text stringlengths 4 267 |
|---|
ስለዚህ አሁን የምንነግርህን ነገር አድርግ፦ ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። |
እነዚህን ሰዎች ይዘህ በመሄድ ከእነሱ ጋር የመንጻት ሥርዓት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ክፈልላቸው። ይህን ካደረግክ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና አንተም ሕጉን እያከበርክ በሥርዓት እንደምትኖር ሁሉም ሰው ያውቃል። |
ከአሕዛብ የመጡትን አማኞች በተመለከተ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋና ከፆታ ብልግና እንዲርቁ ወስነን ደብዳቤ ጽፈንላቸዋል።” |
ከዚያም ጳውሎስ በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ በመሄድ አብሯቸው የመንጻት ሥርዓቱን ፈጸመ፤ የመንጻት ሥርዓቱ የሚያበቃበትን ቀንና ለእያንዳንዳቸው መባ የሚቀርብበትን ጊዜ ለማሳወቅም ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። |
ሰባቱ ቀናት ሊጠናቀቁ በተቃረቡበት ጊዜ ከእስያ የመጡ አይሁዳውያን ጳውሎስን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያዩት ሕዝቡን ሁሉ ለሁከት በማነሳሳት ያዙት፤ |
እንዲህ እያሉም ጮኹ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እርዱን! በሄደበት ቦታ ሁሉ ለሚያገኛቸው ሰዎች ሕዝባችንን፣ ሕጋችንንና ይህን ስፍራ የሚቃወም ትምህርት የሚያስተምረው ይህ ሰው ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የግሪክ ሰዎችን ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞ በመምጣት ይህን ቅዱስ ስፍራ አርክሷል።” |
ይህን ያሉት ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጢሮፊሞስን ከእሱ ጋር ከተማው ውስጥ አይተውት ስለነበር ነው፤ ደግሞም ጳውሎስ ይህን ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞት የገባ መስሏቸው ነበር። |
በመሆኑም ከተማዋ በሙሉ ታወከች፤ ሕዝቡም ግር ብለው እየሮጡ በመምጣት ጳውሎስን ያዙት፤ እየጎተቱም ከቤተ መቅደሱ አወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ። |
ሊገድሉትም እየሞከሩ ሳለ መላዋ ኢየሩሳሌም እንደታወከች የሚገልጽ ወሬ ለሠራዊቱ ሻለቃ ደረሰው፤ |
እሱም ወዲያውኑ ወታደሮችንና የጦር መኮንኖችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነሱ ወረደ። እነሱም ሻለቃውንና ወታደሮቹን ሲያዩ ጳውሎስን መደብደባቸውን ተዉ። |
በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ ቀርቦ በቁጥጥር ሥር አዋለውና በሁለት ሰንሰለት እንዲታሰር አዘዘ፤ ከዚያም ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ። |
ከሕዝቡም መካከል አንዳንዶች አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር ይናገሩ ነበር። ስለዚህ ሻለቃው ከጫጫታው የተነሳ ምንም የተጨበጠ ነገር ማግኘት ስላልቻለ ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲወሰድ አዘዘ። |
ሆኖም ጳውሎስ ወደ ደረጃው በደረሰ ጊዜ ከሕዝቡ ዓመፅ የተነሳ ወታደሮቹ ተሸክመውት ለመሄድ ተገደዱ፤ |
ብዙ ሕዝብም እየተከተለ “ግደለው!” እያለ ይጮኽ ነበር። |
ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈሩ ሊያስገቡት በተቃረቡ ጊዜ ሻለቃውን “አንዴ ላናግርህ?” አለው። ሻለቃውም እንዲህ አለው፦ “ግሪክኛ መናገር ትችላለህ እንዴ? |
አንተ ከዚህ ቀደም ዓመፅ አነሳስተህ 4,000 ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ምድረ በዳ ያሸፈትከው ግብፃዊ አይደለህም?” |
በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እኔ እንኳ በኪልቅያ የምትገኘው የታወቀችው የጠርሴስ ከተማ ነዋሪ የሆንኩ አይሁዳዊ ነኝ። ስለዚህ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ” አለ። |
ከፈቀደለት በኋላ ጳውሎስ ደረጃው ላይ ቆሞ ለሕዝቡ በእጁ ምልክት ሰጠ። ታላቅ ጸጥታ በሰፈነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ |
አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ሰዓት ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደሱ እየወጡ ነበር፤ |
ሰዎችም ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ተሸክመው በማምጣት ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገባው ሰው ምጽዋት እንዲለምን “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደሱ በር አጠገብ በየዕለቱ ያስቀምጡት ነበር። |
ይህ ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ አያቸውና ምጽዋት እንዲሰጡት ይለምናቸው ጀመር። |
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን ትኩር ብለው አዩት፤ ከዚያም ጴጥሮስ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው። |
ሰውየውም የሆነ ነገር ሊሰጡኝ ነው ብሎ በማሰብ ትኩር ብሎ ተመለከታቸው። |
ይሁንና ጴጥሮስ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተራመድ!” አለው። |
ከዚያም ቀኝ እጁን ይዞ አስነሳው። ወዲያውም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጠነከረ፤ |
ዘሎም ተነሳ፤ መራመድም ጀመረ፤ ደግሞም እየተራመደና እየዘለለ እንዲሁም አምላክን እያወደሰ ከእነሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። |
ሰዎቹም ሁሉ ሲራመድና አምላክን ሲያወድስ አዩት። |
ይህ ሰው “ውብ በር” በተባለው የቤተ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው ሰው መሆኑን ስላወቁ በእሱ ላይ በተፈጸመው ሁኔታ እጅግ ተገረሙ፤ በአድናቆትም ተዋጡ። |
ሰውየው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዟቸው ሳለ በዚያ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እጅግ ተደንቀው እነሱ ወዳሉበት “የሰለሞን መተላለፊያ” ወደሚባለው ስፍራ ግር ብለው እየሮጡ መጡ። |
ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞስ በእኛ ኃይል ወይም እኛ ለአምላክ ያደርን በመሆናችን የተነሳ ይህን ሰው እንዲራመድ ያስቻልነው ይመስል ለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ? |
የአባቶቻችን አምላክ ይኸውም የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ የነበረ ቢሆንም በእሱ ፊት የካዳችሁትን አገልጋዩን ኢየሱስን አከበረው። |
አዎ፣ እናንተ ይህን ቅዱስና ጻድቅ ሰው ክዳችሁ ነፍሰ ገዳይ የሆነን ሰው እንዲፈታላችሁ ጠየቃችሁ፤ |
በአንጻሩ ግን የሕይወትን “ዋና ወኪል” ገደላችሁት። አምላክ ግን ከሞት አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን። |
የኢየሱስ ስምና እኛ በስሙ ላይ ያለን እምነት ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን ሰው አጠነከረው። በኢየሱስ አማካኝነት ያገኘነው እምነት ይህ ሰው በሁላችሁም ፊት ፍጹም ጤናማ እንዲሆን አደረገው። |
አሁንም ወንድሞች፣ ገዢዎቻችሁ እንዳደረጉት ሁሉ እናንተም ይህን ያደረጋችሁት ባለማወቅ እንደሆነ አውቃለሁ። |
ይሁንና አምላክ፣ ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበል በነቢያት ሁሉ አፍ አስቀድሞ ያሳወቀው ነገር በዚህ መንገድ እንዲፈጸም አድርጓል። |
“ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ ተመለሱም፤ ከይሖዋም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ |
እንዲሁም ለእናንተ የሾመውን ክርስቶስን ይኸውም ኢየሱስን ይልክላችኋል። |
እሱም አምላክ በጥንቶቹ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ በሰማይ መቆየት ይገባዋል። |
ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል። እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ። |
ያንን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።’ |
ከሳሙኤል ጀምሮ በተከታታይ የተነሱት ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀናት በግልጽ ተናግረዋል። |
እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እንዲሁም አምላክ ለአብርሃም ‘የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ይባረካሉ’ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወራሾች ናችሁ። |
አምላክ አገልጋዩን ካስነሳ በኋላ እያንዳንዳችሁን ከክፉ ሥራችሁ በመመለስ ይባርካችሁ ዘንድ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው።” |
ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ |
የጌታን መንገድ የሚከተሉትን በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው። |
እየተጓዘም ሳለ ወደ ደማስቆ ሲቃረብ ድንገት ከሰማይ የመጣ ብርሃን በዙሪያው አንጸባረቀ፤ |
እሱም መሬት ላይ ወደቀ፤ ከዚያም “ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ። |
ሳኦልም “ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። |
አሁን ተነስተህ ወደ ከተማዋ ግባ፤ ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነገርሃል።” |
አብረው እየተጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፅ የሰሙ ቢሆንም ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም ብለው ቆሙ። |
ሳኦልም ከወደቀበት ተነሳ፤ ዓይኖቹ ቢገለጡም ምንም ነገር ማየት አልቻለም። በመሆኑም እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት። |
ለሦስት ቀንም ምንም ሳያይ እንዲሁም ሳይበላና ሳይጠጣ ቆየ። |
በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ “ሐናንያ!” አለው። እሱም “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ። |
ጌታም እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ‘ቀጥተኛ’ ወደተባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳም ቤት ሳኦል የሚባለውን የጠርሴስ ሰው ፈልግ። እሱም አሁን እየጸለየ ነው፤ |
ሐናንያ የሚባል ሰው እንደሚመጣና ዓይኑ ይበራለት ዘንድ እጁን እንደሚጭንበት በራእይ አይቷል።” |
ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳን አገልጋዮችህ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ ከብዙዎች ሰምቻለሁ። |
ወደዚህ ስፍራ የመጣው ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተሰጥቶት ነው።” |
ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሰው በአሕዛብ እንዲሁም በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን እንዲሸከምለእኔ የተመረጠ ዕቃ ስለሆነ ወደ እሱ ሂድ። |
እኔም ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት በግልጽ አሳየዋለሁ።” |
ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደተባለውም ቤት ገባ፤ እጁንም በላዩ ጭኖ እንዲህ አለው፦ “ወንድሜ ሳኦል፣ ወደዚህ ስትመጣ መንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ የዓይንህ ብርሃን እንዲመለስልህና በመንፈስ ቅዱስ እንድትሞላ እኔን ልኮኛል።” |
ወዲያውም ከዓይኖቹ ላይ ቅርፊት የሚመስሉ ነገሮች ወደቁ፤ እሱም እንደገና ማየት ቻለ። ከዚያም ተነስቶ ተጠመቀ፤ |
እንዲሁም ምግብ በልቶ ብርታት አገኘ። በደማስቆ ካሉ ደቀ መዛሙርት ጋር የተወሰኑ ቀናት ቆየ፤ |
ወዲያውም ስለ ኢየሱስ እሱ የአምላክ ልጅ እንደሆነ በምኩራቦቹ ውስጥ መስበክ ጀመረ። |
የሰሙት ሁሉ ግን እጅግ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረው አይደለም? ወደዚህስ የመጣው እነሱን እያሰረ ለካህናት አለቆች ለማስረከብ አልነበረም?” |
ሳኦል ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ የሚኖሩ አይሁዶችን ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ አሳማኝ ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር። |
በርካታ ቀናት ካለፉ በኋላ አይሁዳውያን እሱን ለመግደል አሴሩ። |
ይሁን እንጂ ሳኦል ሴራቸውን አወቀ። እነሱም ሊገድሉት ስለፈለጉ ቀን ከሌት የከተማዋን በሮች ነቅተው ይጠብቁ ነበር። |
ስለዚህ የእሱ ደቀ መዛሙርት ሳኦልን ወስደው በሌሊት በከተማዋ ቅጥር ላይ ባለ መስኮት በማሾለክ በቅርጫት አወረዱት። |
ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመቀላቀል ጥረት አደረገ፤ እነሱ ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት። |
ስለዚህ በርናባስ ረዳው፤ ሳኦልንም ወደ ሐዋርያት ወስዶ በመንገድ ላይ ጌታን እንዴት እንዳየውና እሱም እንዴት እንዳናገረው እንዲሁም በደማስቆ በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንደተናገረ በዝርዝር ነገራቸው። |
እሱም በኢየሩሳሌም በነፃነት እየተንቀሳቀሰና በጌታ ስም በድፍረት እየተናገረ አብሯቸው ቆየ። |
ግሪክኛ ተናጋሪ ከሆኑ አይሁዳውያን ጋር ይነጋገርና ይከራከር ነበር፤ እነሱ ግን ሊገድሉት ሞከሩ። |
ወንድሞች ይህን ሲያውቁ ወደ ቂሳርያ ይዘውት ወረዱ፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ ላኩት። |
በዚያ ወቅት በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ ያለው ጉባኤ ሁሉ ሰላም አገኘ፤ በእምነትም እየጠነከረ ሄደ፤ መላው ጉባኤ ይሖዋን በመፍራትና መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጠው ማጽናኛ ጋር በመስማማት ይኖር ስለነበር በቁጥር እየበዛ ሄደ። |
ጴጥሮስም በየቦታው እየተዘዋወረ በነበረበት ወቅት በልዳ ወደሚኖሩት ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። |
በዚያም ሽባ በመሆኑ የተነሳ ለስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኛ የሆነ ኤንያስ የተባለ አንድ ሰው አገኘ። |
ጴጥሮስም “ኤንያስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል። ተነሳና አልጋህን አንጥፍ” አለው። እሱም ወዲያውኑ ተነሳ። |
በልዳ እና በሳሮን ሜዳ የሚኖሩ ሁሉ እሱን አይተው በጌታ አመኑ። |
በኢዮጴ ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጉም “ዶርቃ” ማለት ነው። እሷም መልካም በማድረግና ምጽዋት በመስጠት የምትታወቅ ነበረች። |
በዚያን ጊዜም ታማ ሞተች። ሰዎችም አጠቧትና በደርብ ላይ በሚገኘው ክፍል ውስጥ አስቀመጧት። |
ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለነበረች ደቀ መዛሙርቱ ጴጥሮስ በዚያች ከተማ እንዳለ ሲሰሙ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና” ብለው እንዲለምኑት ሁለት ሰዎች ወደ እሱ ላኩ። |
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ተነስቶ አብሯቸው ሄደ። እዚያም ሲደርስ ደርብ ላይ ወደሚገኘው ክፍል ይዘውት ወጡ፤ መበለቶቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ የሠራቻቸውን በርካታ ልብሶችና ቀሚሶች ያሳዩት ነበር። |
ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች። |
እሱም እጇን ይዞ አስነሳት፤ ቅዱሳኑንና መበለቶቹንም ጠርቶ ሕያው መሆኗን አሳያቸው። |
ይህ ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙዎችም በጌታ አመኑ። |
ጴጥሮስም በኢዮጴ ስምዖን በተባለ አንድ ቆዳ ፋቂ ቤት ለበርካታ ቀናት ተቀመጠ። |
ከአምስት ቀን በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከተወሰኑ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ እነሱም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዢው አቀረቡ። |
በተጠራም ጊዜ ጠርጡለስ እንዲህ ሲል ይከሰው ጀመር፦ “ክቡር ፊሊክስ ሆይ፣ በአንተ አማካኝነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ አስተዋይነትህም ለዚህ ሕዝብ መሻሻል አስገኝቷል፤ |
በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። |
ይሁንና አሁን ጊዜህን እንዳልወስድብህ በአጭሩ የምንነግርህን ጉዳይ መልካም ፈቃድህ ሆኖ እንድትሰማን እለምንሃለሁ። |
ይህ ሰው መቅሰፍት ሆኖብናል፤ በዓለም ባሉት አይሁዳውያን ሁሉ መካከል ዓመፅ ያነሳሳል፤ ከዚህም ሌላ የናዝሬታውያን ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ ነው። |
በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር ስላገኘነው ያዝነው። |
አንተ ራስህ ስትመረምረው በእሱ ላይ ያቀረብነው ክስ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ ትችላለህ።” |
አይሁዳውያኑም የተባለው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በመግለጽ በክሱ ተባበሩ። |
አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው። |
ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከ12 ቀን እንደማይበልጥ አንተው ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤ |
እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ከማንም ጋር ስከራከርም ሆነ በምኩራቦች ወይም በከተማው ውስጥ ሕዝቡን ለዓመፅ ሳነሳሳ አላገኙኝም። |
በተጨማሪም አሁን ላቀረቡብኝ ክስ ሁሉ ምንም ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም። |
ይሁን እንጂ በሕጉና በነቢያት የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ስለማምን እነሱ ኑፋቄ ብለው የሚጠሩትን የሕይወት መንገድ እንደምከተልና በዚህም መንገድ ለአባቶቼ አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንደማቀርብ አልክድም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.