text
stringlengths
4
267
በከተማዋም ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም ጥፋት እንዲደርስባት አትረገምም፤ ደግሞም ኢየሩሳሌም ሰዎች ያለስጋት የሚኖሩባት ቦታ ትሆናለች።
“ይሖዋ ኢየሩሳሌምን የሚወጉ ሕዝቦችን ሁሉ የሚቀስፍበት መቅሰፍት ይህ ነው፦ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዓይኖቻቸውም በጉድጓዶቻቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
“በዚያ ቀን ከይሖዋ ዘንድ የመጣ ሽብር በመካከላቸው ይሰራጫል፤ እያንዳንዱም ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ እጁንም በባልንጀራው እጅ ላይ ያነሳል።
ይሁዳም ራሱ በኢየሩሳሌም በሚደረገው ውጊያ ይካፈላል፤ በዙሪያዋም ያሉ ብሔራት ሁሉ ሀብት ይኸውም ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይሰበሰባል።
“በየሰፈሩ ባሉት ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ ግመሎች፣ አህዮችና መንጎች ሁሉ ላይ ተመሳሳይ መቅሰፍት ይወርዳል።
“በኢየሩሳሌም ላይ ከተነሱት ብሔራት ሁሉ የሚተርፉት ሰዎች በሙሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድና የዳስ በዓልን ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።
ይሁንና ከምድር ብሔራት መካከል ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ቢኖሩ ዝናብ አይዘንብላቸውም።
የግብፅ ሰዎች ባይወጡና ወደ ከተማዋ ባይገቡ ዝናብ አይዘንብላቸውም። እንዲያውም ይሖዋ የዳስ በዓልን ለማክበር ባልመጡት ብሔራት ላይ በሚያመጣቸው መቅሰፍቶች ይቀሰፋሉ።
ግብፅ ለፈጸመችው ኃጢአትና የዳስ በዓልን ለማክበር ያልወጡት ብሔራት ሁሉ ለሠሩት ኃጢአት ይህ ቅጣት ይደርስባቸዋል።
“በዚያ ቀን በፈረሶቹ ቃጭል ላይ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው!’ ተብሎ ይጻፋል። በይሖዋ ቤት ያሉት ድስቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች ይሆናሉ።
በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ድስቶች በሙሉ ቅዱስና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ የተወሰኑ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሁሉ ገብተው የተወሰኑትን ድስቶች ለመቀቀያ ይጠቀሙባቸዋል። በዚያ ቀን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ቤት ዳግመኛ ከነአናዊ አይገኝም።”
ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ መጥቶ አንድን ሰው ከእንቅልፉ እንደሚቀሰቅስ ቀሰቀሰኝ።
ከዚያም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልኩት፦ “እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሠራና ላዩ ላይ ሳህን ያለበት መቅረዝ ይታየኛል። በላዩ ላይ ሰባት መብራቶች፣ አዎ ሰባት መብራቶች አሉበት፤ አናቱ ላይ ያሉት ሰባት መብራቶችም ሰባት ቱቦዎች አሏቸው።
ከጎኑም አንዱ ከሳህኑ በስተ ቀኝ፣ አንዱ ደግሞ በስተ ግራ የቆሙ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት።
ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረውም መልአክ “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት።
በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ መሬት ትሆናለህ። “እንዴት ያምራል! እንዴት ያምራል!” እያሉ በሚጮኹበት ጊዜ እሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።’”
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦
“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት ጥለዋል፤ የገዛ እጆቹም ያጠናቅቁታል። እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ።
ሥራው በትንሹ የተጀመረበትን ቀን የናቀ ማን ነው? እነሱ ሐሴት ያደርጋሉና፤ በዘሩባቤልም እጅ ላይ ቱምቢውን ያያሉ። እነዚህ ሰባቱ በመላው ምድር የሚዘዋወሩ የይሖዋ ዓይኖች ናቸው።”
ከዚያም “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት የእነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት።
ለሁለተኛም ጊዜ እንዲህ ስል ጠየቅኩት፦ “በሁለቱ የወርቅ ቱቦዎች አማካኝነት ወርቃማ ፈሳሽ የሚያፈሱት የሁለቱ የወይራ ዛፎች ቅርንጫፎች ትርጉም ምንድን ነው?”
እሱም “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” አለኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት።
እሱም “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ ቅቡዓን ናቸው” አለ።
የፍርድ መልእክት፦ “ስለ እስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል።”ሰማያትን የዘረጋው፣የምድርን መሠረት የጣለውናየሰውን መንፈስ በውስጡ የሠራው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የምታንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ፤ ጠላት ይሁዳንም ሆነ ኢየሩሳሌምን ይከባል።
በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ። ድንጋዩን የሚያነሱት ሁሉ ክፉኛ መጎዳታቸው የማይቀር ነው፤ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሷ ላይ ይሰበሰባሉ።
በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ ጋላቢውንም በእብደት እመታለሁ። ዓይኖቼን በይሁዳ ቤት ላይ አደርጋለሁ፤ የሕዝቦቹን ፈረሶች ሁሉ ግን አሳውራለሁ።
የይሁዳም አለቆች በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አምላካቸው ስለሆነ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ብርታታችን ናቸው’ ይላሉ።
በዚያን ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ የሚነድ ምድጃና በታጨደ እህል መካከል እንዳለ የሚነድ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱም በስተ ቀኝም ሆነ በስተ ግራ፣ በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌምም በገዛ ስፍራዋ ይኸውም በኢየሩሳሌም ዳግመኛ የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች።
“የዳዊት ቤት ውበትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ውበት ከይሁዳ እጅግ የበለጠ እንዳይሆን ይሖዋ በመጀመሪያ የይሁዳን ድንኳኖች ያድናል።
በዚያ ቀን ይሖዋ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዙሪያ መከታ ይሆናል፤ በዚያም ቀን ከእነሱ መካከል የሚሰናከለው እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት እንደ አምላክ፣ በፊታቸውም እንደሚሄደው የይሖዋ መልአክ ይሆናል።
ደግሞም በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን ብሔራት ሁሉ ለማጥፋት ቆርጬ እነሳለሁ።
“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የሞገስንና የምልጃን መንፈስ አፈሳለሁ፤ እነሱም የወጉትን ያዩታል፤ ለአንድያ ልጅም እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኩር ልጅ እንደሚለቀሰው ያለ መራራ ለቅሶም ያለቅሱለታል።
በዚያን ቀን በኢየሩሳሌም የሚለቀሰው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ፣ በሃዳድሪሞን እንደተለቀሰው ለቅሶ ታላቅ ይሆናል።
ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱም ቤተሰብ ለየብቻው ያለቅሳል፤ የዳዊት ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣
የሌዊ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሺምአይ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣
የቀሩትም ቤተሰቦች በሙሉ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።
ዳግመኛም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የመዳብ ተራሮች ነበሩ።
የመጀመሪያውን ሠረገላ የሚጎትቱት ቀይ ፈረሶች፣ ሁለተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ጥቁር ፈረሶች ነበሩ።
ሦስተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ነጭ ፈረሶች፣ አራተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ነጠብጣብ ያለባቸውና ዥጉርጉር ፈረሶች ነበሩ።
ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” ብዬ ጠየቅኩት።
መልአኩ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙ በኋላ፣ ከዚያ የሚወጡት አራቱ የሰማያት መናፍስት ናቸው።
በጥቁር ፈረሶች የሚጎተተው ሠረገላ ወደ ሰሜን ምድር ይወጣል፤ ነጮቹ ፈረሶች ከባሕሩ ባሻገር ወዳለው ምድር ይወጣሉ፤ ነጠብጣብ ያለባቸው ፈረሶች ደግሞ ወደ ደቡብ ምድር ይወጣሉ።
ዥጉርጉሮቹ ፈረሶችም ወጥተው በምድር መካከል ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር።” እሱም “ሂዱ፤ በምድር መካከል ተመላለሱ” አለ። እነሱም በምድር መካከል ይመላለሱ ጀመር።
ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት፣ የይሖዋ መንፈስ በሰሜን ምድር እንዲያርፍ አድርገዋል።”
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦
“በግዞት ከተወሰደው ሕዝብ ያመጡትን ነገር ከሄልዳይ፣ ከጦቢያህና ከየዳያህ ውሰድ፤ በዚያም ቀን፣ ከባቢሎን ከመጡት ከእነዚህ ሰዎች ጋር ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ።
ብርና ወርቅ ወስደህ አክሊል ሥራ፤ ከዚያም በየሆጼዴቅ ልጅ በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ ራስ ላይ አድርገው።
እንዲህም በለው፦ “‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ቀንበጥ ተብሎ የሚጠራው ሰው ይህ ነው። እሱ በገዛ ቦታው ላይ ያቆጠቁጣል፤ የይሖዋንም ቤተ መቅደስ ይሠራል።
የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው፤ ግርማ የሚጎናጸፈውም እሱ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ ደግሞም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ካህን ሆኖ ያገለግላል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ ስምምነት ይኖራል።
አክሊሉም ለሄሌም፣ ለጦቢያህ፣ ለየዳያህና ለሶፎንያስ ልጅ ለሄን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል።
በሩቅ ያሉትም ይመጣሉ፤ በይሖዋ ቤተ መቅደስ የግንባታ ሥራም ይካፈላሉ።” እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ብትሰሙ ይህ ይሆናል።’”
የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ መጣ፦
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለጽዮን በታላቅ ቅንዓት እቀናለሁ፤ ደግሞም በታላቅ ቁጣ ለእሷ እቀናለሁ።’”
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌምም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ተብላ ትጠራለች፤ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ተራራም ቅዱስ ተራራ ተብሎ ይጠራል።’”
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በኢየሩሳሌም አደባባዮች እንደገና ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ርዝመት የተነሳ በእጃቸው ምርኩዝ ይይዛሉ።
የከተማዋም አደባባዮች በዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።’”
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ይህ ነገር ለዚህ ሕዝብ ቀሪዎች የማይቻል ነገር መስሎ ቢታይ እንኳ ለእኔ የማይቻል ነገር ሊመስል ይገባል?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገሮች አድናለሁ።
እኔም አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፤ ሕዝቤም ይሆናሉ፤ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ።’”
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእነዚህ ቀናት በነቢያት አፍ የተነገሩትን እነዚህን ቃላት የምትሰሙ ሁሉ እጃችሁን አበርቱ፤ እነዚህ ቃላት፣ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቤት መሠረት በተጣለበት ጊዜ ነቢያት የተናገሯቸው ናቸው።
ከእነዚያ ቀናት በፊት ለሰውም ሆነ ለእንስሳ የሚከፈል ደሞዝ አልነበረምና፤ ደግሞም ከጠላት የተነሳ በሰላም መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር፤ ሰው ሁሉ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ አድርጌ ነበርና።’
“‘አሁን ግን በዚህ ሕዝብ ቀሪዎች ላይ እንደቀድሞው ዘመን አላደርግም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
‘የሰላም ዘር ይዘራልና፤ የወይን ተክሉ ፍሬ ያፈራል፤ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤ ሰማያትም ጠል ያዘንባሉ፤ እኔም የዚህ ሕዝብ ቀሪዎች እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዲወርሱ አደርጋለሁ።
የይሁዳና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በብሔራት መካከል እርግማን ነበራችሁ፤ አሁን ግን አድናችኋለሁ፤ እናንተም በረከት ትሆናላችሁ። አትፍሩ! እጃችሁን አበርቱ።’
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘“አባቶቻችሁ ስላስቆጡኝ በእናንተ ላይ ጥፋት ላመጣባችሁ ቆርጬ እንደነበርና በዚያም እንዳልተጸጸትኩ ሁሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣
“አሁንም ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት መልካም ለማድረግ ቆርጫለሁ። አትፍሩ!”’
“‘እናንተ እነዚህን ነገሮች ልታደርጉ ይገባል፦ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በከተማዋም በሮች የምትፈርዱት ፍርድ እውነትን የሚያጠናክርና ሰላምን የሚያሰፍን ይሁን።
አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ፤ ማንኛውንም የሐሰት መሐላ አትውደዱ፤ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጠላለሁና’ ይላል ይሖዋ።”
የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአራተኛው ወር፣ የአምስተኛው ወር፣ የሰባተኛው ወርና የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት የፍስሐና የደስታ ይኸውም የሐሴት በዓል ይሆናል። በመሆኑም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።’
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቦችና የብዙ ከተማ ነዋሪዎች በእርግጥ ይመጣሉ፤
በአንዲት ከተማ የሚኖሩ ሰዎችም በሌላ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳየን ለመለመንና የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግ ተነሱ፤ እንሂድ። እኔም እሄዳለሁ።”
ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን” ይላሉ።’”
የፍርድ መልእክት፦ በሚልክያስ በኩል ለእስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦
“እኔ ፍቅር አሳይቻችኋለሁ” ይላል ይሖዋ። እናንተ ግን “ፍቅር ያሳየኸን እንዴት ነው?” አላችሁ። “ኤሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረም?” ይላል ይሖዋ። “እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ፤
ኤሳውንም ጠላሁ፤ ተራሮቹን ባድማ አደረግኩ፤ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁ።”
“ኤዶም ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።
የገዛ ዓይናችሁ ይህን ያያል፤ እናንተም “ይሖዋ በእስራኤል ምድር ከፍ ከፍ ይበል” ትላላችሁ።’”
“እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፣ ‘ልጅ አባቱን፣ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል። እኔ አባት ከሆንኩ ለእኔ የሚገባው ክብር የት አለ? ጌታስ ከሆንኩ መፈራቴ የት አለ?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘እናንተ ግን “ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’
“‘በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ በማቅረብ ነው።’ “‘ደግሞም “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’ “‘“የይሖዋ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።
ዕውሩን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ። ደግሞም አንካሳ ወይም የታመመ እንስሳ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ።’” “እነዚህን እንስሳት እስቲ ለገዢህ ለማቅረብ ሞክር። በአንተ ደስ ይለዋል? ወይስ በሞገስ ዓይን ይቀበልሃል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“አሁንም እባካችሁ፣ ሞገስ እንዲያሳየን አምላክን ተማጸኑ። እንዲህ ያሉ መባዎች በገዛ እጃችሁ ስታቀርቡ ከእናንተ መካከል የእሱን ሞገስ የሚያገኝ ይኖራል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“ከእናንተ መካከል በሮቹን ለመዝጋት ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው? በመሠዊያዬ ላይ እሳት ለማንደድ እንኳ ክፍያ ትጠይቃላችሁና። በእናንተ ፈጽሞ ደስ አልሰኝም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስጦታ አድርጋችሁ በምታቀርቡት በየትኛውም መባ አልደሰትም።”
“ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል። በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“እናንተ ግን ‘የይሖዋ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬው ይኸውም ምግቡ የተናቀ ነው’ በማለት ታረክሱታላችሁ።
በተጨማሪም እናንተ ‘እንዴት አድካሚ ነው!’ ትላላችሁ፤ ደግሞም ትጸየፉታላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “የተሰረቀን፣ አንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ታመጣላችሁ። አዎ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ! ታዲያ ይህን ከእጃችሁ ልቀበል ይገባል?” ይላል ይሖዋ።
“በመንጎቹ መካከል ተባዕት እንስሳ እያለው፣ ስእለት ተስሎ እንከን ያለበትን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ የሚያታልል የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስሜም በብሔራት መካከል የተፈራ ይሆናል።”
“እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ እሱም በፊቴ መንገድ ይጠርጋል። እናንተ የምትፈልጉት እውነተኛው ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበት የቃል ኪዳኑ መልእክተኛም ይመጣል። እነሆ፣ እሱ በእርግጥ ይመጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“ይሁንና እሱ የሚመጣበትን ቀን ሊቋቋም የሚችል ማን ነው? እሱ በሚገለጥበት ጊዜስ ማን ሊቆም ይችላል? እሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ልብስ አጣቢም እንዶድ ይሆናልና።
ደግሞም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያነጻል፤ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያጠራቸዋል፤ ይሖዋም በጽድቅ መባ የሚያቀርብ ሕዝብ ይኖረዋል።
ይሁዳና ኢየሩሳሌም ስጦታ አድርገው የሚያቀርቡት መባ በቀድሞው ጊዜና በጥንት ዘመን እንደነበረው ይሖዋን ደስ ያሰኘዋል።
“ለመፍረድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞቹ፣ በአመንዝሮቹ፣ በሐሰት በሚምሉት ሰዎች እንዲሁም ቅጥር ሠራተኛውን፣ መበለቲቱንና አባት የሌለውን ልጅ በሚያጭበረብሩትና ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ በማይሆኑት ላይ ወዲያውኑ እመሠክርባቸዋለሁ። እነዚህ ሰዎች እኔን አልፈሩም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“እኔ ይሖዋ ነኝና፤ አልለወጥም። እናንተም የያዕቆብ ልጆች ናችሁ፤ ገና አልጠፋችሁም።
ከአባቶቻችሁ ዘመን አንስቶ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፤ ደግሞም ሥርዓቴን አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። እናንተ ግን “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።
“በውኑ ተራ ሰው አምላክን ይሰርቃል? እናንተ ግን እኔን ትሰርቁኛላችሁ።” እናንተም “የሰረቅንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “በምትሰጡት አሥራትና መዋጮ ነው።
እናንተ በእርግጥ የተረገማችሁ ናችሁ፤ ትሰርቁኛላችሁና፤ አዎ፣ መላው ብሔር እንዲህ ያደርጋል።