text
stringlengths
4
267
ለከበባው ውኃ ቅጂ! ምሽጎችሽን አጠናክሪ። ማጥ ውስጥ ግቢ፤ ጭቃውንም ርገጪ፤የጡብ ቅርጽ ማውጫውንም ያዢ።
ይህም ሆኖ እሳት ይበላሻል። ሰይፍ ይቆርጥሻል። እንደ ኩብኩባ ይበላሻል። እንደ ኩብኩባ ተባዢ! አዎ፣ እንደ አንበጣ ተራቢ!
ነጋዴዎችሽን ከሰማያት ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል። ኩብኩባው ቅርፊቱን ከላዩ ላይ ጥሎ ይበርራል።
ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣መኮንኖችሽም እንደ አንበጣ መንጋ ናቸው። ቅዝቃዜ ባለበት ቀን በድንጋይ ቅጥሮች ውስጥ ይሰፍራሉ፤ፀሐይ ስትወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤የት እንደደረሱም ማንም አያውቅም።
የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ እንቅልፍ ተጫጭኗቸዋል፤ታላላቅ ሰዎችህ በመኖሪያቸው ይቀመጣሉ። ሕዝብህ በተራሮቹ ላይ ተበታትነዋል፤የሚሰበስባቸውም የለም።
የደረሰብህን መቅሰፍት የሚያቆም ነገር የለም። ቁስልህ ሊድን የሚችል አይደለም። ስለ አንተ ወሬ የሚሰሙ ሁሉ ያጨበጭባሉ፤በማያባራው ጭካኔህ ያልተጎዳ ማን አለና?”
የሚበትን መጥቶብሻል። ምሽጎቹን ጠብቂ። መንገዱን በትኩረት ተመልከቺ። ወገብሽን ታጠቂ፤ ኃይልሽንም ሁሉ አሰባስቢ።
ይሖዋ የያዕቆብን ክብርከእስራኤል ክብር ጋር ይመልሳልና፤አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፤ቀንበጦቻቸውንም ከጥቅም ውጭ አድርገዋል።
የኃያላኑ ጋሻዎች ቀይ ቀለም የተነከሩ ናቸው፤ተዋጊዎቹ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሰዋል። ለጦርነት ዝግጁ በሚሆንበት ቀን፣የጦር ሠረገላው ብረቶች እንደ እሳት ያብረቀርቃሉ፤ከጥድ የተሠሩት ረጃጅም ጦሮች ይወዛወዛሉ።
የጦር ሠረገሎቹ በጎዳናዎቹ ላይ ይከንፋሉ። በአደባባዮቹም ላይ ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ። እንደሚነድ ችቦ ያበራሉ፤ እንደ መብረቅም ያንጸባርቃሉ።
እሱ አለቆቹን ይጠራል። እነሱ ወደ ፊት ሲገሰግሱ ይሰናከላሉ። ወደ ቅጥሯ እየተጣደፉ ይሄዳሉ፤መከላከያም ያቆማሉ።
የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ፤ቤተ መንግሥቱም ይቀልጣል።
ጉዳዩ ታውጇል፦ እሷ ተጋልጣለች፤ተማርካ ተወስዳለች፤ ሴቶች ባሪያዎቿም ያቃስታሉ፤ደረታቸውን እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ።
ነነዌ ከተቆረቆረችበት ጊዜ አንስቶ እንደ ውኃ ኩሬ ነበረች፤አሁን ግን እነሱ ይሸሻሉ። አንዳንዶች “ቁሙ! ቁሙ!” ብለው ይጮኻሉ። ሆኖም ወደ ኋላ የሚዞር የለም።
ብሩን ዝረፉ፤ ወርቁን ዝረፉ! የተከማቸው ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም። በብዙ ዓይነት የከበሩ ዕቃዎች ተሞልቷል።
ከተማዋ ባዶና ወና እንዲሁም ባድማ ሆናለች! ልባቸው በፍርሃት ቀልጧል፤ ጉልበታቸው ተብረክርኳል፤ ወገባቸውም ተንቀጥቅጧል፤የሁሉም ፊት ቀልቷል።
ደቦል አንበሶቹ የሚመገቡበት፣ማንም ሳያስፈራቸው አንበሳው ግልገሎቹን እየመራ የሚወጣበትየአንበሶቹ ዋሻ የት አለ?
አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያህል አደነ፤ለእንስቶቹም አንቆ ገደለላቸው። ጎሬውን በታደኑ እንስሶች፣ዋሻውንም በተቦጫጨቁ እንስሶች ሞላ።
“እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤“የጦር ሠረገላዋን በጭስ መካከል አቃጥላለሁ፤ደቦል አንበሶችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል። አደንሽን ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ፤የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።”
ነቢዩ ዕንባቆም በራእይ የተቀበለው መልእክት፦
ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ከግፍ እንድታስጥለኝ ስለምን ጣልቃ የማትገባው እስከ መቼ ነው?
ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ? ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ የሚፈጸመው ለምንድን ነው? ጠብና ግጭትስ ለምን በዛ?
ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤ፍትሕም ጨርሶ የለም። ክፉው ጻድቁን ከቦታልና፤ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ተጣሟል።
“ብሔራትን እዩ፣ ደግሞም ልብ በሉ! በመገረም ተመልከቱ፤ ተደነቁም፤እናንተ ቢነገራችሁም እንኳ የማታምኑት አንድ ነገርበዘመናችሁ ይከናወናልና።
እነሆ፣ ጨካኝና ፈጣን የሆነውን ብሔር ይኸውምከለዳውያንን አስነሳለሁና። የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ።
እነሱ አስደንጋጭና አስፈሪ ናቸው። የገዛ ራሳቸውን ፍትሕና ሥልጣን ያቋቁማሉ።
ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፤ከሌሊት ተኩላዎችም ይልቅ ጨካኞች ናቸው። የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ። ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ።
ሁሉም ዓመፅ ለመፈጸም ቆርጠው ይመጣሉ። እንደ ምሥራቅ ነፋስ ፊታቸውን ያቀናሉ፤ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ያፍሳሉ።
በነገሥታት ይሳለቃሉ፤በከፍተኛ ባለሥልጣናትም ላይ ይስቃሉ። በተመሸገ ስፍራ ሁሉ ላይ ይስቃሉ፤የአፈር ቁልልም ሠርተው ይይዙታል።
ከዚያም እንደ ነፋስ ወደ ፊት እየገሰገሱ በምድሪቱ ላይ ያልፋሉ፤ይሁንና በደለኛ ይሆናሉ፤ምክንያቱም የኃይላቸው ምንጭ አምላካቸው እንደሆነ ይናገራሉ።”
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከዘላለም አንስቶ ያለህ አይደለህም? ቅዱስ የሆንከው አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም። ይሖዋ ሆይ፣ እነሱን ፍርድ ለማስፈጸም ሾመሃቸዋል፤ዓለቴ ሆይ፣ እንዲቀጡ አቋቁመሃቸዋል።
ዓይኖችህ ክፉ የሆነውን ነገር እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፤ክፋትንም ዝም ብለህ ማየት አትችልም። ታዲያ ከዳተኛውን ዝም ብለህ የምትመለከተው ለምንድን ነው?ደግሞስ ክፉ ሰው ከእሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጥ ለምን ዝም ትላለህ?
ሰው እንደ ባሕር ዓሣ፣ገዢም እንደሌላቸው መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሆን ለምን ትፈቅዳለህ?
እሱ እነዚህን ሁሉ በመንጠቆ ጎትቶ ያወጣል። በመረቡ ይይዛቸዋል፤በዓሣ ማጥመጃ መረቡም ይሰበስባቸዋል። በዚህም እጅግ ሐሴት ያደርጋል።
በመሆኑም ለመረቡ መሥዋዕት ይሠዋል፤ለዓሣ ማጥመጃ መረቡም መሥዋዕት ያቀርባል፤በእነሱ የተነሳ ድርሻው በቅባት ተሞልቷል፤ምግቡም ምርጥ ነው።
ታዲያ መረቡን ሁልጊዜ ያራግፋል? ብሔራትንስ ያለርኅራኄ መፍጀቱን ይቀጥላል?
ነቢዩ ዕንባቆም በሙሾ ያቀረበው ጸሎት፦
ይሖዋ ሆይ፣ ስለ አንተ የተወራውን ሰምቻለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ፍርሃት አሳደረብኝ። በዓመታት መካከል ሥራህን ሕያው አድርግ! በዓመታትም መካከል ሥራህን አሳውቅ። መዓት በሚወርድበት ጊዜ ምሕረትን አስታውስ።
አምላክ ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ግርማው ሰማያትን ሸፈነ፤ምድርም በውዳሴው ተሞላች።
ጸዳሉ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው። ከእጁ ሁለት ጨረሮች ፈነጠቁ፤ብርታቱም በዚያ ተሰውሯል።
ቸነፈር ከፊቱ ሄደ፤የሚያቃጥል ትኩሳትም እግር በእግር ተከተለው።
ቆመ፤ ምድርንም አንቀጠቀጠ። ባየም ጊዜ ብሔራትን አብረከረካቸው። ዘላለማዊ የሆኑት ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንቶቹ ኮረብቶች ተደፉ። የጥንቶቹ መንገዶች የእሱ ናቸው።
በኩሻን ድንኳኖች ውስጥ ችግር አየሁ። የምድያም የድንኳን ሸራዎች ተንቀጠቀጡ።
ይሖዋ ሆይ፣ ቁጣህ የነደደው በወንዞች ላይ ነው?በእርግጥ በወንዞች ላይ ነው? ወይስ ታላቅ ቁጣህን የገለጽከው በባሕሩ ላይ ነው? በፈረሶችህ ላይ ተቀምጠህ ጋልበሃልና፤ሠረገሎችህ ድል ተቀዳጅተዋል።
የቀስትህ ሽፋን ተነስቷል፤ ቀስትህም ተዘጋጅቷል። ዘንጎቹ በመሐላ ተመድበዋል። (ሴላ) ምድሪቱን በወንዞች ከፈልክ።
ተራሮች አንተን ሲያዩ በሥቃይ ተንፈራገጡ። ዶፍ ዝናብ ጠራርጎ ሄደ። ጥልቁ በኃይል ጮኸ። እጁን ወደ ላይ አነሳ።
ፀሐይና ጨረቃ ከፍ ባለው መኖሪያ ስፍራቸው ቆሙ። ፍላጾችህ እንደ ብርሃን ተወረወሩ። ጦርህ እንደ መብረቅ አብረቀረቀ።
በምድር ላይ በቁጣ ዘመትክ። ብሔራትን በቁጣ ረገጥካቸው።
ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ። የክፉውን ቤት መሪ አደቀቅክ። ቤቱ ከመሠረቱ አንስቶ እስከ አናቱ ድረስ ተጋለጠ። (ሴላ)
እኔን ለመበታተን በቁጣ በተነሱ ጊዜበገዛ ራሱ መሣሪያዎች የተዋጊዎቹን ራስ ወጋህ። እነሱ ጎስቋላውን ሰው በስውር በመዋጥ ሐሴት አድርገዋል።
በባሕር ውስጥ፣ በሚናወጠው ብዙ ውኃ መካከልበፈረሶችህ እየጋለብክ አለፍክ።
እኔ ሰማሁ፤ ሆዴም ታወከ፤ከድምፁ የተነሳ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ። አጥንቶቼም ነቀዙ፤ከታች ያሉት እግሮቼ ተብረከረኩ። ሆኖም የጭንቀትን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ፤ይህ ቀን ጥቃት በሚሰነዝርብን ሕዝብ ላይ ይመጣልና።
የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣የወይን ተክልም ፍሬ ባይሰጥ፣የወይራ ዛፍም ባያፈራ፣እርሻዎቹም እህል ባይሰጡ፣መንጋው ከጉረኖው ቢጠፋ፣ከብቶቹም ሁሉ በረት ውስጥ ባይገኙ፣
እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤አዳኜ በሆነውም አምላክ እደሰታለሁ።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ብርታቴ ነው፤እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ስፍራዎችም ላይ ያስኬደኛል።
በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ። በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትናበምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ።
ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነበው ሰው በቀላሉ እንዲያነበውራእዩን ጻፈው፤ በጽላትም ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ቅረጸው።
ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም። ቢዘገይ እንኳ በተስፋ ጠብቀው! ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና። ራእዩ አይዘገይም!
ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤ውስጡ ቀና አይደለም። ጻድቅ ግን በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል።
በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነእብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም። ፍላጎቱን እንደ መቃብር ያሰፋል፤እሱ እንደ ሞት ነው፤ ደግሞም ሊጠግብ አይችልም። ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል።
እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም? እንዲህ ይላሉ፦‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት! ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው?
አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም? ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ።
ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤በምድሪቱ፣ በከተሞችናበዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።
ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራትለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት!
በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል። ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ ላይ ኃጢአት ሠርተሃል።
ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል።
ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባናበዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት!
እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም?
ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።
እርቃናቸውን ለማየት ሲልታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት!
በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ። አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ። በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤
በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤በምድር፣ በከተሞቿናበውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል።
የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?
እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤በውስጡም እስትንፋስ የለም።
ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው። ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”
በይሁዳ ንጉሥ በአምዖን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያህ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሺ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦
“ማንኛውንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ” ይላል ይሖዋ።
“ሰውንና እንስሳን ጠራርጌ አጠፋለሁ። የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣንእንዲሁም ማሰናከያዎቹንና ክፉ ሰዎችን ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ደግሞም የሰውን ዘር ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ።
“በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይእጄን እዘረጋለሁ፤የባአልን ቀሪዎች ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስምከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤
በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትንእንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡበሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤
ደግሞም ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ የሚሉትን፣ይሖዋን የማይፈልጉትን ወይም እሱን የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”
በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ ፊት ዝም በሉ፤ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና። ይሖዋ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውን ቀድሷል።
“በይሖዋ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱን፣የንጉሡን ወንዶች ልጆችና የባዕዳንን ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።
በዚያም ቀን መድረኩ ላይ የሚወጡትን ሁሉ፣የጌቶቻቸውንም ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ።
በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ከዓሣ በር የጩኸት ድምፅ፣ከከተማዋም ሁለተኛ ክፍል ዋይታ፣ከኮረብቶቹም ታላቅ ሁከት ይሰማል።
እናንተ የማክተሽ ነዋሪዎች፣ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቹ ሁሉ እንዳልነበሩ ሆነዋልና፤ብር የሚመዝኑትም ሁሉ ጠፍተዋል።
በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንናበልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።
ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ። ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም።
ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ ነው! ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው! የይሖዋ ቀን ድምፅ አስፈሪ ነው። በዚያ ተዋጊው ይጮኻል።
ያ ቀን የታላቅ ቁጣ ቀን፣የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤
በተመሸጉ ከተሞችና በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ባሉ ረጃጅም ማማዎች ላይየቀንደ መለከትና የጦርነት ሁካታ ድምፅ የሚሰማበት ቀን ይሆናል።
በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣለሁ፤እነሱም እንደ ዕውር ይሄዳሉ፤ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተዋል። ደማቸው እንደ አቧራ፣አንጀታቸውም እንደ ፋንድያ ይፈስሳል።
በይሖዋ ታላቅ ቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤መላዋ ምድር በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፤ምክንያቱም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋቸዋል።”
ዓመፀኛ ለሆነችው፣ ለረከሰችውና ለጨቋኟ ከተማ ወዮላት!
ማንንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፤ ምንም ዓይነት ተግሣጽ አልተቀበለችም። በይሖዋ አልታመነችም፤ ወደ አምላኳም አልቀረበችም።
በውስጧ ያሉት መኳንንቷ የሚያገሱ አንበሶች ናቸው። ፈራጆቿ የሌሊት ተኩላዎች ናቸው፤ለጠዋት ምንም ሳያስቀሩ አጥንቱን ሁሉ ይግጣሉ።
ነቢያቷ እብሪተኞችና አታላዮች ናቸው። ካህናቷ ቅዱስ የሆነውን ነገር ያረክሳሉ፤በሕጉ ላይ ያምፃሉ።
በመካከሏ ያለው ይሖዋ ጻድቅ ነው፤ እሱ ምንም ዓይነት ስህተት አይፈጽምም። ፍርዱን እንደማይነጥፍ የንጋት ብርሃን፣በየማለዳው ያሳውቃል። ክፉ ሰው ግን ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም።
“ብሔራትን አጥፍቻለሁ፤ በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ያሉ ማማዎቻቸው ወድመዋል። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፍርሻለሁ። ከተሞቻቸው ፈራርሰዋል፤ በዚያ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም አይገኝባቸውም።
እኔም ‘በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ተግሣጽም ትቀበያለሽ’ አልኩ፤ ይህም መኖሪያዋ እንዳይጠፋ ነው፤ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ተጠያቂ አደርጋታለሁ። እነሱ ግን ብልሹ ነገር ለመፈጸም ይበልጥ ጓጉ።