text stringlengths 4 267 |
|---|
ሴትየዋም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አሁን ተረዳሁ። |
አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ አምልኳቸውን ያካሂዱ ነበር፤ እናንተ አይሁዳውያን ግን ሰዎች ማምለክ ያለባቸው በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ።” |
ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፣ እመኚኝ፤ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም አብን የማታመልኩበት ሰዓት ይመጣል። |
እናንተ የማታውቁትን ታመልካላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚጀምረው ከአይሁዳውያን ስለሆነ የምናውቀውን እናመልካለን። |
ይሁንና እውነተኛ አምላኪዎች አብን በመንፈስና በእውነት የሚያመልኩበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ ምክንያቱም አብ እንዲያመልኩት የሚፈልገው እንዲህ ያሉ ሰዎችን ነው። |
አምላክ መንፈስ ነው፤ የሚያመልኩትም በመንፈስና በእውነት ሊያመልኩት ይገባል።” |
ሴትየዋም “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ። እሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ግልጥልጥ አድርጎ ይነግረናል” አለችው። |
ኢየሱስም “እያነጋገርኩሽ ያለሁት እኔ፣ እሱ ነኝ” አላት። |
በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋር ሲነጋገር አይተውም ተደነቁ። ይሁን እንጂ “ምን ፈልገህ ነው?” ወይም “ከእሷ ጋር የምትነጋገረው ለምንድን ነው?” ያለው ማንም አልነበረም። |
ሴትየዋም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማዋ በመሄድ ሰዎቹን እንዲህ አለቻቸው፦ |
“ያደረግኩትን ሁሉ የነገረኝን ሰው መጥታችሁ እዩ። ይህ ሰው ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” |
እነሱም ከከተማዋ ወጥተው ወደ እሱ መጡ። |
በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ረቢ፣ ብላ እንጂ” እያሉ ጎተጎቱት። |
እሱ ግን “እናንተ የማታውቁት የምበላው ምግብ አለኝ” አላቸው። |
ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው “ምግብ ያመጣለት ይኖር ይሆን እንዴ?” ተባባሉ። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና እንዳከናውነው የሰጠኝን ሥራ መፈጸም ነው። |
እናንተ መከር ሊገባ ገና አራት ወር ይቀረዋል ትሉ የለም? እነሆ እላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን ወደ ማሳው አቅንታችሁ አዝመራው እንደነጣ ተመልከቱ። |
አሁንም እንኳ አጫጁ ደሞዙን እየተቀበለና ለዘላለም ሕይወት ፍሬ እየሰበሰበ ነው፤ ስለዚህ ዘሪውም ሆነ አጫጁ በአንድነት ደስ ይላቸዋል። |
ከዚህም የተነሳ ‘አንዱ ይዘራል፤ ሌላኛውም ያጭዳል’ የሚለው አባባል እውነት ነው። |
እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ። ሌሎች በደከሙበት እናንተ የድካማቸው ፍሬ ተካፋዮች ሆናችሁ።” |
ሴትየዋ “ያደረግኩትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ ስለመሠከረች ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በእሱ አመኑ። |
ሳምራውያኑም ወደ እሱ በመጡ ጊዜ አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት፤ እሱም በዚያ ሁለት ቀን ቆየ። |
በመሆኑም ሌሎች ብዙ ሰዎች ከተናገረው ቃል የተነሳ አመኑ፤ |
ሴትየዋንም “ከእንግዲህ የምናምነው አንቺ ስለነገርሽን ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ራሳችን ሰምተናል፤ እንዲሁም ይህ ሰው በእርግጥ የዓለም አዳኝ እንደሆነ አውቀናል” አሏት። |
ከሁለት ቀናት በኋላ ከዚያ ተነስቶ ወደ ገሊላ ሄደ። |
ይሁንና ኢየሱስ ራሱ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ተናግሮ ነበር። |
ገሊላ በደረሰ ጊዜም የገሊላ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ተቀበሉት፤ ምክንያቱም በኢየሩሳሌም በበዓሉ ላይ ተገኝተው በዚያ ያከናወናቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። |
ከዚያም ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ወደለወጠባት በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና በድጋሚ መጣ። በዚህ ጊዜ በቅፍርናሆም፣ ልጁ የታመመበት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን የሆነ አንድ ሰው ነበር። |
ይህ ሰው ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን ሲሰማ ወደ እሱ ሄደና ወደ ቅፍርናሆም ወርዶ በሞት አፋፍ ላይ ያለውን ልጁን እንዲፈውስለት ለመነው። |
ኢየሱስ ግን “መቼም እናንተ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ካላያችሁ ፈጽሞ አታምኑም” አለው። |
የቤተ መንግሥት ባለሥልጣኑም “ጌታዬ፣ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ በቶሎ ድረስ” አለው። |
ኢየሱስም “ሂድ፤ ልጅህ ድኗል” አለው። ሰውየውም ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ። |
ሆኖም ሰውየው ወደዚያ እየወረደ ሳለ ባሪያዎቹ አገኙትና ልጁ በሕይወት እንዳለ ነገሩት። |
እሱም ልጁ ስንት ሰዓት ላይ እንደተሻለው ጠየቃቸው። እነሱም “ትናንት ሰባት ሰዓት ላይ ትኩሳቱ ለቀቀው” ብለው መለሱለት። |
በዚህ ጊዜ አባትየው ልጁ የዳነው ልክ ኢየሱስ “ልጅህ ድኗል” ባለው ሰዓት ላይ መሆኑን አወቀ። እሱና መላው ቤተሰቡም አማኞች ሆኑ። |
ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ ሲመጣ ያከናወነው ሁለተኛው ተአምራዊ ምልክት ነው። |
በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን መግደላዊቷ ማርያም በማለዳ፣ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ መጣች፤ መቃብሩ የተዘጋበትም ድንጋይ ተንከባሎ አየች። |
ስለዚህ ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር እየሮጠች መጥታ “ጌታን ከመቃብሩ ውስጥ ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩትም አናውቅም” አለቻቸው። |
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ አመሩ። |
ሁለቱም አብረው ይሮጡ ጀመር፤ ሆኖም ሌላው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ በመሮጥ መቃብሩ ጋ ደረሰ። |
ጎንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት የበፍታ ጨርቆቹ እዚያ ተቀምጠው አየ፤ ወደ ውስጥ ግን አልገባም። |
ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ ተከትሎት መጥቶ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቆቹም በዚያ ተቀምጠው አየ። |
በራሱ ላይ የነበረው ጨርቅ፣ ከመግነዝ ጨርቆቹ ጋር ሳይሆን ለብቻው ተጠቅልሎ አንድ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየ። |
ከዚያም ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ሌላው ደቀ መዝሙርም ወደ ውስጥ ገባ፤ እሱም አይቶ አመነ። |
ከሞት መነሳት እንዳለበት የሚናገረውን የቅዱስ መጽሐፉን ቃል ገና አልተረዱም ነበር። |
ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ። |
ይሁን እንጂ ማርያም እዚያው መቃብሩ አጠገብ ቆማ ታለቅስ ነበር። እያለቀሰችም ወደ መቃብሩ ውስጥ ለማየት ጎንበስ አለች፤ |
ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክትም የኢየሱስ አስከሬን አርፎበት በነበረው ቦታ አንዱ በራስጌው ሌላው በግርጌው ተቀምጠው አየች። |
እነሱም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?” አሏት። እሷም “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳደረጉትም አላውቅም” አለቻቸው። |
ይህን ካለች በኋላ ዞር ስትል ኢየሱስን በዚያ ቆሞ አየችው፤ ነገር ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቀችም። |
ኢየሱስም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ? የምትፈልጊው ማንን ነው?” አላት። እሷም አትክልተኛው ስለመሰላት “ጌታዬ፣ አንተ ከዚህ ወስደኸው ከሆነ የት እንዳደረግከው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው። |
ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እሷም ዞር ብላ በዕብራይስጥ “ራቦኒ!” አለችው (ትርጉሙም “መምህር!” ማለት ነው)። |
ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ጥብቅ አድርገሽ አትያዥኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግኩምና። ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው’ ብለሽ ንገሪያቸው።” |
መግደላዊቷ ማርያም መጥታ “ጌታን አየሁት!” ብላ ለደቀ መዛሙርቱ አበሰረቻቸው፤ እሱ ያላትንም ነገረቻቸው። |
የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በነበረው በዚያው ቀን ምሽት ላይ ደቀ መዛሙርቱ አይሁዳውያኑን በመፍራታቸው በሮቹን ቆልፈው ተቀምጠው ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። |
ይህን ካለ በኋላ እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን በማየታቸው እጅግ ተደሰቱ። |
ኢየሱስም ዳግመኛ “ሰላም ለእናንተ ይሁን። አብ እኔን እንደላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው። |
ይህን ካለ በኋላ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። |
የማንንም ሰው ኃጢአት ይቅር ብትሉ ኃጢአቱ ይቅር ይባላል፤ ይቅር የማትሉት ሰው ሁሉ ደግሞ ኃጢአቱ እንዳለ ይጸናል።” |
ይሁን እንጂ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ኢየሱስ በመጣበት ጊዜ አብሯቸው አልነበረም። |
ስለዚህ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ጌታን አየነው!” አሉት። እሱ ግን “በእጆቹ ላይ ምስማሮቹ የተቸነከሩበትን ምልክት ካላየሁ እንዲሁም ጣቴን ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ካላስገባሁና እጄን በጎኑ ካላስገባሁ ፈጽሞ አላምንም” አላቸው። |
እንደገናም ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነሱ ጋር ነበር። በሮቹ ተቆልፈው የነበሩ ቢሆንም ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ። |
ከዚያም ቶማስን “ጣትህን እዚህ ክተት፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አስገባ። መጠራጠርህን ተውና እመን” አለው። |
ቶማስም መልሶ “ጌታዬ፣ አምላኬ!” አለው። |
ኢየሱስ “ስላየኸኝ አመንክ? ሳያዩ የሚያምኑ ደስተኞች ናቸው” አለው። |
እርግጥ ኢየሱስ በዚህ ጥቅልል ውስጥ ያልተጻፉ ሌሎች ብዙ ተአምራዊ ምልክቶችም በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል። |
ሆኖም እነዚህ የተጻፉት ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ እንዲሁም የአምላክ ልጅ እንደሆነ እንድታምኑና በማመናችሁም በስሙ አማካኝነት ሕይወት እንዲኖራችሁ ነው። |
የፋሲካ በዓል ከመድረሱ ከስድስት ቀን በፊት ኢየሱስ፣ ከሞት ያስነሳው አልዓዛር ወደሚኖርባት ወደ ቢታንያ መጣ። |
በዚያም የራት ግብዣ አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግላቸው የነበረ ሲሆን አልዓዛር ግን ከእሱ ጋር ከሚበሉት አንዱ ነበር። |
ከዚያም ማርያም ግማሽ ሊትር ገደማ የሚሆን እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በፀጉሯ አብሳ አደረቀች። ቤቱም በዘይቱ መዓዛ ታወደ። |
ሆኖም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነውና አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዲህ አለ፦ |
“ይህ ዘይት በ300 ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” |
እንዲህ ያለው ግን ለድሆች አስቦ ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ የነበረው እሱ በመሆኑ ወደ ሣጥኑ ከሚገባው ገንዘብ የመስረቅ ልማድ ነበረው። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ለቀብሬ ቀን ለማዘጋጀት ብላ ያደረገችው ስለሆነ ይህን ልማድ እንዳትፈጽም አትከልክሏት። |
ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።” |
በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁዳውያን ኢየሱስ እዚያ መኖሩን አውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ለማየት ብቻ ሳይሆን እሱ ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። |
በመሆኑም የካህናት አለቆቹ አልዓዛርንም ለመግደል አሴሩ፤ |
ምክንያቱም በእሱ የተነሳ ብዙ አይሁዳውያን ወደዚያ እየሄዱ በኢየሱስ ያምኑ ነበር። |
በማግስቱም ወደ በዓሉ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ መሆኑን ሰሙ። |
በመሆኑም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ። እንዲህ እያሉም ይጮኹ ጀመር፦ “እንድታድነው እንለምንሃለን! በይሖዋ ስም የሚመጣው የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” |
ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አግኝቶ ተቀመጠበት፤ ይህም የሆነው እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፦ |
“የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ። እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።” |
ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ እነዚህን ነገሮች አላስተዋሉም ነበር፤ ኢየሱስ ክብር በተጎናጸፈ ጊዜ ግን እነዚህ ነገሮች የተጻፉት ስለ እሱ እንደሆነና እነዚህን ነገሮች ለእሱ እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው። |
ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ከሞት ባስነሳበት ጊዜ አብረውት የነበሩት ሰዎች ስላዩት ነገር ይመሠክሩ ነበር። |
ከዚህም የተነሳ ይህን ተአምራዊ ምልክት መፈጸሙን የሰማው ሕዝብ ሊቀበለው ወጣ። |
ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው “ምንም ማድረግ እንዳልቻልን አያችሁ! ተመልከቱ፣ ዓለሙ ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተከትሎታል” ተባባሉ። |
ለአምልኮ ወደ በዓሉ ከመጡት ሰዎች መካከል አንዳንድ ግሪካውያን ነበሩ። |
እነሱም በገሊላ የምትገኘው የቤተሳይዳ ሰው ወደሆነው ወደ ፊልጶስ ቀርበው “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” ብለው ጠየቁት። |
ፊልጶስ መጥቶ ለእንድርያስ ነገረው። ከዚያም እንድርያስና ፊልጶስ መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። |
ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የሰው ልጅ ክብር የሚያገኝበት ሰዓት ደርሷል። |
እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አንዲት የስንዴ ዘር መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች አንድ ዘር ብቻ ሆና ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። |
ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። |
እኔን ሊያገለግል የሚፈልግ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። የሚያገለግለኝንም ሁሉ አብ ያከብረዋል። |
አሁን ተጨንቄአለሁ፤ እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ? አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ይሁንና የመጣሁት ለዚህ ሰዓት ነው። |
አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።” በዚህ ጊዜ “ስሜን አክብሬዋለሁ፤ ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። |
በዚያ ቆመው የነበሩት ብዙ ሰዎች ድምፁን በሰሙ ጊዜ ‘ነጎድጓድ ነው’ አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ አናገረው” አሉ። |
ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ድምፅ የተሰማው ለእኔ ሳይሆን ለእናንተ ሲባል ነው። |
ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ አሁን ይባረራል። |
እኔ ግን ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከተደረግኩ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ወደ ራሴ እስባለሁ።” |
ይህን የተናገረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ዓይነት አሟሟት እንደሚሞት ለማመልከት ነው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.