text stringlengths 4 267 |
|---|
ከእነሱም መካከል አንድ ሕግ አዋቂ እሱን ለመፈተን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ |
“መምህር፣ ከሕጉ ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው?” |
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “‘አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ።’ |
ይህ ከሁሉ የሚበልጠውና የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው። |
ሁለተኛውም ይህንኑ የሚመስል ሲሆን ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል። |
መላው ሕግም ሆነ የነቢያት ቃል በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ የተመሠረቱ ናቸው።” |
ፈሪሳውያን አንድ ላይ ተሰብስበው እንዳሉ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ |
“ስለ መሲሑ ምን ትላላችሁ? የማን ልጅ ነው?” እነሱም “የዳዊት” አሉት። |
እሱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? |
ምክንያቱም ዳዊት ‘ይሖዋ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው’ ሲል ተናግሯል። |
ታዲያ ዳዊት ጌታ ብሎ ከጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?” |
ከዚህ በኋላ አንዲት ቃል ሊመልስለት የቻለም ሆነ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም። |
ከዚያም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ |
“ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚጥሱት ለምንድን ነው? ለምሳሌ፣ ሊበሉ ሲሉ እጃቸውን አይታጠቡም።” |
እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ትእዛዝ የምትጥሱት ለምንድን ነው? |
ለምሳሌ አምላክ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሏል። |
እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ ነው” ካለ |
አባቱን የማክበር ግዴታ የለበትም።’ በመሆኑም ለወጋችሁ ስትሉ የአምላክን ቃል ሽራችኋል። |
እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ስለ እናንተ በትክክል ተንብዮአል፦ |
‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው። |
የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’” |
ከዚያም ሕዝቡን ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ስሙ፤ ደግሞም ይህን ቃል አስተውሉ፦ |
ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፉ የሚገባው አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው ነው።” |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን በተናገርከው ነገር ቅር እንደተሰኙ አውቀሃል?” አሉት። |
እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። |
ተዉአቸው፤ እነሱ ዕውር መሪዎች ናቸው። ስለዚህ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።” |
ጴጥሮስም መልሶ “ምሳሌውን አብራራልን” አለው። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም እስካሁን ማስተዋል ተስኗችኋል? |
ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚዘልቅና ከዚያም ወጥቶ ወደ ጉድጓድ እንደሚገባ አታውቁም? |
ይሁን እንጂ ከአፍ የሚወጣ ሁሉ ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው። |
ለምሳሌ ከልብ ክፉ ሐሳብ፣ ግድያ፣ ምንዝር፣ የፆታ ብልግና፣ ሌብነት፣ በሐሰት መመሥከርና ስድብ ይወጣሉ። |
ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ነገሮች ናቸው፤ እጅን ሳይታጠቡ መብላት ግን ሰውን አያረክስም።” |
ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና አካባቢ ሄደ። |
በዚያ ክልል የምትኖር አንዲት ፊንቄያዊት ሴት መጥታ “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ። ልጄን ጋኔን ስለያዛት ክፉኛ እየተሠቃየች ነው” ብላ ጮኸች። |
እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጣትም። ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ይህች ሴት ከኋላችን እየተከተለች ስለምትጮኽ እባክህ አሰናብታት” እያሉ ይለምኑት ጀመር። |
እሱም መልሶ “እኔ የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች እንጂ ለሌላ ለማንም አይደለም” አለ። |
ሴትየዋ ግን ቀርባ “ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ!” እያለች ሰገደችለት። |
እሱም መልሶ “የልጆችን ዳቦ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ተገቢ አይደለም” አለ። |
እሷም “አዎ ጌታ ሆይ፣ ግን እኮ ቡችሎችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መልሶ “አንቺ ሴት፣ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ በይ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ” አላት። ልጇም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰች። |
ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ መጣ፤ ወደ ተራራ ወጥቶም ተቀመጠ። |
በዚህ ጊዜ እጅግ ብዙ ሰዎች አንካሶችን፣ ሽባዎችን፣ ዓይነ ስውሮችን፣ ዱዳዎችንና ሌሎች በርካታ ሕመምተኞችን ይዘው ወደ እሱ በመምጣት እግሩ ሥር አስቀመጧቸው፤ እሱም ፈወሳቸው። |
ሕዝቡም ዱዳዎች ሲናገሩ፣ ሽባዎች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱና ዓይነ ስውሮች ሲያዩ ተመልክተው እጅግ ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ። |
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ። እንዲሁ ጦማቸውን ልሰዳቸው አልፈልግም፤ መንገድ ላይ ዝለው ሊወድቁ ይችላሉ” አላቸው። |
ደቀ መዛሙርቱ ግን “በዚህ ገለልተኛ ስፍራ ይህን ሁሉ ሕዝብ ሊያጠግብ የሚችል በቂ ዳቦ ከየት እናገኛለን?” አሉት። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ስንት ዳቦ አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “ሰባት ዳቦና ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎች” አሉት። |
እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ ካዘዘ በኋላ |
ሰባቱን ዳቦና ዓሣዎቹን ወሰደ፤ ካመሰገነ በኋላም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ። |
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ። |
የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 4,000 ወንዶች ነበሩ። |
በመጨረሻም ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ጀልባ ተሳፍሮ ወደ መጌዶን ክልል መጣ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ ዲያብሎስ ይፈትነው ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ መራው። |
እሱም 40 ቀንና 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። |
ፈታኙም ቀርቦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። |
እሱ ግን “‘ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰ። |
ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት ላይ አቁሞ |
እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’” |
ኢየሱስም “‘አምላክህን ይሖዋን አትፈታተነው’ ተብሎም ተጽፏል” አለው። |
እንደገናም ዲያብሎስ በጣም ረጅም ወደሆነ ተራራ ወስዶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉና ክብራቸውን አሳየው። |
ከዚያም “አንድ ጊዜ ተደፍተህ ብታመልከኝ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏልና” አለው። |
ከዚያም ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ እነሆም፣ መላእክት መጥተው ያገለግሉት ጀመር። |
ኢየሱስ፣ ዮሐንስ እንደታሰረ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ሄደ። |
ከዚያም ከናዝሬት ወጥቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃዎች፣ በባሕሩ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ መኖር ጀመረ፤ |
ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረው የሚከተለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ |
“ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ወደ ባሕሩ በሚወስደው መንገድ አጠገብ ያላችሁ የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድርና የአሕዛብ ገሊላ ሆይ! |
በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን አዩ፤ ሞት በሰዎች ላይ ባጠላበት ምድር ላሉም ብርሃን ወጣላቸው።” |
ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ስለቀረበ ንስሐ ግቡ” እያለ ይሰብክ ጀመር። |
በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲሄድ ሁለቱን ወንድማማቾች ማለትም ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን እና ወንድሙን እንድርያስን አያቸው፤ እነሱም ዓሣ አጥማጆች ስለነበሩ መረባቸውን ወደ ባሕሩ እየጣሉ ነበር። |
እሱም “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። |
እነሱም ወዲያውኑ መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት። |
ከዚያ እልፍ እንዳለ ሌሎች ሁለት ወንድማማቾችን ማለትም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አያቸው። እነሱም ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ላይ ሆነው መረቦቻቸውን እየጠገኑ ነበር፤ ኢየሱስም ጠራቸው። |
እነሱም ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። |
ከዚያም በምኩራቦቻቸው እያስተማረና የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም በሕዝቡ መካከል ያለውን ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በመላዋ ገሊላ ተዘዋወረ። |
ስለ እሱም የተወራው ወሬ በመላዋ ሶርያ ተዳረሰ፤ ሰዎችም በተለያየ በሽታና ከባድ ሕመም የሚሠቃዩትን፣ ጋኔን የያዛቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችን ሁሉ ወደ እሱ አመጡ፤ እሱም ፈወሳቸው። |
ከዚህም የተነሳ ከገሊላ፣ ከዲካፖሊስ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ተከተሉት። |
“መንግሥተ ሰማያት በወይን እርሻው ላይ የሚሠሩ ሠራተኞችን ለመቅጠር ማልዶ ከወጣ የእርሻ ባለቤት ጋር ይመሳሰላል። |
በቀን አንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከተዋዋለ በኋላ ሠራተኞቹን ወደ ወይን እርሻው ላካቸው። |
በሦስት ሰዓት ገደማም ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈተው የቆሙ ሌሎች ሰዎች አየ፤ |
እነዚህንም ሰዎች ‘እናንተም ወደ ወይኑ እርሻ ሂዱ፤ ተገቢውንም ክፍያ እከፍላችኋለሁ’ አላቸው። |
እነሱም ሄዱ። ዳግመኛም በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንዲሁ አደረገ። |
በመጨረሻም በ11 ሰዓት ገደማ ወጥቶ ቆመው የነበሩ ሌሎች ሰዎች አገኘና ‘ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈታችሁ እዚህ የቆማችሁት ለምንድን ነው?’ አላቸው። |
እነሱም ‘የሚቀጥረን ሰው ስላጣን ነው’ ሲሉ መለሱለት። እሱም ‘እናንተም ወደ ወይኑ እርሻ ሄዳችሁ ሥሩ’ አላቸው። |
“በመሸም ጊዜ የወይኑ እርሻ ባለቤት የሠራተኞቹን ተቆጣጣሪ ‘ሠራተኞቹን ጠርተህ በመጨረሻ ከተቀጠሩት አንስቶ በመጀመሪያ እስከተቀጠሩት ድረስ ደሞዛቸውን ክፈላቸው’ አለው። |
በ11 ሰዓት የተቀጠሩት ሰዎች መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። |
በመሆኑም በመጀመሪያ የተቀጠሩት ሲመጡ እነሱ የበለጠ የሚከፈላቸው መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን እነሱም የተከፈላቸው አንድ አንድ ዲናር ነበር። |
ክፍያውን ሲቀበሉ በእርሻው ባለቤት ላይ ማጉረምረም ጀመሩ፤ |
እንዲህም አሉት፦ ‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት ሰዎች አንድ ሰዓት ብቻ ነው የሠሩት፤ ያም ሆኖ አንተ ቀኑን ሙሉ ስንደክምና በፀሐይ ስንቃጠል ከዋልነው ከእኛ ጋር እኩል አደረግካቸው!’ |
እሱ ግን ከመካከላቸው ለአንዱ እንዲህ አለው፦ ‘የኔ ወንድም፣ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም። የተስማማነው አንድ ዲናር እንድከፍልህ ነው፣ አይደለም እንዴ? |
ስለዚህ ድርሻህን ይዘህ ሂድ። በመጨረሻ ለተቀጠሩት ለእነዚህ ሰዎችም ለአንተ የሰጠሁትን ያህል መስጠት ፈለግኩ። |
በገዛ ገንዘቤ የፈለግኩትን የማድረግ መብት የለኝም? ወይስ እኔ ደግ በመሆኔ ዓይንህ ተመቀኘ?’ |
ስለሆነም ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞች ደግሞ ኋለኞች ይሆናሉ።” |
ወደ ኢየሩሳሌም እየወጡ ሳሉ ኢየሱስ 12ቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ነጥሎ ወሰዳቸው፤ በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ አላቸው፦ |
“እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤ |
እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።” |
ከዚያም የዘብዴዎስ ሚስት ከልጆቿ ጋር ወደ እሱ ቀርባ እየሰገደች አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው። |
እሱም “ምንድን ነው የፈለግሽው?” አላት። እሷም መልሳ “በመንግሥትህ እነዚህን ሁለቱን ልጆቼን፣ አንዱን በቀኝህ አንዱን ደግሞ በግራህ አስቀምጥልኝ” አለችው። |
ኢየሱስም መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ በቅርቡ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁ?” አላቸው። እነሱም “እንችላለን” አሉት። |
እሱም “በእርግጥ የእኔን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” አላቸው። |
የቀሩት አሥሩ ይህን ሲሰሙ በሁለቱ ወንድማማቾች ላይ ተቆጡ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.