text stringlengths 4 267 |
|---|
ኢየሱስም “ወንድምሽ ይነሳል” አላት። |
ማርታም “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንደሚነሳ አውቃለሁ” አለችው። |
ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። በእኔ የሚያምን ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል፤ |
በሕይወት ያለና በእኔ የሚያምን ሁሉ ደግሞ ፈጽሞ አይሞትም። ይህን ታምኛለሽ?” |
እሷም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆንህን አምናለሁ” አለችው። |
ይህን ካለች በኋላም ሄዳ እህቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታት “መምህሩ መጥቷል፤ እየጠራሽ ነው” አለቻት። |
ማርያምም ይህን ስትሰማ በፍጥነት ተነስታ ወደ እሱ ሄደች። |
ይሁንና ኢየሱስ እዚያው ማርታ ያገኘችው ቦታ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር። |
እሷን እያጽናኑ በቤት አብረዋት የነበሩ አይሁዳውያንም ማርያም ፈጥና ተነስታ ስትወጣ ሲያዩ ወደ መቃብሩ ሄዳ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት። |
ማርያምም ኢየሱስ የነበረበት ቦታ ደርሳ ባየችው ጊዜ እግሩ ላይ ተደፋች፤ ከዚያም “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። |
ኢየሱስ እሷ ስታለቅስና አብረዋት የመጡት አይሁዳውያን ሲያለቅሱ ሲያይ እጅግ አዘነ፤ ተረበሸም። |
እሱም “የት ነው ያኖራችሁት?” አለ። እነሱም “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት። |
ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ። |
በዚህ ጊዜ አይሁዳውያኑ “እንዴት ይወደው እንደነበር ተመልከቱ!” አሉ። |
ሆኖም ከእነሱ መካከል አንዳንዶች “የዓይነ ስውሩን ዓይን ያበራው ይህ ሰው ይሄኛውንም እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ። |
ከዚያም ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ታውኮ ወደ መቃብሩ መጣ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን በድንጋይም ተዘግቶ ነበር። |
ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” አለ። የሟቹ እህት ማርታም “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል” አለችው። |
ኢየሱስም “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?” አላት። |
ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። |
እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።” |
ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ። |
የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው። |
በመሆኑም ወደ ማርያም መጥተው ከነበሩትና ያደረገውን ነገር ካዩት አይሁዳውያን መካከል ብዙዎቹ በእሱ አመኑ፤ |
አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ነገሯቸው። |
ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሳንሄድሪንን ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች እያደረገ ስለሆነ ምን ብናደርግ ይሻላል? |
እንዲሁ ብንተወው ሁሉም በእሱ ያምናሉ፤ ሮማውያንም መጥተው ቦታችንንና ሕዝባችንን ይወስዱብናል።” |
ሆኖም ከመካከላቸው አንዱ፣ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ምንም አታውቁም፤ |
ደግሞም ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ፣ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት እንደሚሻል ማሰብ ተስኗችኋል።” |
ይሁንና ይህን የተናገረው ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት ስለነበረ ኢየሱስ ለሕዝቡ እንደሚሞት ትንቢት መናገሩ ነበር፤ |
የሚሞተውም ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ተበታትነው ያሉትን የአምላክ ልጆችም አንድ ላይ መሰብሰብ ይችል ዘንድ ነው። |
ስለዚህ ከዚያን ቀን አንስቶ ሊገድሉት አሴሩ። |
በመሆኑም ኢየሱስ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በአይሁዳውያን መካከል በይፋ መንቀሳቀስ አቆመ፤ ከዚህ ይልቅ በምድረ በዳ አቅራቢያ ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ በዚያም ኤፍሬም ተብላ በምትጠራ ከተማ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። |
በዚህ ወቅት የአይሁዳውያን ፋሲካ ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከፋሲካ በፊት የመንጻት ሥርዓት ለመፈጸም ከገጠር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። |
ኢየሱስንም ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደሱም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ጭራሽ ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” ይባባሉ ነበር። |
የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን መያዝ እንዲችሉ እሱ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሁሉ እንዲጠቁማቸው አዘው ነበር። |
በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከአምላክ ጋር ነበር፤ ቃልም አምላክ ነበር። |
እሱም በመጀመሪያ ከአምላክ ጋር ነበር። |
ሁሉም ነገሮች ወደ ሕልውና የመጡት በእሱ በኩል ነው፤ ያለእሱ ወደ ሕልውና የመጣ አንድም ነገር የለም። |
በእሱ አማካኝነት ሕይወት ወደ ሕልውና መጥቷል፤ ይህ ሕይወት ደግሞ የሰው ብርሃን ነበር። |
ብርሃኑም በጨለማ እየበራ ነው፤ ጨለማውም አላሸነፈውም። |
ከአምላክ የተላከ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም ዮሐንስ ይባላል። |
ይህ ሰው ስለ ብርሃኑ ይመሠክር ዘንድ ምሥክር ሆኖ መጣ፤ ይህን ያደረገው ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእሱ በኩል እንዲያምኑ ነው። |
ያ ብርሃን እሱ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ የመጣው ስለ ብርሃኑ ሊመሠክር ነው። |
ለሁሉም ዓይነት ሰው ብርሃን የሚሰጠው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ደርሶ ነበር። |
እሱም በዓለም ነበረ፤ ዓለምም ወደ ሕልውና የመጣው በእሱ በኩል ነው፤ ሆኖም ዓለም አላወቀውም። |
ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ ነገር ግን የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም። |
ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ስላመኑ የአምላክ ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። |
እነሱም የተወለዱት ከአምላክ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አይደለም። |
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ኖረ፤ አንድያ ልጅ ከአባቱ እንደሚያገኘው ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ እሱም መለኮታዊ ሞገስንና እውነትን ተሞልቶ ነበር። |
(ዮሐንስ ስለ እሱ መሥክሯል፤ እንዲያውም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “‘ከእኔ ኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ብዬ የተናገርኩት ስለ እሱ ነው።”) |
ከእሱ የጸጋ ሙላት የተነሳ ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል። |
ምክንያቱም ሕጉ የተሰጠው በሙሴ በኩል ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው። |
በየትኛውም ጊዜ ቢሆን አምላክን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ስለ እሱ የገለጸልን ከአብ ጎን ያለውና አምላክ የሆነው አንድያ ልጁ ነው። |
አይሁዳውያን “አንተ ማን ነህ?” ብለው እንዲጠይቁት ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩ ጊዜ ዮሐንስ የሰጠው ምሥክርነት ይህ ነው፤ |
“እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ በግልጽ ተናገረ እንጂ ጥያቄውን ከመመለስ ወደኋላ አላለም። |
እነሱም “ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህ?” ሲሉ ጠየቁት። እሱም መልሶ “አይደለሁም” አለ። “ነቢዩ ነህ?” አሉት። እሱም “አይደለሁም!” ሲል መለሰ። |
በዚህ ጊዜ “ለላኩን ሰዎች መልስ መስጠት እንድንችል ታዲያ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?” አሉት። |
እሱም “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ‘የይሖዋን መንገድ አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸው ሰው እኔ ነኝ” አለ። |
ሰዎቹን የላኳቸውም ፈሪሳውያን ነበሩ። |
በመሆኑም “ታዲያ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንክ ለምን ታጠምቃለህ?” ሲሉ ጠየቁት። |
ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃለሁ። እናንተ የማታውቁት ግን በመካከላችሁ ቆሟል፤ |
እሱም ከኋላዬ ይመጣል፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም።” |
ይህ የሆነው ዮሐንስ ሲያጠምቅ ከነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ በሚገኘው በቢታንያ ነበር። |
በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የአምላክ በግ ይኸውላችሁ! |
‘ከኋላዬ አንድ ሰው ይመጣል፤ ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ያልኳችሁ እሱ ነው። |
እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ እኔ በውኃ እያጠመቅኩ የመጣሁበት ምክንያት ግን እሱ ለእስራኤል እንዲገለጥ ነው።” |
በተጨማሪም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምሥክርነት ሰጥቷል፦ “መንፈስ ከሰማይ ወጥቶ እንደ ርግብ ሲወርድ አይቻለሁ፤ በእሱም ላይ አረፈ። |
እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ ሆኖም በውኃ እንዳጠምቅ የላከኝ ራሱ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው ያ ሰው ነው’ አለኝ። |
እኔም አይቻለሁ፤ እሱም የአምላክ ልጅ መሆኑን መሥክሬአለሁ።” |
በማግስቱም ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደገና በዚያ ቆሞ ነበር፤ |
ኢየሱስ ሲያልፍ አይቶም “የአምላክ በግ ይኸውላችሁ!” አለ። |
ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ይህን ሲናገር በሰሙ ጊዜ ኢየሱስን ተከተሉት። |
ከዚያም ኢየሱስ ዞር ብሎ ሲከተሉት አየና “ምን ፈልጋችሁ ነው?” አላቸው። እነሱም “ረቢ፣ የት ነው የምትኖረው?” አሉት (ረቢ ማለት “መምህር” ማለት ነው)፤ |
እሱም “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ ጊዜውም አሥር ሰዓት ገደማ ነበር፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ። |
ዮሐንስ የተናገረውን ከሰሙትና ኢየሱስን ከተከተሉት ሁለት ሰዎች አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር። |
እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሲሑን አገኘነው” አለው (መሲሕ ማለት “ክርስቶስ” ማለት ነው)፤ |
ወደ ኢየሱስም ወሰደው። ኢየሱስም ባየው ጊዜ “አንተ የዮሐንስ ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው (ኬፋ ማለት “ጴጥሮስ” ማለት ነው)። |
በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ። ከዚያም ፊልጶስን አግኝቶ “ተከታዬ ሁን” አለው። |
ፊልጶስም እንደ እንድርያስና እንደ ጴጥሮስ የቤተሳይዳ ከተማ ሰው ነበረ። |
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ “ሙሴ በሕጉ፣ ነቢያት ደግሞ በመጻሕፍት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው። |
ናትናኤል ግን “ደግሞ ከናዝሬት ጥሩ ነገር ሊገኝ ይችላል?” አለው። ፊልጶስም “መጥተህ እይ” አለው። |
ኢየሱስም ናትናኤል ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እሱ “ተንኮል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይኸውላችሁ!” አለ። |
ናትናኤልም “እንዴት ልታውቀኝ ቻልክ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይቼሃለሁ” አለው። |
ናትናኤልም “ረቢ፣ አንተ የአምላክ ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” ሲል መለሰለት። |
ኢየሱስም መልሶ “ያመንከው ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ስላልኩህ ነው? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ገና ታያለህ” አለው። |
ከዚያም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይ ተከፍቶ የአምላክ መላእክት ወደዚያ ሲወጡና የሰው ልጅ ወዳለበት ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ መዘዋወሩን ቀጠለ፤ ምክንያቱም አይሁዳውያን ሊገድሉት ይፈልጉ ስለነበር በይሁዳ ምድር መዘዋወር አልፈለገም። |
ይሁን እንጂ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው የዳስ በዓል ተቃርቦ ነበር። |
ስለዚህ ወንድሞቹ እንዲህ አሉት፦ “ደቀ መዛሙርትህም የምታከናውነውን ሥራ ማየት እንዲችሉ ከዚህ ተነስተህ ወደ ይሁዳ ሂድ። |
በይፋ እንዲታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ሰው የለምና። እነዚህን ነገሮች የምትሠራ ከሆነ ራስህን ለዓለም ግለጥ።” |
ወንድሞቹም ቢሆኑ አላመኑበትም ነበር። |
ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ተስማሚ ነው። |
ዓለም እናንተን የሚጠላበት ምንም ምክንያት የለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ እንደሆነ ስለምመሠክርበት ይጠላኛል። |
እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ እኔ ግን ገና ጊዜዬ ስላልደረሰ ወደ በዓሉ አልሄድም።” |
ይህን ከነገራቸው በኋላ በገሊላ ቆየ። |
ሆኖም ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ። |
በበዓሉም ላይ አይሁዳውያን “ያ ሰው የት አለ?” እያሉ ይፈልጉት ጀመር። |
በሕዝቡም መካከል ስለ እሱ ብዙ ጉምጉምታ ነበር። አንዳንዶች “እሱ ጥሩ ሰው ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “አይደለም። እሱ ሕዝቡን ያሳስታል” ይሉ ነበር። |
እርግጥ አይሁዳውያንን ይፈሩ ስለነበረ ስለ እሱ በግልጽ የሚናገር ሰው አልነበረም። |
በበዓሉም አጋማሽ ላይ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዶ ያስተምር ጀመር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.