text stringlengths 4 267 |
|---|
በመቃብር ለመደበቅ ወደ ታች ቢቆፍሩምእጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማያት ቢወጡምከዚያ አወርዳቸዋለሁ። |
ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁምፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ። ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩምበዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ። |
ጠላቶቻቸው ማርከው ቢወስዷቸውበዚያ ሰይፍ አዛለሁ፤ ሰይፉም ይገድላቸዋል፤ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ዓይኔን በእነሱ ላይ አደርጋለሁ። |
ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን ይነካልና፤እሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች። |
‘ደረጃዎቹን በሰማያት የሚሠራው፣ከምድርም በላይ ሕንፃውን የሚገነባው፣ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣ስሙ ይሖዋ ነው።’ |
‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ። ‘እስራኤልን ከግብፅ ምድር፣ ፍልስጤማውያንን ከቀርጤስ፣ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁም?’ |
‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል። ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’ ይላል ይሖዋ። |
‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋናአንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉየእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ። |
“ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉበሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’ |
‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤ |
በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ። |
‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤ኮረብቶችም ሁሉ በወይን ይጥለቀለቃሉ። |
ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤የወይን ተክል ተክለው ወይኑን ይጠጣሉ፤አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’ |
‘በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፤ከሰጠኋቸውም ምድር ላይዳግመኛ አይነቀሉም’ ይላል አምላክህ ይሖዋ።” |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ኖራ ለማግኘት የኤዶምን ንጉሥ አጥንቶች አቃጥሏል። |
በመሆኑም በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ የቀሪዮትንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤ ሞዓብ በትርምስ፣በቀረርቶና በቀንደ መለከት ድምፅ መካከል ይሞታል። |
ገዢውን ከመካከሏ አስወግዳለሁ፤መኳንንቷንም ሁሉ ከእሱ ጋር እገድላለሁ” ይላል ይሖዋ።’ |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የይሁዳ ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም የይሖዋን ሕግ ንቀዋል፤ሥርዓቱንም አልጠበቁም፤ይልቁንም አባቶቻቸው በተከተሉት በዚያው ውሸት ስተዋል። |
በመሆኑም በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤የኢየሩሳሌምንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’ |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦‘ስለ ሦስቱ የእስራኤል ዓመፅ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤ምክንያቱም ጻድቁን ለብር፣ድሃውንም ለጥንድ ጫማ ሲሉ ይሸጣሉ። |
የችግረኞችን ራስ በምድር አፈር ላይ ይረግጣሉ፤የየዋሆችንም መንገድ ይዘጋሉ። አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ግንኙነት በመፈጸምቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ። |
የብድር መያዣ አድርገው በወሰዱት ልብስ ላይ በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤መቀጫ በማስከፈል ያገኙትን የወይን ጠጅ በአማልክታቸው ቤት ይጠጣሉ።’ |
‘ይሁንና ቁመቱ እንደ አርዘ ሊባኖስ፣ ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የሆነውን አሞራዊበፊታቸው ያጠፋሁት እኔ ነኝ፤ከላይ ያለውን ፍሬውንም ሆነ ከታች ያሉትን ሥሮቹን አጠፋሁ። |
ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤የአሞራዊውንም ምድር እንድትወርሱበምድረ በዳ ለ40 ዓመት መራኋችሁ። |
ከልጆቻችሁ መካከል አንዳንዶቹን ነቢያት፣ከወጣቶቻችሁም መካከል አንዳንዶቹን ናዝራውያን አድርጌ አስነሳሁ። የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይህን አላደረግኩም?’ ይላል ይሖዋ። |
‘እናንተ ግን ናዝራውያኑ የወይን ጠጅ እንዲጠጡ ሰጣችኋቸው፤ነቢያቱንም “ትንቢት አትናገሩ” በማለት አዘዛችኋቸው። |
ስለዚህ በታጨደ እህል የተሞላ ጋሪ ከሥሩ ያለውን እንደሚያደቅ፣ባላችሁበት ስፍራ አደቃችኋለሁ። |
ፈጣኑ ሰው የሚሸሽበት ቦታ አያገኝም፤ብርቱ የሆነው ሰው ኃይሉን ይዞ አይቀጥልም፤ተዋጊውም ሕይወቱን አያድንም። |
ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ፈጣኑም ሮጦ አያመልጥም፤ፈረሰኛውም ሕይወቱን አያድንም። |
ከተዋጊዎቹ መካከል እጅግ ደፋር የሆነው እንኳበዚያን ቀን ራቁቱን ይሸሻል’ ይላል ይሖዋ።” |
“የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ እንደ ሙሾ አድርጌ የምናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦ |
‘ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች፤ዳግመኛም አትነሳም። በገዛ ምድሯ ተጥላለች፤የሚያነሳትም የለም።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘አንድ ሺህ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማ መቶ ሰዎች ብቻ ይቀሯታል፤መቶ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማም አሥር ሰዎች ብቻ ይቀሯታል። ይህ በእስራኤል ቤት ላይ ይደርሳል።’ |
“ይሖዋ ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦ ‘እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ። |
ቤቴልን አትፈልጉ፤ወደ ጊልጋል አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ጊልጋል ያለጥርጥር በግዞት ትወሰዳለችና፤ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለች። |
ይሖዋን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤አለዚያ በዮሴፍ ቤት ላይ ቁጣው እንደ እሳት ይነድዳል፤ቤቴልንም ይበላል፤ የሚያጠፋውም አይኖርም። |
እናንተ ፍትሕን ወደ ጭቁኝ ትለውጣላችሁ፤ጽድቅንም ወደ ምድር ትጥላላችሁ። |
የኪማ ኅብረ ከዋክብትንና የከሲል ኅብረ ከዋክብትን የሠራው፣ድቅድቅ ጨለማን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጠው፣ቀኑንም እንደ ሌሊት ጨለማ የሚያደርገው፣ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድየባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣ስሙ ይሖዋ ነው። |
የተመሸጉትን ቦታዎች በማውደም፣ብርቱ በሆነው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል። |
እነሱ በከተማዋ በር ላይ ሆነው የሚወቅሱትን ይጠላሉ፤እውነት የሚናገሩትንም ይጸየፋሉ። |
ድሃው ለእርሻ ቦታው ኪራይ እንዲከፍል ስለምታደርጉ፣እህሉንም በግብር መልክ ስለምትወስዱ፣በተጠረበ ድንጋይ በሠራችሁት ቤት ውስጥ አትኖሩም፤ደግሞም ከተከላችኋቸው ምርጥ የወይን ተክሎች የሚገኘውን የወይን ጠጅ አትጠጡም። |
ዓመፃችሁ ምን ያህል እንደበዛናኃጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ አውቃለሁና፤ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤ጉቦ ትቀበላላችሁ፤በከተማዋም በር ላይ የድሆችን መብት ትነፍጋላችሁ። |
ስለሆነም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች በዚያን ጊዜ ዝም ይላሉ፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና። |
በሕይወት እንድትኖሩመልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ። የሠራዊት አምላክ ይሖዋምእንደተናገራችሁት ከእናንተ ጋር ይሆናል። |
ክፉ የሆነውን ጥሉ፤ መልካም የሆነውንም ውደዱ፤በከተማዋም በር ላይ ፍትሕ እንዲሰፍን አድርጉ። የሠራዊት አምላክ ይሖዋከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’ |
“ስለዚህ ይሖዋ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በየአደባባዩ ዋይታ ይሆናል፤በየመንገዱም ሰዎች “ወዮ! ወዮ!” ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፣አስለቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።’ |
‘በየወይን እርሻውም ዋይታ ይኖራል፤እኔ በመካከልህ አልፋለሁና’ ይላል ይሖዋ። |
‘የይሖዋን ቀን ለሚናፍቁ ወዮላቸው! የይሖዋ ቀን ለእናንተ ምን ያመጣ ይሆን? ያ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም። |
ይህም ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያስደግፍም እባብ እንደሚነድፈው ዓይነት ይሆናል። |
የይሖዋ ቀን ብርሃን የሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆን የለም?ደግሞስ የብርሃን ጸዳል የሌለበት ጨለማ ይሆን የለም? |
በዓሎቻችሁን እጠላለሁ፤ ደግሞም እንቃለሁ፤የተቀደሱ ጉባኤዎቻችሁ መዓዛም ደስ አያሰኘኝም። |
ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የስጦታ መባዎች ብታቀርቡልኝ እንኳእነዚህ መባዎች አያስደስቱኝም፤ለኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡ እንስሳትም በሞገስ ዓይን አልመለከትም። |
የተደበላለቁ መዝሙሮችህን ከእኔ አርቅ፤በባለ አውታር መሣሪያዎች የምትጫወተውንም ዜማ መስማት አልፈልግም። |
ፍትሕ እንደ ውኃ፣ጽድቅም ያለማቋረጥ እንደሚወርድ ጅረት ይፍሰስ። |
የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ በቆያችሁበት ጊዜመሥዋዕትና የስጦታ መባ አቅርባችሁልኝ ነበር? |
አሁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ ንጉሣችሁ የሆነውን የሳኩትን እንዲሁም የኪዋንን ምስሎች፣ይኸውም የአምላካችሁን ኮከብ ተሸክማችሁ ትሄዳላችሁ። |
እኔም ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ በግዞት እንድትወሰዱ አደርጋለሁ’ ይላል ስሙ ይሖዋ የሆነው የሠራዊት አምላክ።” |
“እናንተ በሰማርያ ተራራ ላይ ያላችሁ፣ችግረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ግፍ የምትፈጽሙና ድሆችን የምትጨቁኑ ሴቶች፣ባሎቻችሁንም ‘የምንጠጣው ነገር አምጡልን!’የምትሉ የባሳን ላሞች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ። |
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በቅድስናው ምሏል፤‘“እነሆ፣ እናንተን በሜንጦ፣ከእናንተ የቀሩትንም በመንጠቆ የሚያነሳበት ቀን እየመጣባችሁ ነው። |
እያንዳንዳችሁ ከፊታችሁ በምታገኟቸው፣ በቅጥሩ ላይ ባሉት ክፍተቶች በኩል ትወጣላችሁ፤ወደ ሃርሞንም ትጣላላችሁ” ይላል ይሖዋ።’ |
‘ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአት ሥሩ፤ወደ ጊልጋልም ሄዳችሁ ብዙ ኃጢአት ፈጽሙ! በማለዳ መሥዋዕቶቻችሁን፣በሦስተኛውም ቀን አሥራቶቻችሁን አቅርቡ። |
እርሾ ያለበትን ዳቦ የሚቃጠል የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትንም መባ በአዋጅ አስነግሩ! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
‘እኔም በከተሞቻችሁ ሁሉ አፋችሁን ባዶ አደረግኩት፤በቤታችሁም ሁሉ የምትበሉት ነገር አሳጣኋችሁ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
‘በተጨማሪም መከር ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኳችሁ፤በአንዱ ከተማ ዝናብ እንዲዘንብ ሳደርግ በሌላው ከተማ ግን እንዳይዘንብ አደረግኩ። አንዱ እርሻ ዝናብ ያገኛል፤ዝናብ ያላገኘው ሌላው እርሻ ግን ይደርቃል። |
በሁለት ወይም በሦስት ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ውኃ ለመጠጣት ወደ አንዲት ከተማ እያዘገሙ ሄዱ፤ይሁንና ጥማቸውን ማርካት አልቻሉም፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
‘በሚያቃጥል ሙቀትና በዋግ መታኋችሁ። የአትክልት ስፍራዎቻችሁንና የወይን እርሻዎቻችሁን አበዛችሁ፤ይሁንና የበለስ ዛፎቻችሁንና የወይራ ዛፎቻችሁን አንበጣ ይበላቸዋል፤ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
‘በግብፅ ላይ የደረሰውን ዓይነት ቸነፈር ሰደድኩባችሁ። ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልኩ፤ ፈረሶቻችሁንም ማረክሁ። የሰፈሮቻችሁ ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግኩ፤እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
‘ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጥኳቸው ሁሉምድራችሁን ገለበጥኩ። እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ጉማጅ ነበራችሁ፤ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
ስለዚህ እስራኤል ሆይ፣ እንዲሁ አደርግብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ይህን ነገር ስለማደርግብህአምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ። |
እነሆ፣ ተራሮችን የሠራው፣ ነፋስን የፈጠረው እሱ ነው፤ሐሳቡ ምን እንደሆነ ለሰው ይነግረዋል፤የንጋት ብርሃንን ያጨልማል፤በምድር ላይ ያሉ ከፍ ያሉ ስፍራዎችን ይረግጣል፤ስሙ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።” |
“በጽዮን በራሳቸው ተማምነው የሚኖሩ፣በሰማርያም ተራራ ያለስጋት የተቀመጡ ወዮላቸው!እነሱ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዋነኛ በሆነው ብሔር ውስጥ የጎላ ስፍራ ያላቸው ናቸው፤ የእስራኤል ቤትም ወደ እነሱ ይመጣል። |
ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ። ከዚያም ተነስታችሁ ወደ ታላቋ ሃማት ሂዱ፤የፍልስጤማውያን ከተማ ወደሆነችውም ወደ ጌት ውረዱ። እነሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉ?የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣል? |
የጥፋትን ቀን ከአእምሯችሁ አውጥታችሁየዓመፅ አገዛዝ እንዲሰፍን ታደርጋላችሁ? |
የመንጋውን ጠቦቶች እንዲሁም የሰቡ ጥጃዎችን እየበሉከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ይተኛሉ፤ በድንክ አልጋም ላይ ይንጋለላሉ፤ |
በገና እየተጫወቱ የመጣላቸውን ዘፈን ያቀናብራሉ፤እንደ ዳዊትም የሙዚቃ መሣሪያዎች ይፈለስፋሉ፤ |
በትላልቅ ጽዋዎች የወይን ጠጅ ሞልተው ይጠጣሉ፤ምርጥ የሆኑ ዘይቶችም ይቀባሉ። በዮሴፍ ላይ ስለደረሰው መቅሰፍት ግን ግድ የላቸውም። |
ስለዚህ እነሱ በግዞት ከሚወሰዱት መካከል የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ፤ተንጋለው በመዝናናት የሚያሳልፉት ጊዜም ያበቃል። |
‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በራሱ ምሏል’ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘“የያዕቆብን ኩራት እጸየፋለሁ፤የማይደፈሩ ማማዎቹን እጠላለሁ፤ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ። |
“‘“በአንድ ቤት ውስጥ አሥር ሰዎች ቢቀሩ እነሱም ይሞታሉ። |
እነሱን አንድ በአንድ አውጥቶ ለማቃጠል አንድ ዘመድ ይመጣል። አጥንቶቻቸውን ከቤት ውስጥ ያወጣል፤ ከዚያም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ላለ ሰው ‘ከአንተ ጋር የቀሩ ሌሎች ሰዎች አሉ?’ ይለዋል። ሰውየውም ‘ማንም የለም!’ ይላል። ከዚያም ‘ዝም በል! ይህ የይሖዋ ስም የሚጠራበት ጊዜ አይደለም’ ይላል።” |
ትእዛዝ የሰጠው ይሖዋ ነውና፤እሱም ትልቁን ቤት አመድ፣ትንሹንም ቤት የፍርስራሽ ክምር ያደርጋል። |
ፈረሶች በቋጥኝ ላይ ይሮጣሉ?ሰውስ እዚያ ላይ በከብት ያርሳል? እናንተ ፍትሕን ወደ መርዛማ ተክል፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ ጭቁኝ ለውጣችኋልና። |
እናንተ ከንቱ በሆነ ነገር ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ደግሞም “በራሳችን ብርታት ኃይለኞች ሆነን የለም?” ትላላችሁ። |
ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ አንድ ብሔር አመጣለሁ’ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤‘እነሱም ከሌቦሃማት አንስቶ እስከ አረባ ደረቅ ወንዝ ድረስ ይጨቁኗችኋል።’” |
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ፣ የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት ነበር። |
ከዚያም “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት” ብዬ መለስኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሷል። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅር አልላቸውም። |
‘በዚያን ቀን የቤተ መቅደሱ መዝሙሮች ወደ ዋይታ ይቀየራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘በየቦታው የተጣሉ ብዙ አስከሬኖች ይኖራሉ፤ ዝምታ ይስፈን!’ |
እናንተ ድሆችን የምትረጋግጡ፣በምድሪቱ ላይ ያሉትንም የዋሆች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤ |
እንዲህም ትላላችሁ፦ ‘እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው የሚያልፈው መቼ ነው?አዝመራችንንስ መሸጥ እንድንችል ሰንበት የሚያልፈው መቼ ነው? ያን ጊዜ በሐሰተኛ ሚዛን ለማጭበርበርየኢፍ መስፈሪያውን ማሳነስ፣ሰቅሉንም ከፍ ማድረግ እንችላለን፤ |
ደግሞም ችግረኛውን በብር፣ድሃውንም በጥንድ ጫማ ዋጋ እንገዛለን፤መናኛውንም እህል መሸጥ እንችላለን።’ |
የያዕቆብ ክብር የሆነው ይሖዋ በራሱ ምሏል፦‘ሥራቸውን ሁሉ ፈጽሞ አልረሳም። |
ከዚህ የተነሳ አገሪቱ ትሸበራለች፤በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ። ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ አትነሳም?በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ወደ ላይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ ወደ ታች አትወርድም?’ |
‘በዚያ ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣‘ፀሐይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ብሩህ በሆነ ቀንም ምድሪቱን አጨልማለሁ። |
በዓሎቻችሁን ወደ ሐዘን፣መዝሙሮቻችሁንም ሁሉ ወደ ሙሾ እለውጣለሁ። ወገብን ሁሉ ማቅ አስታጥቃለሁ፤ ራስንም ሁሉ እመልጣለሁ፤ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሳሉ፤ፍጻሜውም እንደ መራራ ቀን ይሆናል።’ |
‘እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ የምሰድበት ጊዜ ይመጣል’ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤‘ረሃቡ የይሖዋን ቃል የመስማት ረሃብ እንጂምግብን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም። |
እነሱ ከባሕር ወደ ባሕር፣ከሰሜንም ወደ ምሥራቅ ይባዝናሉ። የይሖዋን ቃል ፍለጋ በየቦታው ይንከራተታሉ፤ ሆኖም አያገኙትም። |
በዚያ ቀን፣ ውብ የሆኑት ደናግልናወጣት ወንዶች ከውኃ ጥም የተነሳ ራሳቸውን ይስታሉ፤ |
በሰማርያ በደል የሚምሉደግሞም “ዳን ሆይ፣ ሕያው በሆነው በአምላክህ እምላለሁ!” እንዲሁም “ሕያው በሆነው በቤርሳቤህ መንገድ እምላለሁ!” የሚሉ ሰዎች፣ ይወድቃሉ፤ ዳግመኛም አይነሱም።’” |
የአብድዩ ራእይ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ “ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦ ‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’” |
“እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር አድርጌሃለሁ፤አንተ እጅግ ተንቀሃል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.