text stringlengths 4 267 |
|---|
ሌሎቹ ደግሞ ጥሩ አፈር ላይ ወድቀው ፍሬ ማፍራት ጀመሩ፤ አንዱ 100፣ አንዱ 60፣ ሌላውም 30 እጥፍ አፈራ። |
ጆሮ ያለው ይስማ።” |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው “በምሳሌ የምትነግራቸው ለምንድን ነው?” አሉት። |
እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ቅዱስ ሚስጥሮች የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ ለእነሱ ግን አልተሰጣቸውም። |
ላለው ሁሉ ይጨመርለታል፤ ደግሞም ይትረፈረፍለታል፤ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። |
በምሳሌ የምነግራቸው ለዚህ ነው፤ ቢያዩም የሚያዩት እንዲያው በከንቱ ነውና፤ ቢሰሙም የሚሰሙት እንዲያው በከንቱ ነው፤ ትርጉሙንም አያስተውሉም። |
ደግሞም የኢሳይያስ ትንቢት በእነሱ ላይ እየተፈጸመ ነው። ትንቢቱ እንዲህ ይላል፦ ‘መስማቱን ትሰማላችሁ ግን በፍጹም ትርጉሙን አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ ግን በፍጹም ልብ አትሉም። |
ምክንያቱም በዓይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው እንዲሁም በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል፤ በጆሯቸው ሰምተው ምላሽ አልሰጡም፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።’ |
“እናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ፣ ጆሮዎቻችሁም ስለሚሰሙ ደስተኞች ናችሁ። |
እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ግን አላዩም፤ አሁን የምትሰሙትን ነገር ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ግን አልሰሙም። |
“እንግዲህ እናንተ ዘር የዘራውን ሰው ምሳሌ ስሙ። |
አንድ ሰው የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውል ከሆነ ክፉው መጥቶ በልቡ ውስጥ የተዘራውን ዘር ይነጥቀዋል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ዘር ይህ ነው። |
በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን ሲሰማ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበል ሰው ነው። |
ሆኖም ቃሉ በውስጡ ሥር ስለማይሰድ የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ በቃሉ የተነሳም መከራ ወይም ስደት ሲደርስበት ወዲያው ይሰናከላል። |
በእሾህ መካከል የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማ ነው፤ ይሁንና የዚህ ሥርዓት ጭንቀት እንዲሁም ሀብት ያለው የማታለል ኃይል ቃሉን ያንቀዋል፤ የማያፈራም ይሆናል። |
በጥሩ አፈር ላይ የተዘራው ደግሞ ቃሉን የሚሰማና የሚያስተውል ነው፤ ፍሬም ያፈራል፤ አንዱ 100፣ አንዱም 60፣ ሌላውም 30 እጥፍ ይሰጣል።” |
ደግሞም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር ከዘራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። |
ነገር ግን ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው ላይ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። |
እህሉ አድጎ ፍሬ ባፈራ ጊዜ እንክርዳዱም አብሮ ታየ። |
ስለሆነም የቤቱ ጌታ ባሪያዎች፣ ወደ እሱ ቀርበው ‘ጌታ ሆይ፣ በእርሻህ ላይ የዘራኸው ጥሩ ዘር አልነበረም እንዴ? ታዲያ እንክርዳዱ ከየት መጣ?’ አሉት። |
እሱም ‘ይህን ያደረገው ጠላት ነው’ አላቸው። ባሪያዎቹም ‘ታዲያ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህ?’ አሉት። |
እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ‘እንክርዳዱን ስትነቅሉ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉ ስለምትችሉ ተዉት። |
እስከ መከር ጊዜ ድረስ አብረው ይደጉ፤ በመከር ወቅት አጫጆቹን፣ በመጀመሪያ እንክርዳዱን ሰብስቡና እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩ፤ ከዚያም ስንዴውን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡ እላቸዋለሁ።’” |
ደግሞም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው ወስዶ እርሻው ውስጥ ከተከላት አንዲት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤ |
የሰናፍጭ ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ያነሰች ብትሆንም ስታድግ ግን ከተክሎች ሁሉ በልጣ ዛፍ ስለምትሆን የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቿ ላይ መስፈሪያ ያገኛሉ።” |
አሁንም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት አንዲት ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ ከሦስት ትላልቅ መስፈሪያ ዱቄት ጋር ከደባለቀችው እርሾ ጋር ይመሳሰላል።” |
ኢየሱስ ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ። እንዲያውም ያለምሳሌ አይነግራቸውም ነበር፤ |
ይህም የሆነው “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከምሥረታው ጊዜ አንስቶ የተሰወሩትን ነገሮች አውጃለሁ” ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው። |
ከዚያም ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “በእርሻው ውስጥ ስላለው እንክርዳድ የተናገርከውን ምሳሌ አብራራልን” አሉት። |
እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ጥሩውን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ |
እርሻው ዓለም ነው። ጥሩው ዘር ደግሞ የመንግሥቱ ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱ ግን የክፉው ልጆች ናቸው፤ |
እንክርዳዱን የዘራው ጠላት፣ ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ሲሆን አጫጆቹ ደግሞ መላእክት ናቸው። |
በመሆኑም እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል ሁሉ በዚህ ሥርዓት መደምደሚያም እንዲሁ ይሆናል። |
የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነሱም እንቅፋት የሚፈጥሩትን ነገሮች ሁሉና ዓመፅ የሚፈጽሙትን ሰዎች ከመንግሥቱ ይለቅማሉ፤ |
ወደ እሳታማ እቶንም ይጥሏቸዋል። በዚያም ያለቅሳሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ። |
በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ። ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ። |
“መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ ከተደበቀ ውድ ሀብት ጋር ይመሳሰላል፤ አንድ ሰው ባገኘው ጊዜ ሸሸገው፤ ከመደሰቱም የተነሳ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ እርሻውን ገዛው። |
“በተጨማሪም መንግሥተ ሰማያት ጥሩ ዕንቁ ከሚፈልግ ተጓዥ ነጋዴ ጋር ይመሳሰላል። |
ከፍተኛ ዋጋ ያለው አንድ ዕንቁ ባገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ወዲያውኑ በመሸጥ ዕንቁውን ገዛው። |
“ደግሞም መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር ተጥሎ የተለያየ ዓይነት ዓሣ ከሰበሰበ መረብ ጋር ይመሳሰላል። |
መረቡ በሞላ ጊዜ ወደ ባሕሩ ዳር ጎትተው አወጡት፤ ከዚያም ተቀምጠው ጥሩ ጥሩውን እየለዩ በዕቃ ውስጥ አስቀመጡ፤ መጥፎ መጥፎውን ግን ጣሉት። |
በዚህ ሥርዓት መደምደሚያም እንደዚሁ ይሆናል። መላእክት ተልከው ክፉዎችን ከጻድቃን ይለያሉ፤ |
ወደ እሳታማ እቶንም ይጥሏቸዋል። በዚያም ያለቅሳሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ። |
እሱም “የዚህ ሁሉ ትርጉም ገብቷችኋል?” አላቸው። እነሱም “አዎ” አሉት። |
ከዚያም ኢየሱስ “እንደዚያ ከሆነ፣ ስለ መንግሥተ ሰማያት የተማረ ማንኛውም የሕዝብ አስተማሪ ከከበረ ሀብት ማከማቻው አዲስና አሮጌ ዕቃ ከሚያወጣ የቤት ጌታ ጋር ይመሳሰላል” አላቸው። |
ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች ተናግሮ ሲጨርስ ከዚያ ስፍራ ተነስቶ ሄደ። |
ወደ ትውልድ አገሩ ከመጣ በኋላ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ጀመር፤ ሰዎቹም ተገርመው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ተአምራት የማድረግ ችሎታ ከየት አገኘ? |
ይህ የአናጺው ልጅ አይደለም? እናቱስ ማርያም አይደለችም? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉም? |
እህቶቹስ ሁሉ የሚኖሩት ከእኛ ጋር አይደለም? ታዲያ ይህን ሁሉ ከየት አገኘው?” |
ከዚህም የተነሳ ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን “ነቢይ በገዛ አገሩና በገዛ ቤቱ ካልሆነ በስተቀር በሌላ ቦታ ሁሉ ይከበራል” አላቸው። |
በእሱ ባለማመናቸው በዚያ ብዙ ተአምራት አልፈጸመም። |
ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረቡና በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ወደ ቤተፋጌ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ |
እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ እዚያ እንደደረሳችሁም አንዲት የታሰረች አህያ ከነውርንጭላዋ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው። |
ማንም ሰው ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ይልካቸዋል።” |
ይህም የሆነው ነቢዩ እንዲህ ብሎ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፦ |
“ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፦ ‘እነሆ ንጉሥሽ ገር ሆኖ በአህያ፣ አዎ በአህያይቱ ግልገል በውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።’” |
ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። |
አህያይቱንና ውርንጭላዋን አምጥተው መደረቢያዎቻቸውን በላያቸው ላይ አደረጉ፤ እሱም ተቀመጠባቸው። |
ከሕዝቡ መካከል አብዛኞቹ መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ ከዛፎች ላይ ቅርንጫፎች እየቆረጡ በመንገዱ ላይ ያነጥፉ ነበር። |
በተጨማሪም ከፊት ከፊቱ የሚሄደውና ከኋላው የሚከተለው ሕዝብ “የዳዊትን ልጅ እንድታድነው እንለምንሃለን! በይሖዋ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! በሰማይ የምትኖረው ሆይ፣ እንድታድነው እንለምንሃለን!” ብሎ ይጮኽ ነበር። |
ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም “ይህ ሰው ማን ነው?” በማለት መላዋ ከተማ ታወከች። |
ሕዝቡም “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው!” ይል ነበር። |
ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ በቤተ መቅደሱ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን መቀመጫዎችም ገለባበጠ። |
እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አድርጋችሁታል።” |
ቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዳለም ዓይነ ስውሮችና አንካሶች ወደ እሱ መጡ፤ እሱም ፈወሳቸው። |
የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ያደረጋቸውን አስደናቂ ነገሮች እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ “የዳዊትን ልጅ እንድታድነው እንለምንሃለን!” እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ ተቆጥተው |
“እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህ?” አሉት። ኢየሱስም “አዎ እሰማለሁ። ‘ከልጆችና ከሕፃናት አፍ ምስጋና አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁም?” አላቸው። |
ከዚያም ትቷቸው ከከተማዋ ከወጣ በኋላ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ እዚያም አደረ። |
በማለዳም ወደ ከተማዋ እየተመለሰ ሳለ ተራበ። |
በመንገድ ዳር አንድ የበለስ ዛፍ አየና ወደ እሷ ሄደ፤ ሆኖም ከቅጠል በቀር ምንም ስላላገኘባት “ከእንግዲህ ወዲህ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስ ዛፏም ወዲያውኑ ደረቀች። |
ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው “የበለስ ዛፏ እንዲህ በአንዴ ልትደርቅ የቻለችው እንዴት ነው?” አሉ። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ እኔ በበለስ ዛፏ ላይ ያደረግኩትን ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት እንኳ ይሆንላችኋል። |
እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትጠይቁትን ነገር ሁሉ ታገኛላችሁ።” |
ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እያስተማረ ሳለ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ። መልሱን ከነገራችሁኝ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፦ |
ዮሐንስ እንዲያጠምቅ ሥልጣን የሰጠው ማን ነው? አምላክ ነው ወይስ ሰው?” እነሱ ግን እርስ በርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ጀመር፦ “‘አምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ |
‘ሰው’ ብንል ደግሞ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ስለሚያየው ሕዝቡን እንፈራለን።” |
ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት። እሱ ደግሞ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም። |
“ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ ‘ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ እርሻ ሄደህ ሥራ’ አለው። |
ልጁም መልሶ ‘አልሄድም’ አለው፤ በኋላ ግን ጸጸተውና ሄደ። |
ሁለተኛውንም ቀርቦ እንደዚሁ አለው። ልጁም መልሶ ‘እሺ አባዬ፣ እሄዳለሁ’ አለው፤ ግን አልሄደም። |
ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነሱም “የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ዝሙት አዳሪዎች ወደ አምላክ መንግሥት በመግባት ረገድ ይቀድሟችኋል። |
ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ መጣ፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም። ይሁን እንጂ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ዝሙት አዳሪዎች አመኑት፤ እናንተ ይህን አይታችሁም እንኳ ጸጸት ተሰምቷችሁ እሱን ለማመን አልፈለጋችሁም። |
“ሌላም ምሳሌ ስሙ፦ የወይን እርሻ ያለማ አንድ ባለ ርስት ነበር፤ ዙሪያውንም አጠረው፤ በዚያም የወይን መጭመቂያ ቆፈረ እንዲሁም ማማ ሠራ፤ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። |
ፍሬው የሚሰበሰብበት ወቅት ሲደርስ ድርሻውን እንዲያመጡለት ባሪያዎቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። |
ገበሬዎቹ ግን ባሪያዎቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። |
ከበፊቶቹ የሚበዙ ሌሎች ባሪያዎች በድጋሚ ላከ፤ ይሁንና በእነሱም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። |
በመጨረሻም ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከው። |
ገበሬዎቹ ልጁን ሲያዩት እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ኑ እንግደለው፤ ርስቱንም እንውረስ!’ ተባባሉ። |
ስለዚህ ያዙትና ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት። |
እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚህን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?” |
የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎችም “ክፉዎች ስለሆኑ ከባድ ጥፋት ያደርስባቸዋል፤ ከዚያም የወይን እርሻውን፣ ፍሬውን በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እንዲህ የሚለውን የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል አላነበባችሁም? ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ። ይህ የይሖዋ ሥራ ነው፤ ለዓይናችንም ድንቅ ነው።’ |
የአምላክ መንግሥት ከእናንተ ተወስዶ ፍሬውን ለሚያፈራ ሕዝብ ይሰጣል የምላችሁ ለዚህ ነው። |
በተጨማሪም በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።” |
የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያኑ ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ ስለ እነሱ እንደተናገረ ገባቸው። |
ሊይዙት ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ሕዝቡን ፈሩ፤ ምክንያቱም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያየው ነበር። |
በዚያ ወቅት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ፤ |
“መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” ይል ነበር። |
“አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን መንገድ አዘጋጁ፤ ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል” ተብሎ በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረለት እሱ ነው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.