text stringlengths 4 267 |
|---|
የካህናት አለቆችና አንዳንድ የታወቁ አይሁዳውያንም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለእሱ አቀረቡ። ከዚያም ፊስጦስን ይለምኑት ጀመር፤ |
ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም በማስመጣት እንዲተባበራቸው ጠየቁት። ይህን ያሉት ግን መንገድ ላይ አድፍጠው ጳውሎስን ሊገድሉት አስበው ስለነበር ነው። |
ይሁን እንጂ ፊስጦስ፣ ጳውሎስ እዚያው ቂሳርያ ታስሮ እንደሚቆይና እሱ ራሱም በቅርቡ ወደዚያ እንደሚመለስ ነገራቸው። |
“በመሆኑም ከእናንተ መካከል ሥልጣን ያላቸው ከእኔ ጋር ይውረዱና ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ ይክሰሱት” አላቸው። |
ስለዚህ ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከአሥር ቀን ያልበለጠ ጊዜ ከእነሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ። |
ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁዳውያን በዙሪያው ቆመው በማስረጃ ያልተደገፉ በርካታ ከባድ ክሶች አቀረቡበት። |
ጳውሎስ ግን “እኔ በአይሁዳውያን ሕግ ላይም ሆነ በቤተ መቅደሱ ወይም በቄሳር ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም” ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ። |
ፊስጦስም በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ እኔ ባለሁበት መዳኘት ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው። |
ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “እኔ ልዳኝበት በሚገባኝ በቄሳር የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተ ራስህ በሚገባ እንደተገነዘብከው በአይሁዳውያን ላይ የፈጸምኩት ምንም በደል የለም። |
በእርግጥ ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁና ለሞት የሚያበቃ ነገር ፈጽሜ ከሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ ሰዎች ያቀረቡብኝ ክስ ሁሉ መሠረተ ቢስ ከሆነ ግን እነሱን ለማስደሰት ብሎ ማንም ሰው እኔን ለእነሱ አሳልፎ የመስጠት መብት የለውም። ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!” |
በዚህ ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተመካከረ በኋላ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልክ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ሲል መለሰለት። |
የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ለፊስጦስ ክብር ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቂሳርያ መጡ። |
በዚያም ብዙ ቀናት ስለቆዩ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ በማቅረብ እንዲህ አለው፦ “ፊሊክስ እስር ቤት የተወው አንድ ሰው አለ፤ |
ኢየሩሳሌም በነበርኩበት ጊዜ የካህናት አለቆቹና የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ይህን ሰው በመክሰስ እንዲፈረድበት ጥያቄ አቅርበው ነበር። |
እኔ ግን ክስ የቀረበበት ሰው ከከሳሾቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልስ መስጠት የሚችልበት አጋጣሚ ሳያገኝ እንዲሁ ሰውን ለማስደሰት ተብሎ ብቻ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት እንዳልሆነ ገለጽኩላቸው። |
ስለዚህ ከሳሾቹ ወደዚህ በመጡ ጊዜ ምንም ሳልዘገይ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጬ ሰውየውን እንዲያመጡት አዘዝኩ። |
ከሳሾቹም ቆመው በተናገሩ ጊዜ እኔ የጠበቅኩትን ያህል ከባድ በደል እንደፈጸመ የሚያሳይ ክስ አላቀረቡበትም። |
ከዚህ ይልቅ ከእሱ ጋር ይከራከሩ የነበረው ስለ ገዛ አምልኳቸውና ስለሞተው፣ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ኢየሱስ ስለተባለ ሰው ነው። |
እኔም ይህን ክርክር እንዴት እንደምፈታው ግራ ስለገባኝ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ መፋረድ ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅኩት። |
ጳውሎስ ግን አውግስጦስ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ታስሮ እንዲቆይ ይግባኝ ጠየቀ፤ በመሆኑም ወደ ቄሳር እስከምልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቆይ አዘዝኩ።” |
በዚህ ጊዜ አግሪጳ ፊስጦስን “እኔም ይህ ሰው ሲናገር ብሰማው ደስ ይለኝ ነበር” አለው። እሱም “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። |
ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር ደምቀው እንዲሁም በሻለቃዎችና በከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ታጅበው ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ገቡ፤ ፊስጦስም ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ። |
ፊስጦስም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ አግሪጳና ከእኛ ጋር እዚህ የተሰበሰባችሁ ሁሉ፣ ይህ የምታዩት ሰው በኢየሩሳሌምም ሆነ እዚህ፣ አይሁዳውያን ሁሉ ከእንግዲህ በሕይወት ሊኖር አይገባውም እያሉ በመጮኽ ለእኔ አቤቱታ ያቀረቡበት ሰው ነው። |
እኔ ግን ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር እንዳልፈጸመ ተረድቻለሁ። በመሆኑም እሱ ራሱ ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ ልልከው ወስኛለሁ። |
ይሁንና ስለ እሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው ምንም የተረጋገጠ ነገር አላገኘሁም። ስለዚህ አሁን በችሎቱ ፊት ከተመረመረ በኋላ ልጽፈው የምችለው ነገር አገኝ ዘንድ በእናንተ ሁሉ ፊት በተለይ ደግሞ በአንተ በንጉሥ አግሪጳ ፊት አቀረብኩት። |
ምክንያቱም አንድን እስረኛ የተከሰሰበትን ምክንያት ሳይገልጹ መላክ ተገቢ አልመሰለኝም።” |
በአንጾኪያ ባለው ጉባኤ ውስጥ ነቢያትና አስተማሪዎች ነበሩ፤ እነሱም፦ በርናባስ፣ ኒጌር ማለትም ጥቁር ተብሎ የሚጠራው ሲምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአውራጃ ገዢ ከሆነው ከሄሮድስ ጋር የተማረው ምናሔና ሳኦል ናቸው። |
እነዚህ ይሖዋን እያገለገሉና እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ” አለ። |
እነሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው። |
ሰዎቹም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዙ። |
ስልማና በደረሱ ጊዜም የአምላክን ቃል በአይሁዳውያን ምኩራቦች ማወጅ ጀመሩ። ዮሐንስም እንደ አገልጋይ ሆኖ ይረዳቸው ነበር። |
ደሴቲቱን ከዳር እስከ ዳር አዳርሰው እስከ ጳፎስ ተጓዙ፤ በዚህ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የነበረ አንድ አይሁዳዊ አገኙ። |
እሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ የሮም አገረ ገዢ ጋር ነበር። ይህ አገረ ገዢ የአምላክን ቃል ለመስማት ስለጓጓ በርናባስንና ሳኦልን ጠራቸው። |
ይሁን እንጂ ጠንቋዩ ኤልማስ አገረ ገዢው ይህን እምነት እንዳይቀበል ለማከላከል ፈልጎ ይቃወማቸው ጀመር። (ኤልማስ የተባለው ስም ትርጉም ጠንቋይ ማለት ነው።) |
በዚህ ጊዜ፣ ጳውሎስ ተብሎ የሚጠራው ሳኦል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ተመለከተው፤ |
ከዚያም እንዲህ አለው፦ “አንተ ተንኮልና ክፋት ሁሉ የሞላብህ፣ የዲያብሎስ ልጅ፣ የጽድቅም ሁሉ ጠላት! ቀና የሆነውን የይሖዋን መንገድ ማጣመምህን አትተውም? |
እነሆ፣ የይሖዋ እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዓይነ ስውር ትሆናለህ፤ ለተወሰነ ጊዜም የፀሐይ ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑም ጭጋግና ጨለማ ዓይኑን ጋረደው፤ እጁን ይዞ የሚመራው ሰው ለማግኘትም ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ። |
አገረ ገዢውም ስለ ይሖዋ በተማረው ነገር ተደንቆ ስለነበር ይህን ባየ ጊዜ አማኝ ሆነ። |
ጳውሎስና ባልደረቦቹ ከጳፎስ ተነስተው በባሕር ላይ በመጓዝ ጵንፍልያ ውስጥ ወዳለችው ወደ ጴርጌ ሄዱ። ዮሐንስ ግን ከእነሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። |
እነሱ ግን ጉዟቸውን በመቀጠል ከጴርጌ ተነስተው በጵስድያ ወደምትገኘው ወደ አንጾኪያ መጡ። በሰንበት ቀንም ወደ ምኩራብ ገብተው ተቀመጡ። |
የሕጉና የነቢያት መጻሕፍት በሕዝቡ ፊት ከተነበበ በኋላ የምኩራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ፣ ሕዝቡን የሚያበረታታ የምትናገሩት ቃል ካላችሁ ተናገሩ” የሚል መልእክት ላኩባቸው። |
ስለዚህ ጳውሎስ ተነስቶ በእጁ ምልክት በመስጠት እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሰዎችም ሆናችሁ አምላክን የምትፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ስሙ። |
የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጠ፤ በግብፅ ምድር ባዕዳን ሆነው ይኖሩ በነበረበት ጊዜም ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ በኃያል ክንዱም ከዚያ አወጣቸው። |
ለ40 ዓመት ያህልም በምድረ በዳ ታገሣቸው። |
በከነአን ምድር የነበሩትን ሰባት ብሔራት ካጠፋ በኋላ ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጣቸው። |
ይህ ሁሉ የሆነው በ450 ዓመት ያህል ጊዜ ውስጥ ነው። “ይህ ከሆነ በኋላ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው። |
ከዚያ በኋላ ግን ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ጠየቁ፤ አምላክም ከቢንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለ40 ዓመት አነገሠላቸው። |
እሱን ከሻረው በኋላ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እሱ የምፈልገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል’ ሲል የመሠከረለትን ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ አስነሳላቸው። |
አምላክ በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር ለእስራኤል አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን አመጣ። |
ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት በይፋ ሰብኮ ነበር። |
ይሁንና ዮሐንስ ተልእኮውን በማጠናቀቅ ላይ ሳለ ‘እኔ ማን እመስላችኋለሁ? እኔ እኮ እሱ አይደለሁም። ይሁን እንጂ ከእኔ በኋላ ሌላ ይመጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ ለመፍታት እንኳ አልበቃም’ ይል ነበር። |
“ወንድሞች፣ እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ እንዲሁም በመካከላችሁ ያሉ አምላክን የሚፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ይህ የመዳን ቃል ለእኛ ተልኳል። |
የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና የሃይማኖት መሪዎቻቸው የእሱን ማንነት አልተገነዘቡም፤ በእሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ግን በየሰንበቱ ከፍ ባለ ድምፅ የሚነበበውን ነቢያት የተናገሩትን ቃል ፈጸሙ። |
ለሞት የሚያበቃ አንድም ምክንያት ባያገኙበትም እንኳ ያስገድለው ዘንድ ጲላጦስን ወተወቱት። |
ስለ እሱ የተጻፈውን ነገር ሁሉ ከፈጸሙ በኋላም ከእንጨት ላይ አውርደው መቃብር ውስጥ አኖሩት። |
ሆኖም አምላክ ከሞት አስነሳው፤ |
እሱም ከገሊላ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ አብረውት ለሄዱት ሰዎች ለብዙ ቀናት ታያቸው። እነሱም አሁን ስለ እሱ ለሕዝቡ እየመሠከሩ ነው። |
“ስለሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለተገባው ቃል የሚገልጸውን ምሥራች እያወጅንላችሁ ነው። |
አምላክ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት ለእነሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ሙሉ በሙሉ ፈጽሞታል፤ ይህም የሆነው በሁለተኛው መዝሙር ላይ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ’ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው። |
አምላክ ኢየሱስን የማይበሰብስ አካል ሰጥቶ ከሞት አስነስቶታል፤ ይህን አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር ‘ለዳዊት ቃል የተገባውን የማይከስም ታማኝ ፍቅር አሳያችኋለሁ’ ብሏል። |
ስለዚህ በሌላም መዝሙር ላይ ‘ታማኝ አገልጋይህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ብሏል። |
በአንድ በኩል፣ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ አምላክን ካገለገለ በኋላ በሞት አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ መበስበስን አይቷል። |
በሌላ በኩል ግን አምላክ ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ መበስበስን አላየም። |
“ስለዚህ ወንድሞች፣ በእሱ በኩል የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ አሁን እየታወጀላችሁ እንዳለ እወቁ፤ |
በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም። |
ስለዚህ በነቢያት መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ የተነገረው ነገር በእናንተ ላይ እንዳይደርስ ተጠንቀቁ፦ |
‘እናንተ ፌዘኞች፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም በዝርዝር ቢነግራችሁ እንኳ ፈጽሞ የማታምኑትን ሥራ በእናንተ ዘመን እያከናወንኩ ነውና።’” |
እየወጡ ሳሉም ሰዎቹ ስለዚሁ ጉዳይ በሚቀጥለው ሰንበትም እንዲነግሯቸው ለመኗቸው። |
በምኩራቡ የተደረገው ስብሰባ ከተበተነ በኋላ ከአይሁዳውያንና ወደ ይሁዲነት ተለውጠው አምላክን ከሚያመልኩት መካከል ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሏቸው፤ እነሱም ሰዎቹን በማነጋገር የአምላክን ጸጋ አጥብቀው እንደያዙ እንዲቀጥሉ አሳሰቧቸው። |
በቀጣዩ ሰንበት የከተማዋ ሕዝብ ሁሉ ማለት ይቻላል፣ የይሖዋን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ። |
አይሁዳውያንም ሕዝቡን ባዩ ጊዜ በቅናት ተሞልተው ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በመቃወም ይሳደቡ ጀመር። |
በዚህ ጊዜ ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት እንዲህ አሏቸው፦ “የአምላክ ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። እናንተ ግን ወደ ጎን ገሸሽ እያደረጋችሁትና የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ እየፈረዳችሁ ስለሆነ እኛም ለአሕዛብ እንሰብካለን። |
ይሖዋ ‘እስከ ምድር ዳር ድረስ መዳንን እንድታመጣ ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሾሜሃለሁ’ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶናልና።” |
ከአሕዛብ ወገን የሆኑት ይህን ሲሰሙ እጅግ በመደሰት የይሖዋን ቃል አከበሩ፤ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸው ሁሉ አማኞች ሆኑ። |
ከዚህም በተጨማሪ የይሖዋ ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ እየተስፋፋ ሄደ። |
ይሁንና አይሁዳውያን ፈሪሃ አምላክ ያላቸውን የተከበሩ ሴቶችና በከተማዋ የሚኖሩትን ታላላቅ ወንዶች በመቀስቀስ በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት አስነሱ፤ ከክልላቸውም አስወጧቸው። |
እነሱም የእግራቸውን አቧራ አራግፈው ወደ ኢቆንዮን ሄዱ። |
ደቀ መዛሙርቱም በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። |
ከእነሱ በግድ ከተለያየን በኋላ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ በመጓዝ ቆስ ደረስን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ሮድስ አመራን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ሄድን። |
ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜ ተሳፍረን ጉዟችንን ቀጠልን። |
የቆጵሮስ ደሴት በታየችን ጊዜ በስተ ግራ ትተናት ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከቡ ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለነበረበት እኛም እዚያ ወረድን። |
ደቀ መዛሙርቱን ፈልገን ካገኘን በኋላ በዚያ ሰባት ቀን ቆየን። እነሱም በመንፈስ ተመርተው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ደጋግመው ነገሩት። |
የቆይታ ጊዜያችን ባለቀ ጊዜ ከዚያ ተነስተን ጉዟችንን ጀመርን፤ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ከከተማዋ እስክንወጣ ድረስ ሸኙን። ከዚያም በባሕሩ ዳርቻ ተንበርክከን ጸለይን፤ |
በኋላም ተሰነባበትን። ከዚያም እኛ ወደ መርከቡ ገባን፤ እነሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። |
ከጢሮስ ተነስተን በመርከብ በመጓዝ ጴጤሌማይስ ደረስን፤ እዚያም ለወንድሞች ሰላምታ ካቀረብን በኋላ አብረናቸው አንድ ቀን ቆየን። |
በማግስቱ ከዚያ ተነስተን ቂሳርያ ደረስን፤ በዚያም ከሰባቱ ወንዶች አንዱ ወደሆነው ወደ ወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን እሱ ጋ አረፍን። |
ይህ ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ያላገቡ ሴቶች ልጆች ነበሩት። |
ለብዙ ቀናት እዚያ ከተቀመጥን በኋላ አጋቦስ የሚባል አንድ ነቢይ ከይሁዳ ወረደ። |
ወደ እኛም መጥቶ የጳውሎስን ቀበቶ በመውሰድ የራሱን እግርና እጅ ካሰረ በኋላ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‘አይሁዳውያን የዚህን ቀበቶ ባለቤት በኢየሩሳሌም እንዲህ አድርገው ያስሩታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።’” |
ይህን ስንሰማ እኛም ሆንን በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ እንለምነው ጀመር። |
በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እያለቀሳችሁ ልቤን ለምን ታባባላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም እንኳ ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ። |
እሱን ለማሳመን ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ “እንግዲህ የይሖዋ ፈቃድ ይሁን” ብለን ዝም አልን። |
ከዚህ በኋላ ለጉዞው ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመርን። |
በቂሳርያ ከሚኖሩት ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ ወደምናርፍበት ሰው ቤት እኛን ለመውሰድ አብረውን ሄዱ፤ ይህ ሰው ምናሶን የተባለ የቆጵሮስ ሰው ሲሆን ከቀድሞዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር። |
ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን። |
በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤ ሽማግሌዎቹም ሁሉ በዚያ ነበሩ። |
ሰላምታ ካቀረበላቸውም በኋላ፣ እሱ ባከናወነው አገልግሎት አማካኝነት አምላክ በአሕዛብ መካከል የፈጸማቸውን ነገሮች በዝርዝር ይተርክላቸው ጀመር። |
እነሱም ይህን ከሰሙ በኋላ አምላክን አመሰገኑ፤ እሱን ግን እንዲህ አሉት፦ “ወንድም፣ ከአይሁዳውያን መካከል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞች እንዳሉ ታውቃለህ፤ ደግሞም ሁሉም ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው። |
እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል። |
እንግዲህ ምን ማድረግ ይሻላል? መምጣትህን እንደሆነ መስማታቸው አይቀርም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.