text stringlengths 4 267 |
|---|
በመሆኑም በይሁዳ ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ። |
አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕዝቡን እያስተማረና ምሥራቹን እያወጀ ሳለ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር መጡ፤ |
ከዚያም “እስቲ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት። |
እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፦ |
ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን ያገኘው ከአምላክ ነው ወይስ ከሰው?” |
እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ |
‘ከሰው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብለው ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” |
ስለዚህ ‘ከየት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው መለሱለት። |
ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው። |
ከዚያም ለሕዝቡ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማና ለገበሬዎች አከራየ፤ ወደ ሌላ አገር ሄዶም ረዘም ላለ ጊዜ ቆየ። |
ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን እንዲልኩለት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ይሁንና ገበሬዎቹ ባሪያውን ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት። |
እሱ ግን በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። ይሄኛውንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን ሰደዱት። |
አሁንም ሦስተኛ ባሪያ ላከ፤ እሱንም ካቆሰሉት በኋላ አውጥተው ጣሉት። |
በዚህ ጊዜ የወይን እርሻው ባለቤት ‘ምን ባደርግ ይሻላል? የምወደውን ልጄን እልካለሁ። መቼም እሱን ያከብሩታል’ አለ። |
ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ርስቱ የእኛ እንዲሆን እንግደለው’ ተባባሉ። |
ከዚያም ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት። ታዲያ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል? |
ይመጣና እነዚህን ገበሬዎች ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።” ሕዝቡም ይህን ሲሰሙ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ። |
ኢየሱስም እነሱን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “ታዲያ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ትርጉሙ ምንድን ነው? |
በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።” |
በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ የተናገረው እነሱን አስቦ እንደሆነ ስለተረዱ በዚያኑ ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሕዝቡን ፈሩ። |
በቅርብ ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ በንግግሩ እንዲያጠምዱት ጻድቅ መስለው የሚቀርቡ ሰዎችን በድብቅ ቀጥረው ላኩ፤ ይህን ያደረጉት ለመንግሥትና ለአገረ ገዢው አሳልፈው ለመስጠት ነው። |
የተላኩትም ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ “መምህር፣ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም እንደማታዳላ፣ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፦ |
ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባናል ወይስ አይገባንም?” |
እሱ ግን ተንኮላቸው ገብቶት እንዲህ አላቸው፦ |
“እስቲ አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ላይ ያለው ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” እነሱም “የቄሳር” አሉ። |
እሱም “እንግዲያው የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ ስጡ” አላቸው። |
እነሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ከዚህ ይልቅ በመልሱ በመገረም ዝም አሉ። |
ሆኖም በትንሣኤ ከማያምኑት ሰዱቃውያን መካከል አንዳንዶቹ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፦ |
“መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሎ ጽፎልናል። |
እንግዲህ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ሆኖም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። |
ሁለተኛውም እንደዚሁ፤ |
ሦስተኛውም አገባት። በዚሁ አኳኋን ሰባቱም አግብተዋት ልጆች ሳይወልዱ ሞቱ። |
በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። |
እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?” |
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ሥርዓት ልጆች ያገባሉ እንዲሁም ይዳራሉ፤ |
ሆኖም የሚመጣውን ሥርዓት መውረስና የሙታን ትንሣኤን ማግኘት የሚገባቸው አያገቡም እንዲሁም አይዳሩም። |
እንዲያውም እንደ መላእክት ስለሆኑ ከዚያ በኋላ ሊሞቱ አይችሉም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለሆኑም የአምላክ ልጆች ናቸው። |
ይሁንና ሙሴም እንኳ ስለ ቁጥቋጦው በሚገልጸው ታሪክ ላይ ይሖዋን ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ በጠራው ጊዜ ሙታን እንደሚነሡ አስታውቋል። |
እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ በእሱ ፊት ሁሉም ሕያዋን ናቸውና።” |
በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት “መምህር፣ ጥሩ ብለሃል” አሉ። |
ከዚያ በኋላ አንድም ጥያቄ ሊጠይቁት አልደፈሩም። |
እሱ ደግሞ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ሰዎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ? |
ምክንያቱም ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ |
ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’ |
ስለዚህ ዳዊት ‘ጌታ’ ብሎ ጠርቶታል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?” |
ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ |
“ዘርፋፋ ልብስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ከሚሹ እንዲሁም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣ በራት ግብዣ ላይም የክብር ቦታ መያዝ ከሚፈልጉ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ |
እነሱ የመበለቶችን ቤት ያራቁታሉ፤ ለታይታ ብለውም ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ። እነዚህ የከፋ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።” |
በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ እርስ በርስ እየተጋፋ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ ኢየሱስ በቅድሚያ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከፈሪሳውያን እርሾ ይኸውም ከግብዝነት ተጠንቀቁ። |
ይሁንና የተሰወረ መገለጡ፣ ሚስጥር የሆነም መታወቁ አይቀርም። |
ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በጓዳ የምታንሾካሹኩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። |
በተጨማሪም ወዳጆቼ ሆይ፣ እላችኋለሁ፣ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በላይ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ። |
ይልቁንስ ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፦ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም የመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎ፣ እላችኋለሁ እሱን ፍሩ። |
አምስት ድንቢጦች አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ሁለት ሳንቲሞች ይሸጡ የለም? ሆኖም አንዷም እንኳ በአምላክ ዘንድ አትረሳም። |
የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል። አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ። |
“እላችኋለሁ፣ በሰዎች ፊት የሚመሠክርልኝን ሁሉ የሰው ልጅም በአምላክ መላእክት ፊት ይመሠክርለታል። |
በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ ግን በአምላክ መላእክት ፊት ይካዳል። |
በሰው ልጅ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ይቅር ይባልለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን ይቅር አይባልም። |
በሕዝባዊ ሸንጎዎች እንዲሁም በመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት ፊት ሲያቀርቧችሁ እንዴት ብለን ወይም ምን ብለን የመከላከያ መልስ እንሰጣለን ወይም ደግሞ ምን እንላለን ብላችሁ አትጨነቁ፤ |
ምን መናገር እንዳለባችሁ መንፈስ ቅዱስ በዚያኑ ሰዓት ያስተምራችኋልና።” |
ከዚያም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው “መምህር፣ ወንድሜ ውርሳችንን እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው። |
ኢየሱስም “አንተ ሰው፣ በእናንተ መካከል ፈራጅና ዳኛ እንድሆን ማን ሾመኝ?” አለው። |
ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ተጠበቁ” አላቸው። |
ይህን ካለ በኋላ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው መሬቱ ብዙ ምርት አስገኘለት። |
በመሆኑም ‘ምርቴን የማከማችበት ቦታ ስለሌለኝ ምን ባደርግ ይሻላል?’ ብሎ በልቡ ማሰብ ጀመረ። |
ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ |
ነፍሴንም “ነፍሴ ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ |
አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው። |
ለራሱ ሀብት የሚያከማች በአምላክ ዘንድ ግን ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።” |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንበላለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ። |
ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ የላቀ ዋጋ አለውና። |
ቁራዎችን ተመልከቱ፦ አይዘሩም፣ አያጭዱም እንዲሁም የእህል ማከማቻ ወይም ጎተራ የላቸውም፤ ሆኖም አምላክ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ የላቀ ዋጋ የላችሁም? |
ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ይኖራል? |
ታዲያ እንዲህ ያለውን ትንሽ ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌሎች ነገሮች ለምን ትጨነቃላችሁ? |
እስቲ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፦ አይለፉም ወይም አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ያን ያህል ክብር የነበረው ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም። |
አምላክ ዛሬ ያለውንና ነገ ወደ ምድጃ የሚጣለውን በሜዳ ያለ ተክል እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ! |
ስለዚህ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት ነገር ከልክ በላይ አታስቡ፤ እንዲሁም አትጨነቁ፤ |
እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዓለም ያሉ ሰዎች አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው፤ ይሁንና አባታችሁ እነዚህ ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። |
ይልቁንስ ዘወትር መንግሥቱን ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ይሰጧችኋል። |
“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤ አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና። |
ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ። የማያረጁ የገንዘብ ኮሮጆዎች አዘጋጁ፤ አዎ፣ ሌባ በማይደርስበት፣ ብልም ሊበላው በማይችልበት በሰማያት ለራሳችሁ የማያልቅ ውድ ሀብት አከማቹ። |
ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና። |
“ወገባችሁን ታጠቁ፤ መብራታችሁንም አብሩ፤ |
ጌታቸው ከሠርግ እስኪመለስ እንደሚጠባበቁና መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት እንደተዘጋጁ ዓይነት ሰዎች ሁኑ። |
ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠባበቁ የሚያገኛቸው ባሪያዎች ደስተኞች ናቸው! እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታቸው ለሥራ ካሸረጠና በማዕድ እንዲቀመጡ ካደረገ በኋላ ቆሞ ያስተናግዳቸዋል። |
በሁለተኛው ክፍለ ሌሊትም ይምጣ በሦስተኛው፣ ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ካገኛቸው ደስተኞች ናቸው! |
ነገር ግን ይህን እወቁ፤ አንድ ሰው ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር። |
እናንተም የሰው ልጅ ይመጣል ብላችሁ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁ።” |
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ እየተናገርክ ያለኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም?” አለው። |
ጌታም እንዲህ አለ፦ “ጌታው ምንጊዜም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው በአገልጋዮቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ በእርግጥ ማን ነው? |
ጌታው ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው! |
እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። |
ነገር ግን ያ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ የሚመጣው ዘግይቶ ነው’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ እንዲሁም መብላት፣ መጠጣትና መስከር ቢጀምር |
የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤ ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤ ዕጣውንም ታማኝ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ያደርገዋል። |
ደግሞም የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ተዘጋጅቶ ያልጠበቀው ወይም ጌታው የጠየቀውን ነገር ያላደረገው ያ ባሪያ ብዙ ግርፋት ይገረፋል። |
ነገር ግን ሳያውቅ፣ ግርፋት የሚገባው ድርጊት የፈጸመ ጥቂት ይገረፋል። በእርግጥም ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይጠበቅበታል፤ ብዙ ኃላፊነት የተሰጠውም ብዙ ይጠበቅበታል። |
“እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኮስ ነው፤ ታዲያ እሳቱ ከተቀጣጠለ ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ? |
እርግጥ እኔ የምጠመቀው አንድ ጥምቀት አለኝ፤ ይህ እስኪፈጸም ድረስ በጣም ተጨንቄአለሁ! |
የመጣሁት በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን ይመስላችኋል? በፍጹም አይደለም፤ እላችኋለሁ፣ የመጣሁት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ለመከፋፈል ነው። |
ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤት ውስጥ እርስ በርስ የተከፋፈሉ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ ሁለቱ ደግሞ በሦስቱ ላይ ይነሳሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.