text stringlengths 4 267 |
|---|
በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ አንተ የሰው ልጅ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ብርሃኑ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ይቆያል። ጨለማ እንዳይውጣችሁ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃን ሂዱ፤ በጨለማ የሚሄድ ሁሉ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። |
የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ ሄደ፤ ከእነሱም ተሰወረ። |
በፊታቸው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች ቢፈጽምም በእሱ አላመኑም፤ |
ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን ነገር ያመነ ማን ነው? የይሖዋስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” |
ደግሞም ኢሳይያስ ሊያምኑ ያልቻሉበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ |
“በዓይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው ዓይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል።” |
ኢሳይያስ ይህን የተናገረው የክርስቶስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እሱም ተናገረ። |
ያም ሆኖ ከገዢዎችም እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእሱ አመኑ፤ ይሁንና ፈሪሳውያን ከምኩራብ እንዳያባርሯቸው ስለፈሩ በእሱ ማመናቸውን በግልጽ አይናገሩም ነበር፤ |
ይህም የሆነው ከሰው የሚገኘውን ክብር ከአምላክ ከሚገኘው ክብር አስበልጠው ስለወደዱ ነው። |
ይሁን እንጂ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን ሁሉ በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ጭምር ያምናል፤ |
እኔን የሚያይ ሁሉ የላከኝንም ያያል። |
በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። |
ይሁንና ማንም ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቅ ከሆነ የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለምና። |
እኔን የሚንቀውንና ቃሌን የማይቀበለውን ሁሉ የሚፈርድበት አለ። በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት የተናገርኩት ቃል ነው። |
እኔ የተናገርኩት በራሴ ተነሳስቼ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ ምን እንደምልና ምን እንደምናገር ያዘዘኝ የላከኝ አብ ራሱ ነው። |
ደግሞም የእሱ ትእዛዝ የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ። ስለዚህ ምንጊዜም የምናገረው ልክ አባቴ በነገረኝ መሠረት ነው።” |
ኢየሱስ ስለ እነዚህ ነገሮች ከጸለየ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የቄድሮንን ሸለቆ ተሻግሮ ወደ አንድ የአትክልት ስፍራ ሄደ፤ እሱና ደቀ መዛሙርቱም ወደ አትክልት ስፍራው ገቡ። |
ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ጊዜ በዚህ ስፍራ ይገናኝ ስለነበር አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያውቅ ነበር። |
ስለዚህ ይሁዳ አንድ የወታደሮች ቡድን እንዲሁም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን የተላኩ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አስከትሎ መጣ፤ እነሱም ችቦና መብራት እንዲሁም መሣሪያ ይዘው ነበር። |
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የሚደርስበትን ነገር ሁሉ ስላወቀ ወደ ፊት ራመድ ብሎ “ማንን ነው የምትፈልጉት?” አላቸው። |
እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” ሲሉ መለሱለት። እሱም “እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ከእነሱ ጋር ቆሞ ነበር። |
ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እኔ ነኝ” ሲላቸው ወደ ኋላ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ። |
ዳግመኛም “ማንን ነው የምትፈልጉት?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” አሉት። |
ኢየሱስም መልሶ “እኔ ነኝ አልኳችሁ እኮ። የምትፈልጉት እኔን ከሆነ እነዚህን ተዉአቸው ይሂዱ” አለ። |
ይህም የሆነው “ከሰጠኸኝ ከእነዚህ መካከል አንዱም እንኳ አልጠፋብኝም” ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። |
በዚህ ጊዜ ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው። የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር። |
ይሁን እንጂ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ሰይፉን ወደ ሰገባው መልስ። አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት አይኖርብኝም?” አለው። |
ከዚያም ወታደሮቹና የጦር አዛዡ እንዲሁም ከአይሁዳውያን የተላኩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት። |
በመጀመሪያም ወደ ሐና ወሰዱት፤ ምክንያቱም ሐና በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው የቀያፋ አማት ነበር። |
ቀያፋ ደግሞ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ለእነሱ የተሻለ እንደሚሆን ለአይሁዳውያን ምክር የሰጠው ሰው ነው። |
ስምዖን ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን እየተከተሉ ነበር። ይህን ደቀ መዝሙር ሊቀ ካህናቱ ያውቀው ስለነበር ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ፤ |
ጴጥሮስ ግን ውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር። ስለሆነም ሊቀ ካህናቱ የሚያውቀው ይህ ደቀ መዝሙር ወጥቶ በር ጠባቂዋን አነጋገራትና ጴጥሮስን አስገባው። |
በር ጠባቂ የነበረችውም አገልጋይ ጴጥሮስን “አንተም ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አለችው። እሱም “አይደለሁም” አለ። |
ብርድ ስለነበር ባሪያዎቹና የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ባቀጣጠሉት ከሰል ዙሪያ ቆመው እየሞቁ ነበር። ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። |
በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ። አይሁዳውያን ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኩራብና በቤተ መቅደሱ ሁልጊዜ አስተምር ነበር፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም። |
እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? እኔ የነገርኳቸውን ነገር የሰሙትን ሰዎች ጠይቃቸው። እነዚህ የተናገርኩትን ያውቃሉ።” |
ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አንዱ በጥፊ መታውና “ለካህናት አለቃው የምትመልሰው እንዲህ ነው?” አለው። |
ኢየሱስም “የተሳሳተ ነገር ተናግሬ ከሆነ ስህተቴ ምን እንደሆነ ንገረኝ፤ የተናገርኩት ነገር ትክክል ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?” ሲል መለሰለት። |
ከዚያም ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው። |
ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “አንተም ከእሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አሉት። እሱም “አይደለሁም” ሲል ካደ። |
ከሊቀ ካህናቱ ባሪያዎች አንዱ ይኸውም ጴጥሮስ ጆሮውን የቆረጠው ሰው ዘመድ “በአትክልቱ ስፍራ ከእሱ ጋር አይቼህ አልነበረም?” አለው። |
ይሁን እንጂ ጴጥሮስ እንደገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። |
ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ ገዢው መኖሪያ ወሰዱት። ጊዜውም ማለዳ ነበር። ሆኖም እነሱ ፋሲካን መብላት ይችሉ ዘንድ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው መኖሪያ አልገቡም። |
ስለዚህ ጲላጦስ እነሱ ወዳሉበት ወጥቶ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ክስ ምንድን ነው?” አላቸው። |
እነሱም መልሰው “ይህ ሰው ጥፋተኛ ባይሆን ኖሮ ለአንተ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር” አሉት። |
ስለዚህ ጲላጦስ “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው። አይሁዳውያኑም “እኛ ማንንም ሰው ለመግደል ሕግ አይፈቅድልንም” አሉት። |
ይህ የሆነው ኢየሱስ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። |
ስለሆነም ጲላጦስ ወደ ገዢው መኖሪያ ተመልሶ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” አለው። |
ኢየሱስም መልሶ “ይህ የራስህ ጥያቄ ነው ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነግረውህ ነው?” አለው። |
ጲላጦስም “እኔ አይሁዳዊ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የራስህ ሕዝብና የካህናት አለቆች ናቸው። ያደረግከው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም። መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል ቢሆን ኖሮ በአይሁዳውያን እጅ እንዳልወድቅ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም።” |
በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው። እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው። ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።” |
ጲላጦስም “እውነት ምንድን ነው?” አለው። ይህን ከተናገረ በኋላ እንደገና አይሁዳውያኑ ወዳሉበት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም። |
ከዚህም በላይ በልማዳችሁ መሠረት በፋሲካ አንድ ሰው ለእናንተ መፍታቴ አይቀርም። ስለዚህ የአይሁዳውያንን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” |
እነሱም እንደገና በመጮኽ “ይህን ሰው አንፈልግም፤ በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የገሊላን ማለትም የጥብርያዶስን ባሕር አቋርጦ ወደ ማዶ ተሻገረ። |
ብዙ ሰዎችም ኢየሱስ የታመሙትን በመፈወስ የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት። |
ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ። |
በዚያን ጊዜ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው ፋሲካ ተቃርቦ ነበር። |
ኢየሱስም ቀና ብሎ ብዙ ሕዝብ ወደ እሱ እየመጣ እንዳለ ሲመለከት ፊልጶስን “እነዚህ ሰዎች የሚበሉት ዳቦ ከየት ብንገዛ ይሻላል?” አለው። |
ሆኖም ይህን ያለው ሊፈትነው ብሎ እንጂ ለማድረግ ያሰበውን ያውቅ ነበር። |
ፊልጶስም “እያንዳንዱ ሰው ትንሽ ትንሽ እንዲደርሰው ለማድረግ እንኳ የ200 ዲናር ዳቦ አይበቃም” ሲል መለሰለት። |
ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ እንዲህ አለው፦ |
“አምስት የገብስ ዳቦና ሁለት ትናንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ትንሽ ልጅ እዚህ አለ። ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይበቃል?” |
ኢየሱስም “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉ” አለ። በስፍራው ብዙ ሣር ስለነበር ሰዎቹ በዚያ ተቀመጡ፤ ወንዶቹም 5,000 ያህል ነበሩ። |
ኢየሱስ ዳቦዎቹን ወስዶ ካመሰገነ በኋላ በዚያ ለተቀመጡት ሰዎች አከፋፈለ፤ ትናንሾቹን ዓሣዎችም ልክ እንደዚሁ አደለ፤ እነሱም የሚፈልጉትን ያህል ወሰዱ። |
በልተው ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ” አላቸው። |
ስለዚህ ከአምስቱ የገብስ ዳቦ ሰዎቹ በልተው የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ። |
ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ። |
ከዚያም ኢየሱስ ሰዎቹ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ። |
በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤ |
በጀልባም ተሳፍረው ባሕሩን በማቋረጥ ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሱ። በዚያን ሰዓት ጨልሞ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ገና ወደ እነሱ አልመጣም ነበር። |
በተጨማሪም ኃይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለነበረ ባሕሩ ይናወጥ ጀመር። |
ይሁን እንጂ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ገደማ እንደቀዘፉ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቃረብ ተመልክተው ፈሩ። |
እሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው። |
ከዚያም ወዲያው ጀልባዋ ላይ አሳፈሩት፤ ጀልባዋም ሊሄዱ ወዳሰቡበት ቦታ በፍጥነት ደረሰች። |
በማግስቱም፣ በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች ባሕሩ ላይ ከአንዲት ትንሽ ጀልባ በስተቀር ሌላ ጀልባ እንዳልነበረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን በጀልባዋ እንደሄዱ፣ ኢየሱስ ግን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንዳልተሳፈረ ተረዱ። |
ሆኖም ከጥብርያዶስ የተነሱ ጀልባዎች፣ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን ዳቦ ወደበሉበት አካባቢ መጡ። |
ሕዝቡ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን ባወቁ ጊዜ በጀልባዎቻቸው ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። |
ከባሕሩ ማዶ ባገኙትም ጊዜ “ረቢ፣ መቼ ወደዚህ መጣህ?” አሉት። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የምትፈልጉኝ ተአምራዊ ምልክት ስላያችሁ ሳይሆን ዳቦ ስለበላችሁና ስለጠገባችሁ ነው። |
ለሚጠፋ ምግብ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ዘላቂ ለሆነውና የዘላለም ሕይወት ለሚያስገኘው ምግብ ሥሩ፤ ምክንያቱም አብ ይኸውም አምላክ ራሱ እሱን እንደተቀበለው አሳይቷል።” |
እነሱም “ታዲያ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ሥራ ለመሥራት ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። |
ኢየሱስም መልሶ “አምላክ የሚቀበለው ሥራማ እሱ በላከው ሰው ማመን ነው” አላቸው። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንብህ ምን ተአምራዊ ምልክት ትፈጽማለህ? ምን ነገርስ ትሠራለህ? |
‘ይበሉ ዘንድ ከሰማይ ምግብ ሰጣቸው’ ተብሎ በተጻፈው መሠረት አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ።” |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከሰማይ የወረደውን ምግብ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ አባቴ ግን እውነተኛውን ምግብ ከሰማይ ይሰጣችኋል። |
ምክንያቱም አምላክ የሚሰጠው ምግብ ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወት የሚያስገኝ ነው።” |
እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምግብ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ እኔ ነኝ። ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ፈጽሞ አይራብም፤ እንዲሁም በእኔ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይጠማም። |
ነገር ግን “አይታችሁኝም እንኳ አታምኑም” ብያችሁ ነበር። |
አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ፈጽሞ አላባርረውም፤ |
ከሰማይ የመጣሁት የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ነውና። |
የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንዱም እንኳ እንዳይጠፋብኝና በመጨረሻው ቀን ሁሉንም ከሞት እንዳስነሳቸው ነው። |
ምክንያቱም የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያውቅና በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ።” |
ከዚያም አይሁዳውያን “ከሰማይ የወረደው ምግብ እኔ ነኝ” በማለቱ በኢየሱስ ላይ ያጉረመርሙ ጀመር። |
ደግሞም “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለም? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለም እንዴ? ታዲያ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?” አሉ። |
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.