text stringlengths 4 267 |
|---|
የመግቢያው ወርድ አሥር ክንድ ነበር፤ በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች አምስት አምስት ክንድ ነበሩ። የውጨኛውን መቅደስ ርዝመት ሲለካ 40 ክንድ ሆነ፤ ወርዱ ደግሞ 20 ክንድ ሆነ። |
ከዚያም ወደ ውስጥ ገብቶ በመግቢያው ጎን ላይ ያለውን ዓምድ ውፍረት ሲለካ ሁለት ክንድ ሆነ፤ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበር። በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች ሰባት ክንድ ነበሩ። |
ከዚያም ከውጨኛው መቅደስ ትይዩ ያለውን ክፍል ለካ፤ ርዝመቱም 20 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ሆነ። እሱም “ይህ ቅድስተ ቅዱሳኑ ነው” አለኝ። |
ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ሲለካ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ሆነ። በቤተ መቅደሱ ጎን ዙሪያውን ያሉት ክፍሎች ወርድ አራት ክንድ ነበር። |
በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች ከበላያቸው ሁለት ፎቅ ነበራቸው፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ 30 ክፍሎች ነበሩ። በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ፣ በጎን በኩል ያሉትን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም እነዚህ ተሸካሚዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም። |
በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ጠመዝማዛ መተላለፊያ ነበር፤ ላይ ወደሚገኙት ክፍሎች ሲወጣ የመወጣጫዎቹ ወርድ ይጨምር ነበር። አንድ ሰው ከታች ተነስቶ በመካከለኛው ፎቅ በኩል ወደ መጨረሻው ፎቅ ሲወጣ ፎቁ እየሰፋ ይሄድ ነበር። |
በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከፍ ያለ መሠረት መኖሩን አየሁ፤ በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች መሠረትም እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሙሉ ዘንግ ይኸውም ስድስት ክንድ ነበር። |
በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች የውጨኛው ግንብ ወርድ አምስት ክንድ ነበር። በጎን ካሉት ክፍሎች አጠገብ የቤተ መቅደሱ ክፍል የሆነ ክፍት ቦታ ነበር። |
በቤተ መቅደሱና በመመገቢያ ክፍሎቹ መካከል በሁለቱም በኩል ወርዱ 20 ክንድ የሆነ ቦታ ነበር። |
በሰሜን አቅጣጫ፣ በጎን በኩል ባሉት ክፍሎችና ክፍት በሆነው ቦታ መካከል መግቢያ ነበር፤ በደቡብ አቅጣጫም ሌላ መግቢያ ነበር። ክፍት የሆነው ቦታ በሁሉም አቅጣጫ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር። |
በምዕራብ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ትይዩ ያለው ሕንፃ ወርዱ 70 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 90 ክንድ ነበር፤ የሕንፃው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን አምስት ክንድ ነበር። |
ቤተ መቅደሱን ሲለካ ርዝመቱ 100 ክንድ ሆነ። ክፍት የሆነው ስፍራ፣ ሕንፃውና ግንቦቹ ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። |
ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የቤተ መቅደሱ የፊተኛው ክፍልና ክፍት የሆነው ስፍራ ወርድ 100 ክንድ ነበር። |
በሁለቱም ጎን ያሉትን መተላለፊያዎቹን ጨምሮ በጀርባ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ጋር ትይዩ የሆነውን ሕንፃ ርዝመት ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። እንዲሁም ውጨኛውን መቅደስ፣ ውስጠኛውን መቅደስና የግቢውን በረንዳዎች ለካ፤ |
ደግሞም በሦስቱም ቦታዎች ያሉትን ደፎች፣ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና መተላለፊያዎች ለካ። ከደፉ አጠገብ ከወለሉ አንስቶ እስከ መስኮቶቹ ድረስ የእንጨት ማስጌጫዎች ነበሩ፤ መስኮቶቹም ተሸፍነው ነበር። |
ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። |
ግንቡ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። |
ሰው የሚመስለው ፊት በአንድ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ምስል የዞረ ሲሆን፣ አንበሳ የሚመስለው ፊት ደግሞ በሌላ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ዞሮ ነበር። በዚህ መንገድ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ተቀርጸው ነበር። |
በመቅደሱ ግድግዳ ላይ ከወለሉ አንስቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር። |
የመቅደሱ መቃኖች አራት ማዕዘን ናቸው። ከቅዱሱ ስፍራ ፊት ለፊት |
ቁመቱ ሦስት ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ የሆነ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ነበር። የማዕዘን ቋሚዎች ነበሩት፤ መሠረቱና ጎኖቹ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ። እሱም “በይሖዋ ፊት ያለው ጠረጴዛ ይህ ነው” አለኝ። |
የውጨኛው መቅደስና ቅዱሱ ስፍራ እያንዳንዳቸው ሁለት በሮች ነበሯቸው። |
በሮቹ ታጣፊ የሆኑ ሁለት ሳንቃዎች ነበሯቸው፤ እያንዳንዱ በር ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት። |
በግድግዳው ላይ ያሉት ዓይነት ኪሩቦችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች በመቅደሱ በሮች ላይ ተቀርጸው ነበር። በተጨማሪም በውጭ በኩል ከፊት ለፊት በረንዳው ላይ ከእንጨት የተሠራ ወጣ ያለ ነገር ነበር። |
እንዲሁም በበረንዳው ግራና ቀኝ፣ ከቤተ መቅደሱ ጎን ባሉት ክፍሎች ላይና በታዛው አካባቢ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ። |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ቤት እንቆቅልሽና ምሳሌ ተናገር። |
እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትላልቅ ክንፎችና ረጃጅም ማርገብገቢያዎች ያሉት እንዲሁም መላ አካሉ ዥጉርጉር በሆኑ ላባዎች የተሸፈነው ታላቁ ንስር ወደ ሊባኖስ መጥቶ የአርዘ ሊባኖስን ጫፍ ያዘ። |
አናቱ ላይ ያለውን ቀንበጥ ቀጥፎ ወደ ነጋዴዎች ምድር አመጣው፤ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው። |
ከዚያም ከምድሪቱ ዘር የተወሰነውን ወስዶ ለም በሆነ መሬት ላይ ዘራው። እንደ ሪጋ ዛፍ ብዙ ውኃ ባለበት ቦታ አጠገብ ተከለው። |
በመሆኑም ዘሩ በቀለ፤ አጭርና የተንሰራፋ እንዲሁም ወደ ራሱ አቅጣጫ የበቀሉ ቅጠሎች ያሉት የወይን ተክል ሆነ፤ ሥሮቹም ከበታቹ አደጉ። በዚህ ሁኔታ የወይን ተክል ሆነ፤ ቀንበጦችና ቅርንጫፎችም አወጣ። |
“‘“ደግሞም ትላልቅ ክንፎች ያሉትና የክንፎቹ ላባዎች ረጃጅም የሆኑ ሌላ ታላቅ ንስር መጣ። ከዚያም ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ከተተከለበት የአትክልት መደብ አሻግሮ በታላቅ ጉጉት ወደ እሱ ዘረጋ፤ ውኃ ያጠጣውም ዘንድ ቅርንጫፎቹን ወደ እሱ ሰደደ። |
ቅርንጫፎችን እንዲያወጣና ፍሬ እንዲያፈራ እንዲሁም ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን ብዙ ውኃ ባለበት አቅራቢያ መልካም መሬት ላይ ተተክሎ ነበር።”’ |
“እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ያድግ ይሆን? ሰው ሥሮቹን ነቅሎ አይጥልም? ፍሬው እንዲበሰብስ አያደርግም? ቀንበጦቹስ እንዲጠወልጉ አያደርግም? የወይኑ ተክል በጣም ስለሚደርቅ ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድም ሆነ ብዙ ሰው አያስፈልግም። |
ተነቅሎ በሌላ ቦታ ቢተከልስ ያድግ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲነፍስበት ሙሉ በሙሉ አይደርቅም? በበቀለበት የአትክልት መደብ ላይ ይደርቃል።”’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ። |
በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው። ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤ |
ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው። |
ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ በእሱ ላይ ዓመፀ። ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’ |
“‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “እሱን ንጉሥ አድርጎ የሾመው ንጉሥ በሚኖርበት ቦታ ይኸውም በባቢሎን ይሞታል፤ ይህ ሰው መሐላውን አቃሎበታል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሶበታል። |
ብዙ ሕይወት ለማጥፋት የአፈር ቁልል በሚደለደልበትና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የፈርዖን ታላቅ ሠራዊትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወታደሮች ሊረዱት አይችሉም። |
እሱ መሐላውን አቃሏል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሷል። ቃል ቢገባለትም እንኳ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጓል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አያመልጥም።”’ |
“‘በመሆኑም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ መሐላዬን መናቁና ቃል ኪዳኔን ማፍረሱ የሚያስከትልበትን መዘዝ በራሱ ላይ አመጣበታለሁ። |
መረቤን በላዩ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል። ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ክህደት ስለፈጸመ በዚያ እፋረደዋለሁ። |
ከወታደሮቹ መካከል የሸሹት ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በሕይወት የተረፉትም በየአቅጣጫው ይበታተናሉ። በዚህ ጊዜም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩ ታውቃላችሁ።”’ |
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከረጅሙ የአርዘ ሊባኖስ ጫፍ ላይ ቀንበጥ ቀጥፌ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹም ጫፍ ላይ ለጋ የሆነውን ቀጥፌ ረጅምና ግዙፍ በሆነ ተራራ ላይ እኔ ራሴ እተክለዋለሁ። |
ረጅም በሆነ የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎቹም ያድጋሉ፤ ፍሬም ያፈራል፤ ደግሞም የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ይሆናል። በሥሩም የወፍ ዓይነቶች ሁሉ ይኖራሉ፤ በቅጠሎቹም ጥላ ሥር ያርፋሉ። |
የዱር ዛፎች ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ዛፍ ዝቅ ዝቅ ያደረግኩት፣ ዝቅ ያለውን ዛፍ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደረግኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ ለምለሙን ዛፍ አድርቄአለሁ፤ ደረቁም ዛፍ እንዲለመልም አድርጌአለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌአለሁ።”’” |
በ11ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቁጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፦‘በታላቅነትህ ከማን ጋር ትመሳሰላለህ? |
አንድ አሦራዊ፣ በሊባኖስ ያደገ አርዘ ሊባኖስ ነበር፤አርዘ ሊባኖሱ ጥላ እንደሚሰጡ ችፍግ ብለው ያደጉ ዛፎች፣ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች ያሉት እጅግ ረጅም ዛፍ ሲሆንጫፉም ደመናትን ይነካ ነበር። |
ውኃዎቹ ትልቅ ዛፍ እንዲሆን አደረጉት፤ ጥልቅ ከሆኑት ምንጮች የተነሳ ዛፉ በጣም ረጅም ሆነ። በተተከለበት ቦታ ዙሪያ ጅረቶች ነበሩ፤የውኃ መውረጃዎቻቸውም በሜዳ ያሉትን ዛፎች ሁሉ ያጠጡ ነበር። |
ከዚህም የተነሳ ቁመቱ በሜዳ ካሉት ከሌሎቹ ዛፎች ሁሉ ረዘመ። ብዙ ቅርንጫፎች አወጣ፤ ጅረቶቹ ብዙ ውኃ ስለነበራቸውቅርንጫፎቹ ረጃጅም ሆኑ። |
የሰማይ ወፎች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጇቸውን ሠሩ፤የዱር እንስሳትም ሁሉ ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ፤ከጥላውም ሥር ብዙ ሕዝብ ያላቸው ብሔራት ሁሉ ሰፈሩ። |
ከውበቱና ከቅርንጫፎቹ ርዝመት የተነሳ ግርማ ሞገስ ተላበሰ፤ሥሮቹን ብዙ ውኃ ወዳለበት ስፍራ ሰዶ ነበርና። |
በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያሉ ሌሎች አርዘ ሊባኖሶች ሊተካከሉት አልቻሉም። ከጥድ ዛፎች መካከል የእሱ ዓይነት ቅርንጫፎች ያሉት አንድም ዛፍ የለም፤የአርሞን ዛፎችም ከእሱ ቅርንጫፎች ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያለ የትኛውም ዛፍ በውበቱ አይወዳደረውም። |
ብዙ ቅጠሎች ያሉት ውብ ዛፍ አድርጌ ሠራሁት፤በእውነተኛው አምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ያሉ ሌሎች ዛፎችም ሁሉ ቀኑበት።’ |
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቁመቱ እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ጫፉን በደመናት መካከል ከፍ ስላደረገና በቁመቱ የተነሳ ልቡ ስለታበየ፣ |
ኃያል ለሆነ የብሔራት ገዢ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። እሱም በእርግጥ ይነሳበታል፤ በክፋቱም የተነሳ እጥለዋለሁ። |
ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት ባዕዳን ቆርጠው ይጥሉታል፤ በተራሮችም ላይ ጥለውት ይሄዳሉ፤ ቅጠሎቹም በየሸለቆው ይረግፋሉ፤ ቅርንጫፎቹም በምድሪቱ ላይ ባሉ ጅረቶች ሁሉ ላይ ተሰባብረው ይወድቃሉ። የምድር ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ሥር ወጥተው ትተውት ይሄዳሉ። |
የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ግንዱ ላይ ይሰፍራሉ፤ የዱር እንስሳትም ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይኖራሉ። |
ይህም የሚሆነው በውኃዎች አጠገብ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸውም ቁመታቸው በጣም እንዳይረዝም ወይም ጫፋቸውን በደመናት መካከል ከፍ እንዳያደርጉ እንዲሁም ውኃ የጠገበ አንድም ዛፍ ቁመቱ እነሱ ጋ እንዳይደርስ ነው። ሁሉም ለሞት ይዳረጋሉና፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት የሰው ልጆች ጋር በአንድነት ከምድር በታች ይወርዳሉ።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ መቃብር በሚወርድበት ቀን ሰዎች እንዲያዝኑ አደርጋለሁ። ስለዚህ ጥልቅ የሆኑትን ውኃዎች እሸፍናለሁ፤ ጅረቶቹንም እገታለሁ፤ ይህም በገፍ የሚፈስሱት ውኃዎች ይቋረጡ ዘንድ ነው። ከእሱ የተነሳ ሊባኖስን አጨልማለሁ፤ በሜዳም ያሉ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። |
ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ሁሉ ጋር ወደ መቃብር በማወርደው ጊዜ ሲወድቅ በሚሰማው ድምፅ ብሔራት እንዲናወጡ አደርጋለሁ፤ ከምድርም በታች የኤደን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ግሩም የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እንዲሁም ውኃ የጠገቡት ዛፎች ሁሉ ይጽናናሉ። |
ከእሱ ጋር እንዲሁም በብሔራት መካከል በጥላው ሥር ይኖሩ ከነበሩት ደጋፊዎቹ ጋር በሰይፍ የታረዱት ወዳሉበት ወደ መቃብር ወርደዋል።’ |
“‘በኤደን ካሉት ዛፎች መካከል የአንተ ዓይነት ክብርና ታላቅነት ያለው የትኛው ነው? ይሁንና ከኤደን ዛፎች ጋር ከምድር በታች ትወርዳለህ። ባልተገረዙት መካከል፣ በሰይፍ ከታረዱት ጋር ትጋደማለህ። ይህ በፈርዖንና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
“‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በምትከፋፈሉበት ጊዜ ከምድሪቱ ላይ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡ። ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሁን። ስፍራው በሙሉ ቅዱስ ድርሻ ይሆናል። |
በዚህ ቦታ ውስጥ ለቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግል 500 ክንድ በ500 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ቦታ ይኖራል፤ በሁሉም በኩል 50 ክንድ የሆነ የግጦሽ መሬት ይኖረዋል። |
ከተለካው መሬት ላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 የሆነ ስፍራ ለካ፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውም መቅደስ በዚያ ውስጥ ይሆናል። |
ይሖዋን ለማገልገል ለሚቀርቡትና በመቅደሱ ለሚያገለግሉት ካህናት ቅዱስ ድርሻ ይሆናል። ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን ቅዱስ ስፍራ ይሆናል። |
“‘በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤ እነሱም 20 የመመገቢያ ክፍሎችን ርስት አድርገው ይወስዳሉ። |
“‘እናንተም የከተማዋ ርስት እንዲሆን ርዝመቱ 25,000 ክንድ (መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ትይዩ የሆነ) ወርዱ ደግሞ 5,000 ክንድ የሆነ ቦታ ትሰጣላችሁ። ይህም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። |
“‘አለቃው መዋጮ ተደርጎ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ለከተማዋ ከተሰጠው ቦታ ግራና ቀኝ መሬት ይኖረዋል። መሬቱ መዋጮ ተደርጎ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ አጠገብ ይሆናል። ደግሞም በስተ ምዕራብና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይሆናል። ከምዕራቡ ወሰን እስከ ምሥራቁ ወሰን ድረስ ያለው ርዝመት ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ድርሻ ጋር ተመሳሳይ ነው። |
ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ አለቆቼ በሕዝቤ ላይ ግፍ አይፈጽሙም፤ ምድሪቱንም ለእስራኤል ቤት ሰዎች በየነገዳቸው ይሰጧቸዋል።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ የእስራኤል አለቆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!’ “‘ግፍና ጭቆና መፈጸማችሁን አቁሙ፤ ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ። የሕዝቤን ንብረት መቀማታችሁን ተዉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
‘ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የኢፍ መስፈሪያና ትክክለኛ የባዶስ መስፈሪያ ተጠቀሙ። |
ለኢፍ መስፈሪያና ለባዶስ መስፈሪያ ቋሚ የሆነ መመዘኛ መኖር አለበት። የባዶስ መስፈሪያው አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን፤ የኢፍ መስፈሪያውም አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን። ሆሜር መደበኛ መመዘኛ ይሆናል። |
አንድ ሰቅል 20 ጌራ ይሁን። ደግሞም 20 ሰቅል፣ 25 ሰቅልና 15 ሰቅል አንድ ላይ ሲደመር አንድ ማኔህ ይሁንላችሁ።’ |
“‘የምትሰጡት መዋጮ ይህ ነው፦ ከእያንዳንዱ ሆሜር ስንዴ የኢፍ አንድ ስድስተኛ፣ ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ ደግሞ የኢፍ አንድ ስድስተኛ መዋጮ ታደርጋላችሁ። |
የሚሰጠው ዘይት የሚለካው በባዶስ መስፈሪያ ይሆናል። አንድ ባዶስ፣ የቆሮስ አንድ አሥረኛ ነው፤ አሥር ባዶስ ደግሞ አንድ ሆሜር ነው፤ አሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋር እኩል ነውና። |
ደግሞም ከእስራኤል መንጎች መካከል ከየሁለት መቶው አንድ በግ ስጡ። እነዚህ ስጦታዎች ለሕዝቡ ማስተሰረያ እንዲሆኑ ለእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ ለሚቃጠል መባና ለኅብረት መሥዋዕት ይውላሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“‘የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ይህን መዋጮ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣል። |
አለቃውም በበዓላት፣ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ወቅት፣ በየሰንበቱና ለእስራኤል ቤት ሰዎች በተወሰኑት በዓላት ወቅት ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ፣ የእህሉን መባና የመጠጡን መባ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። ለእስራኤል ቤት ሰዎች ማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ፣ የእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርበው እሱ ነው።’ |
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከከብቶቹ መካከል ምንም እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ወስደህ መቅደሱን ከኃጢአት አንጻው። |
ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ። |
አንድ ሰው በስህተትና ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ ከወሩ በሰባተኛው ቀን እንዲሁ አድርግ፤ እናንተም ለቤተ መቅደሱ ማስተሰረያ ታቀርባላችሁ። |
“‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በ14ኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ። ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። |
በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለምድሩ ነዋሪ ሁሉ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ ወይፈን ያቀርባል። |
በዓሉ በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀናት፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና እንከን የሌለባቸውን ሰባት አውራ በጎች ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ደግሞም ለኃጢአት መባ በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቀርባል። |
በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ወይፈን አንድ ኢፍ፣ ለእያንዳንዱም አውራ በግ አንድ ኢፍ የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። |
“‘በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ በበዓሉ ወቅት ለሰባት ቀናት ይህንኑ የኃጢአት መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና ዘይት ያቅርብ።’” |
“ስለ እስራኤል አለቆች ሙሾ አውጣ፤ |
እንዲህም በል፦‘እናትህ ምን ነበረች? በአንበሶች መካከል ያለች እንስት አንበሳ ነበረች። በብርቱ ደቦል አንበሶች መሃል ተኛች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች። |
ከግልገሎቿ መካከል አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው፤ እሱም ብርቱ ደቦል አንበሳ ሆነ። አድኖ መብላት ተማረ፤ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ። |
ብሔራት ስለ እሱ ሰሙ፤ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶም ያዙት፤በስናግም እየጎተቱ ወደ ግብፅ ምድር አመጡት። |
እሷም በትዕግሥት ስትጠባበቅ ከቆየች በኋላ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው ተገነዘበች። በመሆኑም ከግልገሎቿ መካከል ሌላውን ወስዳ እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ አድርጋ ላከችው። |
እሱም በአንበሶች መካከል ይጎማለል ጀመር፤ ብርቱ ደቦል አንበሳም ሆነ። አድኖ መብላት ተማረ፤ ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ። |
በማይደፈሩት ማማዎቻቸው መካከል አደባ፤ ከተሞቻቸውንም አወደመ፤ከዚህም የተነሳ ግሳቱ ወና በሆነችው ምድር ላይ አስተጋባ። |
በዙሪያው ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሔራት መረባቸውን በእሱ ላይ ለመዘርጋት ተነሱበት፤እሱም ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.