text stringlengths 4 267 |
|---|
ነቢያትና ሕጉ በሙሉ እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ተንብየዋልና፤ |
እንግዲህ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆናችሁ ‘ይመጣል የተባለው ኤልያስ’ እሱ ነው። |
ጆሮ ያለው ይስማ። |
“ይህን ትውልድ ከማን ጋር ላመሳስለው? በገበያ ስፍራ ተቀምጠው ጓደኞቻቸውን እየተጣሩ እንዲህ ከሚሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላል፦ |
‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን በሐዘን ደረታችሁን አልደቃችሁም።’ |
በተመሳሳይም ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ ሰዎች ግን ‘ጋኔን አለበት’ አሉ። |
የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ ሰዎች ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉ። የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ መሆኗ በሥራዋ ተረጋግጧል።” |
ከዚያም ብዙ ተአምራት የፈጸመባቸውን ከተሞች ንስሐ ባለመግባታቸው የተነሳ እንዲህ ሲል ይነቅፋቸው ጀመር፦ |
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። |
አንቺም ቅፍርናሆም ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር ትወርጃለሽ፤ ምክንያቱም በአንቺ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በሰዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ በኖረች ነበር። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም ምድር ይቀልላታል።” |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። |
አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና። |
አባቴ ሁሉንም ነገር ለእኔ ሰጥቶኛል፤ ከአብ በስተቀር ወልድን በሚገባ የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብን በሚገባ የሚያውቅ ማንም የለም። |
እናንተ የደከማችሁና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ። |
ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ ገርና በልቤ ትሑት ነኝ፤ ለራሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ። |
ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።” |
ኢየሱስ ይህን ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ |
“እንደምታውቁት ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ ይከበራል፤ የሰው ልጅም በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አልፎ ይሰጣል።” |
በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ ተብሎ በሚጠራው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው |
የተንኮል ዘዴ በመጠቀም ኢየሱስን ለመያዝና ለመግደል ሴራ ጠነሰሱ። |
ይሁን እንጂ “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይፈጠር በበዓሉ ወቅት መሆን የለበትም” ይሉ ነበር። |
ኢየሱስ በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን ቤት ሳለ |
አንዲት ሴት በጣም ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እሱ ቀረበች፤ እየበላ ሳለም ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር። |
ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? |
ይህ ዘይት እኮ በውድ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር።” |
ኢየሱስ ስለ ምን እየተነጋገሩ እንዳለ አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች። |
ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም። |
ይህች ሴት ዘይቱን በሰውነቴ ላይ ስታፈስ እኔን ለቀብር ማዘጋጀቷ ነው። |
እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ይህ ምሥራች በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።” |
ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ |
“እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አላቸው። እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች ሊሰጡት ተስማሙ። |
ስለዚህ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ነበር። |
የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው “ፋሲካን እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት። |
እሱም “ወደ ከተማ ሄዳችሁ እገሌ የተባለውን ሰው፣ ‘መምህሩ “የተወሰነው ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በቤትህ አከብራለሁ” ብሏል’ በሉት” አላቸው። |
ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ። |
በመሸም ጊዜ ከ12 ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ። |
እየበሉ ሳሉም “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ። |
እነሱም በዚህ እጅግ አዝነው ሁሉም ተራ በተራ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር። |
እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው። |
እርግጥ፣ የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።” |
አሳልፎ ሊሰጠው የተዘጋጀው ይሁዳም “ረቢ፣ እኔ እሆን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው። |
እየበሉም ሳሉ ኢየሱስ ቂጣ አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆረሰው፤ ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ በመስጠት “እንኩ፣ ብሉ። ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” አለ። |
ጽዋ አንስቶም አምላክን ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁም ከዚህ ጠጡ፤ |
ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈሰውን ‘የቃል ኪዳን ደሜን’ ያመለክታል። |
ነገር ግን እላችኋለሁ፦ በአባቴ መንግሥት አዲሱን ወይን ከእናንተ ጋር እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከአሁን በኋላ ከዚህ ወይን አልጠጣም።” |
በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ። |
ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ’ ተብሎ ስለተጻፈ በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ላይ በሚደርሰው ነገር የተነሳ ትሰናከላላችሁ። |
ከተነሳሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።” |
ይሁንና ጴጥሮስ መልሶ “ሌሎቹ ሁሉ በአንተ ምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልሰናከልም!” አለው። |
ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። |
ጴጥሮስም “አብሬህ መሞት ቢያስፈልገኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” አለው። የቀሩት ደቀ መዛሙርትም ሁሉ እንደዚሁ አሉ። |
ከዚያም ኢየሱስ ከእነሱ ጋር ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጣ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “ወደዚያ ሄጄ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው። |
ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ከሄደ በኋላ እጅግ ያዝንና ይረበሽ ጀመር። |
ከዚያም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ። እዚህ ሁኑና ከእኔ ጋር ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው። |
ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት በግንባሩ ተደፍቶ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ። ሆኖም እንደ እኔ ፈቃድ ሳይሆን እንደ አንተ ፈቃድ ይሁን” ብሎ ጸለየ። |
ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸውና ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት እንኳ ነቅታችሁ መጠበቅ አልቻላችሁም? |
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሳታሰልሱም ጸልዩ። እርግጥ፣ መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው።” |
እንደገናም ሄዶ ለሁለተኛ ጊዜ “አባቴ ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ሳልጠጣው ይለፍ። ካልሆነ ግን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም” ሲል ጸለየ። |
ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው። |
እንደገናም ትቷቸው ሄደና ለሦስተኛ ጊዜ ስለዚያው ነገር ደግሞ ጸለየ። |
ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ የሚሰጥበት ሰዓት ደርሷል። |
ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።” |
ገና እየተናገረ ሳለ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የተላኩ ሰይፍና ቆመጥ የያዙ ብዙ ሰዎችም አብረውት ነበሩ። |
አሳልፎ የሚሰጠውም “እኔ የምስመው ሰው እሱ ነው፤ ያዙት” በማለት ምልክት ሰጥቷቸው ነበር። |
ይሁዳም በቀጥታ ወደ ኢየሱስ በመሄድ “ረቢ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ብሎ ሳመው። |
ኢየሱስ ግን “ወዳጄ፣ እዚህ የተገኘህበት ዓላማ ምንድን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ቀርበው ኢየሱስን ያዙት፤ አሰሩትም። |
ሆኖም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ሰዶ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ጆሮውን ቆረጠው። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፤ ሰይፍ የሚመዙ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ። |
ለመሆኑ በዚህች ቅጽበት ከ12 ሌጌዎን የሚበልጡ መላእክት እንዲልክልኝ አባቴን መጠየቅ የማልችል ይመስልሃል? |
እንዲህ ከሆነ ታዲያ፣ እንደዚህ ሊሆን ይገባል የሚሉት ቅዱሳን መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?” |
በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ የመጣችሁት እኔን ለመያዝ ነው? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ አስተምር ነበር፤ ሆኖም ያን ጊዜ አልያዛችሁኝም። |
ይህ ሁሉ የሆነው ግን በነቢያት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።” በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ። |
ኢየሱስን ያሰሩት ሰዎች ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ወደተሰበሰቡበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት። |
ይሁንና ጴጥሮስ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ በርቀት ይከተለው ነበር፤ ወደ ውስጥ ከገባ በኋላም መጨረሻውን ለማየት ከቤቱ አገልጋዮች ጋር ተቀመጠ። |
በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ ኢየሱስን ለመግደል በእሱ ላይ የሐሰት የምሥክርነት ቃል እየፈለጉ ነበር። |
ይሁንና ብዙ የሐሰት ምሥክሮች ቢቀርቡም ምንም ማስረጃ አላገኙም። በኋላ ሁለት ሰዎች ቀርበው |
“ይህ ሰው ‘የአምላክን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ ልሠራው እችላለሁ’ ብሏል” አሉ። |
በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ቆሞ “ምንም መልስ አትሰጥም? እነዚህ ሰዎች በአንተ ላይ ስለሰጡት ምሥክርነት ምን ትላለህ?” አለው። |
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆን አለመሆንህን እንድትነግረን በሕያው አምላክ አስምልሃለሁ!” አለው። |
ኢየሱስም “አንተው ራስህ ተናገርከው። ነገር ግን እላችኋለሁ፦ ከዚህ በኋላ የሰው ልጅ በኃያሉ ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያላችሁ” አለው። |
በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ እንዲህ አለ፦ “አምላክን ተሳድቧል! ከዚህ በላይ ምን ምሥክሮች ያስፈልጉናል? ስድቡን እንደሆነ እናንተም ሰምታችኋል። |
እንግዲህ ምን ትላላችሁ?” እነሱም “ሞት ይገባዋል” ብለው መለሱ። |
ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፤ በቡጢም መቱት። ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት |
“ክርስቶስ ሆይ፣ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን?” አሉት። |
ጴጥሮስ ከቤት ውጭ፣ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ወደ እሱ መጥታ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው። |
እሱ ግን “ስለ ምን እየተናገርሽ እንዳለ አላውቅም” በማለት በሁሉም ፊት ካደ። |
ወደ ግቢው መግቢያ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሴት አየችውና በዚያ ለነበሩት ሰዎች “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር” አለች። |
እሱም “ሰውየውን አላውቀውም!” ብሎ በመማል ዳግመኛ ካደ። |
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካባቢው ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን “አነጋገርህ ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አሉት። |
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሰውየውን አላውቀውም!” በማለት ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ። |
ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። |
የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ፦ |
አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ |
ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤ኤስሮን ራምን ወለደ፤ |
ራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ |
ሰልሞን ከረዓብ ቦዔዝን ወለደ፤ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ |
እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ፤ |
ሰለሞን ሮብዓምን ወለደ፤ሮብዓም አቢያህን ወለደ፤አቢያህ አሳን ወለደ፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.