text stringlengths 4 267 |
|---|
ገና እየተናገረ ሳለ ብዙ ሰዎች መጡ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ የተባለውም ሰው ይመራቸው ነበር፤ ሊስመውም ወደ ኢየሱስ ተጠጋ። |
ኢየሱስ ግን “ይሁዳ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህ?” አለው። |
በዙሪያው የነበሩትም አዝማሚያውን ሲያዩ “ጌታ ሆይ፣ በሰይፍ እንምታቸው?” አሉት። |
እንዲያውም ከመካከላቸው አንዱ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው። |
ኢየሱስ ግን መልሶ “ተዉ!” አለ። ጆሮውንም ዳሶ ፈወሰው። |
ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ? |
በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም። ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።” |
ከዚያም ሰዎቹ ይዘው ወሰዱትና ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተል ነበር። |
በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ። |
ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። |
እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ። |
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው አየውና “አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ አይደለሁም” አለ። |
አንድ ሰዓት ያህል ካለፈ በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው “ይህ ሰው፣ የገሊላ ሰው ስለሆነ በእርግጥ ከእሱ ጋር ነበር!” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። |
ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ ምን እንደምታወራ አላውቅም” አለ። ገና እየተናገረም ሳለ ዶሮ ጮኸ። |
በዚህ ጊዜ ጌታ ዞር ብሎ ጴጥሮስን ትክ ብሎ አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። |
ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። |
ኢየሱስን የያዙት ሰዎችም እየመቱት ያሾፉበት ጀመር፤ |
ፊቱንም ከሸፈኑት በኋላ “እስቲ ትንቢት ተናገር! የመታህ ማን ነው?” እያሉ ይጠይቁት ነበር። |
በእሱም ላይ ሌላ ብዙ የስድብ ቃል ይሰነዝሩ ነበር። |
በነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችንና ጸሐፍትን ጨምሮ የሕዝቡ ሽማግሌዎች ጉባኤ አንድ ላይ ተሰበሰበ፤ ኢየሱስንም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሻቸው አምጥተው እንዲህ አሉት፦ |
“አንተ ክርስቶስ ከሆንክ ንገረን።” እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ብነግራችሁም እንኳ ፈጽሞ አታምኑም። |
ብጠይቃችሁም አትመልሱም። |
ያም ሆነ ይህ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኃያሉ አምላክ ቀኝ ይቀመጣል።” |
በዚህ ጊዜ ሁሉም “ስለዚህ የአምላክ ልጅ ነህ ማለት ነው?” አሉት። እሱም “የአምላክ ልጅ መሆኔን እናንተው ራሳችሁ እየተናገራችሁ ነው” አላቸው። |
እነሱም “ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልገናል? እኛ ራሳችን ከገዛ አፉ ሰምተነዋል” አሉ። |
አንድ ቀን ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በዙሪያው ተሰበሰቡ። |
ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም “ይህ ሰው ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነሱም ጋር ይበላል” እያሉ አጉረመረሙ። |
በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፦ |
“ከእናንተ መካከል 100 በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበት 99ኙን በምድረ በዳ ትቶ የጠፋችውን እስኪያገኝ ድረስ አይፈልግም? |
በሚያገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ላይ ይሸከማታል። |
ቤት ሲደርስም ጓደኞቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋችውን በጌን ስላገኘኋት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ይላቸዋል። |
እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ መግባት ከማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል። |
“ወይም ደግሞ አሥር ድራክማ ሳንቲሞች ያሏት አንዲት ሴት አንዱ ድራክማ ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤቷን በመጥረግ እስክታገኘው ድረስ በደንብ አትፈልገውም? |
ሳንቲሙን ባገኘችው ጊዜም ጓደኞቿንና ጎረቤቶቿን በአንድነት ጠርታ ‘የጠፋብኝን ድራክማ ሳንቲም ስላገኘሁት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ትላቸዋለች። |
እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በአምላክ መላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል።” |
ከዚያም እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። |
ታናሽየውም ልጅ አባቱን ‘አባቴ ሆይ፣ ከንብረትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። በመሆኑም አባትየው ንብረቱን ለልጆቹ አካፈላቸው። |
ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሽየው ልጅ ያለውን ነገር ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በዚያም ልቅ የሆነ ሕይወት በመኖር ንብረቱን አባከነ። |
ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር በሙሉ ከባድ ረሃብ ተከሰተ፤ በዚህ ጊዜ ችግር ላይ ወደቀ። |
ከችግሩም የተነሳ ከዚያ አገር ሰዎች ወደ አንዱ ሄዶ የሙጥኝ አለ፤ ሰውየውም አሳማ እንዲጠብቅለት ወደ ሜዳ ላከው። |
እሱም አሳማዎቹ የሚመገቡትን ምግብ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን የሚሰጠው አልነበረም። |
“ወደ ልቦናው ሲመለስ ግን እንዲህ አለ፦ ‘ስንቶቹ የአባቴ ቅጥር ሠራተኞች ምግብ ተርፏቸው እኔ እዚህ በረሃብ ልሞት ነው! |
ተነስቼ ወደ አባቴ በመሄድ እንዲህ እለዋለሁ፦ “አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። |
ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም። ከቅጥር ሠራተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ።”’ |
ስለዚህ ተነስቶ ወደ አባቱ ሄደ። ገና ሩቅ ሳለም አባቱ አየው፤ በዚህ ጊዜ አንጀቱ ተላወሰ፤ እየሮጠ ሄዶም አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው። |
ከዚያም ልጁ ‘አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። |
አባትየው ግን ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ቶሎ በሉ! ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጥታችሁ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት። |
የሰባውንም ጥጃ አምጥታችሁ እረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት። |
ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል። ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር። |
“በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በእርሻ ቦታ ነበር፤ ተመልሶ መጥቶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ። |
ስለዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው። |
አገልጋዩም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደህና ስለመጣም አባትህ የሰባውን ጥጃ አርዶለታል’ አለው። |
እሱ ግን ተቆጣ፤ ወደ ቤት ለመግባትም አሻፈረኝ አለ። ከዚያም አባቱ ወጥቶ ይለምነው ጀመር። |
እሱም መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ እኔ ስንት ዓመት ሙሉ እንደ ባሪያ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ መቼም ቢሆን ከትእዛዝህ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ አንተ ግን ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም። |
ሆኖም ሀብትህን ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያወደመው ይህ ልጅህ ገና ከመምጣቱ የሰባውን ጥጃ አረድክለት።’ |
በዚህ ጊዜ አባቱ እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ደግሞም የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው። |
ሆኖም ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል። ስለዚህ ልንደሰትና ሐሴት ልናደርግ ይገባል።’” |
ከዚያም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም ሳለ መንፈስ ይመራው ነበር፤ |
በዚያም 40 ቀን ቆየ፤ ዲያብሎስም ፈተነው። በእነዚህም ቀናት ምንም ስላልበላ መጨረሻ ላይ ተራበ። |
በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህ ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን እዘዝ” አለው። |
ኢየሱስ ግን “‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት። |
ቀጥሎም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍ ያለ ቦታ አወጣውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው። |
ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህ መንግሥታት ክብር ተሰጥቶኛል፤ እኔ ደግሞ ለፈለግኩት መስጠት ስለምችል ለአንተ እሰጥሃለሁ። |
ስለዚህ አንድ ጊዜ በፊቴ ተደፍተህ ብታመልከኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” |
ኢየሱስም መልሶ “‘ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው። |
ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት ላይ አቁሞ እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ |
እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘አንተን እንዲጠብቁ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ |
እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’” |
ኢየሱስም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን አትፈታተነው’ ተብሏል” አለው። |
ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ። ዝናውም በዙሪያው ባለ አገር ሁሉ ተሰራጨ። |
በተጨማሪም በምኩራቦቻቸው ማስተማር ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያከብረው ነበር። |
ከዚያም ወዳደገበት ቦታ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነስቶ ቆመ። |
የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልልም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም ተርትሮ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፦ |
“የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ለድሆች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ለተማረኩት ነፃነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቆኑትን ነፃ እንዳወጣ |
እንዲሁም የይሖዋን ሞገስ ስለሚያገኙበት ዓመት እንድሰብክ ልኮኛል።” |
ከዚያም ጥቅልሉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። |
እሱም “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው። |
ሁሉም ስለ እሱ መልካም ነገር ይናገሩ ጀመር፤ ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላትም በመደነቅ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “‘አንተ ሐኪም፣ እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን አባባል እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም። ‘በቅፍርናሆም እንደተደረገ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ አገርም አድርግ’ ትሉኛላችሁ።” |
እንዲህም አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት አያገኝም። |
እውነቱን ልንገራችሁ፦ ለምሳሌ በኤልያስ ዘመን ሰማይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋና በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጽኑ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ። |
ሆኖም ኤልያስ በሲዶና አገር በሰራፕታ ትኖር ወደነበረች አንዲት መበለት ተላከ እንጂ ከእነዚህ ሴቶች ወደ አንዷም አልተላከም። |
በተጨማሪም በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመን በእስራኤል ብዙ የሥጋ ደዌ በሽተኞች ነበሩ፤ ሆኖም ከሶርያዊው ከንዕማን በስተቀር ከእነሱ መካከል አንድም ሰው አልነጻም።” |
በምኩራቡ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤ |
ተነስተውም እያጣደፉ ከከተማው አስወጡት፤ ቁልቁል ገፍትረው ሊጥሉትም ፈልገው ከተማቸው ወደምትገኝበት ተራራ አፋፍ ወሰዱት። |
እሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ። |
ከዚያም በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ። እዚያም በሰንበት ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤ |
በሥልጣን ይናገር ስለነበረም ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ። |
በምኩራቡም ውስጥ ርኩስ መንፈስ ማለትም ጋኔን ያደረበት አንድ ሰው ነበር፤ ሰውየውም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦ |
“እንዴ! የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ።” |
ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ከጣለው በኋላ ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ። |
በዚህ ጊዜ ሁሉም በመገረም “እንዴ! ይህ ምን ዓይነት አነጋገር ነው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛል፤ እነሱም ታዘው ይወጣሉ!” ሲሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። |
ስለ ኢየሱስ የሚወራው ወሬም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተዳረሰ። |
ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት። |
እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር። |
ፀሐይ ስትጠልቅም ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው። |
አጋንንትም “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉና እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም አውቀው ስለነበር እንዳይናገሩ ከለከላቸው። |
በነጋም ጊዜ ወጥቶ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ። ሕዝቡ ግን ፈልገው ፈላልገው ያለበት ቦታ ድረስ መጡ፤ እንዳይሄድባቸውም ለመኑት። |
እሱ ግን “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” አላቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.