text stringlengths 4 267 |
|---|
እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማና የላከኝን የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ ወደ ፍርድም አይመጣም፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግሯል። |
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሙታን የአምላክን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። |
አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና። |
እሱ የሰው ልጅ ስለሆነ የመፍረድ ሥልጣን ሰጥቶታል። |
በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤ |
መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ። |
በራሴ ተነሳስቼ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ መፈጸም ስለምፈልግ የምፈርደው የጽድቅ ፍርድ ነው። |
“እኔ ብቻ ስለ ራሴ ብመሠክር ምሥክርነቴ እውነት አይደለም። |
ስለ እኔ የሚመሠክር ሌላ አለ፤ ደግሞም እሱ ስለ እኔ የሚሰጠው ምሥክርነት እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። |
ወደ ዮሐንስ ሰዎች ልካችሁ ነበር፤ እሱም ለእውነት መሥክሯል። |
ይሁን እንጂ እኔ የሰው ምሥክርነት አያስፈልገኝም፤ ይህን የምናገረው ግን እናንተ እንድትድኑ ነው። |
ያ ሰው የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበር፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በእሱ ብርሃን እጅግ ለመደሰት ፈቃደኞች ነበራችሁ። |
እኔ ግን ከዮሐንስ የበለጠ ምሥክር አለኝ፤ ምክንያቱም አባቴ እንዳከናውነው የሰጠኝ ሥራ ማለትም እየሠራሁት ያለው ይህ ሥራ አብ እንደላከኝ ይመሠክራል። |
የላከኝ አብም ራሱ ስለ እኔ መሥክሯል። እናንተ መቼም ቢሆን ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤ |
እሱ የላከውንም ስለማታምኑ ቃሉ በልባችሁ ውስጥ አይኖርም። |
“እናንተ በቅዱሳን መጻሕፍት የዘላለም ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ እነሱን ትመረምራላችሁ፤ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሠክሩ ናቸው። |
ሆኖም ሕይወት እንድታገኙ ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም። |
እኔ ከሰው ክብር መቀበል አልፈልግም፤ |
ይሁንና እናንተ የአምላክ ፍቅር በውስጣችሁ እንደሌለ በሚገባ አውቃለሁ። |
እኔ በአባቴ ስም መጣሁ፤ እናንተ ግን አልተቀበላችሁኝም። ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ ትቀበሉታላችሁ። |
እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትሰጣጡና ከአንዱ አምላክ የሚገኘውን ክብር የማትፈልጉ ሆናችሁ ሳላችሁ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? |
እኔ በአብ ፊት የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ፤ እሱም ተስፋ የጣላችሁበት ሙሴ ነው። |
ደግሞም ሙሴን ብታምኑት ኖሮ እኔንም ታምኑኝ ነበር፤ እሱ ስለ እኔ ጽፏልና። |
ሆኖም እሱ የጻፈውን ካላመናችሁ እኔ የምናገረውን እንዴት ታምናላችሁ?” |
“ልባችሁ አይረበሽ። በአምላክ እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። |
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ። ይህ ባይሆን ኖሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤ ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና። |
ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ። |
እኔ ወደምሄድበትም ቦታ የሚወስደውን መንገድ ታውቃላችሁ።” |
ቶማስም “ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም። ታዲያ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። |
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። |
እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ታውቁት ነበር፤ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ታውቁታላችሁ፤ ደግሞም አይታችሁታል።” |
ፊልጶስም “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። |
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ፊልጶስ፣ ከእናንተ ጋር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ ኖሬም እንኳ አላወቅከኝም? እኔን ያየ ሁሉ አብንም አይቷል። ታዲያ እንዴት ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? |
እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም? የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው። |
እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ አብም ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እመኑኝ፤ ካልሆነ ደግሞ ከተሠሩት ሥራዎች የተነሳ እመኑ። |
እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን ሁሉ እኔ የምሠራቸውን ሥራዎች ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ እሱ ከእነዚህ የበለጡ ሥራዎች ይሠራል። |
በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። |
ማንኛውንም ነገር በስሜ ከለመናችሁ እኔ አደርገዋለሁ። |
“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዛቴን ትጠብቃላችሁ። |
እኔም አብን እጠይቃለሁ፤ እሱም ለዘላለም ከእናንተ ጋር የሚሆን ሌላ ረዳት ይሰጣችኋል፤ |
እሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን አብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስላለ ታውቁታላችሁ። |
ሐዘን ላይ ትቻችሁ አልሄድም። ወደ እናንተ እመጣለሁ። |
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ ምክንያቱም እኔ እኖራለሁ፤ እናንተም ትኖራላችሁ። |
እኔ ከአባቴ ጋር አንድነት እንዳለኝ፣ እናንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳላችሁና እኔም ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። |
እኔን የሚወደኝ ትእዛዛቴን የሚቀበልና የሚጠብቅ ነው። እኔን የሚወደኝን ሁሉ ደግሞ አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” |
የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላው ይሁዳ “ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን ለመግለጥ ያሰብከው ለምንድን ነው?” አለው። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ማንም ሰው እኔን የሚወደኝ ከሆነ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፣ እኛም ወደ እሱ መጥተን መኖሪያችንን ከእሱ ጋር እናደርጋለን። |
እኔን የማይወደኝ ሁሉ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ እየሰማችሁት ያለው ቃል ደግሞ የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። |
“አሁን ከእናንተ ጋር እያለሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። |
ሆኖም አብ በስሜ የሚልከው ረዳት ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል እንዲሁም የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል። |
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ። እኔ ሰላም የምሰጣችሁ ዓለም በሚሰጥበት መንገድ አይደለም። ልባችሁ አይረበሽ፤ በፍርሃትም አይዋጥ። |
‘እሄዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ’ እንዳልኳችሁ ሰምታችኋል። ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ ከእኔ አብ ይበልጣልና። |
በመሆኑም በሚፈጸምበት ጊዜ እንድታምኑ ከመፈጸሙ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ። |
የዚህ ዓለም ገዢ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም። |
ይሁን እንጂ እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት እየሠራሁ ነው። ተነሱ ከዚህ እንሂድ። |
“እኔ እውነተኛው የወይን ተክል ነኝ፤ አትክልተኛው ደግሞ አባቴ ነው። |
በእኔ ላይ ያለውን፣ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቆርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ደግሞ ይበልጥ እንዲያፈራ ያጠራዋል። |
እናንተ ከነገርኳችሁ ቃል የተነሳ አሁን ንጹሐን ናችሁ። |
ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ያለኝን አንድነት ጠብቄ እኖራለሁ። ቅርንጫፉ ከወይኑ ተክል ጋር ተጣብቆ ካልኖረ በራሱ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ እናንተም ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። |
እኔ የወይኑ ተክል ነኝ፤ እናንተ ደግሞ ቅርንጫፎቹ ናችሁ። ማንኛውም ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ከኖረና እኔም ከእሱ ጋር አንድ ሆኜ ከኖርኩ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ እናንተ ከእኔ ተለይታችሁ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉምና። |
አንድ ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ካልኖረ እንደ ቅርንጫፍ ይጣልና ይደርቃል። ሰዎችም እንዲህ ያሉትን ቅርንጫፎች ሰብስበው እሳት ውስጥ በመጣል ያቃጥሏቸዋል። |
እናንተ ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ከጠበቃችሁና ቃሌ በልባችሁ ከኖረ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ብትጠይቁ ይፈጸምላችኋል። |
ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብታሳዩ በዚህ አባቴ ይከበራል። |
አብ እኔን እንደወደደኝ፣ እኔም እናንተን እንዲሁ ወድጃችኋለሁ። እናንተም በፍቅሬ ኑሩ። |
እኔ የአብን ትእዛዛት ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም ትእዛዛቴን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። |
“እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ እኔ ያገኘሁትን ደስታ እንድታገኙና የእናንተም ደስታ የተሟላ እንዲሆን ነው። |
ትእዛዜ ይህ ነው፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። |
ሕይወቱን ለወዳጆቹ ሲል አሳልፎ ከሚሰጥ ሰው የበለጠ ፍቅር ያለው ማንም የለም። |
የማዛችሁን ነገር የምትፈጽሙ ከሆነ ወዳጆቼ ናችሁ። |
ከእንግዲህ ባሪያዎች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን ነገር አያውቅም። እኔ ግን ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ ስላሳወቅኳችሁ ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ። |
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩና ፍሬያችሁ ጸንቶ እንዲኖር ሾሜያችኋለሁ፤ የመረጥኳችሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ ነው። |
“እነዚህን ነገሮች የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። |
ዓለም ቢጠላችሁ፣ እናንተን ከመጥላቱ በፊት እኔን እንደጠላኝ ታውቃላችሁ። |
የዓለም ክፍል ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር። አሁን ግን እኔ ከዓለም መረጥኳችሁ እንጂ የዓለም ክፍል ስላልሆናችሁ ከዚህ የተነሳ ዓለም ይጠላችኋል። |
ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ ደግሞ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። |
ሆኖም የላከኝን ስለማያውቁት በስሜ ምክንያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደርጉባችኋል። |
መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር። አሁን ግን ለኃጢአታቸው የሚያቀርቡት ሰበብ የለም። |
እኔን የሚጠላ ሁሉ አባቴንም ይጠላል። |
ሌላ ማንም ያላደረገውን ነገር በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔን አይተዋል እንዲሁም እኔንም ሆነ አባቴን ጠልተዋል። |
ይሁን እንጂ ይህ የሆነው ‘ያለምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው። |
ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ከአብ የሚወጣው ረዳት ይኸውም የእውነት መንፈስ ሲመጣ እሱ ስለ እኔ ይመሠክራል፤ |
እናንተም ደግሞ ትመሠክራላችሁ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያ አንስቶ ከእኔ ጋር ነበራችሁ። |
ጌታ፣ ከዮሐንስ ይበልጥ ብዙ ደቀ መዛሙርት እያፈራና እያጠመቀ መሆኑን ፈሪሳውያን እንደሰሙ ባወቀ ጊዜ፣ |
(እርግጥ ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም) |
ይሁዳን ለቆ እንደገና ወደ ገሊላ ሄደ። |
ሆኖም በሰማርያ በኩል ማለፍ ነበረበት። |
ስለሆነም ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው መሬት አጠገብ ወዳለችው ሲካር ወደተባለች የሰማርያ ከተማ መጣ። |
ደግሞም በዚያ የያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ ነበረ። ኢየሱስም ከጉዞው የተነሳ ደክሞት ስለነበር በውኃ ጉድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ። ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር። |
አንዲት የሰማርያ ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። |
(ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማዋ ሄደው ነበር።) |
ሳምራዊቷም “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እኔን ሳምራዊቷን እንዴት የምጠጣው ውኃ ስጪኝ ትለኛለህ?” አለችው። (ይህን ያለችው አይሁዳውያን ከሳምራውያን ጋር ምንም ግንኙነት ስላልነበራቸው ነው።) |
ኢየሱስም መልሶ “የአምላክን ነፃ ስጦታ ብታውቂና ‘የምጠጣው ውኃ ስጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ አንቺ ራስሽ ትጠይቂው ነበር፤ እሱም የሕይወት ውኃ ይሰጥሽ ነበር” አላት። |
እሷም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ውኃ መቅጃ እንኳ የለህም፤ ጉድጓዱ ደግሞ ጥልቅ ነው። ታዲያ ይህን የሕይወት ውኃ ከየት ታገኛለህ? |
አንተ ይህን የውኃ ጉድጓድ ከሰጠን እንዲሁም ከልጆቹና ከከብቶቹ ጋር ከዚህ ጉድጓድ ከጠጣው ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህ?” |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል። |
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ፈጽሞ አይጠማም፤ ከዚህ ይልቅ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝ የውኃ ምንጭ ይሆናል።” |
ሴትየዋም “ጌታዬ፣ እንዳልጠማም ሆነ ውኃ ለመቅዳት ወደዚህ ቦታ እንዳልመላለስ ይህን ውኃ ስጠኝ” አለችው። |
እሱም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመልሰሽ ነይ” አላት። |
ሴትየዋም “ባል የለኝም” ብላ መለሰችለት። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “‘ባል የለኝም’ ማለትሽ ትክክል ነው። |
ምክንያቱም አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን አብሮሽ ያለው ሰው ደግሞ ባልሽ አይደለም። ስለዚህ የተናገርሽው እውነት ነው።” |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.