text stringlengths 4 267 |
|---|
ሆኖም በዚያኑ ዕለት ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ እንዲህ አለው፦ “አይዞህ፣ አትፍራ! ምክንያቱም በኢየሩሳሌም ስለ እኔ በሚገባ እንደመሠከርክ ሁሉ በሮምም ልትመሠክርልኝ ይገባል።” |
በነጋም ጊዜ አይሁዳውያን በጳውሎስ ላይ በማሴር እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውኃ ላለመቅመስ ተማማሉ። |
ይህን ሴራ ለመፈጸም የተማማሉት ሰዎች ቁጥራቸው ከ40 በላይ ነበር። |
እነሱም ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ሽማግሌዎቹ ሄደው እንዲህ አሉ፦ “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ አንዳች እህል ላለመቅመስ ጽኑ መሐላ ተማምለናል። |
ስለዚህ እናንተ ከሳንሄድሪን ሸንጎ ጋር ሆናችሁ የጳውሎስን ጉዳይ ይበልጥ ማጣራት የምትፈልጉ በማስመሰል እሱን ወደ እናንተ እንዲያመጣው ለሠራዊቱ ሻለቃ ንገሩት። ይሁንና እኛ እዚህ ከመድረሱ በፊት እሱን ለመግደል ተዘጋጅተን እንጠብቃለን።” |
ይሁን እንጂ የጳውሎስ የእህቱ ልጅ አድብተው ጥቃት ለመሰንዘር እንዳሰቡ በመስማቱ ወደ ጦር ሰፈሩ ገብቶ ጉዳዩን ለጳውሎስ ነገረው። |
ጳውሎስም ከመኮንኖቹ አንዱን ጠርቶ “ይህ ወጣት ለሠራዊቱ ሻለቃ የሚነግረው ነገር ስላለው ወደ እሱ ውሰደው” አለው። |
እሱም ወደ ሻለቃው ይዞት ሄደና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ወጣት የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ጠየቀኝ” አለው። |
ሻለቃውም እጁን ይዞ ለብቻው ገለል ካደረገው በኋላ “ልትነግረኝ የፈለግከው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። |
እሱም እንዲህ አለ፦ “አይሁዳውያን ስለ ጳውሎስ ጉዳይ በዝርዝር ማወቅ የፈለጉ በማስመሰል ነገ ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ እንድታመጣው ሊጠይቁህ ተስማምተዋል። |
አንተ ግን በዚህ እንዳትታለል፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድብተው በእሱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየጠበቁ ነው፤ ደግሞም እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህልም ሆነ ውኃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን ፈቃድ እየተጠባበቁ ነው።” |
በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ “ይህን ነገር ለእኔ መንገርህን ለማንም እንዳታወራ” ብሎ ካዘዘው በኋላ ወጣቱን አሰናበተው። |
ከዚያም ከመኮንኖቹ መካከል ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ወደ ቂሳርያ የሚሄዱ 200 ወታደሮች እንዲሁም 70 ፈረሰኞችና ጦር የያዙ 200 ሰዎች አዘጋጁ። |
በተጨማሪም ጳውሎስን ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊሊክስ በደህና ለማድረስ የሚጓዝባቸው ፈረሶች አዘጋጁ።” |
እንዲህ የሚል ደብዳቤም ጻፈ፦ |
“ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፤ ለክቡር አገረ ገዢ ለፊሊክስ፦ ሰላም ለአንተ ይሁን። |
አይሁዳውያን ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ሆኖም የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅኩ ወዲያውኑ ከወታደሮቼ ጋር ደርሼ አዳንኩት። |
እሱን የከሰሱት ለምን እንደሆነ ለማወቅ ስለፈለግኩም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጓቸው አቀረብኩት። |
የተከሰሰውም ከሕጋቸው ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤ ሆኖም ለሞት ወይም ለእስር የሚያበቃ አንድም ክስ አላገኘሁም። |
ይሁንና በዚህ ሰው ላይ የተሸረበ ሴራ እንዳለ ስለተነገረኝ ወዲያውኑ ወደ አንተ ልኬዋለሁ፤ ከሳሾቹም ክሳቸውን በአንተ ፊት እንዲያቀርቡ አዝዤአቸዋለሁ።” |
ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት። |
በማግስቱም ፈረሰኞቹ ከጳውሎስ ጋር ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ እነሱ ወደ ጦር ሰፈሩ ተመለሱ። |
ፈረሰኞቹም ቂሳርያ በደረሱ ጊዜ ደብዳቤውን ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም አስረከቡት። |
እሱም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ የየትኛው አውራጃ ሰው እንደሆነ ጠየቀ፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ተረዳ። |
ከዚያም “ከሳሾችህ ሲመጡ ጉዳይህን በደንብ አየዋለሁ” አለው። በሄሮድስም ቤተ መንግሥት ውስጥ በጥበቃ ሥር ሆኖ እንዲቆይ አዘዘ። |
በዚያን ወቅት የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማከፋፈል ሥራ መበለቶቻቸው ቸል ስለተባሉባቸው ዕብራይስጥ ተናጋሪ በሆኑት አይሁዳውያን ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ። |
ስለዚህ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን በሙሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፦ “በማዕድ ምግብ ለማከፋፈል ስንል የአምላክን ቃል የማስተማር ሥራችንን ብንተው ተገቢ አይሆንም። |
ስለዚህ ወንድሞች፣ ለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ እንድንሾማቸው ከእናንተ መካከል መልካም ስም ያተረፉ፣ በመንፈስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ወንዶች ምረጡ፤ |
እኛ ግን በጸሎትና ቃሉን በማስተማሩ ሥራ ላይ ሙሉ በሙሉ እናተኩራለን።” |
የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኛቸው፤ ስለሆነም ጠንካራ እምነት የነበረውንና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት ተለውጦ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። |
ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። |
ከዚህም የተነሳ የአምላክ ቃል መስፋፋቱን ቀጠለ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄደ፤ በጣም ብዙ ካህናትም ይህን እምነት ተቀበሉ። |
እስጢፋኖስም ጸጋና ኃይል ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ይፈጽም ነበር። |
ይሁን እንጂ ‘ነፃ የወጡ ሰዎች ምኩራብ’ ተብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ከተወሰኑ የቀሬና፣ የእስክንድርያ፣ የኪልቅያና የእስያ ሰዎች ጋር መጥተው እስጢፋኖስን ተከራከሩት። |
ይሁንና ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። |
ስለዚህ “ይህ ሰው በሙሴና በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” ብለው እንዲናገሩ አንዳንድ ሰዎችን በድብቅ አግባቡ። |
በተጨማሪም ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን እንዲሁም ጸሐፍትን ቀሰቀሱ፤ ከዚያም ድንገት መጡና በኃይል ይዘው ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ ወሰዱት። |
የሐሰት ምሥክሮችም አቀረቡ፤ እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን የሚቃወም ነገር ከመናገር ሊቆጠብ አልቻለም። |
ለምሳሌ ያህል፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያፈርሰውና ሙሴ ያስተላለፈልንን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” |
በሳንሄድሪን ሸንጎ ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ ትኩር ብለው ሲያዩት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው። |
ሳኦልም በእሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በሚገኘው ጉባኤ ላይ ከባድ ስደት ተነሳ፤ ከሐዋርያት በስተቀር ደቀ መዛሙርቱ በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ ክልሎች ሁሉ ተበተኑ። |
ሆኖም ለአምላክ ያደሩ ሰዎች እስጢፋኖስን ወስደው ቀበሩት፤ ታላቅ ለቅሶም አለቀሱለት። |
ሳኦልም በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ ጀመረ። በየቤቱ እየገባ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ጎትቶ በማውጣት ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር። |
ይሁን እንጂ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት በሄዱበት ቦታ ሁሉ የአምላክን ቃል ምሥራች ሰበኩ። |
በዚህ ጊዜ ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ሄዶ ስለ ክርስቶስ ይሰብክላቸው ጀመር። |
ሕዝቡ ፊልጶስ የሚናገረውን ሲሰሙና የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ሲመለከቱ ሁሉም በአንድ ልብ በትኩረት ይከታተሉት ጀመር። |
ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችም ነበሩ፤ ርኩሳን መናፍስቱም በከፍተኛ ድምፅ እየጮኹ ይወጡ ነበር። በተጨማሪም ሽባና አንካሳ የነበሩ በርካታ ሰዎች ተፈወሱ። |
ከዚህም የተነሳ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። |
በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ከዚህ ቀደም አስማት እየሠራ የሰማርያን ሕዝብ ያስደምም የነበረ ሲሆን ታላቅ ሰው እንደሆነ አድርጎም ይናገር ነበር። |
ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ፣ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራ ‘የአምላክ ኃይል’ ነው” በማለት ትልቅ ቦታ ይሰጡት ነበር። |
ረዘም ላለ ጊዜ በአስማት ሥራው ሲያስደንቃቸው ስለቆየ የሚለውን ሁሉ ይቀበሉ ነበር። |
ይሁንና ስለ አምላክ መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምሥራች እያወጀ የነበረውን ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም ይጠመቁ ጀመር። |
ስምዖን ራሱም አማኝ ሆነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ አይለይም ነበር፤ ምልክቶችና ታላላቅ ተአምራት ሲፈጸሙ በማየት ይደነቅ ነበር። |
በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሲሰሙ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው፤ |
እነሱም ወደዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው። |
ምክንያቱም በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር። |
ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ እነሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። |
ስምዖንም ሐዋርያት እጃቸውን የጫኑበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደሚቀበል አይቶ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል በመግባት |
“እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ለእኔም ስጡኝ” አላቸው። |
ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የአምላክን ነፃ ስጦታ በገንዘብ ማግኘት እንደምትችል ስላሰብክ የብር ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። |
ልብህ በአምላክ ፊት ቀና ስላልሆነ በዚህ አገልግሎት ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ ዕድል ፋንታ የለህም። |
ስለዚህ ከዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ፤ ምናልባት የልብህ ክፉ ሐሳብ ይቅር ይባልልህ እንደሆነ ይሖዋን ተማጸን፤ |
መራራ መርዝና የክፋት ባሪያ እንደሆንክ አያለሁና።” |
ስምዖንም መልሶ “ከተናገራችሁት ነገር አንዱም እንዳይደርስብኝ እባካችሁ ይሖዋን ማልዱልኝ” አላቸው። |
ጴጥሮስና ዮሐንስ የተሟላ ምሥክርነት ከሰጡና የይሖዋን ቃል ከተናገሩ በኋላ የሰማርያ ሰዎች በሚኖሩባቸው በርካታ መንደሮች ምሥራቹን እያወጁ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። |
ይሁንና የይሖዋ መልአክ ፊልጶስን “ተነስተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ የበረሃ መንገድ ነው።) |
እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ |
እየተመለሰም ሳለ በሠረገላው ውስጥ ተቀምጦ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነብ ነበር። |
መንፈስም ፊልጶስን “ሂድና ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። |
ፊልጶስ ከሠረገላው ጎን እየሮጠ ጃንደረባው የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ጮክ ብሎ ሲያነብ ሰማና “ለመሆኑ የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው። |
እሱም “የሚመራኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ፊልጶስንም ሠረገላው ላይ ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ለመነው። |
ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፉ ክፍል የሚከተለው ነበር፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት እሱም አፉን አልከፈተም። |
ውርደት በደረሰበት ወቅት ፍትሕ ተነፈገ። ስለ ትውልዱ ማን በዝርዝር ሊናገር ይችላል? ምክንያቱም ሕይወቱ ከምድር ላይ ተወግዷል።” |
ጃንደረባውም ፊልጶስን “እባክህ ንገረኝ፣ ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው ወይስ ስለ ሌላ ሰው?” አለው። |
ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህ ቅዱስ መጽሐፍ አንስቶም ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች ነገረው። |
እየተጓዙም ሳሉ ውኃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “ውኃ ይኸውና፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው። |
ከዚያም ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወርደው ውኃው ውስጥ ገቡ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው። |
ከውኃውም በወጡ ጊዜ፣ የይሖዋ መንፈስ ወዲያውኑ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ፊልጶስን ከዚያ በኋላ አላየውም፤ ይሁንና ደስ ብሎት ጉዞውን ቀጠለ። |
በኋላ ግን ፊልጶስ በአሽዶድ ታየ፤ ቂሳርያም እስኪደርስ ድረስ በሚያልፍበት ክልል በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ምሥራቹን ያውጅ ነበር። |
እንግዲያው ‘አምላክ ሕዝቡን ትቷል ማለት ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! ምክንያቱም እኔም ራሴ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከአብርሃም ዘር፣ ከቢንያም ነገድ ነኝ። |
አምላክ መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸውን ሰዎች አልተዋቸውም። ቅዱስ መጽሐፉ ኤልያስ እስራኤልን በአምላክ ፊት በከሰሰበት ጊዜ የሆነውን ነገር በተመለከተ ምን እንደሚል አታውቁም? |
“ይሖዋ ሆይ፣ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋል፤ እኔ ብቻ ቀረሁ፤ አሁንም ሕይወቴን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ነው።” |
ይሁንና አምላክ የሰጠው መልስ ምን ነበር? “ለባአል ያልተንበረከኩ 7,000 ሰዎች አሉኝ።” |
ስለዚህ በዚህ መንገድ በጸጋ የተመረጡ ቀሪዎች በአሁኑ ዘመንም አሉ። |
የተመረጡት በጸጋ ከሆነ በሥራ መሆኑ ቀርቷል፤ አለዚያ ጸጋው ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር። |
እንግዲህ ምን ማለት እንችላለን? እስራኤል አጥብቆ ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም፤ የተመረጡት ግን አገኙት። የቀሩት የማስተዋል ስሜታቸው ደነዘዘ፤ |
ይህም “አምላክ እስከ ዛሬ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ ጣለባቸው፤ የማያይ ዓይንና የማይሰማ ጆሮ ሰጣቸው” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። |
በተጨማሪም ዳዊት እንዲህ ብሏል፦ “ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ እንዲሁም እንቅፋትና ቅጣት ይሁንባቸው። |
ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤ ጀርባቸውም ጎብጦ እንዲቀር አድርግ።” |
በመሆኑም ‘የተሰናከሉት ወድቀው እንዲቀሩ ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! ከዚህ ይልቅ እነሱ ሕጉን በመተላለፋቸው ለአሕዛብ የመዳን መንገድ ተከፈተ፤ ይህም የሆነው እነሱን ለማስቀናት ነው። |
እነሱ ሕጉን መተላለፋቸው ለዓለም በረከት ከሆነና የእነሱ ማነስ ለአሕዛብ በረከት ካስገኘ ቁጥራቸው መሙላቱማ ምን ያህል ታላቅ በረከት ያስገኝ ይሆን! |
አሁን ደግሞ የምናገረው ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ነው። ለአሕዛብ የተላክሁ ሐዋርያ እንደመሆኔ መጠን አገልግሎቴን አከብራለሁ፤ |
ይህን የማደርገው የገዛ ወገኖቼ የሆኑትን በማስቀናት ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን ማዳን እችል እንደሆነ ብዬ ነው። |
የእነሱ መጣል ለዓለም እርቅ ካስገኘ፣ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር ማለት አይሆንም? |
በተጨማሪም በኩራት ተደርጎ የተወሰደው የሊጡ ክፍል ቅዱስ ከሆነ ሊጡ በሙሉ ቅዱስ ነው፤ እንዲሁም ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው። |
ይሁን እንጂ ከቅርንጫፎቹ መካከል አንዳንዶቹ ቢሰበሩና አንተ የዱር ወይራ ሆነህ ሳለህ በእነሱ መካከል ከተጣበቅክ እንዲሁም ከወይራው ዛፍ ሥር ከሚገኘው በረከት ተካፋይ ከሆንክ |
በተሰበሩት ቅርንጫፎች ላይ አትታበይ። በእነሱ ላይ የምትታበይ ከሆነ ግን አንተን የተሸከመህ ሥሩ ነው እንጂ አንተ ሥሩን እንዳልተሸከምከው አስታውስ። |
ይሁንና “ቅርንጫፎቹ የተሰበሩት እኔ በቦታቸው እንድጣበቅ ነው” ብለህ ታስብ ይሆናል። |
እውነት ነው! እነሱ ባለማመናቸው ተሰብረዋል፤ አንተ ግን በእምነት ቆመሃል። ቢሆንም መፍራት እንጂ መታበይ አይገባህም። |
አምላክ በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራ ለአንተም አይራራምና። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.