text
stringlengths
4
267
በስናግ ጎትተው በእንስሳት ጎጆ ውስጥ በመክተት ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ከዚያ በኋላ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ እንዳይሰማ በዚያ አሰሩት።
እናትህ በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ በደምህ ውስጥ ያለ የወይን ተክል ነበረች። ከውኃው ብዛት የተነሳ ፍሬ አፈራች፤ ብዙ ቅርንጫፎችም ነበሯት።
ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆኑ ጠንካራ ቅርንጫፎች አወጣች። አድጋ ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ረጅም ሆነች፤ደግሞም ከርዝመቷና ከቅጠሎቿ ብዛት የተነሳ ጎልታ ታየች።
ሆኖም በቁጣ ተነቀለች፤ ወደ ምድርም ተጣለች፤የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀው። ጠንካራ ቅርንጫፎቿ ተሰብረው ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።
በዚህ ጊዜ በምድረ በዳ፣ውኃ በሌለበት ደረቅ ምድር ተተከለች።
እሳት ከቅርንጫፎቿ ወጥቶ ቀንበጦቿንና ፍሬዋን በላ፤በእሷም ላይ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ፣ ለገዢዎችም የሚሆን በትረ መንግሥት አልተረፈም። “‘ይህ ሙሾ ነው፤ ሙሾ ሆኖም ያገለግላል።’”
የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ “‘በአንድ አገር ላይ ሰይፍ አመጣሁ እንበል፤ በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ሰው በመምረጥ ጠባቂ አድርጎ ሾመው፤
እሱም በአገሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት በመንፋት ሕዝቡን አስጠነቀቀ።
አንድ ሰው የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰምቶ ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ ሳያደርግ ቢቀር፣ ሰይፍም መጥቶ ሕይወቱን ቢያጠፋ፣ ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።
የቀንደ መለከቱን ድምፅ ቢሰማም ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ አላደረገም። ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። ቢጠነቀቅ ኖሮ ሕይወቱ በተረፈ ነበር።
“‘ነገር ግን ጠባቂው ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት ባይነፋና ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፣ ሰይፍም መጥቶ ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት ቢያጠፋ፣ ይህ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከጠባቂው እጅ እሻለሁ።’
“የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው።
ክፉውን ሰው ‘አንተ ክፉ ሰው፣ በእርግጥ ትሞታለህ!’ ባልኩት ጊዜ፣ ክፉውን ሰው አካሄዱን እንዲያስተካክል ባታስጠነቅቀው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ ከሠራው በደል የተነሳ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ።
ሆኖም ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው አካሄዱን ለማስተካከል ፈቃደኛ ባይሆን፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን በእርግጥ ታድናለህ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ‘እናንተ እንዲህ ብላችኋል፦ “ዓመፃችንና ኃጢአታችን እጅግ ከብዶናል፤ በዚህም የተነሳ እየመነመንን ሄደናል፤ ታዲያ እንዴት በሕይወት መቀጠል እንችላለን?”’
እንዲህ በላቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በክፉው ሰው ሞት ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም ክፉው ሰው አካሄዱን አስተካክሎ በሕይወት እንዲኖር እፈልጋለሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለምን ትሞታላችሁ?”’
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘ጻድቁ ሰው በሚያምፅበት ጊዜ ጽድቁ አያድነውም፤ ክፉውም ሰው ከክፋቱ በሚመለስበት ጊዜ በክፋቱ አይሰናከልም፤ ደግሞም ጻድቅ የሆነ ማንኛውም ሰው ኃጢአት በሚሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም።
ጻድቁን ሰው “በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ” ባልኩት ጊዜ በገዛ ጽድቁ ታምኖ መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ ከጽድቅ ሥራው መካከል አንዱም አይታሰብም፤ ይልቁንም መጥፎ ነገር በመፈጸሙ ይሞታል።
“‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣
ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም።
ከሠራቸው ኃጢአቶች ውስጥ አንዱም አይታወስበትም። ፍትሕና ጽድቅ የሆነውን ነገር ስላደረገ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።’
“ይሁንና ወገኖችህ ፍትሐዊ ያልሆነው የእነሱ መንገድ ሆኖ ሳለ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብለዋል።
“ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህ የተነሳ ይሞታል።
ሆኖም ክፉ ሰው ከክፋቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል።
“ይሁንና እናንተ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብላችኋል። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።”
ከረጅም ጊዜ በኋላ ይኸውም በተማረክን በ12ኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ ሰው ወደ እኔ መጥቶ “ከተማዋ ተመታች!” አለኝ።
ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ሰውየው ጠዋት ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት፣ አምላክ አፌን ከፈተልኝ። እኔም አፌ ተከፍቶ በድጋሚ መናገር ቻልኩ።
ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነዚህ የፈራረሱ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ በማለት ይናገራሉ፦ ‘አብርሃም አንድ ራሱ ብቻ ነበር፤ ይሁንና ምድሪቱን ወረሰ። እኛ ግን ብዙ ነን፤ በእርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች።’
“ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዓይኖቻችሁን አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶቻችሁ ታነሳላችሁ፤ ደምም ታፈሳላችሁ። ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?
በሰይፋችሁ ታምናችኋል፤ አስጸያፊ ልማዶች ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት አርክሳችኋል። ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?”’
“አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፈራረሱት ቦታዎች የሚኖሩት ሰዎች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ አውላላ ሜዳ ላይ ያሉትንም ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽጎችና በዋሻዎች ውስጥ ያሉትም በበሽታ ይሞታሉ።
ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከልክ ያለፈ ኩራቷም ይጠፋል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤ የሚያልፍባቸውም አይኖርም።
ደግሞም በፈጸሟቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ወገኖችህ በየግድግዳው ሥርና በየቤቱ በራፍ ላይ ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ አንተ ይነጋገራሉ። አንዱ ሌላውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፣ ‘ና፣ ከይሖዋ የመጣውን ቃል እንስማ’ ይለዋል።
እንደ ሕዝቤ በፊትህ ለመቀመጥ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም በተግባር አያውሉትም። በአፋቸው ይሸነግሉሃልና፤ ልባቸው ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይስገበገባል።
እነሆ፣ አንተ ለእነሱ ባማረ ድምፅ እንደሚዘፈንና በባለ አውታር መሣሪያ አሳምረው እንደሚጫወቱት የፍቅር ዘፈን ሆነህላቸዋል። ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም አንዳቸውም አያደርጉትም።
ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ፣ ደግሞም ይፈጸማል፣ በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ።”
መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የይሖዋ ቤት የምሥራቅ በር አመጣኝ። በዚያም በበሩ መግቢያ ላይ 25 ሰዎች አየሁ፤ ከእነሱም መካከል የሕዝቡ አለቆች የሆኑት የአዙር ልጅ ያአዛንያህና የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ነበሩ።
ከዚያም አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህች ከተማ መጥፎ ምክር የሚመክሩ ናቸው።
እነሱ ‘አሁን ቤት የምንሠራበት ጊዜ አይደለም? ከተማዋ ድስት ናት፤ እኛ ደግሞ ሥጋ ነን’ ይላሉ።
“ስለዚህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር።”
ከዚያም የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የተናገራችሁት ነገር ትክክል ነው፤ የምታስቡትን ነገር አውቃለሁ።
በዚህች ከተማ ብዙዎች እንዲሞቱ አድርጋችኋል፤ ጎዳናዎቿንም በሙታን ሞልታችኋል።”’”
“ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በከተማዋ ዙሪያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች፣ እነሱ ሥጋው ናቸው፤ ከተማዋ ደግሞ ድስቱ ናት። እናንተ ግን ከውስጧ ትወሰዳላችሁ።’”
“‘ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ አመጣባችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
‘ከእሷ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የፍርድ እርምጃም እወስድባችኋለሁ።
በሰይፍ ትወድቃላችሁ። በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።
ከተማዋ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ እንዳለ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤
እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። በሥርዓቴ አልተመላለሳችሁምና፤ ድንጋጌዎቼንም አላከበራችሁም፤ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች ተከተላችሁ።’”
ትንቢት ተናግሬ እንደጨረስኩ የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቀሪዎች ፈጽመህ ልታጠፋ ነው?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽኩ።
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ወንድሞችህን ይኸውም የመቤዠት መብት ያላቸውን ወንድሞችህንና የእስራኤልን ቤት ሁሉ ‘ከይሖዋ ራቁ። ምድሪቱ የእኛ ናት፤ ለእኛ ርስት ሆና ተሰጥታለች’ ብለዋቸዋል።
ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሩቅ ወዳሉ ብሔራት በግዞት እንዲወሰዱና በብዙ አገሮች መካከል እንዲበተኑ ባደርግም በሄዱባቸው አገሮች ውስጥ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።”’
“ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ደግሞም ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች አመጣችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።
እነሱም ወደዚያ ይመለሳሉ፤ በላይዋም ላይ ያሉትን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉና ጸያፍ የሆኑ ልማዶች ሁሉ ያስወግዳሉ።
እኔም ያልተከፋፈለ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ የሥጋ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤
ይህም ደንቦቼን አክብረው እንዲመላለሱ እንዲሁም ድንጋጌዎቼን እንዲጠብቁና እንዲታዘዙ ነው። በዚህ ጊዜ እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”’
“‘“ሆኖም አስጸያፊ ነገሮቻቸውንና ጸያፍ የሆኑ ልማዶቻቸውን አጥብቀው ለመከተል በልባቸው ቆርጠው የተነሱትን በተመለከተ፣ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’”
በዚህ ጊዜ ኪሩቦቹ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ነበሩ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር።
ከዚያም የይሖዋ ክብር ከከተማዋ ተነስቶ ወደ ላይ ወጣ፤ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ባለው ተራራም ላይ ቆመ።
ከዚያም መንፈስ፣ በአምላክ ኃይል አማካኝነት በተሰጠኝ ራእይ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ደግሞም በከለዳውያን ምድር ወዳሉት ግዞተኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ተለየ።
እኔም ይሖዋ ያሳየኝን ነገር ሁሉ በግዞት ላሉት ሰዎች መናገር ጀመርኩ።
የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ይሖዋም በመንፈሱ ወሰደኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ መካከልም አኖረኝ፤ ስፍራውም በአጥንቶች ተሞልቶ ነበር።
እሱም በዙሪያቸው እንዳልፍ አደረገኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ ላይ በጣም ብዙ አጥንቶች ወድቀው አየሁ፤ አጥንቶቹም በጣም ደርቀው ነበር።
እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች ሕያው ሊሆኑ ይችላሉ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩ።
እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ስለ እነዚህ አጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እናንተ ደረቅ አጥንቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ “እስትንፋስ እንዲገባባችሁ አደርጋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ።
ጅማት አደርግላችኋለሁ፤ ሥጋም አለብሳችኋለሁ፤ በቆዳም እሸፍናችኋለሁ፤ እስትንፋስም አስገባባችኋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’”
ከዚያም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ። ትንቢቱን እንደተናገርኩ የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ።
ከዚያም አጥንቶቹ ጅማትና ሥጋ ሲለብሱ አየሁ፤ በቆዳም ተሸፈኑ። ሆኖም በውስጣቸው ገና እስትንፋስ አልነበረም።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ለነፋሱ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ነፋስ ሆይ፣ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፤ ሕያው እንዲሆኑም በእነዚህ በተገደሉት ሰዎች ላይ ንፈስ።”’”
ስለዚህ ባዘዘኝ መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ እስትንፋስም ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ፤ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ሆኑ።
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው። እነሱ ‘አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል። ከሌሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠናል’ ይላሉ።
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን እከፍታለሁ፤ ከመቃብሮቻችሁም ውስጥ አስነሳችኋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ።
ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን ስከፍትና ከመቃብሮቻችሁ ውስጥ ሳስነሳችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’
‘መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ አሰፍራችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩና ይህን እንዳደረግኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ይሖዋ።”
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት የእስራኤል ሰዎች’ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’ ብለህ ጻፍበት።
ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ ሁለቱንም አንድ ላይ ያዛቸው።
ወገኖችህ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትነግረንም?’ ብለው ሲጠይቁህ፣
እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’
የጻፍክባቸውን በትሮች ማየት እንዲችሉ በእጅህ ያዝ።
“ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።
በምድሪቱ፣ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ፤ በሁሉም ላይ አንድ ንጉሥ ይገዛል፤ ከእንግዲህ ሁለት ብሔራት አይሆኑም፤ ደግሞም ተከፍለው ሁለት መንግሥታት አይሆኑም።
ከእንግዲህ ወዲህ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው፣ ጸያፍ በሆኑት ልማዶቻቸውና በሚፈጽሟቸው በደሎች ሁሉ ራሳቸውን አያረክሱም። ታማኝነት በማጉደል ከሠሩት ኃጢአት ሁሉ እታደጋቸዋለሁ፤ ደግሞም አነጻቸዋለሁ። እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔ ራሴም አምላካቸው እሆናለሁ።
“‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል። ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።
አባቶቻችሁ በኖሩባት፣ ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይቀመጣሉ፤ እነሱና ልጆቻቸው እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው በእሷ ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤ አገልጋዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃቸው ይሆናል።
“‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ዘላለማዊ ይሆናል። እነሱንም አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ እንዲሁም መቅደሴን በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ።
ድንኳኔ ከእነሱ ጋር ይሆናል፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ ብሔራት እስራኤልን የቀደስኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
በ11ኛው ዓመት፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች! አሁን እሷ ስለጠፋች ሁሉም ነገር ይሳካልኛል፤ ደግሞም እበለጽጋለሁ’ ስላለች፣
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ።
እነሱ የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ማማዎቿንም ያወድማሉ፤ አፈሯን ከላይዋ ጠርጌ አስወግዳለሁ፤ የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርጋታለሁ።
በባሕር መካከል የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች።’ “‘እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራትም ይበዘብዟታል።
በገጠር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይመታሉ፤ ሰዎችም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
“ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ በጢሮስ ላይ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ከሰሜን አመጣለሁ፤ እሱ ፈረሶችን፣ የጦር ሠረገሎችን፣ ፈረሰኞችንና ብዙ ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ያለው የነገሥታት ንጉሥ ነው።
በገጠር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማል፤ በአንቺም ላይ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ይገነባል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ በአንቺም ላይ ትልቅ ጋሻ ያነሳል።