ነበር። |
የበረንዳው ርዝመት 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 11 ክንድ ነበር። ሰዎች ወደዚያ የሚወጡት በደረጃዎች ነበር። በጎንና በጎን ባሉት ምሰሶዎች አጠገብ በግራና በቀኝ አንድ አንድ ዓምድ ነበር። |
በአሥረኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በ12ኛው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙረህ በእሱና በመላዋ ግብፅ ላይ ትንቢት ተናገር። |
እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በአባይ ጅረቶች መካከል የተጋደምክና‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው።የሠራሁት ለገዛ ራሴ ነው’ የምትል አንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት፣ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፣ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። |
በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ከቅርፊትህ ጋር እንዲጣበቁ አደርጋለሁ። ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት የአባይ ዓሣዎች ሁሉ ጋር ከአባይ ወንዝህ መካከል አወጣሃለሁ። |
አንተንም ሆነ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉትን ዓሣዎች ሁሉ በረሃ ላይ እጥላለሁ። አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህም ሆነ የሚያነሳህ አይኖርም። ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ። |
በዚያን ጊዜ የግብፅ ነዋሪዎች ሁሉ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ለእስራኤል ቤት ከአገዳ የተሻለ ድጋፍ መሆን አልቻሉምና። |
እጅህን ሲይዙህ ተሰበርክ፤ትከሻቸውንም ወጋህ። በተመረኮዙህ ጊዜ ተሰበርክ፤እግራቸውም እንዲብረከረክ አደረግክ።” |
“‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤ በአንተ ዘንድ የሚገኘውን ሰውም ሆነ እንስሳ አጠፋለሁ። |
የግብፅ ምድር ባድማና ወና ይሆናል፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ አንተ ‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና። |
ስለዚህ በአንተና በአባይ ወንዝህ ላይ ተነስቻለሁ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል እስከ ሰዌኔ ብሎም እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ ባድማ፣ ደረቅና ወና አደርጋለሁ። |
የሰው እግርም ሆነ የከብት ኮቴ አያልፍባትም፤ ለ40 ዓመትም ማንም አይኖርባትም። |
የግብፅን ምድር ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ለ40 ዓመት ያህል ባድማ ይሆናሉ፤ ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።” |
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ከ40 ዓመት በኋላ ግብፃውያንን ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል እሰበስባቸዋለሁ፤ |
የተማረኩትን ግብፃውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ጳትሮስ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.