text stringlengths 4 267 |
|---|
አርዮክም ዳንኤልን ወዲያውኑ በንጉሡ ፊት አቅርቦ “ከይሁዳ ግዞተኞች መካከል የሕልሙን ትርጉም ለንጉሡ ማሳወቅ የሚችል ሰው አግኝቻለሁ” አለው። |
ንጉሡም ብልጣሶር የተባለውን ዳንኤልን “ያየሁትን ሕልምና ትርጉሙን በእርግጥ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። |
ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ከጠቢባኑ፣ ከጠንቋዮቹ፣ አስማተኛ ከሆኑት ካህናት ወይም ከኮከብ ቆጣሪዎቹ መካከል ንጉሡ የጠየቀውን ሚስጥር መግለጥ የሚችል የለም። |
ይሁንና ሚስጥርን የሚገልጥ አምላክ በሰማያት አለ፤ እሱም በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነጾር አሳውቆታል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኸው ሕልምና የተመለከትካቸው ራእዮች እነዚህ ናቸው፦ |
“ንጉሥ ሆይ፣ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ታስብ ነበር፤ ሚስጥርን የሚገልጠውም አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አሳውቆሃል። |
ይህ ሚስጥር ለእኔ የተገለጠልኝ ከሰው ሁሉ የላቀ ጥበብ ስላለኝ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በልብህ ታስባቸው የነበሩትን ነገሮች ታውቅ ዘንድ የሕልሙ ትርጉም ለንጉሡ እንዲገለጥ ነው። |
“ንጉሥ ሆይ፣ በትኩረት እየተመለከትክ ሳለ አንድ ግዙፍ ምስል አየህ። ግዙፍ የሆነውና እጅግ የሚያብረቀርቀው ይህ ምስል በፊትህ ቆሞ ነበር፤ መልኩም በጣም የሚያስፈራ ነበር። |
የምስሉ ራስ ከጥሩ ወርቅ፣ ደረቱና ክንዶቹ ከብር፣ ሆዱና ጭኖቹ ከመዳብ፣ |
ቅልጥሞቹ ከብረት የተሠሩ ሲሆን እግሮቹ ከፊሉ ብረት፣ ከፊሉ ደግሞ ሸክላ ነበሩ። |
አንተም አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቅቃቸው አየህ። |
በዚህ ጊዜ ብረቱ፣ ሸክላው፣ መዳቡ፣ ብሩና ወርቁ ሁሉም በአንድነት ተሰባበሩ፤ በበጋ ወቅት በአውድማ ላይ እንደሚቀር ገለባም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራርጎ ወሰዳቸው። ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ትልቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ። |
“ሕልሙ ይህ ነው፤ አሁን ደግሞ ትርጉሙን ለንጉሡ እናሳውቃለን። |
ንጉሥ ሆይ፣ አንተ የነገሥታት ንጉሥ ነህ፤ የሰማይ አምላክ መንግሥትን፣ ኃይልን፣ ብርታትንና ክብርን ሰጥቶሃል፤ |
ደግሞም በየትኛውም ቦታ የሚኖሩትን ሰዎችም ሆነ የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎች በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፤ በሁሉም ላይ ገዢ አድርጎሃል፤ የወርቁ ራስ አንተ ራስህ ነህ። |
“ይሁንና ከአንተ በኋላ፣ ከአንተ ያነሰ ሌላ መንግሥት ይነሳል፤ ከዚያም መላውን ምድር የሚገዛ ሌላ ሦስተኛ የመዳብ መንግሥት ይነሳል። |
“አራተኛው መንግሥት ደግሞ እንደ ብረት የጠነከረ ይሆናል። ብረት ሁሉንም ነገር እንደሚሰባብርና እንደሚፈጭ ሁሉ፣ እሱም እንደሚያደቅ ብረት እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ይሰባብራቸዋል፤ ደግሞም ያደቅቃቸዋል። |
“እግሮቹና ጣቶቹ ከፊሉ ሸክላ፣ ከፊሉ ደግሞ ብረት ሆነው እንዳየህ ሁሉ መንግሥቱም የተከፋፈለ ይሆናል፤ ሆኖም ብረቱና የሸክላ ጭቃው ተደባልቆ እንዳየህ ሁሉ በተወሰነ መጠን የብረት ጥንካሬ ይኖረዋል። |
የእግሮቹ ጣቶች ከፊሉ ብረት፣ ከፊሉ ሸክላ እንደሆኑ ሁሉ ይህም መንግሥት በከፊል ብርቱ፣ በከፊል ደግሞ ደካማ ይሆናል። |
ብረቱና የሸክላ ጭቃው ተደባልቀው እንዳየህ ሁሉ እነሱም ከሕዝቡ ጋር ይደባለቃሉ፤ ሆኖም ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይዋሃድ ሁሉ እነሱም አንዱ ከሌላው ጋር አይጣበቁም። |
“በእነዚያ ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት ለሌላ ሕዝብ አይሰጥም። እነዚህን መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤ እሱም ብቻውን ለዘላለም ይቆማል፤ |
አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ብረቱን፣ መዳቡን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ሲያደቅ እንዳየህ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል። ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ለንጉሡ አሳውቆታል። ሕልሙ እውነት፣ ትርጉሙም አስተማማኝ ነው።” |
ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነጾር በዳንኤል ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ዳንኤልንም እጅግ አከበረው። ደግሞም ስጦታና ዕጣን እንዲቀርብለት አዘዘ። |
ንጉሡም ዳንኤልን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥም አምላካችሁ የአማልክት አምላክና የነገሥታት ጌታ እንዲሁም ሚስጥርን የሚገልጥ ነው፤ ምክንያቱም አንተ ይህን ሚስጥር መግለጥ ችለሃል።” |
ከዚያም ንጉሡ ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ብዙ የከበሩ ስጦታዎችም ሰጠው፤ የመላው ባቢሎን አውራጃ ገዢና የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ዋና አስተዳዳሪ አደረገው። |
ዳንኤልም ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን በባቢሎን አውራጃ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ያገለግል ነበር። |
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ተብሎ የተጠራው ዳንኤል አንድ ራእይ ተሰጠው፤ ይህም መልእክት እውነት ነው፤ መልእክቱም ስለ አንድ ታላቅ ውጊያ ይገልጻል። እሱም መልእክቱን ተረድቶት ነበር፤ ያየውንም ነገር ማስተዋል ችሎ ነበር። |
በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ። |
ሦስቱ ሳምንታት እስኪያበቁ ድረስ ምርጥ ምግብ አልበላሁም፤ ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ አልቀመስኩም እንዲሁም ሰውነቴን ቅባት አልተቀባሁም። |
በመጀመሪያው ወር በ24ኛው ቀን በታላቁ ወንዝ ይኸውም በጤግሮስ ዳርቻ ሳለሁ፣ |
ቀና ብዬ ስመለከት በፍታ የለበሰና ወገቡ ላይ በዑፋዝ ወርቅ የተሠራ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ። |
ሰውነቱ እንደ ክርስቲሎቤ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዓይኖቹ እንደሚንቦገቦግ ችቦ፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደሚያብረቀርቅ መዳብ፣ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር። |
ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርኩ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ግን ራእዩን አላዩም። ነገር ግን እጅግ ስለተሸበሩ ሸሽተው ተደበቁ። |
እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ይህን ታላቅ ራእይ በተመለከትኩ ጊዜም በውስጤ ምንም ኃይል አልቀረም፤ ግርማ ሞገስ የተላበሰው ቁመናዬ ተለወጠ፤ ኃይሌም በሙሉ ተሟጠጠ። |
ከዚያም ሲናገር ድምፁን ሰማሁ፤ ሆኖም ሲናገር እየሰማሁት ሳለ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፍቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ። |
በዚህ ጊዜ አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤ ከቀሰቀሰኝ በኋላ በእጄና በጉልበቴ ተደግፌ እንድነሳ አደረገኝ። |
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “እጅግ የተወደድክ ዳንኤል ሆይ፣ የምነግርህን ቃል አስተውል። በነበርክበት ቦታ ላይ ቁም፤ ወደ አንተ ተልኬ መጥቼአለሁና።” ይህን ሲለኝ እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ። |
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ አትፍራ። እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ልባዊ ጥረት ማድረግና በአምላክህ ፊት ራስህን ዝቅ ማድረግ ከጀመርክበት ቀን አንስቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የመጣሁት ከቃልህ የተነሳ ነው። |
ሆኖም የፋርስ ንጉሣዊ ግዛት አለቃ ለ21 ቀናት ተቋቋመኝ። በኋላ ግን ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም በዚያን ጊዜ ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ቆየሁ። |
ራእዩ ከብዙ ዘመን በኋላ የሚፈጸም ስለሆነ በዘመኑ መጨረሻ በሕዝብህ ላይ የሚደርሰውን ነገር አስረዳህ ዘንድ መጥቻለሁ።” |
ይህን ቃል በነገረኝ ጊዜ ወደ መሬት አቀረቀርኩ፤ መናገርም ተሳነኝ። |
በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እኔም አፌን ከፍቼ በፊቴ ቆሞ የነበረውን እንዲህ አልኩት፦ “ጌታዬ ሆይ፣ ከራእዩ የተነሳ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፤ ኃይሌም ተሟጥጧል። |
ስለዚህ የጌታዬ አገልጋይ ከጌታዬ ጋር እንዴት መነጋገር ይችላል? አሁን ምንም ኃይል የለኝምና፤ በውስጤም የቀረ እስትንፋስ የለም።” |
ሰው የሚመስለው እንደገና ዳሰሰኝ፤ አበረታኝም። |
ከዚያም “አንተ እጅግ የተወደድክ ሰው ሆይ፣ አትፍራ። ሰላም ለአንተ ይሁን። በርታ፣ አይዞህ በርታ” አለኝ። እንዲህ ባለኝ ጊዜ ተበረታትቼ “ጌታዬ ሆይ፣ ብርታት ሰጥተኸኛልና ተናገር” አልኩት። |
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ወደ አንተ የመጣሁት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አሁን ከፋርስ አለቃ ጋር ለመዋጋት ተመልሼ እሄዳለሁ። እኔ ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። |
ሆኖም በእውነት መጽሐፍ ላይ የሠፈሩትን ነገሮች እነግርሃለሁ። ከእነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ የሕዝብህ አለቃ ከሆነው ከሚካኤል በስተቀር በእጅጉ ሊረዳኝ የሚችል የለም። |
ንጉሥ ቤልሻዛር ለሺህ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በእነሱም ፊት የወይን ጠጅ እየጠጣ ነበር። |
ቤልሻዛር የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው አባቱ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የወርቅና የብር ዕቃዎች፣ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጧቸው አዘዘ። |
በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም፣ በአምላክ ቤት ከነበረው ቤተ መቅደስ የወሰዷቸውን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም ቁባቶቹና ቅምጦቹ ጠጡባቸው። |
እነሱም የወይን ጠጅ እየጠጡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን አወደሱ። |
ወዲያውኑም የሰው እጅ ጣቶች ብቅ ብለው በንጉሡ ቤተ መንግሥት፣ በመቅረዙ ትይዩ ባለው ግድግዳ ልስን ላይ መጻፍ ጀመሩ፤ ንጉሡም የሚጽፈውን እጅ አየ። |
በዚህ ጊዜ ንጉሡ ፊቱ ገረጣ፤ ወደ አእምሮው የመጣው ሐሳብ አሸበረው፤ ወገቡም ተንቀጠቀጠ፤ ጉልበቶቹም ይብረከረኩ ጀመር። |
ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጠንቋዮቹን፣ ከለዳውያኑንና ኮከብ ቆጣሪዎቹን እንዲያመጧቸው አዘዘ። ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ጽሑፍ የሚያነብና ትርጉሙን የሚነግረኝ ማንኛውም ሰው ሐምራዊ ልብስ ይለብሳል፤ አንገቱ ላይ የወርቅ ሐብል ይደረግለታል፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ይሆናል።” |
በዚህ ጊዜ የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ሆኖም ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጉሙን ለንጉሡ ማሳወቅ አልቻሉም። |
በመሆኑም ንጉሥ ቤልሻዛር እጅግ ፈራ፤ ፊቱም ገረጣ፤ መኳንንቱም ግራ ተጋቡ። |
ንግሥቲቱም ንጉሡና መኳንንቱ የተናገሩትን በሰማች ጊዜ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገባች። እንዲህም አለች፦ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ኑር። በፍርሃት አትዋጥ፤ ፊትህም አይለዋወጥ። |
በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው አለ። በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብ፣ የእውቀት ብርሃንና ጥልቅ ማስተዋል ተገኝቶበት ነበር። አባትህ ንጉሥ ናቡከደነጾር የአስማተኛ ካህናቱ፣ የጠንቋዮቹ፣ የከለዳውያኑና የኮከብ ቆጣሪዎቹ አለቃ አድርጎ ሾመው፤ ንጉሥ ሆይ፣ ይህን ያደረገው አባትህ ነው። |
ንጉሡ፣ ብልጣሶር ብሎ የሰየመው ዳንኤል ሕልምን በመተርጎም ረገድ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ችሎታ፣ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል እንዲሁም እንቆቅልሽንና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ነበረው። እንግዲህ ዳንኤል ይጠራ፤ እሱም ትርጉሙን ይነግርሃል።” |
በመሆኑም ዳንኤልን በንጉሡ ፊት አቀረቡት። ንጉሡም ዳንኤልን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ምድር ካመጣቸው የይሁዳ ግዞተኞች አንዱ የሆንከው ዳንኤል አንተ ነህ? |
የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ እንዲሁም የእውቀት ብርሃን፣ ጥልቅ ማስተዋልና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥበብ እንደተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ። |
ይህን ጽሑፍ አንብበው ትርጉሙን እንዲያሳውቁኝ ጥበበኞችንና ጠንቋዮችን በፊቴ አቅርበዋቸው ነበር፤ እነሱ ግን የመልእክቱን ትርጉም መናገር አልቻሉም። |
አንተ ግን የመተርጎምና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ። አሁንም ይህን ጽሑፍ አንብበህ ትርጉሙን ልታሳውቀኝ ከቻልክ ሐምራዊ ልብስ ትለብሳለህ፤ አንገትህ ላይ የወርቅ ሐብል ይደረግልሃል፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ትሆናለህ።” |
በዚህ ጊዜ ዳንኤል ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ስጦታህ ለራስህ ይሁን፤ ገጸ በረከቶችህንም ለሌሎች ስጥ። ይሁንና ጽሑፉን ለንጉሡ አነባለሁ፤ ትርጉሙንም አሳውቀዋለሁ። |
ንጉሥ ሆይ፣ ልዑሉ አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነጾር መንግሥት፣ ታላቅነት፣ ክብርና ግርማ ሰጠው። |
ታላቅነትን ስላጎናጸፈው ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች የተውጣጡ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር። የፈለገውን ይገድል ወይም በሕይወት እንዲኖር ይፈቅድ፣ የፈለገውን ከፍ ከፍ ያደርግ ወይም ያዋርድ ነበር። |
ሆኖም ልቡ ታብዮና አንገተ ደንዳና ሆኖ የእብሪተኝነት መንፈስ ባሳየ ጊዜ ከመንግሥቱ ዙፋን እንዲወርድ ተደረገ፤ ክብሩንም ተገፈፈ። |
ከሰው ልጆች መካከል ተሰደደ፤ ልቡም ወደ አውሬ ልብ ተለወጠ፤ መኖሪያውም ከዱር አህዮች ጋር ሆነ። ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና የፈለገውን በመንግሥቱ ላይ እንደሚያስቀምጥ እስኪያውቅ ድረስ እንደ በሬ ሣር በላ፤ ሰውነቱም በሰማያት ጠል ረሰረሰ። |
“ቤልሻዛር ሆይ፣ አንተ ግን ልጁ እንደመሆንህ መጠን ይህን ሁሉ ብታውቅም ትሕትና አላሳየህም። |
ይልቁንም በሰማያት ጌታ ላይ ታበይክ፤ የቤተ መቅደሱንም ዕቃ አስመጣህ። ከዚያም አንተና መኳንንትህ እንዲሁም ቁባቶችህና ቅምጦችህ በእነዚህ ዕቃዎች የወይን ጠጅ ጠጣችሁ፤ አንዳች ነገር ማየትም ሆነ መስማት ወይም ማወቅ የማይችሉትን ከብር፣ ከወርቅ፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት አወደሳችሁ። እስትንፋስህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርክም። |
ስለዚህ ይህን እጅ የላከው እሱ ነው፤ ይህም ጽሑፍ ተጻፈ። |
የተጻፈውም ጽሑፍ፣ ‘ሚኒ፣ ሚኒ፣ ቲቄል እና ፋርሲን’ ይላል። |
“የቃላቱ ትርጉም ይህ ነው፦ ሚኒ ማለት አምላክ የመንግሥትህን ዘመን ቆጠረው፤ ወደ ፍጻሜም አመጣው ማለት ነው። |
“ቲቄል ማለት በሚዛን ተመዘንክ፤ ጉድለትም ተገኘብህ ማለት ነው። |
“ፊሬስ ማለት ደግሞ መንግሥትህ ተከፈለ፤ ለሜዶናውያንና ለፋርሳውያን ተሰጠ ማለት ነው።” |
በዚህ ጊዜ ቤልሻዛር ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ዳንኤልንም ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤ በአንገቱም ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቁለት፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ሆኖ መሾሙን አወጁ። |
በዚያኑ ሌሊት ከለዳዊው ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ። |
ሜዶናዊው ዳርዮስም መንግሥቱን ተረከበ፤ ዕድሜውም 62 ዓመት ገደማ ነበር። |
“ከንጉሥ ናቡከደነጾር፣ በመላው ምድር ለሚኖሩ ከተለያዩ ብሔራትና ቋንቋዎች ለተውጣጡ ሕዝቦች፦ ሰላም ይብዛላችሁ! |
ልዑሉ አምላክ ለእኔ ያደረጋቸውን ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ሥራዎች ስነግራችሁ ደስ ይለኛል። |
ተአምራዊ ምልክቱ እንዴት ታላቅ ነው! ድንቅ ሥራውም በዓይነቱ ልዩ ነው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፤ የመግዛት ሥልጣኑም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል። |
“እኔ ናቡከደነጾር በቤቴ ዘና ብዬ፣ በቤተ መንግሥቴም ደልቶኝ እኖር ነበር። |
አንድ አስፈሪ ሕልም አየሁ። በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ወደ አእምሮዬ ይመጡ የነበሩት ምስሎችና ራእዮች አስፈሩኝ። |
ስለዚህ ያየሁትን ሕልም ትርጉም እንዲያሳውቁኝ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ በፊቴ እንዲያቀርቧቸው አዘዝኩ። |
“በዚህ ጊዜ አስማተኞቹ ካህናት፣ ጠንቋዮቹ፣ ከለዳውያኑና ኮከብ ቆጣሪዎቹ ገቡ። ያየሁትን ሕልም ስነግራቸው ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ አልቻሉም። |
በመጨረሻም በአምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል በፊቴ ቀረበ፤ እኔም ያየሁትን ሕልም ነገርኩት፦ |
“‘የአስማተኛ ካህናት አለቃ የሆንከው ብልጣሶር ሆይ፣ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ ውስጥ እንዳለና ለመግለጥ የሚያስቸግርህ ምንም ዓይነት ሚስጥር እንደሌለ በሚገባ አውቃለሁ። በመሆኑም በሕልሜ ያየኋቸውን ራእዮችና ትርጉማቸውን ግለጽልኝ። |
“‘በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ ባየኋቸው ራእዮች ላይ፣ በምድር መካከል ቁመቱ እጅግ ረጅም የሆነ አንድ ዛፍ ቆሞ ተመለከትኩ። |
ዛፉም አድጎ ጠንካራ ሆነ፤ ጫፉም እስከ ሰማያት ደረሰ፤ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ይታይ ነበር። |
ቅጠሉ ያማረ፣ ፍሬውም በጣም ብዙ ሲሆን ዛፉ ላይ ለሁሉ የሚሆን መብል ነበር። የዱር እንስሳት በጥላው ሥር ያርፉ፣ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቹ ላይ ይቀመጡ ነበር፤ ፍጥረታትም ሁሉ ከእሱ ይመገቡ ነበር። |
“‘በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ራእዮቹን ስመለከት ቅዱስ የሆነ አንድ ጠባቂ ከሰማያት ሲወርድ አየሁ። |
እሱም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ዛፉን ቁረጡ፤ ቅርንጫፎቹን ጨፍጭፉ፤ ቅጠሎቹን አራግፉ፤ ፍሬውንም በትኑ! የዱር እንስሳቱ ከሥሩ፣ ወፎቹም ከቅርንጫፎቹ ላይ ይሽሹ። |
ጉቶው ግን በብረትና በመዳብ ታስሮ በሜዳ ሣር መካከል ከነሥሩ መሬት ውስጥ ይቆይ። በሰማያትም ጠል ይረስርስ፤ ዕጣ ፋንታውም በምድር ተክሎች መካከል ከአራዊት ጋር ይሁን። |
ልቡ ከሰው ልብ ይለወጥ፤ የአውሬም ልብ ይሰጠው፤ ሰባት ዘመናትም ይለፉበት። |
ይህ ነገር በጠባቂዎች ታውጇል፤ የፍርድ ውሳኔውም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይህም ልዑሉ አምላክ በሰው ልጆች መንግሥት ላይ እንደሚገዛ እንዲሁም መንግሥቱን ለወደደው እንደሚሰጥና ከሰዎች ሁሉ የተናቀውን እንደሚሾምበት በሕይወት ያሉ ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።” |
“‘እኔ ንጉሥ ናቡከደነጾር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፣ በመንግሥቴ ውስጥ የሚኖሩት ሌሎቹ ጠቢባን ሁሉ ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ ስላልቻሉ አንተ ትርጉሙን ንገረኝ። የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ትርጉሙን ልታሳውቀኝ ትችላለህ።’ |
“በዚህ ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በድንጋጤ ተዋጠ፤ ወደ አእምሮው የመጣው ሐሳብም በጣም አስፈራው። “ንጉሡም ‘ብልጣሶር ሆይ፣ ሕልሙና ትርጉሙ አያስፈራህ’ አለው። “ብልጣሶርም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታዬ ሆይ፣ ሕልሙ ለሚጠሉህ፣ ትርጉሙም ለጠላቶችህ ይሁን። |
“‘አንተ ያየኸው ዛፍ ይኸውም በጣም ያደገውና የጠነከረው፣ ጫፉ እስከ ሰማያት የደረሰውና ከየትኛውም የምድር ክፍል የሚታየው፣ |
ቅጠሉ ያማረውና ፍሬው የበዛው፣ ለሁሉም የሚሆን መብል ያለበት፣ የዱር እንስሳት መጠለያ የሆነውና በቅርንጫፎቹ ላይ የሰማይ ወፎች የሚኖሩበት ዛፍ፣ |
ንጉሥ ሆይ፣ አንተ ነህ፤ ምክንያቱም አንተ ታላቅና ብርቱ ሆነሃል፤ ታላቅነትህ ገንኖ እስከ ሰማያት ደርሷል፤ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ተንሰራፍቷል። |
“‘ንጉሡም አንድ ቅዱስ ጠባቂ “ዛፉን ቆርጣችሁ አጥፉት፤ ጉቶው ግን በብረትና በመዳብ ታስሮ በሜዳ ሣር መካከል ከነሥሩ መሬት ውስጥ ይቆይ። በሰማያትም ጠል ይረስርስ፤ ሰባት ዘመናትም እስኪያልፉበት ድረስ ዕጣ ፋንታው ከዱር አራዊት ጋር ይሁን” እያለ ከሰማያት ሲወርድ አይቷል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.