text stringlengths 4 267 |
|---|
‘ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሳበት ቀን ድረስእኔን በተስፋ ተጠባበቁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ብሔራትን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፣በእነሱም ላይ መዓቴንና የሚነደውን ቁጣዬን ሁሉ ለማውረድ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፌአለሁና፤መላዋ ምድር በቅንዓቴ እሳት ትበላለች። |
በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ስም እንዲጠሩናእጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲያገለግሉትቋንቋቸውን ለውጬ ንጹሕ ቋንቋ እሰጣቸዋለሁ።’ |
የሚለምኑኝ ሰዎች ይኸውም የተበተኑት ሕዝቦቼየኢትዮጵያ ወንዞች ከሚገኙበት ስፍራ ስጦታ ያመጡልኛል። |
በዚያን ቀን በእኔ ላይ በማመፅ በፈጸምሻቸው ሥራዎች ሁሉለኀፍረት አትዳረጊም፤በዚያን ጊዜ በትዕቢት ጉራ የሚነዙትን ከመካከልሽ አስወግዳለሁና፤አንቺም ከእንግዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ፈጽሞ አትታበዪም። |
እኔም ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ በመካከላችሁ እንዲቀር አደርጋለሁ፤እነሱም የይሖዋን ስም መጠጊያቸው ያደርጉታል። |
የእስራኤል ቀሪዎች ምንም ዓይነት ክፋት አይሠሩም፤ውሸት አይናገሩም፤ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ይልቁንም ይመገባሉ፤ ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።” |
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ! እስራኤል ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ! የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በሙሉ ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ! |
ይሖዋ በአንቺ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ሽሯል። ጠላትሽን ከአንቺ መልሷል። የእስራኤል ንጉሥ ይሖዋ በመካከልሽ ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት አያስፈራሽም። |
በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦ “ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ። እጆችሽ አይዛሉ። |
አምላክሽ ይሖዋ በመካከልሽ ነው። እንደ ኃያል ተዋጊ ያድናል። በታላቅ ደስታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። ለአንቺ ፍቅር በማሳየቱ ረክቶ ዝም ይላል። በእልልታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። |
በበዓላትሽ ላይ ባለመገኘታቸው ያዘኑትን ሰዎች እሰበስባለሁ፤ለእሷ ሲሉ በደረሰባቸው ነቀፋ የተነሳ ወደ አንቺ አልመጡም። |
እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤የተበተነችውንም እሰበስባለሁ። ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ። |
በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜበምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና” ይላል ይሖዋ። |
እናንተ ኀፍረት የማይሰማችሁ ሕዝቦች ሆይ፣በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አዎ ተሰብሰቡ። |
የተላለፈው ውሳኔ ከመፈጸሙ በፊት፣ቀኑ እንደ ገለባ ከማለፉ በፊት፣የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ሳይመጣባችሁ፣የይሖዋ የቁጣ ቀን ሳይደርስባችሁ፣ |
እናንተ የጽድቅ ድንጋጌዎቹን የምታከብሩ፣በምድር ላይ የምትኖሩ የዋሆች ሁሉ ይሖዋን ፈልጉ። ጽድቅን ፈልጉ፤ የዋህነትን ፈልጉ። ምናልባት በይሖዋ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል። |
ጋዛ የተተወች ከተማ ትሆናለችና፤አስቀሎንም ባድማ ትሆናለች። አሽዶድ በጠራራ ፀሐይ ትባረራለች፤ኤቅሮንም ከሥሯ ትመነገላለች። |
“በባሕሩ ዳርቻ ለሚኖረው ሕዝብ ይኸውም ለከሪታውያን ብሔር ወዮለት! የይሖዋ ቃል በአንተ ላይ ነው። የፍልስጤማውያን ምድር የሆንሽው ከነአን ሆይ፣ አጠፋሻለሁ፤አንድም ነዋሪ አይተርፍም። |
የባሕሩ ዳርቻም መሰማሪያ ይሆናል፤ለእረኞች የውኃ ጉድጓድና ለበጎች ከድንጋይ የተሠራ ጉረኖ ይኖረዋል። |
ከይሁዳ ቤት ለቀሩት ሰዎች መኖሪያ ስፍራ ይሆናል፤በዚያም የግጦሽ ቦታ ያገኛሉ። በምሽት በአስቀሎን ቤቶች ውስጥ ይተኛሉ። አምላካቸው ይሖዋ ትኩረቱን በእነሱ ላይ ያደርጋልና፤የተማረኩባቸውንም ሰዎች መልሶ ይሰበስባል።” |
“ሞዓብ የሰነዘረችውን ነቀፋና የአሞናውያንን ስድብ ሰምቻለሁ፤እነሱ በሕዝቤ ላይ ተሳልቀዋል፤ ግዛታቸውንም ለመውሰድ በእብሪት ዝተዋል። |
ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ። የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል። |
ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤ምክንያቱም በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል። |
ይሖዋ በእነሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በምድር ላይ ያሉትን አማልክት ሁሉ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋልና፤የብሔራት ደሴቶች ሁሉ በያሉበት ሆነውለእሱ ይሰግዳሉ። |
እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ። |
እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል። |
መንጎች ይኸውም ሁሉም ዓይነት የዱር እንስሳት በውስጧ ይተኛሉ። ሻላ እና ጃርት በፈራረሱት ዓምዶቿ መካከል ያድራሉ። የዝማሬ ድምፅ በመስኮት ይሰማል። ደጃፍ ላይ ፍርስራሽ ይኖራል፤የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶቹ እንዲጋለጡ ያደርጋልና። |
በልቧ ‘እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም’ ስትል የነበረችውያለስጋት የተቀመጠችው ኩሩዋ ከተማ ይህች ናት። ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!የዱር እንስሳት የሚተኙባት ስፍራ ሆናለች። በእሷ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ያፏጫል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።” |
ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል የይሁዳ ገዢ ወደሆነው ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ወደሆነው ወደ የሆጼዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነዚህ ሰዎች “የይሖዋ ቤት የሚገነባበት ጊዜ ገና አልደረሰም” ይላሉ።’” |
የይሖዋም ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል እንዲህ ሲል በድጋሚ መጣ፦ |
“ይህ ቤት ፈርሶ እያለ፣ እናንተ በሚያምር እንጨት በተለበጡ ቤቶቻችሁ ውስጥ የምትኖሩበት ጊዜ ነው? |
አሁንም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ። |
ብዙ ዘር ዘራችሁ፤ የምትሰበስቡት ግን ጥቂት ነው። ትበላላችሁ፤ ሆኖም አትጠግቡም። ትጠጣላችሁ፤ ሆኖም አትረኩም። ትለብሳላችሁ፤ የሚሞቀው ሰው ግን የለም። ተቀጥሮ የሚሠራው ደሞዙን ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ከረጢት ውስጥ ያስቀምጣል።’” |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ።’ |
“‘ወደ ተራራው ወጥታችሁ ጥርብ እንጨት አምጡ። እኔ ደስ እንድሰኝበትና እንድከበርበት ቤቱን ሥሩ’ ይላል ይሖዋ።” |
“‘ብዙ ነገር ጠበቃችሁ፤ ሆኖም ያገኛችሁት ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ባመጣችሁትም ጊዜ እፍ ብዬ በተንኩት። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። ‘የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ እያንዳንዳችሁ የገዛ ቤታችሁን ለማሳመር ስለምትሯሯጡ ነው። |
ስለዚህ ከእናንተ በላይ ያሉት ሰማያት ጠል ማዝነባቸውን አቆሙ፤ ምድርም ፍሬዋን አልሰጥ አለች። |
እኔም በምድር ላይ፣ በተራሮች ላይ፣ በእህሉ ላይ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ ላይ፣ በዘይቱ ላይ፣ ምድሪቱ በምታበቅለው ነገር ላይ፣ በሰዎች ላይ፣ በመንጎች ላይ እንዲሁም እጆቻችሁ በደከሙበት ነገር ሁሉ ላይ ድርቅን ጠራሁ።’” |
የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ የየሆጼዴቅ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱና የቀረው ሕዝብ በሙሉ የአምላካቸውን የይሖዋን ድምፅ እንዲሁም ነቢዩ ሐጌ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ አምላካቸው ይሖዋ ልኮታልና፤ ሕዝቡም ከይሖዋ የተነሳ ፈሩ። |
ከዚያም የይሖዋ መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ከይሖዋ በተሰጠው ተልእኮ መሠረት ለሕዝቡ “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ይላል ይሖዋ” የሚል መልእክት ተናገረ። |
ስለዚህ ይሖዋ የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ መንፈስ በሙሉ አነሳሳ፤ እነሱም መጥተው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመሩ። |
ይህ የሆነው ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን ነበር። |
በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ21ኛው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልንና ሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን ልጅ ኢያሱን እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ እባክህ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦ |
‘የዚህ ቤት የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደነበረ ያየ ሰው በመካከላችሁ አለ? አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር ከምንም የማይቆጠር አይደለም?’ |
“‘አሁን ግን ዘሩባቤል፣ በርታ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የየሆጼዴቅ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ፣ አንተም በርታ።’ “‘እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ፣ በርቱና ሥሩ’ ይላል ይሖዋ። “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
‘ከግብፅ በወጣችሁበት ጊዜ የገባሁላችሁን ቃል አስታውሱ፤ መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራል። አትፍሩ።’” |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ።’ |
“‘ብሔራትንም ሁሉ አናውጣለሁ፤ በብሔራትም ሁሉ መካከል ያሉ የከበሩ ነገሮች ይመጣሉ፤ ደግሞም ይህን ቤት በክብር እሞላዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
“‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
“‘ይህ ቤት ወደፊት የሚጎናጸፈው ክብር ከቀድሞው የበለጠ ይሆናል’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” |
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ነቢዩ ሐጌ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ፣ ካህናቱን ስለ ሕጉ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦ |
“አንድ ሰው በልብሱ እጥፋት የተቀደሰ ሥጋ ቢይዝና ልብሱ ዳቦ፣ ወጥ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት ወይም ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምግብ ቢነካ፣ የነካው ነገር ቅዱስ ይሆናል?”’” ካህናቱ “አይሆንም!” ብለው መለሱ። |
ከዚያም ሐጌ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ “አስከሬን በመንካቱ የረከሰ ሰው ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱን ቢነካ የተነካው ነገር ይረክሳል?” ካህናቱ “አዎ፣ ይረክሳል” ብለው መለሱ። |
ሐጌም እንዲህ አለ፦ “‘ይህም ሕዝብ እንዲሁ ነው፤ ይህም ብሔር በፊቴ እንዲሁ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ የሚያቀርቡት ማንኛውም ነገር የረከሰ ነው።’ |
“‘አሁን ግን እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ይህን ልብ በሉ፦ በይሖዋ ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት፣ |
ያኔ ሁኔታው ምን ይመስል ነበር? አንድ ሰው 20 መስፈሪያ አገኛለሁ ብሎ እህል ወደተከመረበት ቦታ በመጣ ጊዜ 10 መስፈሪያ ብቻ አገኘ፤ ደግሞም አንድ ሰው 50 መለኪያ የወይን ጠጅ ለማግኘት ወደ ወይን መጭመቂያው በመጣ ጊዜ 20 መለኪያ ብቻ አገኘ፤ |
እናንተን ይኸውም የእጃችሁን ሥራ ሁሉ በሚለበልብና በሚያደርቅ ነፋስ፣ በዋግና በበረዶ መታሁ፤ ይሁንና አንዳችሁም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። |
“‘በዛሬው ዕለት ይኸውም በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቤተ መቅደስ መሠረት ተጥሏል። እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ ይህን ልብ በሉ፦ |
በጎተራ ውስጥ የቀረ ዘር አሁንም አለ? የወይን ተክሉ፣ በለሱ፣ ሮማኑና የወይራ ዛፉ እስካሁን ድረስ ፍሬ አላፈሩም። ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’” |
በወሩ 24ኛ ቀን የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ሐጌ መጣ፦ |
“ለይሁዳ ገዢ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፦ ‘ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ። |
የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የብሔራት መንግሥታትንም ብርታት አጠፋለሁ፤ ሠረገላውንና የሚቀመጡበትን ሰዎች እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቹና ጋላቢዎቻቸውም እያንዳንዳቸው በገዛ ወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።’” |
“‘የሰላትያል ልጅ አገልጋዬ ዘሩባቤል ሆይ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በዚያ ቀን እወስድሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ደግሞም እንደ ማኅተም ቀለበት አደርግሃለሁ፤ ምክንያቱም የመረጥኩት አንተን ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” |
“ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት አርዘ ሊባኖሶችህን እንድትበላበሮችህን ክፈት። |
የጥድ ዛፍ ሆይ፣ አርዘ ሊባኖሱ ስለወደቀ ዋይ ዋይ በል፤ታላላቆቹ ዛፎች ወድመዋል! እናንተ የባሳን የባሉጥ ዛፎች፣ጥቅጥቅ ያለው ጫካ ስለጠፋ ዋይ ዋይ በሉ! |
ስሙ! እረኞች ግርማ ሞገሳቸው ስለተገፈፈዋይ ዋይ ይላሉ። አዳምጡ! በዮርዳኖስ አጠገብ ያሉት ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ስለወደሙደቦል አንበሶች ያገሳሉ። |
“አምላኬ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለእርድ የተዘጋጀውን መንጋ ጠብቅ፤ |
የገዟቸው አርደዋቸዋል፤ ሆኖም ተጠያቂ አይሆኑም። የሚሸጧቸውም “ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን፤ ባለጸጋ እሆናለሁና” ይላሉ። እረኞቻቸውም ምንም ዓይነት ርኅራኄ አያሳዩአቸውም።’ |
“‘ከእንግዲህ ለምድሪቱ ነዋሪዎች አልራራላቸውም’ ይላል ይሖዋ። ‘በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው እጅና በንጉሡ እጅ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ እነሱም ምድሪቱን ያደቋታል፤ እኔም እነሱን ከእጃቸው አልታደግም።’” |
እናንተ ጉስቁልና የደረሰባችሁ የመንጋው አባላት፣ ለመታረድ የተዘጋጀውን መንጋ መጠበቅ ጀምሬአለሁ፤ ይህን ያደረግኩትም ለእናንተ ስል ነው። ስለዚህ ሁለት በትሮችን ወስጄ አንደኛውን በትር “ደስታ፣” ሌላኛውን ደግሞ “ኅብረት” ብዬ ጠራሁት፤ እኔም መንጋውን መጠበቅ ጀመርኩ። |
ደግሞም በአንድ ወር ውስጥ ሦስት እረኞችን አባረርኩ፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን መታገሥ ስላልቻልኩና እነሱም እኔን ስለተጸየፉኝ ነው። |
እንዲህም አልኩ፦ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም። የምትሞተው ትሙት፤ የምትጠፋውም ትጥፋ። የቀሩት ደግሞ አንዳቸው የሌላውን ሥጋ ይብሉ።” |
ስለዚህ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን በማፍረስ “ደስታ” የተባለውን በትሬን ወስጄ ሰበርኩት። |
በመሆኑም በዚያን ቀን ቃል ኪዳኑ ፈረሰ፤ ይመለከቱኝ የነበሩት የተጎሳቆሉት የመንጋው አባላትም ይህ የይሖዋ ቃል መሆኑን አወቁ። |
ከዚያም “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደሞዜን ስጡኝ፤ ካልሆነ ግን ተዉት” አልኳቸው። እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ። |
ከዚያም ይሖዋ “እኔን የገመቱበትን የከበረ ዋጋ ይኸውም ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ ጣለው” አለኝ። እኔም 30ውን የብር ሰቅል ወስጄ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ ጣልኩት። |
ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውን ወንድማማችነት በማፍረስ “ኅብረት” የተባለውን ሁለተኛውን በትሬን ሰበርኩት። |
ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እንግዲህ የሰነፍ እረኛ መሣሪያዎችን ውሰድ። |
በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሳለሁና። እያለቁ ያሉትን በጎች አይንከባከብም፤ ግልገሎቹን አይፈልግም ወይም የተጎዳውን አይፈውስም አሊያም መቆም የሚችሉትን አይቀልብም። ከዚህ ይልቅ የሰባውን በግ ሥጋ ይበላል፤ የበጎቹንም ሰኮና ቆርጦ ይጥላል። |
መንጋውን ለሚተው የማይረባ እረኛዬ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይመታዋል። ክንዱ ሙሉ በሙሉ ይሰልላል፤ቀኝ ዓይኑም ሙሉ በሙሉ ይታወራል።” |
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስምንተኛው ወር የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“ይሖዋ በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቆጥቶ ነበር። |
“እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ወደ እኔ ተመለሱ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”’ |
“‘የቀደሙት ነቢያት “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ‘እባካችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ራቁ’ ይላል በማለት የነገሯቸውን አባቶቻችሁን አትምሰሉ።”’ “‘እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለእኔም ትኩረት አልሰጡም’ ይላል ይሖዋ። |
“‘አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያቱስ ለዘላለም መኖር ችለዋል? |
ይሁን እንጂ አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ያዘዝኳቸው ቃልና ድንጋጌ በአባቶቻችሁ ላይ ደርሶ የለም?’ በመሆኑም ወደ እኔ ተመልሰው እንዲህ አሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በወሰነው መሠረት እንደ መንገዳችንና እንደ ሥራችን አደረገብን።’” |
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ ሺባት በተባለው በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ፣ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“በሌሊት ራእይ አየሁ። አንድ ሰው ቀይ ፈረስ እየጋለበ ነበር፤ እሱም በሸለቆው ውስጥ በሚገኙት የአደስ ዛፎች መካከል ቆመ፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡኒና ነጭ ፈረሶች ነበሩ።” |
እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ እነማን ናቸው?” አልኩ። ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ “እነዚህ እነማን እንደሆኑ አሳይሃለሁ” ሲል መለሰልኝ። |
ከዚያም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ የነበረው ሰው “እነዚህ በምድር ላይ እንዲመላለሱ ይሖዋ የላካቸው ናቸው” አለ። |
እነሱም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ ለነበረው የይሖዋ መልአክ “በምድር ላይ ተመላለስን፤ እነሆም መላዋ ምድር ጸጥታና እርጋታ ሰፍኖባታል” አሉት። |
የይሖዋም መልአክ እንዲህ አለ፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በእነዚህ 70 ዓመታት የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ምሕረትህን የምትነፍጋቸው እስከ መቼ ነው?” |
ይሖዋም ሲያነጋግረኝ ለነበረው መልአክ ደግነት በተሞላባቸውና በሚያጽናኑ ቃላት መለሰለት። |
ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ “እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ። |
ዘና ብለው በተቀመጡት ብሔራት ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ፤ ምክንያቱም በመጠኑ ብቻ ተቆጥቼ እያለ እነሱ ግን ከልክ ያለፈ እርምጃ ወሰዱ።”’ |
“ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት እመለሳለሁ፤ የገዛ ቤቴም በውስጧ ይገነባል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “በኢየሩሳሌምም ላይ የመለኪያ ገመድ ይዘረጋል።”’ |
“በድጋሚ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከተሞቼ እንደገና መልካም ነገር ይትረፈረፍባቸዋል፤ ይሖዋም እንደገና ጽዮንን ያጽናናል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።”’” |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.