text stringlengths 4 267 |
|---|
በክንክራኦስ ጉባኤ የምታገለግለውን እህታችንን ፌበንን ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ፤ |
በጌታ የእምነት ባልደረባችሁ እንደመሆኗ መጠን ለቅዱሳን በሚገባ ሁኔታ ተቀበሏት፤ የምትፈልገውንም እርዳታ ሁሉ አድርጉላት፤ ምክንያቱም እሷ እኔን ጨምሮ ለብዙ ወንድሞች ድጋፍ ሆናለች። |
በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ |
እነሱ ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠዋል፤ እኔ ብቻ ሳልሆን በአሕዛብ መካከል የሚገኙ ጉባኤዎችም ሁሉ ያመሰግኗቸዋል። |
በቤታቸው ላለው ጉባኤም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ከመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች አንዱ የሆነውን የምወደውን ኤጲኔጦስን ሰላም በሉልኝ። |
ለእናንተ ብዙ የደከመችውን ማርያምን ሰላም በሉልኝ። |
ዘመዶቼ የሆኑትንና አብረውኝ የታሰሩትን እንዲሁም በሐዋርያት ዘንድ ስመጥር የሆኑትንና ከእኔ ቀደም ብለው የክርስቶስ ተከታዮች የሆኑትን አንድሮኒኮስንና ዩኒያስን ሰላም በሉልኝ። |
በጌታ ለምወደው ለአምጵልያጦስ ሰላምታዬን አቅርቡልኝ። |
በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኡርባኖስንና የምወደውን እስጣኩስን ሰላም በሉልኝ። |
በክርስቶስ ዘንድ መልካም ስም ያተረፈውን አጵሌስን ሰላም በሉልኝ። የአርስጦቡሉስ ቤተሰብ ለሆኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
ዘመዴን ሄሮድዮንን ሰላም በሉልኝ። የጌታ ተከታዮች የሆኑትን የናርኪሰስን ቤተሰቦች ሰላም በሉልኝ። |
በጌታ ሆነው በትጋት የሚሠሩትን ጥራይፊናና ጥራይፎሳ የተባሉትን ሴቶች ሰላም በሉልኝ። የምንወዳትን ጰርሲስን ሰላም በሉልኝ፤ በጌታ ሥራ ብዙ ደክማለችና። |
የጌታ ምርጥ አገልጋይ ለሆነው ለሩፎስ እንዲሁም እኔም እንደ እናቴ ለማያት ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
አሲንክሪጦስን፣ ፍሌጎንን፣ ሄርሜስን፣ ጳጥሮባን፣ ሄርማስንና ከእነሱ ጋር ያሉትን ወንድሞች ሰላም በሉልኝ። |
ፊሎሎጎስንና ዩልያን፣ ኔርዩስንና እህቱን፣ ኦሊምጳስን እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሁሉ ሰላም በሉልኝ። |
በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ ጉባኤዎች በሙሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። |
እንግዲህ ወንድሞች፣ ክፍፍል ከሚፈጥሩና ለእንቅፋት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ከሚያመጡ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች የተማራችሁትን ትምህርት የሚጻረሩ ናቸው፤ ይህን ከሚያደርጉ ሰዎች ራቁ። |
እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ለጌታችን ለክርስቶስ ሳይሆን ለራሳቸው ፍላጎት ባሪያዎች ናቸው፤ በለሰለሰ አንደበትና በሽንገላ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ። |
ታዛዥነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ሆኗል፤ ስለዚህ እኔ በእናንተ እጅግ እደሰታለሁ። ይሁንና ለመልካም ነገር ጥበበኞች እንድትሆኑ፣ ለክፉ ነገር ደግሞ አላዋቂዎች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። |
ሰላም የሚሰጠው አምላክ በቅርቡ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይጨፈልቀዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። |
የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ዘመዶቼ የሆኑት ሉክዮስ፣ ያሶንና ሶሲጳጥሮስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። |
ይህን ደብዳቤ በጽሑፍ ያሰፈርኩት እኔ ጤርጥዮስም በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። |
እኔንም ሆነ መላውን ጉባኤ የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላም ይላችኋል። የከተማዋ የግምጃ ቤት ሹም ኤርስጦስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ወንድሙ ቁአስጥሮስም ሰላም ይላችኋል። |
አምላክ ለረጅም ዘመናት ተሰውሮ ከቆየው ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እኔ በማውጀው ምሥራችና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰበከው መልእክት መሠረት ሊያጸናችሁ ይችላል። |
አሁን ግን ሕዝቦች ሁሉ እምነት እንዲኖራቸውና እሱን እንዲታዘዙ ቅዱሱ ሚስጥር፣ በዘላለማዊው አምላክ ትእዛዝ መሠረት ትንቢታዊ በሆኑ ቅዱሳን መጻሕፍት አማካኝነት በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲገለጥና እንዲታወቅ ተደርጓል፤ |
እሱ ብቻ ጥበበኛ ለሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። |
ስለዚህ አሁን በእምነት አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን እንኑር፤ |
ደግሞም በኢየሱስ አማካኝነት የአምላክን ጸጋ ለማግኘት በእምነት ወደ እሱ መቅረብ የቻልን ሲሆን ይህን ጸጋ አሁን አግኝተናል፤ የአምላክንም ክብር እንደምናገኝ ተስፋ በማድረግ እጅግ እንደሰት። |
በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራ ውስጥ እያለንም እጅግ እንደሰት፤ ምክንያቱም መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን፤ |
ጽናትም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንድናገኝ ያስችለናል፤ ተቀባይነት ማግኘት ደግሞ ተስፋን ያጎናጽፋል፤ |
ተስፋውም ሳይፈጸም ቀርቶ ለሐዘን አይዳርገንም፤ ምክንያቱም የአምላክ ፍቅር፣ በተሰጠን መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን ውስጥ ፈሷል። |
ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ ለኃጢአተኞች ሞቷልና። |
ለጻድቅ ሰው የሚሞት ማግኘት በጣም አዳጋች ነው፤ ለጥሩ ሰው ለመሞት የሚደፍር ግን ምናልባት ይገኝ ይሆናል። |
ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል። |
ከእንግዲህ በደሙ ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን በእሱ አማካኝነት ከአምላክ ቁጣ እንደምንድን ይበልጥ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። |
ጠላቶች ሆነን ሳለን በልጁ ሞት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ከታረቅን አሁን ታርቀን ሳለንማ በእሱ ሕይወት እንደምንድን የተረጋገጠ ነው። |
ይህም ብቻ ሳይሆን አሁን እርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ሐሴት እያደረግን ነው። |
ስለሆነም በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ። |
ሕጉ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ላይ ነበርና፤ ሆኖም ሕግ በሌለበት ማንም በኃጢአት አይጠየቅም። |
ይሁንና አዳም ትእዛዝ በመተላለፍ የሠራውን ዓይነት ኃጢአት ባልሠሩት ላይም እንኳ ሳይቀር ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት በሁሉ ላይ ነገሠ፤ አዳም በኋላ ለሚመጣው አምሳያ ነበር። |
ሆኖም ስጦታው ያስገኘው ነገር በደሉ ካስከተለው ነገር የተለየ ነው። ምክንያቱም በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋል፤ ይሁንና የአምላክ ጸጋና ነፃ ስጦታው በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ አማካኝነት ለብዙ ሰዎች ወደር የሌለው ጥቅም አስገኝቷል! |
በተጨማሪም ነፃ ስጦታው ያስገኘው ውጤት የአንዱ ሰው ኃጢአት ካመጣው ውጤት የተለየ ነው። ምክንያቱም አንድን በደል ተከትሎ የመጣው ፍርድ ኩነኔን አስከትሏል፤ ብዙዎች በደል ከፈጸሙ በኋላ ግን አምላክ ጻድቃን እንዲባሉ የሚያስችል ስጦታ ሰጥቷል። |
በአንድ ሰው በደል የተነሳ ሞት በዚህ ሰው በኩል ከነገሠ የአምላክን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅን ነፃ ስጦታ የሚቀበሉትማ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሕይወት አግኝተው ነገሥታት ሆነው እንደሚገዙ ይበልጥ የተረጋገጠ ነው! |
ስለዚህ አንድ በደል ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲኮነኑ እንዳደረገ ሁሉ አንድ የጽድቅ ድርጊትም ሁሉም ዓይነት ሰዎች ጻድቃን ናችሁ ተብለው ለሕይወት እንዲበቁ ያስችላል። |
ምክንያቱም በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ ሁሉ በአንዱ ሰው መታዘዝም ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። |
ሕጉ የመጣው ሰዎች ብዙ በደል እንደሚፈጽሙ ለማሳየት ነው። ይሁን እንጂ ሰዎች ብዙ ኃጢአት ሲፈጽሙ አምላክ ታላቅ ጸጋ አሳያቸው። |
ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ኃጢአት ከሞት ጋር እንደነገሠ ሁሉ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ አማካኝነት እንዲነግሥ ነው። |
በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በአመለካከት ልዩነት ላይ ተመሥርታችሁ አትፍረዱ። |
አንድ ሰው እምነቱ ማንኛውንም ነገር እንዲበላ ይፈቅድለታል፤ በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነ ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል። |
ማንኛውንም ነገር የሚበላ የማይበላውን አይናቅ፤ የማይበላው ደግሞ በሚበላው ላይ አይፍረድ፤ ይህን ሰው አምላክ ተቀብሎታልና። |
በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እሱ ቢቆምም ሆነ ቢወድቅ ለጌታው ነው። እንዲያውም ይሖዋ እንዲቆም ሊያደርገው ስለሚችል ይቆማል። |
አንድ ሰው አንዱ ቀን ከሌላው ቀን የበለጠ እንደሆነ አድርጎ ያስባል፤ ሌላው ደግሞ አንዱ ቀን ከሌሎቹ ቀናት ሁሉ የተለየ እንዳልሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ ሰው ሙሉ በሙሉ ያመነበትን ውሳኔ ያድርግ። |
አንድን ቀን የሚያከብር ለይሖዋ ብሎ ያከብራል። ማንኛውንም ነገር የሚበላም አምላክን ስለሚያመሰግን ለይሖዋ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለይሖዋ ብሎ አይበላም፤ ይሁንና አምላክን ያመሰግናል። |
እንዲያውም ከመካከላችን ለራሱ ብቻ ብሎ የሚኖር የለም፤ ለራሱ ብቻ ብሎም የሚሞት የለም። |
ብንኖር የምንኖረው ለይሖዋ ነውና፤ ብንሞትም የምንሞተው ለይሖዋ ነው። ስለዚህ ብንኖርም ሆነ ብንሞት የይሖዋ ነን። |
ክርስቶስ የሞተውና ዳግም ሕያው የሆነው ለዚህ ዓላማ ይኸውም በሙታንም ሆነ በሕያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ነውና። |
ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? አንተ ደግሞ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በአምላክ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና። |
“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ እኔ አምላክ መሆኔን በይፋ ይመሠክራል’” ተብሎ ተጽፏልና። |
ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለአምላክ መልስ እንሰጣለን። |
ስለሆነም ከእንግዲህ አንዳችን በሌላው ላይ አንፍረድ፤ ከዚህ ይልቅ በአንድ ወንድም ፊት የሚያደናቅፍ ወይም የሚያሰናክል ነገር ላለማስቀመጥ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ። |
የጌታ ኢየሱስ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ አውቄአለሁ ደግሞም አምኛለሁ፤ አንድ ነገር ለአንድ ሰው ርኩስ የሚሆነው ያ ነገር ርኩስ ነው ብሎ ሲያስብ ብቻ ነው። |
አንተ በምግብ የተነሳ ወንድምህ ቅር እንዲሰኝ ካደረግክ በፍቅር መመላለስህን ትተሃል ማለት ነው። ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ። |
በመሆኑም መልካም ነው ብላችሁ የምታደርጉት ነገር በሌሎች ዘንድ በመጥፎ እንዳይነሳ ተጠንቀቁ። |
የአምላክ መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም። |
በዚህ መንገድ ክርስቶስን እንደ ባሪያ የሚያገለግል ሁሉ በአምላክ ፊት ተቀባይነት፣ በሰዎችም ዘንድ ሞገስ ያገኛልና። |
ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንተናነጽበትን ነገር ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ። |
ለምግብ ብለህ የአምላክን ሥራ ማፍረስ ተው። እርግጥ ነው፣ ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ሆኖም አንድ ሰው መብላቱ ሌሎችን የሚያደናቅፍ ከሆነ ጎጂ ነው። |
ወንድምህ የሚሰናከልበት ከሆነ ሥጋ አለመብላት፣ የወይን ጠጅ አለመጠጣት ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ የተሻለ ነው። |
እንግዲህ እምነትህ በአንተና በአምላክ መካከል ያለ ጉዳይ ይሁን። ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ካደረገ በኋላ መልሶ ራሱን የማይኮንን ሰው ደስተኛ ነው። |
እየተጠራጠረ ከበላ ግን የበላው በእምነት ስላልሆነ ቀድሞውንም ተኮንኗል። ደግሞም በእምነት ያልተደረገ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው። |
እኛ በእምነት ጠንካሮች የሆን ጠንካሮች ያልሆኑትን ሰዎች ድክመት ልንሸከም ይገባል እንጂ ራሳችንን የምናስደስት መሆን የለብንም። |
እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን የሚጠቅመውንና የሚያንጸውን ነገር በማድረግ እናስደስተው። |
ክርስቶስ እንኳ ራሱን አላስደሰተምና፤ ይህም “ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። |
በምናሳየው ጽናትና ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏልና። |
ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላክ፣ ሁላችሁም ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያድርግ፤ |
ይኸውም በኅብረትና በአንድ ድምፅ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታከብሩ ነው። |
ስለዚህ ክርስቶስ እኛን እንደተቀበለን ሁሉ አምላክ እንዲከበር እናንተም አንዳችሁ ሌላውን ተቀበሉ። |
ክርስቶስ፣ አምላክ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ሲል ለተገረዙት አገልጋይ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤ በተጨማሪም አገልጋይ የሆነው፣ አምላክ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለማረጋገጥ |
እንዲሁም ብሔራት አምላክን ስለ ምሕረቱ ያከብሩት ዘንድ ነው። ይህም “ስለዚህ በብሔራት መካከል በይፋ አወድስሃለሁ፤ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። |
ደግሞም “እናንተ ብሔራት፣ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” ይላል። |
እንደገናም “ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያወድሱት” ይላል። |
እንዲሁም ኢሳይያስ “የእሴይ ሥር ይገለጣል፤ ብሔራትንም የሚገዛው ይነሳል፤ ብሔራትም ተስፋቸውን በእሱ ላይ ይጥላሉ” ይላል። |
በእሱ በመታመናችሁ የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ እንዲትረፈረፍላችሁ ተስፋ የሚሰጠው አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ። |
ወንድሞቼ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ በጥሩነት የተሞላችሁ እንደሆናችሁ፣ የተሟላ እውቀት እንዳላችሁና አንዳችሁ ሌላውን መምከር እንደምትችሉ እኔ ራሴ ስለ እናንተ እርግጠኛ መሆን ችያለሁ። |
ይሁን እንጂ አንዳንድ ጉዳዮችን ግልጥልጥ አድርጌ የጻፍኩላችሁ ተጨማሪ ማሳሰቢያ ልሰጣችሁ ስለፈለግኩ ነው። ይህን የማደርገው ከአምላክ በተሰጠኝ ጸጋ የተነሳ ነው። |
ይህ ጸጋ የተሰጠኝም ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው። የአምላክን ምሥራች በማወጁ ቅዱስ ሥራ የምካፈለው እነዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ፣ ተቀባይነት ያለው መባ ሆነው ለአምላክ እንዲቀርቡ ነው። |
ስለዚህ ለአምላክ ከማቀርበው አገልግሎት ጋር በተያያዘ በክርስቶስ ኢየሱስ ሐሴት የማደርግበት ምክንያት አለኝ። |
አሕዛብ ታዛዦች እንዲሆኑ ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት ስላከናወነው ነገር ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም። ይህን ያከናወነው እኔ በተናገርኩትና ባደረግኩት ነገር |
እንዲሁም በተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ደግሞም በአምላክ መንፈስ ኃይል ነው፤ በመሆኑም ከኢየሩሳሌም አንስቶ ዙሪያውን እስከ እልዋሪቆን ድረስ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ ሰብኬአለሁ። |
በዚህ መንገድ የክርስቶስ ስም አስቀድሞ በታወቀበት ቦታ ምሥራቹን ላለመስበክ የተቻለኝን ሁሉ ጥረት አድርጌአለሁ፤ ይህን ያደረግኩት ሌላ ሰው በጣለው መሠረት ላይ መገንባት ስላልፈለግኩ ነው፤ |
ይህም “ከዚህ በፊት ስለ እሱ ምንም ያልተነገራቸው ያያሉ፤ ያልሰሙም ያስተውላሉ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። |
በተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ እናንተ መምጣት ሳልችል የቀረሁትም በዚህ ምክንያት ነው። |
አሁን ግን በዚህ አካባቢ ባሉት አገሮች ያልሰበክሁበት ክልል የለም፤ ደግሞም ለብዙ ዓመታት ወደ እናንተ ለመምጣት ስጓጓ ቆይቻለሁ። |
በመሆኑም ወደ ስፔን በምጓዝበት ጊዜ እንደማገኛችሁና እናንተ ጋ ለተወሰነ ጊዜ ቆይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ ጥቂት መንገድ እንደምትሸኙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። |
አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም ልጓዝ ነው። |
በመቄዶንያና በአካይያ ያሉት ወንድሞች በኢየሩሳሌም ባሉት ቅዱሳን መካከል ለሚገኙት ድሆች መዋጮ በመስጠት ያላቸውን ነገር በደስታ አካፍለዋልና። |
አዎ፣ ይህን ያደረጉት በፈቃደኝነት ነው፤ ደግሞም የእነሱ ዕዳ ነበረባቸው፤ ምክንያቱም አሕዛብ የእነሱን መንፈሳዊ ነገር ከተካፈሉ እነሱ ደግሞ ለሚያስፈልጓቸው ቁሳዊ ነገሮች የማዋጣት ዕዳ አለባቸው። |
ስለሆነም ይህን ሥራ ካከናወንኩና መዋጮውን ካስረከብኳቸው በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ ስፔን እሄዳለሁ። |
ደግሞም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ የክርስቶስን የተትረፈረፈ በረከት ይዤላችሁ እንደምመጣ አውቃለሁ። |
እንግዲህ ወንድሞች፣ ስለ እኔ አምላክን በመለመን ከእኔ ጋር አብራችሁ በጸሎት እንድትተጉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከመንፈስ በሚገኘው ፍቅር አበረታታችኋለሁ፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.