text stringlengths 4 267 |
|---|
አይሁዳውያንም በጣም ተገርመው “ይህ ሰው ትምህርት ቤት ገብቶ ሳይማር ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዴት እንዲህ ሊያውቅ ቻለ?” አሉ። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የማስተምረው ትምህርት የራሴ ሳይሆን ከላከኝ የመጣ ነው። |
ማንም የእሱን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልግ ከሆነ ይህ ትምህርት ከአምላክ የመጣ ይሁን ከራሴ ለይቶ ያውቃል። |
ከራሱ አመንጭቶ የሚናገር ሁሉ ራሱ እንዲከበር ይፈልጋል፤ የላከው እንዲከበር የሚፈልግ ሁሉ ግን እሱ እውነተኛ ነው፤ በእሱም ዘንድ ዓመፅ የለም። |
ሕጉን የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም? ሆኖም አንዳችሁም ሕጉን አትታዘዙም። እኔን ለመግደል የምትፈልጉት ለምንድን ነው?” |
ሕዝቡም “አንተ ጋኔን አለብህ። ሊገድልህ የፈለገው ደግሞ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ነገር ስለሠራሁ ሁላችሁም ተደነቃችሁ። |
እስቲ ይህን ልብ በሉ፦ ሙሴ የግርዘትን ሕግ ሰጣችሁ (ይህ ሕግ የተሰጠው ከአባቶች ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም)፤ እናንተም በሰንበት ሰው ትገርዛላችሁ። |
የሙሴ ሕግ እንዳይጣስ ሲባል በሰንበት ቀን ሰው የሚገረዝ ከሆነ እኔ በሰንበት አንድን ሰው መፈወሴ ይህን ያህል ሊያስቆጣችሁ ይገባል? |
የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ፍረዱ።” |
በዚህ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፦ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለም እንዴ? |
እሱ ግን ይኸው በአደባባይ እየተናገረ ነው፤ እነሱም ምንም አላሉትም። ገዢዎቹ ይህ ሰው በእርግጥ ክርስቶስ እንደሆነ አስበው ይሆን? |
ሆኖም እኛ ይህ ሰው ከየት እንደመጣ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም።” |
ከዚያም ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እያስተማረ ሳለ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እኔ ማን እንደሆንኩም ሆነ ከየት እንደመጣሁ ታውቃላችሁ። የመጣሁትም በራሴ ተነሳስቼ አይደለም፤ ሆኖም የላከኝ በእውን ያለ ነው፤ እናንተም አታውቁትም። |
እኔ ግን የእሱ ተወካይ ሆኜ የመጣሁ ስለሆንኩ አውቀዋለሁ፤ የላከኝም እሱ ነው።” |
በመሆኑም ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም። |
ይሁንና ከሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእሱ አምነው “ክርስቶስስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው የበለጠ ብዙ ተአምራዊ ምልክት ያደርጋል እንዴ?” ይሉ ነበር። |
ፈሪሳውያን ሕዝቡ በጉምጉምታ ስለ እሱ የሚያወራውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያኑም ይይዙት ዘንድ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኩ። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ። |
እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም።” |
በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሰው ልናገኘው የማንችለው ወዴት ሊሄድ ቢያስብ ነው? በግሪካውያን መካከል ተበታትነው ወደሚገኙት አይሁዳውያን ሄዶ ግሪካውያንን ሊያስተምር አስቦ ይሆን እንዴ? |
‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?” |
የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “የተጠማ ካለ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። |
በእኔ የሚያምን ሁሉ ቅዱስ መጽሐፉ እንደሚለው ‘ሕይወት የሚሰጥ የውኃ ጅረት ከውስጡ ይፈስሳል።’” |
ይሁን እንጂ ይህን ሲል በእሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ መናገሩ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክብሩን ገና ስላልተጎናጸፈ መንፈስ አልተሰጠም ነበር። |
ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር። |
ሌሎችም “ይህ ክርስቶስ ነው” ይሉ ነበር። አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “ክርስቶስ የሚመጣው ከገሊላ ነው እንዴ? |
ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና ዳዊት ከኖረበት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለም?” |
ስለዚህ እሱን በተመለከተ በሕዝቡ መካከል ክፍፍል ተፈጠረ። |
ይሁንና አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልያዘውም። |
ከዚያም የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ፈሪሳውያኑ ተመልሰው ሄዱ፤ እነሱም ጠባቂዎቹን “ለምን ይዛችሁት አልመጣችሁም?” አሏቸው። |
ጠባቂዎቹም “ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም” ብለው መለሱ። |
ፈሪሳውያኑ ግን እንዲህ አሏቸው፦ “እናንተም ተታለላችሁ? |
ከገዢዎች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእሱ ያመነ አለ? |
ሕጉን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ግን የተረገመ ነው።” |
ቀደም ሲል ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረውና ከእነሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው፦ |
“ሕጋችን በመጀመሪያ ግለሰቡ የሚለውን ሳይሰማና ምን እያደረገ እንዳለ ሳያውቅ ይፈርድበታል?” |
እነሱም “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ? ከገሊላ አንድም ነቢይ እንደማይነሳ ቅዱሳን መጻሕፍትን መርምረህ ተረዳ” አሉት። |
የፋሲካ በዓል ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ ስላወቀ በዓለም የነበሩትንና የወደዳቸውን ተከታዮቹን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው። |
በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር። ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ውስጥ ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር። |
ኢየሱስ፣ አብ ሁሉን ነገር በእጁ እንደሰጠው እንዲሁም ከአምላክ እንደመጣና ወደ አምላክ እንደሚሄድ ያውቅ ስለነበር |
ከራት ተነስቶ መደረቢያውን አስቀመጠ። ፎጣ ወስዶም ወገቡ ላይ አሸረጠ። |
ከዚያም በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና ባሸረጠው ፎጣ ማድረቅ ጀመረ። |
ከዚያም ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ። ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ልታጥብ ነው?” አለው። |
ኢየሱስም መልሶ “እያደረግኩት ያለውን ነገር አሁን አትረዳውም፤ በኋላ ግን ትረዳዋለህ” አለው። |
ጴጥሮስም “በፍጹም እግሬን አታጥብም” አለው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ምንም ድርሻ አይኖርህም” ሲል መለሰለት። |
ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ” አለው። |
ኢየሱስም “ገላውን የታጠበ ሁለመናው ንጹሕ በመሆኑ ከእግሩ በስተቀር መታጠብ አያስፈልገውም። እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ ሁላችሁም ግን አይደላችሁም” አለው። |
ምክንያቱም አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ማን እንደሆነ ያውቅ ነበር። “ሁላችሁም ንጹሐን አይደላችሁም” ያለው ለዚህ ነው። |
እግራቸውን አጥቦ ካበቃና መደረቢያውን ለብሶ ዳግመኛ በማዕድ ከተቀመጠ በኋላ እንዲህ አላቸው፦ “ምን እንዳደረግኩላችሁ አስተዋላችሁ? |
እናንተ ‘መምህር’ እና ‘ጌታ’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እንደዚያ ስለሆንኩም እንዲህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል ነው። |
ስለዚህ እኔ ጌታና መምህር ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብኩ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል። |
እኔ እንዳደረግኩላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ አርዓያ ሆኜላችኋለሁ። |
እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ የተላከም ከላከው አይበልጥም። |
እነዚህን ነገሮች ስለምታውቁ ብትፈጽሟቸው ደስተኞች ናችሁ። |
ይህን ስል ስለ ሁላችሁም መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኳቸውን አውቃለሁ። ይሁንና ‘ከማዕዴ ይበላ የነበረ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ’ የሚለው የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። |
ገና ሳይፈጸም በፊት አሁን የምነግራችሁ፣ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እሱ መሆኔን እንድታምኑ ነው። |
እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ የምልከውን የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ሁሉ ደግሞ የላከኝንም ይቀበላል።” |
ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል በግልጽ ተናገረ። |
ደቀ መዛሙርቱም ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ግራ ገብቷቸው እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር። |
ከእነሱ አንዱ ይኸውም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ኢየሱስ አጠገብ ጋደም ብሎ ነበር። |
ስምዖን ጴጥሮስም ለዚህ ደቀ መዝሙር ምልክት በመስጠት “ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ንገረን” አለው። |
እሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ “ጌታ ሆይ፣ ማን ነው?” አለው። |
ኢየሱስም “ይህን የማጠቅሰውን ቁራሽ ዳቦ የምሰጠው ሰው ነው” ሲል መለሰ። ከዚያም ዳቦውን አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። |
ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት። ስለዚህ ኢየሱስ “እያደረግከው ያለኸውን ነገር ቶሎ አድርገው” አለው። |
ይሁን እንጂ በማዕድ ከተቀመጡት መካከል አንዳቸውም ለምን እንዲህ እንዳለው አልገባቸውም። |
እንዲያውም አንዳንዶቹ ይሁዳ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ ስለነበር ለበዓሉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዲገዛ ወይም ለድሆች የሆነ ነገር እንዲሰጥ ኢየሱስ ያዘዘው መስሏቸው ነበር። |
ስለዚህ ይሁዳ ቁራሹን ዳቦ ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ ወጣ። ጊዜውም ሌሊት ነበር። |
ይሁዳ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ክብር ተጎናጸፈ፤ አምላክም በእሱ አማካኝነት ከበረ። |
አምላክ ራሱም ያከብረዋል፤ ደግሞም ወዲያውኑ ያከብረዋል። |
ልጆቼ ሆይ፣ ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ። እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁዳውያን ‘ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኳቸው ሁሉ አሁን ደግሞ ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ። |
እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። |
እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።” |
ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ በኋላ ግን ትከተለኛለህ” ሲል መለሰ። |
ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ሕይወቴን ስለ አንተ አሳልፌ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ” አለው። |
ኢየሱስም “ሕይወትህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህ? እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል መለሰ። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር እንደገና ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ። የተገለጠውም በዚህ መንገድ ነበር፤ |
ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ፣ የገሊላ ቃና ሰው የሆነው ናትናኤል፣ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ። |
ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነሱም “እኛም አብረንህ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተው ሄዱና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፤ በዚያ ሌሊት ግን አንድም ዓሣ አልያዙም። |
ይሁን እንጂ ጎህ ሲቀድ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም ነበር። |
ከዚያም ኢየሱስ “ልጆቼ፣ የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “የለንም!” ብለው መለሱለት። |
እሱም “መረቡን ከጀልባዋ በስተ ቀኝ ጣሉት፤ ዓሣ ታገኛላችሁ” አላቸው። እነሱም መረቡን ጣሉ፤ ከዓሣውም ብዛት የተነሳ መረቡን መጎተት አቃታቸው። |
በዚህ ጊዜ፣ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን ሲሰማ ከወገቡ በላይ ራቁቱን ስለነበር መደረቢያውን ለበሰና ዘሎ ባሕሩ ውስጥ ገባ። |
ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከባሕሩ ዳርቻ ብዙም ሳይርቁ 90 ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ስለነበሩ በዓሣዎች የተሞላውን መረብ እየጎተቱ በትንሿ ጀልባ መጡ። |
ወደ ባሕሩ ዳርቻ በደረሱ ጊዜ በከሰል ፍም ላይ የተቀመጠ ዓሣ እንዲሁም ዳቦ አዩ። |
ኢየሱስ “አሁን ከያዛችሁት ዓሣ የተወሰነ አምጡ” አላቸው። |
ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጀልባዋ ላይ ወጥቶ በትላልቅ ዓሣዎች የተሞላውን መረብ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ጎተተው፤ የዓሣዎቹም ብዛት 153 ነበር። መረቡ ይህን ያህል ብዙ ዓሣ ቢይዝም አልተቀደደም። |
ኢየሱስ “ኑ፣ ቁርሳችሁን ብሉ” አላቸው። ጌታ መሆኑን አውቀው ስለነበር ከደቀ መዛሙርቱ መካከል “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። |
ኢየሱስም መጥቶ ዳቦውን አነሳና ሰጣቸው፤ ዓሣውንም አንስቶ እንዲሁ አደረገ። |
ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር። |
ቁርስ በልተው ከጨረሱም በኋላ ኢየሱስ፣ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን መግብ” አለው። |
ደግሞም ለሁለተኛ ጊዜ “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ግልገሎቼን ጠብቅ” አለው። |
ለሦስተኛ ጊዜም “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ በጣም ትወደኛለህ?” አለው። ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ “በጣም ትወደኛለህ?” ብሎ ስለጠየቀው አዘነ። በመሆኑም “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ግልገሎቼን መግብ። |
እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት ሳለህ ራስህ ለብሰህ ወደፈለግክበት ቦታ ትሄድ ነበር። ስታረጅ ግን እጅህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያለብስሃል፤ ወደማትፈልግበትም ቦታ ይወስድሃል።” |
ይህን የተናገረው፣ ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት አምላክን እንደሚያከብር ለማመልከት ነበር። ይህን ካለ በኋላ “እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። |
ጴጥሮስ ዞር ሲል ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር ራት በበሉ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ፣ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው። |
ጴጥሮስም ባየው ጊዜ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ ይህስ ሰው ምን ይሆናል?” አለው። |
ኢየሱስም “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ? አንተ እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። |
በመሆኑም ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚል ወሬ በወንድሞች መካከል ተሰራጨ። ይሁንና ኢየሱስ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ?” አለው እንጂ አይሞትም አላለውም። |
ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረውና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ እሱ የሚሰጠው ምሥክርነትም እውነት እንደሆነ እናውቃለን። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.