text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ቀንዶች አየሁ። |
በመሆኑም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። እሱም “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” ሲል መለሰልኝ። |
ከዚያም ይሖዋ አራት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች አሳየኝ። |
እኔም “እነዚህ የመጡት ምን ሊያደርጉ ነው?” ስል ጠየቅኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ፣ ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ ይሁዳን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው። እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ደግሞ እነሱን ለማሸበር፣ ይሁዳን ይበታትኗት ዘንድ በምድሯ ላይ ቀንዶቻቸውን ያነሱትን የብሔራቱን ቀንዶች ለመጣል ይመጣሉ።” |
ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ኪስሌው በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በአራተኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። |
የቤቴል ሰዎች ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳያቸው ለመለመን ሳሬጸርንና ረጌምሜሌክን ከሰዎቹ ጋር ላኩ፤ |
እነሱም የሠራዊት ጌታን የይሖዋን ቤት ካህናትና ነቢያቱን “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግኩት በአምስተኛው ወር ማልቀስና መጾም ይኖርብኛል?” ብለው ጠየቁ። |
የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ |
“ለምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ ‘ለ70 ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ዋይ ዋይ ስትሉ፣ ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር? |
ትበሉና ትጠጡ በነበረበት ጊዜስ ትበሉና ትጠጡ የነበረው ለራሳችሁ አልነበረም? |
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉት ከተሞቿ በሰዎች ተሞልተውና ሰላም ሰፍኖባቸው በነበረበት ጊዜ እንዲሁም ሰዎች በኔጌብና በሸፌላ ይኖሩ በነበረበት ወቅት ይሖዋ በቀድሞዎቹ ነቢያት አማካኝነት ያወጀውን ቃል መታዘዝ አልነበረባችሁም?’” |
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ ዘካርያስ መጣ፦ |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነተኛ ፍትሕ ላይ ተመሥርታችሁ ፍረዱ፤ አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ፍቅርና ምሕረት አሳዩ። |
መበለቲቱንም ሆነ አባት የሌለውን ልጅ፣ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰውም ሆነ ድሃውን አታታሉ፤ ደግሞም አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ።’ |
እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም፤ በግትርነትም ጀርባቸውን ሰጡ፤ ላለመስማትም ሲሉ ጆሯቸውን ደፈኑ። |
ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና ቃል አልታዘዙም። ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።” |
“‘እኔ ስጠራቸው እንዳልሰሙኝ ሁሉ እነሱ ሲጣሩም አልሰማቸውም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
‘ደግሞም ወደማያውቋቸው ብሔራት ሁሉ በአውሎ ነፋስ በተንኳቸው፤ ምድሪቱም ትተዋት ከሄዱ በኋላ ባድማ ሆነች፤ በእሷ የሚያልፍ ወይም ወደ እሷ የሚመለስ ማንም የለም፤ የተወደደችውን ምድር አስፈሪ ቦታ አድርገዋታልና።’” |
“በዚያ ቀን፣ ኃጢአታቸውንና ርኩሰታቸውን ለማንጻት ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የውኃ ጉድጓድ ይቆፈራል። |
“በዚያ ቀን” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “የጣዖቶቹን ስም ከምድሪቱ ላይ እደመስሳለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ አይታወሱም፤ ደግሞም ነቢያቱንና የርኩሰት መንፈሱን ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ። |
አንድ ሰው ዳግመኛ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባትና እናቱ ‘በይሖዋ ስም ሐሰት ስለተናገርክ በሕይወት አትኖርም’ ይሉታል። ደግሞም የወለዱት አባትና እናቱ ትንቢት በመናገሩ ይወጉታል። |
“በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ትንቢት በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በገዛ ራእዩ ያፍራል፤ ሰዎችንም ለማታለል የነቢያት ዓይነት ፀጉራም ልብስ አይለብስም። |
ደግሞም እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ነቢይ አይደለሁም። ይልቁንም አራሽ ነኝ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ልጅ ሳለሁ ባሪያ አድርጎ ገዝቶኛል።’ |
አንድ ሰውም ‘በትከሻዎችህ መካከል ያሉት ቁስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቆሰልኩት ነው’ ይላል።” |
“ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛዬ ይኸውምበወዳጄ ላይ ንቃ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “እረኛውን ምታ፤ መንጋውም ይበተን፤እኔም እጄን ታናናሽ በሆኑት ላይ አዞራለሁ።” |
“በምድሪቱም ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣“በእሷ ላይ ካለው ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤አንድ ሦስተኛው ግን በውስጧ ይቀራል። |
ደግሞም አንድ ሦስተኛው በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ብር እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ። እነሱ ስሜን ይጠራሉ፤እኔም እመልስላቸዋለሁ። ‘እነሱ ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነሱ ደግሞ ‘ይሖዋ አምላካችን ነው’ ይላሉ።” |
እሱም ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በይሖዋ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፤ ሰይጣንም እሱን ለመቃወም በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?” |
ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። |
መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን “ያደፈውን ልብሱን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም እሱን “እነሆ፣ ጥፋትህን አስወግጄልሃለሁ፤ ደግሞም ጥሩ ልብስ ትለብሳለህ” አለው። |
እኔም “በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም ይደረግለት” አልኩ። እነሱም ንጹሑን ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት፤ የይሖዋም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። |
ከዚያም የይሖዋ መልአክ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመንገዶቼ ብትመላለስና በፊቴ ኃላፊነቶችህን ብትወጣ፣ በቤቴ ፈራጅ ሆነህ ታገለግላለህ፤ ቅጥር ግቢዎቼንም ትንከባከባለህ፤ እኔም እዚህ በቆሙት መካከል በነፃነት የመቅረብ መብት እሰጥሃለሁ።’ |
“‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ! |
በኢያሱ ፊት ያስቀመጥኩትን ድንጋይ እዩ! በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እኔም በላዩ ላይ ጽሑፍ እቀርጻለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።’ |
“‘በዚያ ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘እያንዳንዳችሁ ጎረቤታችሁን ከወይናችሁና ከበለስ ዛፋችሁ ሥር እንዲቀመጥ ትጋብዛላችሁ።’” |
የፍርድ መልእክት፦ “የይሖዋ ቃል በሃድራክ ምድር ላይ ነው፤ደማስቆንም ዒላማው አድርጓል፤የይሖዋ ዓይን በሰው ዘርናበእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ነውና፤ |
አዋሳኟ የሆነችውን ሃማትንም ዒላማው አድርጓል፤ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ቢሆኑም እንኳ ጢሮስንና ሲዶናን ዒላማው አድርጓል። |
ጢሮስ የመከላከያ ግንብ ገንብታለች። ብርን እንደ አቧራ፣ወርቅንም በመንገድ ላይ እንዳለ አፈር ቆልላለች። |
እነሆ፣ ይሖዋ ንብረቷን ይወስዳል፤ሠራዊቷንም ባሕሩ ውስጥ ይደመስሳል፤እሷም በእሳት ትበላለች። |
አስቀሎን ይህን አይታ ትፈራለች፤ጋዛ በጣም ትጨነቃለች፤ኤቅሮንም እንዲሁ ትሆናለች፤ ምክንያቱም ተስፋ የምታደርግባት ለኀፍረት ትዳረጋለች። ከጋዛ ንጉሥ ይጠፋል፤አስቀሎንም ሰው አልባ ትሆናለች። |
ዲቃላም በአሽዶድ ይቀመጣል፤እኔም የፍልስጤምን ኩራት አስወግዳለሁ። |
በደም የተበከሉትን ነገሮች ከአፉ፣አስጸያፊ የሆኑትንም ነገሮች ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ከእሱም የሚተርፈው ማንኛውም ሰው የአምላካችን ይሆናል፤እሱም በይሁዳ እንደ አለቃ፣ኤቅሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። |
የሚገባም ሆነ የሚወጣ እንዳይኖር፣ቤቴን ለመጠበቅ በውጭ በኩል ድንኳን እተክላለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ በመካከላቸው የሚያልፍ አሠሪ አይኖርም፤አሁን በገዛ ዓይኔ አይቼዋለሁና። |
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል። እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤ትሑት ነው፤ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ ላይ ይቀመጣል። |
የጦር ሠረገላውን ከኤፍሬም፣ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ። የጦርነቱ ቀስት ይወሰዳል። እሱም ለብሔራት ሰላምን ያውጃል፤ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርእንዲሁም ከወንዙ እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል። |
አንቺ ሴት፣ በእኔና በአንቺ መካከል ካለው የደም ቃል ኪዳን የተነሳእስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቼ እልካቸዋለሁ። |
እናንተ ተስፋ ያላችሁ እስረኞች ወደ ምሽጉ ተመለሱ። ዛሬ እንዲህ እልሻለሁ፦‘ድርሻሽን እጥፍ አድርጌ እከፍልሻለሁ። |
ይሁዳን በእጄ እንዳለ ደጋን እወጥረዋለሁና። ደጋኑን በኤፍሬም እሞላዋለሁ፤ጽዮን ሆይ፣ ወንዶች ልጆችሽን እቀሰቅሳለሁ፤ግሪክ ሆይ፣ በወንዶች ልጆችሽ ላይ ይነሳሉ፤ጽዮን ሆይ፣ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።’ |
ይሖዋ በእነሱ ላይ ይገለጣል፤ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወነጨፋል። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ቀንደ መለከት ይነፋል፤እሱም ከደቡብ አውሎ ነፋሳት ጋር ይሄዳል። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ይከላከልላቸዋል፤እነሱም የሚወነጨፍባቸውን ድንጋይ ውጠው ያስቀራሉ፤ ደግሞም ያመክናሉ። ይጠጣሉ፤ የወይን ጠጅ እንደጠጣም ሰው ይንጫጫሉ፤እንዲሁም እንደ ሳህኖቹናእንደ መሠዊያው ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ። |
በዚያ ቀን አምላካቸው ይሖዋ፣እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፤በአክሊል ላይ እንዳሉ ፈርጦች በምድሩ ላይ ያብረቀርቃሉና። |
ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ያማረ ነው! እህል ወጣት ወንዶችን፣አዲስ የወይን ጠጅም ደናግሉን ያለመልማል።” |
እኔም ቀና ብዬ ስመለከት በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው አየሁ። |
ከዚያም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት። እሱም “ወርዷና ርዝመቷ ምን ያህል እንደሆነ አውቅ ዘንድ ኢየሩሳሌምን ለመለካት እየሄድኩ ነው” ሲል መለሰልኝ። |
እነሆም፣ ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ። |
ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች። |
እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’” |
“ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር ሽሹ” ይላል ይሖዋ። “ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና” ይላል ይሖዋ። |
“ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ። |
ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣ እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን ይነካል። |
አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። |
“የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል ይሖዋ። |
“በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ። |
ይሖዋ ይሁዳን በተቀደሰው ምድር ላይ ድርሻው አድርጎ ይወርሰዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል። |
የሰው ልጆች ሁሉ፣ በይሖዋ ፊት ጸጥ በሉ፤ በቅዱስ መኖሪያው ሆኖ እርምጃ እየወሰደ ነውና። |
“በበልግ ዝናብ ወቅት ይሖዋ ዝናብ እንዲያዘንብላችሁ ጠይቁ። ነጎድጓድ የቀላቀለ ደመና የሚያመጣው፣ለሰዎች ዝናብ የሚያዘንበው፣ለእያንዳንዱም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል የሚሰጠው ይሖዋ ነው። |
የተራፊም ምስሎች አታላይ ነገር ተናግረዋልና፤ሟርተኞችም የሐሰት ራእይ አይተዋል። ከንቱ ስለሆኑ ሕልሞች ይናገራሉ፤በከንቱም ሊያጽናኑ ይሞክራሉ። ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ እንደ በግ ይቅበዘበዛል። እረኛ ስለሌለ ይሠቃያል። |
በእረኞቹ ላይ ቁጣዬ ይነዳል፤ጨቋኞቹንም መሪዎች ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ መንጋው፣ ወደ ይሁዳ ቤት አዙሯልና፤ግርማ ሞገስ እንደተላበሰው የጦር ፈረሱ እነሱንም ግርማ ሞገስ አላብሷቸዋል። |
ከእሱ ቁልፍ የሆነ ሰው፣ድጋፍ የሚሰጥ ገዢናየጦርነት ቀስት ይወጣል፤ተቆጣጣሪዎች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ከእሱ ይወጣሉ። |
እነሱም በጦርነት ጊዜ፣በመንገድ ላይ ያለን ጭቃ እንደሚረግጡ ተዋጊዎች ይሆናሉ። ይሖዋ ከእነሱ ጋር ስለሆነ ይዋጋሉ፤የጠላት ፈረሰኞችም ኀፍረት ይከናነባሉ። |
የይሁዳን ቤት ከሁሉ የላቀ አደርጋለሁ፤የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ። ምሕረት ስለማሳያቸውቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እመልሳቸዋለሁ፤እነሱም ፈጽሞ እንዳልጣልኳቸው ሰዎች ይሆናሉ፤እኔ ይሖዋ አምላካቸው ነኝና፤ ደግሞም እመልስላቸዋለሁ። |
የኤፍሬም ሰዎች እንደ ኃያል ተዋጊ ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደጠጣ ሰው ሐሴት ያደርጋል። ልጆቻቸው ይህን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤ልባቸውም በይሖዋ ደስ ይለዋል። |
‘አፏጭቼ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤እዋጃቸዋለሁና፣ ብዙ ይሆናሉ፤መባዛታቸውንም ይቀጥላሉ። |
በሕዝቦች መካከል እንደ ዘር ብበትናቸውም፣በሩቅ ስፍራዎች ሆነው ያስታውሱኛል፤ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ያንሰራራሉ፤ ደግሞም ይመለሳሉ። |
ከግብፅ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከአሦርም አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ወደ ጊልያድ ምድርና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም። |
እሱም ባሕሩን አስጨንቆ ያልፋል፤በባሕሩም ውስጥ ሞገዱን ይመታል፤የአባይ ጥልቆች በሙሉ ይደርቃሉ። የአሦር ኩራት ይዋረዳል፤የግብፅም በትረ መንግሥት ይወገዳል። |
በይሖዋ ብርቱ አደርጋቸዋለሁ፤በስሙም ይሄዳሉ’ ይላል ይሖዋ።” |
ዳግመኛ ቀና ብዬ ስመለከት የሚበር ጥቅልል አየሁ። |
እሱም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “ርዝመቱ 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10 ክንድ የሆነ የሚበር ጥቅልል አያለሁ” ስል መለስኩለት። |
ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በመላው ምድር ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ ምክንያቱም የሚሰርቁ ሁሉ በአንደኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም፤ ደግሞም በሐሰት የሚምሉ ሁሉ በሌላኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም። |
‘እኔ ልኬዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘ወደ ሌባውም ቤት ይገባል፤ በስሜ በሐሰት ወደሚምለውም ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ቤት ውስጥ ይቀመጣል፤ እንጨቱንና ድንጋዩን ጨምሮ ቤቱን ይበላዋል።’” |
ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ ወደ እኔ ቀርቦ “እባክህ ቀና ብለህ የምትወጣውን ነገር ተመልከት” አለኝ። |
እኔም “ምንድን ነች?” አልኩ። እሱም መልሶ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለ። አክሎም “በምድሪቱ ሁሉ የሰዎቹ መልክ ይህ ነው” አለ። |
እኔም ከእርሳስ የተሠራው ክቡ መክደኛ ሲነሳ አየሁ፤ በመስፈሪያዋም ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። |
እሱም “ይህች ሴት ክፋትን ታመለክታለች” አለኝ። ከዚያም የኢፍ መስፈሪያዋ ውስጥ መልሶ ጣላት፤ ቀጥሎም ከእርሳስ የተሠራውን ከባዱን መክደኛ መስፈሪያዋ አፍ ላይ ገጠመው። |
ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት ሁለት ሴቶች ወደ ፊት ሲመጡ አየሁ፤ በነፋስም መካከል ወደ ላይ ተወነጨፉ። ክንፎቻቸው የራዛ ዓይነት ክንፎች ነበሩ። እነሱም መስፈሪያዋን በምድርና በሰማይ መካከል አነሷት። |
እኔም ያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “የኢፍ መስፈሪያዋን ወዴት እየወሰዷት ነው?” ስል ጠየቅኩት። |
እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ቤት ሊሠሩላት ወደ ሰናኦር ምድር እየወሰዷት ነው፤ ቤቱም በተዘጋጀ ጊዜ በዚያ በተገቢው ቦታዋ ላይ ያስቀምጧታል።” |
“እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ከአንቺ የተማረከው በመካከልሽ ይከፋፈላል። |
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ ብሔራትን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች፤ ቤቶቹ ይዘረፋሉ፤ ሴቶቹም ይደፈራሉ። የከተማዋም እኩሌታ ለግዞት ይዳረጋል፤ ከሕዝቡ መካከል የሚቀሩት ሰዎች ግን ከከተማዋ አይወገዱም። |
“ይሖዋ ይወጣል፤ በጦርነት ቀን እንደሚዋጋው እነዚያን ብሔራት ይዋጋል። |
በዚያ ቀን እግሮቹ በስተ ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ትይዩ በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ አንስቶ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሁለት ይከፈላል፤ እጅግ ትልቅ ሸለቆም ይፈጠራል፤ የተራራው አንዱ ግማሽ ወደ ሰሜን፣ ሌላው ግማሽ ደግሞ ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል። |
እናንተ በተራሮቼ መካከል ወዳለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በተራሮቹ መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አዜል ድረስ ይደርሳልና። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ ሸሽታችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁንም ትሸሻላችሁ። አምላኬ ይሖዋም ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ከእሱ ጋር ይሆናሉ። |
“በዚያ ቀን ደማቅ ብርሃን አይኖርም፤ ነገሮች ሁሉ ባሉበት ይረጋሉ። |
ያም ቀን የይሖዋ ቀን ተብሎ የሚታወቅ ልዩ ቀን ይሆናል። ቀንም ሆነ ሌሊት አይሆንም፤ በመሸም ጊዜ ብርሃን ይኖራል። |
በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ሕያው ውኃዎች ይወጣሉ፤ ግማሾቹ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ባሕር፣ ግማሾቹ ደግሞ በስተ ምዕራብ ወዳለው ባሕር ይፈስሳሉ። ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል። |
ይሖዋም በመላው ምድር ላይ ይነግሣል። በዚያ ቀን ይሖዋ አንድ፣ ስሙም አንድ ይሆናል። |
“ከጌባ አንስቶ ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ እስካለችው እስከ ሪሞን ድረስ መላው ምድር እንደ አረባ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በቀድሞ ስፍራዋ ላይ ትነሳለች፤ የሰዎችም መኖሪያ ትሆናለች፤ ደግሞም ከቢንያም በር አንስቶ እስከ መጀመሪያው በርና እስከ ማዕዘን በር ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ እንዲሁም ከሃናንኤል ማማ አንስቶ እስከ ንጉሡ የወይን መጭመቂያዎች ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ ሰው ይኖርበታል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.