text stringlengths 4 267 |
|---|
የርስቱን ቀሪዎች ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና። |
ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል። ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ። |
በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ። |
እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችናየእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ። ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም? |
ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ። |
የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ። |
በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱ ግን አይመልስላቸውም። ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል። |
ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣በጥርሳቸው ሲነክሱ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል።” |
‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤ ራእይም አታዩም፤ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም። ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል። |
ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤ሟርተኞችም ይዋረዳሉ። ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖርሁሉም አፋቸውን ይሸፍናሉ።’” |
እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግርበይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ። |
ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤ |
ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ። |
መሪዎቿ በጉቦ ይፈርዳሉ፤ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤ነቢያቷም በገንዘብ ያሟርታሉ። ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም? ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም” እያሉ በይሖዋ ይመካሉ። |
ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤የቤቱም ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ይሆናል። |
“መጥፎ ነገር ለሚሸርቡናበአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው። |
እርሻን ይመኛሉ፤ ነጥቀውም ይይዙታል፤ቤቶችንም ይመኛሉ፤ ደግሞም ይወስዳሉ፤የሰውን ቤት፣የሰውንም ርስት አታለው ይወስዳሉ። |
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል።” ‘እነሆ፣ በዚህ ወገን ላይ ጥፋት ላመጣ አስቤአለሁ፤ እናንተም ከዚህ ጥፋት አታመልጡም። ከእንግዲህ ወዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ ይህ የጥፋት ጊዜ ነውና። |
በዚያም ቀን ሰዎች እናንተን አስመልክተው ምሳሌ ይናገራሉ፤በእናንተም የተነሳ አምርረው ያለቅሳሉ። እንዲህ ይላሉ፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! የሕዝቤን ድርሻ ለሌሎች ሰጥቷል፤ ከእኔም ወስዶታል! እርሻዎቻችንን ለከዳተኛው ይሰጣል።” |
ስለዚህ በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ፣ምድሪቷን ለማከፋፈል በገመድ የሚለካ ሰው አይኖርህም። |
“አትስበኩ!” ብለው ይሰብካሉ፤“እነዚህን ነገሮች መስበክ አይገባቸውም፤ውርደት አይደርስብንም!” |
የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ “የይሖዋ መንፈስ አይታገሥም? እነዚህንስ ነገሮች ያደረገው እሱ ነው?” ሲባል ሰምተሃል? ቀና በሆነ መንገድ ለሚሄዱ የገዛ ቃሌ መልካም ነገር አያስገኝም? |
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የገዛ ሕዝቤ ጠላት ሆኖ ተነስቷል። ከጦርነት እንደሚመለሱ ሰዎች በልበ ሙሉነት ከሚያልፉት ላይየሚያምረውን ጌጥ ከልብሱ ጋር በይፋ ገፈፋችሁ። |
የሕዝቤን ሴቶች ከሚያምረው ቤታቸው አፈናቀላችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ። |
ተነሱና ከዚህ ሂዱ፤ ይህ የማረፊያ ቦታ አይደለምና። ከርኩሰት የተነሳ ጥፋት ይመጣል፤ ጥፋቱም ከባድ ነው። |
አንድ ሰው ነፋስንና ማታለያን ተከትሎ ቢሄድና “ስለ ወይን ጠጅና ስለ መጠጥ እሰብክላችኋለሁ” ብሎ ውሸት ቢናገር ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ሰባኪ ይሆናል! |
ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ። በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’ |
የሚሰብረውም ከፊታቸው ይሄዳል፤እነሱም ሰብረው በበሩ በኩል ያልፋሉ፤ በዚያም ወጥተው ይሄዳሉ። ንጉሣቸው በፊታቸው ያልፋል፤ይሖዋም ከፊታቸው ይሄዳል።” |
“አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል። የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል። |
ከይሁዳ አእላፋት መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል። |
ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ። |
እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል። እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና። |
እሱም ሰላም ያመጣል። አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠበእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን እናስነሳበታለን። |
እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤የናምሩድንም ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል። |
የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ። |
በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም። |
እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።” |
“በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ። |
በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ። |
ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም አስማተኛ በመካከልህ አይኖርም። |
የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም። |
የማምለኪያ ግንዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፤ከተሞችህንም እደመስሳለሁ። |
ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።” |
በዘመኑ መጨረሻየይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ። |
ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ። እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። |
እሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤በሩቅ ካሉ ኃያላን ብሔራት ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል። እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም። |
እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና። |
ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን። |
“በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“የሚያነክሰውን እሰበስባለሁ፤ደግሞም የተበተኑትንናያንገላታኋቸውን ሰዎች አንድ ላይ እሰበስባለሁ። |
የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት አደርጋለሁ፤ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። |
አንተም የመንጋው ማማ፣የጽዮን ሴት ልጅ ጉብታ ሆይ፣አንተ ወዳለህበት ይመለሳል፤ አዎ፣ የመጀመሪያው ግዛትህ፣የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለሳል። |
አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽም?ወይስ አማካሪሽ ጠፍቷል?ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት የምትሠቃዪው ለዚህ ነው? |
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና። እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤በዚያም ይታደግሻል፤በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል። |
አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ። |
ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤ዓላማውንም አይረዱም፤እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና። |
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነስተሽ እህሉን ውቂ፤ቀንድሽን ወደ ብረት፣ሰኮናሽንም ወደ መዳብ እለውጣለሁና፤አንቺም ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ። በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።” |
ይሖዋ የሚለውን እባካችሁ ስሙ። ተነሱ፤ በተራሮች ፊት ሙግታችሁን አቅርቡ፤ኮረብቶችም ቃላችሁን ይስሙ። |
ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ጽኑ የምድር መሠረቶች፣የይሖዋን ሙግት ስሙ፤ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር ሙግት አለውና፤ከእስራኤልም ጋር ይከራከራል፦ |
“ሕዝቤ ሆይ፣ ምን ያደረግኩህ ነገር አለ? ያደከምኩህስ ምን አድርጌ ነው? እስቲ መሥክርብኝ። |
ከግብፅ ምድር አወጣሁህ፤ከባርነትም ቤት ዋጀሁህ፤ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን በፊትህ ላክሁ። |
ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያሴረብህን ነገር፣የቢዖር ልጅ በለዓምም የሰጠውን መልስ እባክህ አስታውስ፤የይሖዋን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድከሺቲም እስከ ጊልጋል ድረስ የሆነውን ነገር አስታውስ።” |
በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ? ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችናየአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ? |
ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል? ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ? |
ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣ ታማኝነትን እንድትወድናልክህን አውቀህ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው! |
የይሖዋ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል፤ጥበበኞች ስምህን ይፈራሉ። የበትሩን ድምፅና ቅጣቱን የወሰነውን ስሙ። |
ክፉ በሆነ ሰው ቤት፣ በክፋት የተገኘ ሀብትእንዲሁም አስጸያፊ የሆነ ጎዶሎ የኢፍ መስፈሪያ አሁንም አለ? |
አባይ ሚዛንና የተዛቡ የድንጋይ መለኪያዎች የያዘ ከረጢት እየተጠቀምኩንጹሕ ሥነ ምግባር ሊኖረኝ ይችላል? |
ባለጸጎቿ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ነዋሪዎቿም ውሸት ይናገራሉ፤ምላሳቸው በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው። |
“ስለዚህ መትቼ አቆስልሃለሁ፤ከኃጢአትህ የተነሳ አጠፋሃለሁ። |
ትበላለህ፤ ግን አትጠግብም፤ሆድህም ባዶ ይሆናል። የምትወስዳቸውን ነገሮች ጠብቀህ ማቆየት አትችልም፤ጠብቀህ ያቆየኸውንም ነገር ሁሉ ለሰይፍ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። |
ዘር ትዘራለህ፤ ሆኖም የምታጭደው ነገር አይኖርም። የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ሆኖም ዘይቱን አትጠቀምበትም፤ደግሞም አዲስ ወይን ትጨምቃለህ፤ ሆኖም የወይን ጠጅ አትጠጣም። |
የኦምሪን ደንቦችና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ትከተላላችሁና፤ምክራቸውንም ተከትላችሁ ትሄዳላችሁ። ስለዚህ አንተን መቀጣጫ፣ነዋሪዎቿንም ማፏጫ አደርጋለሁ፤የሰዎችንም ፌዝ ትሸከማላችሁ።” |
በነነዌ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፦ |
ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግና የሚበቀል አምላክ ነው፤ይሖዋ ይበቀላል፤ ቁጣውንም ለመግለጽ ዝግጁ ነው። ይሖዋ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ለጠላቶቹም ቁጣ ያከማቻል። |
ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ይሁንና ይሖዋ ተገቢውን ቅጣት ከመስጠት ፈጽሞ ወደኋላ አይልም። መንገዱ በአደገኛ ነፋስና በወጀብ ውስጥ ነው፤ደመናት ከእግሩ በታች እንዳለ አቧራ ናቸው። |
ባሕሩን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ወንዞቹንም በሙሉ ያደርቃቸዋል። ባሳንና ቀርሜሎስ ይጠወልጋሉ፤የሊባኖስ አበባዎችም ይጠወልጋሉ። |
ከእሱ የተነሳ ተራሮች ይንቀጠቀጣሉ፤ኮረብቶችም ይቀልጣሉ። ከፊቱም የተነሳ ምድር፣የብስና በላዩ የሚኖሩት ሁሉ ይናወጣሉ። |
በቁጣው ፊት ማን ሊቆም ይችላል? የንዴቱን ትኩሳት ሊቋቋም የሚችልስ ማን ነው? ቁጣው እንደ እሳት ይፈስሳል፤ዓለቶችም ከእሱ የተነሳ ይፈረካከሳሉ። |
ይሖዋ ጥሩ ነው፤ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው። እሱን መጠጊያ ማድረግ የሚፈልጉትን ያውቃል። |
ጠራርጎ በሚወስድ ጎርፍ ስፍራዋን ፈጽሞ ያጠፋል፤ጠላቶቹንም ጨለማ ያሳድዳቸዋል። |
በይሖዋ ላይ የምታሴሩት ምንድን ነው? እሱ ፈጽሞ ያጠፋል። ጭንቀት ዳግመኛ አይመጣም። |
እርስ በርሳቸው እንደ እሾህ ተጠላልፈዋልና፤መጠጥ ጠጥተው እንደሰከሩ ሰዎች ናቸው፤ሆኖም እንደደረቀ ገለባ እሳት ይበላቸዋል። |
በይሖዋ ላይ ክፉ ነገር የሚያሴር፣ከንቱ ምክርም የሚሰጥ ከመካከልሽ ይወጣል። |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም እንኳ የተሟላ ኃይል ያላቸውና ብዙዎች ቢሆኑምይቆረጣሉ፤ ደግሞም ይጠፋሉ። መከራ አሳይቼሃለሁ፤ ከዚያ በኋላ ግን መከራ አላመጣብህም። |
አሁንም ቀንበሩን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤እስራትህንም እበጥሳለሁ። |
ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ሲል አዟል፦‘ከእንግዲህ ስምህን የሚያስጠራ አይኖርም። የተቀረጹትን ምስሎችና ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች ከአማልክትህ ቤት አስወግዳለሁ። የተናቅክ ስለሆንክ መቃብር አዘጋጅልሃለሁ።’ |
እነሆ ምሥራች ይዞ የሚመጣ፣ሰላምንም የሚያውጅ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው። ይሁዳ ሆይ፣ በዓሎችሽን አክብሪ፤ ስእለትሽን ፈጽሚ፤ከእንግዲህ ወዲህ የማይረባ ሰው በመካከልሽ አያልፍምና። እንዲህ ያለው ሰው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል።” |
ለደም አፍሳሿ ከተማ ወዮላት! በማታለልና በዝርፊያ የተሞላች ናት። ከማደን ቦዝና አታውቅም! |
የአለንጋ ድምፅና የመንኮራኩር ኳኳቴ ይሰማል፤ፈረሶች ሲጋልቡና ሠረገሎች ሲፈተለኩ ይታያል። |
ፈረስ ጋላቢው ይጋልባል፤ ሰይፉ ያንጸባርቃል፤ ጦሩ ያብረቀርቃል፤የተገደሉት በጣም ብዙ ናቸው፤ የአስከሬን ክምር ይታያል፤ሬሳው ስፍር ቁጥር የለውም። አስከሬኖቹም ያደናቅፏቸዋል። |
ይህ የሆነው ዝሙት አዳሪዋ በምትፈጽመው በርካታ የአመንዝራነት ተግባር የተነሳ ነው፤እሷ ብሔራትን በምንዝሯ፣ ወገኖችንም በጥንቆላዋ የምታጠምድ፣የምታምርና የምትማርክ እንዲሁም በጥንቆላ የተካነች ናት። |
“እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤“ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ ድረስ እገልበዋለሁ፤ብሔራትም እርቃንሽን፣መንግሥታትም ነውርሽን እንዲያዩ አደርጋለሁ። |
ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤የተናቅሽ አደርግሻለሁ፤ማላገጫም እንድትሆኚ አደርጋለሁ። |
አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች! የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል። አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ? |
አንቺ በአባይ የመስኖ ቦዮች አጠገብ ከነበረችው ከኖአሞን ትሻያለሽ? እሷ በውኃ የተከበበች ነበረች፤ባሕሩም ሀብት ያስገኝላት፣ እንደ ቅጥርም ሆኖ ያገለግላት ነበር። |
ኢትዮጵያና ግብፅ ገደብ የለሽ የኃይል ምንጮቿ ነበሩ። ፑጥና ሊቢያውያን ረዳቶቿ ነበሩ። |
ይሁንና እሷም እንኳ በግዞት ተወሰደች፤ተማርካም ሄደች። ልጆቿም በየመንገዱ ማዕዘን ተፈጠፈጡ። በተከበሩ ሰዎቿ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ታላላቅ ሰዎቿም ሁሉ በእግር ብረት ታሰሩ። |
አንቺም ትሰክሪያለሽ፤ደግሞም ትሰወሪያለሽ። ከጠላት የምትሸሸጊበት ቦታ ትፈልጊያለሽ። |
ምሽጎችሽ ሁሉ የመጀመሪያዎቹን የበሰሉ ፍሬዎች እንደያዙ የበለስ ዛፎች ናቸው፤ዛፎቹ ከተነቀነቁ ፍሬዎቹ ረግፈው በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃሉ። |
እነሆ፣ ወታደሮችሽ በመካከልሽ እንዳሉ ሴቶች ናቸው። የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ይከፈታሉ። የበሮችሽን መቀርቀሪያዎች እሳት ይበላቸዋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.