text stringlengths 4 267 |
|---|
የሠሩት ሥራ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ምክንያቱም በመካከላቸው የአመንዝራነት መንፈስ አለ፤ለይሖዋም እውቅና አይሰጡም። |
የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤እስራኤልና ኤፍሬም የሠሩት በደል አሰናክሏቸዋል፤ይሁዳም ከእነሱ ጋር ተሰናክሏል። |
መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም። እሱ ከእነሱ ርቋል። |
እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና። አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን ይውጣል። |
በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም መለከት ንፉ! ‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን ቀረርቶ አሰሙ። |
ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ። |
የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው። በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ። |
ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና። |
በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ። |
ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከትኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ። ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም። |
እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና። እኔ ራሴ ቦጫጭቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ የሚታደጋቸውም አይኖርም። |
እሄዳለሁ፤ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ እስኪሸከሙም ድረስ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤በዚህ ጊዜም ሞገሴን ይሻሉ። በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።” |
“እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ። |
ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤እኛም ወይፈኖች እንደምናቀርብ፣ የከንፈራችንን ውዳሴ እናቀርብልሃለን። |
አሦር አያድነንም። ፈረሶችን አንጋልብም፤ከእንግዲህም ወዲህ የገዛ እጆቻችን የሠሩትን “አምላካችን ሆይ!” አንልም፤አባት የሌለው ልጅ ምሕረት ያገኘው በአንተ ነውና።’ |
እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ። በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤ምክንያቱም ቁጣዬ ከእሱ ተመልሷል። |
እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እሱም እንደ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል። |
ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል። |
እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ። እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ። ዝናው እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል። |
ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል። መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ። እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ። ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።” |
ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል። ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ። የይሖዋ መንገዶች ቀና ናቸውና፤ጻድቃንም በመንገዶቹ ላይ ይሄዳሉ፤በደለኞች ግን በእነሱ ይሰናከላሉ። |
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም። |
የሐሰት መሐላ፣ ውሸት፣ ነፍስ ግድያ፣ስርቆትና ምንዝር ተስፋፍቷል፤ደም የማፍሰስ ወንጀልም በላይ በላዩ ይፈጸማል። |
ከዚህም የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤በእሷም ላይ የሚኖሩ ሁሉ ይመነምናሉ፤የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎችየባሕር ዓሣዎችም እንኳ ሳይቀሩ ይጠፋሉ። |
“ይሁን እንጂ ማንም ሰው አይሟገት ወይም ሌላውን አይውቀስ፤ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚሟገት ሰው ነውና። |
ስለዚህ እናንተ በጠራራ ፀሐይ ትሰናከላላችሁ፤የጨለመ ይመስል ነቢዩም ከእናንተ ጋር ይሰናከላል። እናታችሁንም ጸጥ አሰኛታለሁ። |
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁእኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ ስለረሳችሁእኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ። |
እነሱ በበዙ ቁጥር በእኔ ላይ የሚሠሩት ኃጢአት በዝቷል። ክብራቸውን ወደ ውርደት እለውጣለሁ። |
የሕዝቤ ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፤ደግሞም እነሱ በደል እንዲሠሩ ይቋምጣሉ። |
ሕዝቡንም ሆነ ካህኑንለተከተሉት መንገድ ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤አድራጎታቸው ያስከተለውንም መዘዝ በላያቸው አመጣለሁ። |
ይበላሉ፤ ሆኖም አይጠግቡም። ሴሰኞች ይሆናሉ፤ ሆኖም ቁጥራቸው አይጨምርም፤ምክንያቱም ይሖዋን ችላ ብለዋል። |
ምንዝር፣ ያረጀ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ፣ሰው ትክክል የሆነውን ነገር ለመፈጸም ያለውን ልባዊ ፍላጎት ያጠፋሉ። |
ሕዝቤ ከእንጨት የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን ያማክራሉ፤በትራቸው የሚላቸውን ነገር ያደርጋሉ፤ምክንያቱም የአመንዝራነት መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል፤በአመንዝራነታቸው የተነሳም ለአምላካቸው ለመገዛት አሻፈረን ይላሉ። |
በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤ደግሞም በኮረብቶች ላይእንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው። ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች ይሆናሉ፤ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። |
ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች በመሆናቸው፣ምራቶቻችሁም በማመንዘራቸው አልቀጣቸውም። ወንዶቹ ከጋለሞታዎች ጋር ተያይዘው ይሄዳሉና፤ከቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪዎችም ጋር መሥዋዕት ያቀርባሉ፤እንዲህ ያለ ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ይጠፋል። |
እስራኤል ሆይ፣ አንቺ ብታመነዝሪምይሁዳ ግን ተመሳሳይ በደል አትፈጽም። ወደ ጊልጋል ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤‘ሕያው ይሖዋን!’ ብላችሁም አትማሉ። |
እስራኤል እንደ እልኸኛ በሬ እልኸኛ ሆናለችና። ታዲያ ይሖዋ እንደ በግ ጠቦት በተንጣለለ የግጦሽ መስክ ያሰማራቸዋል? |
ኤፍሬም ከጣዖቶች ጋር ተቆራኝቷል። በቃ ተዉት! |
መጠጣቸው ሲያልቅሴሰኞች ይሆናሉ። ገዢዎቿም ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ። |
ነፋስ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፤እነሱም ባቀረቧቸው መሥዋዕቶች ያፍራሉ።” |
“ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል። ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል። ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ። |
ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ድርጊቱም ብድራት ይከፍለዋል። |
በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ። |
ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ። ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።” አምላክ በቤቴል አገኘው፤ በዚያም እኛን አነጋገረን፤ |
እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።የመታሰቢያ ስሙ ይሖዋ ነው። |
“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ታማኝ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ምንጊዜም በአምላክህ ተስፋ አድርግ። |
ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤እሱ ማጭበርበር ይወዳል። |
ኤፍሬም ‘በእርግጥ እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤ሀብት አካብቻለሁ። ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል። |
ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ። በተወሰነው ጊዜ እንደነበረው ሁሉ፣እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ። |
ለነቢያቱ ተናገርኩ፤ራእዮቻቸውን አበዛሁ፤በነቢያቱም በኩል ምሳሌዎችን ተናገርኩ። |
በጊልያድ ማታለልና ውሸት አለ። በጊልጋል በሬዎችን ሠውተዋል፤በተጨማሪም መሠዊያዎቻቸው በእርሻ ትልም ላይ እንዳለ የድንጋይ ክምር ናቸው። |
ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፤እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል በዚያ አገለገለ፤ሚስት ለማግኘትም ሲል በግ ጠባቂ ሆነ። |
ይሖዋ በነቢይ አማካኝነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣው፤በነቢይም አማካኝነት ጠበቀው። |
ኤፍሬም ግን እጅግ በደለው፤ደም በማፍሰስ የፈጸመው በደል በላዩ ላይ ይሆናል፤ላመጣበትም ነቀፋ ጌታው ብድራት ይከፍለዋል።” |
“ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤እሱ ቦጫጭቆናል፤ ሆኖም ይፈውሰናል። እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል። |
ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል። በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤እኛም በፊቱ እንኖራለን። |
ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን። የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብወደ እኛ ይመጣል።” |
“ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና። |
ከዚህም የተነሳ በነቢያቴ አማካኝነት እቆራርጣቸዋለሁ፤በአፌም ቃል እገድላቸዋለሁ። በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል። |
ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና። |
እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ። በዚያም እኔን ከዱኝ። |
ጊልያድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ናት፤ከተማዋ በደም ጨቅይታለች። |
የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው። በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና። |
በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ። በዚያ ኤፍሬም ያመነዝራል፤እስራኤል ራሱን አርክሷል። |
በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜመከር ይጠብቅሃል።” |
“ቀንደ መለከት ንፋ! ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለጣሱበይሖዋ ቤት ላይ ጠላት እንደ ንስር ይመጣል። |
‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ። |
እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል። ጠላት ያሳደው። |
እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ። መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም። በገዛ ራሳቸው ላይ ጥፋት ለማምጣትበብራቸውና በወርቃቸው ጣዖቶች ሠሩ። |
ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል። ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል። ንጹሕ መሆን የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው? |
ይህ ከእስራኤል ነውና። የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል። |
ነፋስን ይዘራሉ፤አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። አገዳው፣ የደረሰ ፍሬ የለውም፤እህሉ፣ ዱቄት አላስገኘም። ፍሬ ቢያፈራ እንኳ ባዕዳን ይበሉታል። |
የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ። በብሔራት መካከልማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ። |
ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል። |
ፍቅረኞቻቸውን ያፈሩት ከብሔራት ቢሆንም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ንጉሥና መኳንንት በጫኑባቸው ሸክም የተነሳ ሥቃይ ይደርስባቸዋል። |
ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል። ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል። |
በሕጌ ውስጥ ያለውን አብዛኛውን ነገር ጽፌለታለሁ፤እነሱ ግን እንግዳ ነገር አድርገው ቆጠሩት። |
መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም። በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል። እነሱ ወደ ግብፅ ተመልሰዋል። |
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል። እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።” |
ወደ ፐቱኤል ልጅ፣ ወደ ኢዩኤል የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ |
“እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤የአገሪቱም ነዋሪዎች ሁሉ ልብ በሉ። በእናንተም ዘመን ይሁን በአባቶቻችሁ ዘመንእንዲህ ያለ ነገር ተከስቶ ያውቃል? |
ይህን ለልጆቻችሁ ተናገሩ፤ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፣የእነሱ ልጆች ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ይናገሩ። |
ከአውዳሚ አንበጣ የተረፈውን የአንበጣ መንጋ በላው፤ከአንበጣ መንጋ የተረፈውንም ኩብኩባ በላው፤ከኩብኩባ የተረፈውን ደግሞ የማይጠግብ አንበጣ በላው። |
እናንተ ሰካራሞች ንቁ፤ ደግሞም አልቅሱ! እናንተ የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉጣፋጩ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ላይ ስለተወሰደ ዋይ ዋይ በሉ። |
ኃያል የሆነና የሕዝቡ ብዛት ስፍር ቁጥር የሌለው ብሔር ምድሬን ወሮታልና። ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤ መንገጭላውም የአንበሳ መንገጭላ ነው። |
የወይን ተክሌን አጠፋው፤ የበለስ ዛፌንም ጉቶ አደረገው፤ቅርፊታቸውን ሙልጭ አድርጎ ልጦ ወዲያ ጣላቸው፤በቅርንጫፎቻቸው ላይ አንድም ልጥ አልቀረም። |
ማቅ ለብሳ ለልጅነት ሙሽራዋ እንደምታለቅስ ድንግልዋይ ዋይ በዪ። |
የእህል መባና የመጠጥ መባ ከይሖዋ ቤት ተቋርጧል፤የይሖዋ አገልጋዮች የሆኑት ካህናቱም ሐዘን ላይ ናቸው። |
እርሻው ወድሟል፤ ምድሪቱ አዝናለች፤እህሉ ወድሟልና፤ አዲሱ ወይን ደርቋል፤ ዘይቱም ተሟጧል። |
ገበሬዎች አፍረዋል፤ የወይን አትክልት ሠራተኞች ዋይ ዋይ ይላሉ፤ይህም የሆነው ከስንዴውና ከገብሱ የተነሳ ነው፤የእርሻው መከር ጠፍቷልና። |
ወይኑ ደርቋል፤የበለስ ዛፉም ጠውልጓል። ሮማኑ፣ ዘንባባው፣ ፖሙናበሜዳው ላይ ያለው ዛፍ ሁሉ ደርቋል፤በሕዝቡ መካከል የነበረው ደስታ ወደ ኀፍረት ተለውጧልና። |
እናንተ ካህናት ማቅ ልበሱ፤ ደግሞም ሐዘን ተቀመጡ፤እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ ዋይ ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ፣ ማቅ ለብሳችሁ እደሩ፤ከአምላካችሁ ቤት የእህል መባና የመጠጥ መባ ተቋርጧልና። |
ጾም አውጁ! የተቀደሰ ጉባኤ ጥሩ። ሽማግሌዎቹንና የምድሪቱን ነዋሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ ቤት ሰብስቡ፤እርዳታም ለማግኘት ወደ ይሖዋ ጩኹ። |
ከቀኑ የተነሳ ወዮላችሁ! የይሖዋ ቀን ቀርቧልና፤ሁሉን ከሚችለው አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል! |
ምግብ ከዓይናችን ፊት፣ሐሴትና ደስታም ከአምላካችን ቤት ጠፍቶ የለም? |
ዘሮቹ ከአካፋዎቻቸው ሥር ጠውልገዋል። ጎተራዎቹም ተራቁተዋል። ጎታዎቹ ፈራርሰዋል፤ እህሉ ደርቋልና። |
መንጎቹ እንኳ ሳይቀሩ ያቃስታሉ! ከብቶቹ ግራ ተጋብተው ይቅበዘበዛሉ፤ መሰማሪያ የላቸውምና! የበጎቹም መንጋ ቅጣቱን ይቀበላል። |
ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ፤በምድረ በዳ ያለውን የግጦሽ መሬት እሳት በልቶታልና፤በሜዳ ያሉትንም ዛፎች ሁሉ ነበልባል አቃጥሏቸዋል። |
የዱር አራዊትም እንኳ አንተን በጉጉት ይጠባበቃሉ፤ምክንያቱም የውኃ ጅረቶቹ ደርቀዋል፤በምድረ በዳ ያለውን የግጦሽ መሬትም እሳት በልቶታል።” |
“እነሆ፣ በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜየይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች ስመልስ፣ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.